የመረጃ ቲቪ ጋዜጠኛ ላይ የደረሰው ጥቃት ስርዓት አልበኝነትና የሕግ የበላይነት አለመረጋገጡ ማሳያ ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በለገጣፎ ያለውን የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ ለመዘገብ ወደ አከባቢው ያቀኑት የመረጃ ቲቪ ጋዜጠኞች በሆኑት ጋዜጠኛ ፋሲል አረጋ እና በካሜራ ማኑ ሃብታሙ ላይ የደረሰው ጥቃትና እገታ በሃገሪቱ ላይ የሚታየው የስርዓት አልበኝነትና የሕግ የበላይነት አለመረጋገጥ ማሳያ ነው። ይህ ጥቃት የተፈጸመው ሕዝብ በተሰበሰበት እና የጸጥታ ኃይሎች ባሉበት መሆኑ ደግሞ የበለጠ የለውጥ ሂደቱ በጥርጣሬ እንዲታይ ያደርገዋል።

በኢትዮጵያ ለውጥ አለ ተብሎ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ላይ በነጻ ፕሬስ ቤተሰቦች ላይ የተፈጸመው ወንጀል ሕግን የጣሰና የሰብዓዊ መብቶችን የረገጠ የካድሬዎች ተግባር ነው። የጸጥታ ኃይሎች ከስርዓት አልበኞች ጋር ተባብረው የፈጸሙት ድርጊት በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ ሽብር ነው። በለገጣፎ በሕዝብ ላይ የሚካሔደው አስተዳደራዊ ሽብር አልበቃ ብሎ በቦታው ላይ የተገኙ ጋዜጠኞችን መደብደብና ማገት በኦሮሚያ ክልል የሰፈነው ሽብርን ገሃድ ያወጣ ስለመሆኑ ምስክር አያሻውም ።

በለገጣፎ አስተዳደሪዊ በደል ደርሶባቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድምጽ ለመሆን በቦታው ለዘገባ የተሰማሩ ጋዜጠኞች ምንም የፈጸሙት ወንጀልም ይሁም መንግስትን የሚያስከፋ ጥፋት አልፈጸሙም። በለገጣፎ የተሰማሩ ስርዓት አልበኛ ካድሬዎች የሚያደርጉት ጥቃት ሊወገዝ የሚገባው ወንጀል መሆኑን መንግስት እያወቀ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱና የሚዲያ ሽፋን እንዳያገኝ ማድረጉ ሌላኛው የመንግስት ጥፋት ሲሆን የጸጥታ ኃይሎች ከስርዓት አልበኞች ጋር መተባበራቸው ወንጀሉን የከፋ ያደርገዋል።

ስለዚህ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የደረሰውን ጥቃት በመመልከት ጥቃት አድራሾቹ ለፍርድ እንዲቀርቡና ካሳ ለተጎጂዎች እንዲከፈል በማድረግ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ግዴታ አለበት። በዜጎች ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም ስንል መንግስት የዜጎችን ደሕንነት የማስጠበቅ ግዴታ አለበት እያልን ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

1 COMMENT

  1. Oh, my God !

    What does this tell us: ” ይህ ጥቃት የተፈጸመው ሕዝብ በተሰበሰበት እና የጸጥታ ኃይሎች ባሉበት መሆኑ ደግሞ የበለጠ የለውጥ ሂደቱ በጥርጣሬ እንዲታይ ያደርገዋል።” ?

    Does that mean the Abiy government has dropped the mask and is showing its true face ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.