እንደውም ከ7-15 ዓመት ያሳስር ነበር እኛ ወደዛ አልሄድንም? የኦሮሚያ ባለስልጣናት (ሰርፀ ደስታ)

በአለፈው የመሬት የክልሉ የመሬት አስተዳደር ስለ ለገጣፎ ከተማ ቤቶች መፍረስ ሲጠየቁ ሰጡት የተባለው መልስ (እኔ አልሰማሁትም) ሲገርመኝ ነበር፡፡ ዛሬ የከተማዋ ከንቲባ ደገመችው፡፡ ይሄ ነገር ሕግን ከአለማወቅ ይሆን በተለመደ ማን አለብኝነት አልገባኝም፡፡ ለመሆኑ ግን ከ7-15ዓመት የሚያሳስርን ጥፋት የሚወስን ማን ነው? ቤትስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማፍረስ ይቻላል? ይሄን የማቀርበው የአገሪቱ ሕግ ምን እንደሆነ ለምታውቁ እንድታብራሩልን ነው፡፡

ሕዝብ ይፍረድ! የኦሮሞ ሕዝብ እንዲህ በስምህ የሚነግዱ ሌላ ተልዕኮ ያነገቡ ጽንፈኞች ማውጣትና ለፍርድ ማቅረብ አለብህ::የለገጣፎ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ሐቢባ እና ግብረአበሮቿ ለፍርድ ይቅረቡ ስንል ማስረጃ ይዘን ነው::ለሁሉም ህዝብ አለመቆሟን እራሷን በጽንፈኛው የኦዴፓ አንጃ አደራጅታ እየሰራች መሆኑን በኦኤምኤን ላይ የተናገረችው ማስረጃ ይሔው:::"ሐቢባ ለአንድ ለኦሮሞ ( ብሔር ለማጭበርበር ነው) እራሷን እና አመራር ቲሟን አደራጅታ እየሰራች መሆኑን እንድታውቁት ነው" ብላ በራሷ ላይ መስክራለች: በአቶ ለማ ለለገጣፎ ጉዳይ የተመደበው አጣሪ ኮሚቴ ግለሰቧ ይህን የተናገረችውን ከግንዛቤ አስገብቶ ለፍርድ ሊያቀርባት ይገባል::ኦዴፓ ውስጥ ተጨናንቀው በአንድ ቤት የሚኖሩትን ምስኪኖች ወራሪ ያላሉ አመራሩን ሐቢባ ለፍርፋሪ ያደሩ ትለላቸዋለች::አዲስ አበባ ምስኪን ቀን ሰራተኞች ቀን አዲስ አበባ ድንጋይ ሲፈልጡ ወለው ምሽት ላይ ከከተማ ወጣ ብለው እንደለገጣፎ ከተማ እየሔዱ በጠባብ ቤት ለአራትና ለአምስት ተጣበው ማደራቸው ለሐቢባ ወረራ ነው::ሐቢባ መጀመርያ የዘረኝነት አይኗን ልታጠራ ይገባታል::ለሐቢባ ሕዝብ ለማገልገል በከንቲባነት መቀመጥ ማለት የብሔር ትግል ላይ መሆን ማለት ነው::የሌላን መውረር ስትል ከባዕድ ሀገር እንደመጡ ሰዎች ዓይነት አድርጋ ነው::የእናቶች ዋይታ! ደግሞ አሁን ለሐቢባ ጫጫታ ነው::ከእዚህ በላይ ፋሺዝም ከእዚህ በላይ ናዚዝም ከየት ይመጣል??

Posted by Getachew Bekele on Sunday, February 24, 2019

እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሕግ ይሄን የሚፈቅድ ከሆነ ችግሩ የሚመጣው ከራሱ ከሕጉ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንግዲህ በወሮበላ አመራሮች እንደተፈለገ ሊታሰብ ይችላል፡፡ አንድን ነገር ሕገ-ወጥ ነው ለማለት ሕገ-ወጥ ለመሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡እኔ እንደሚገባኝ አንድ ከተማ አስተዳደር በሕገ-ወጥ መንገድ ቦታ ተይዞብኛል ሲል ለፍርድ ቤት አቅርቦ ሒድቱ ጭምር ታይቶ ፍርድ ቤት ካረጋገጠ በኋላ ነው ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ የሚቻለው፡፡   ሰሞኑን በለገዳዲ ለገጣፎ እየሆነ ያለው ዘልማዳዊ አሰራር ወይስ ሕጋዊ ነው? የከተማዋ ከንቲባና የክልሉ መሬት አስተዳደር ኃላፊ በሕጉ መሠረት እንደውም ከ7-15 ዓመት ያሳስራል እኛ ግን ወደዛ አልሄድንም ይሉናል፡፡ በዚህ ሊደነቁ እንደሚገባ አይነት ነገር ነው የሚናገሩት፡፡ ለመሆኑ ያለፍርድ ቤት ውሳኔ እነሱ ሕገ ወጥ ስላሉት ብቻ አንድን ሰው እንስተው እስር ቤት መክተት ይችላሉ? ማሰር ከልቻሉ ደግሞ ቤቱንም ማፍረስ ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚችሉበት አሰራር ለመሆኑ እጅጉን አጠያያቂ ነው፡፡ በፍርድ ቤት ደግሞ ማን እንደሚረታ (ትክክለኛ ፍትህ ከተሠጠ) አይታወቅም፡፡ ምን አልባትም ሕገወጡ የከተማው አስተዳደር ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄን መንገድ ተከትሎ እርመጃ ሲወሰድ ሰው ሕግን ይፈራል፡፡

ሰሞኑን በለገጣፎ እየሆነ ያለው ሂደት ብዙ ጥያቄዎችን ነው የስነሳብኝ፡፡ ይሄ ጉዳይ ለገጣፎን የተለየ አያደርገውም፡፡ ግን የለገጣፎው ክስተት ነገሮችን ለማስተዋል ምክነያት ሆነ እንጂ፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ አገሪቱ ውስጥ ያሉት የከተማ አስተዳደር ነን የሚሉ ሁሉ የሚከተሉት ይሄንኑ የጉልበተኛ የሚመስል አካሂድ ስለሆነ፡፡ ይህ አሰራር በዘልማድ ነው ወይስ ሕጋዊ? ዛሬ  በሚዲያ የለገጣፎዋ ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች ሲወያዩ ሰማሁ፡፡ ነገሩ በዶዘር ብድግ ብሎ ቤት ማፍረስን ያህል ቀላል ሆኖ አላየሁትም፡፡

 1. ይህ ሕገ-ወጥ የተባለው ግንባታ በዋናነት ዛሬ ይሁን በፊር የነበሩ እስከቀበሌ ያሉ አመራሮች አሉበት
 2. መሬት የሸጡ ገበሬዎች አሉበት
 3. ግንባታ የገነቡ አሉበት

አሁን እርምጃ እየተወሰደ ያለው ሕገ-ወጥ በተባሉ ቤቶች ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ላይ ግን ሕግ የለም፡፡ የቀድሞው ይሁን የአሁኑ ከተማ አስተዳደር እስከቀበሌ ያሉ በዚህ ጉዳይ ከተሳተፉ ቀድሚያ ሊጠየቁ የሚገባው እነሱ ናቸው፡፡ የፍርድ ሂደት ቢኖር ይሄ ይሆን ነበር ግን የፍርድ ሂደት ስለሌ ተጠቂ ሚስኪን ገንዘቡን አውጥቶ መሬት ገዝቶ ቤት የሰራ ደሀ ነው፡፡ ይሄን ሕገ-ወጥ የተባልን ሥራ የሰራ የአስተዳደር ሰው ግን ወይ እዛው ቤት አፍራሽ ነው ወይም ሌላ ቦታ ምን አልባትም ከፍ ላለ ቦታ ተሾሟል፡፡ መሬት መሸጥ መለወጥ አይቻልም፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙም ባላምንበትም እንደሕግ ግን መሬት የሸጡም ያስጠይቃቸዋል፡፡ ሆኖም ሚስኪን ገበሬ መሬቱን የከተማው አስተዳደር ስለሚቀማው (ካሳ ብሎ ጠብታ በመስጠት) ጠቀም ያለ ገንዘብ ለሚሰጡት ሕገ-ወጥ ለተባሉት መሸጥ ይፈልጋል፡፡ እንደ እውነቱ  እዚህ ጋር በቂ ካሳ የማይከፍል ከሆነ ከተማው የገበሬውን መሬት የሚወስድበት መብት ሊኖረው አይችልም፡፡ ይሄም ገበሬው ፍትህ የሚሰጠው ፍርድ ቤት ካለ ነው፡፡ ወሮበላ አስተዳደር ባለበት ግን ለማንም አቤት ማለት አይችልምና ያለው አማራጭ መሸጥ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ገበሬን ሕገ ወጥ ነህ ማለት ከተቻለ እንግዲህ ሕገ-ወጡ ሕጉ ራሱ ነውና ሕጉም ራሱን ይፈትሽ፡፡ በሶስተኛ ሕገ-ወጥ ግንባታ ገንብተዋል የተባሉት ናቸው፡፡ እነዚህንም በአብዛኛው በተለይ ሚስኪኖቹን ወደዚህ ወሳኔ የሚወስዳቸው በሕጋዊ መንገድ መሬት ማግኘት ስለማይችሉ ነው፡፡ እንደ ዜጋ የሚያስችላቸው እድል ቢኖር እንኳን፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ችግር የከተማ አስተዳደሮች ናቸው፡፡ የሆነ ሆኖ ፍርድ ቤት በሚወስነው እነሱም የራሳቸውን ቅጣት ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ ሂደቱ ታይቶ በምህረት ወይም በነጻ ሊረቱም ይችላሉ፡፡ አልፎም ካሳ ሊቀበሉ ይችላለ፡፡

ለገጣፎ እንደከተማ የተገኘችው በ1998 ነው ተብሏል፡፡ ከንቲባዋ እንደምትለው አሁን ሁለተኛ ዙር ፕላን ስንጀምር ነው ብዙ ሕገወጥ ግንባታ ያገኘንው ትላለች፡፡ ለመሆኑ ከተማው በፊት ያልደረሰባቸው ቦታ በሌላ ዙር ሲደርስ ቦታው ላይ ቀድሞ ለተገኘ ግንባታ ሕገ-ወጥ ነው ማለት ይችላል ወይ? ይህ ማለት ደግሞ ግንባታው ከሕገ-ወጥነት ነጻ ነው ማለት ሳይሆን የዚህ ግንባታ ጉዳይ ከከተማው አስተዳደር በዘለለ ሊታይ አይገባውም ወይ? ለከተማው ይሄን ቦታ ወደከተማው አካት ብሎ መሬቱን መፈቅድለት ማለቴ ነው፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ መሬቱን ሰጨው አካል ይሄን ከአረጋገጠና እንዲህ ያለ ችግር ወይም ሌላ ከሕግ ጋር የተያያዘ ችግር ከጨረሰ በኋላ ነው ለከተማ አስተዳደሩ መስጠት ያለበት፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ግን ይሄ ቦታ ለእኔ ተሰጥቶኛልና እዚህ ቦታ የተገነባ ሕገ-ወጥ ነው ሊል አይችልም፡፡ ቦታውን ቀድሞ የያዘው በምን ሕጋዊ አግባብ እንደያዘው አያውቅምና፡፡ እንዲህ ያሉ ነገሮች ከሕግ አንጻር እንዴት ይታያሉ? ይሄና መሠል ጉዳዮች በድንብ ቢስተዋሉ፡፡ መንግስት ሕግ ለማስከበር ቁርጠኛ ነኝ ከአለ የሕግ መሠረት ያለውን መንገድ መከተል ግድ ይለዋል፡፡ በማንም ላይ እርምጃ ከመውሰድ በፊት ግን በመዋቅሩ ላይ ሆነው እንዲህ ያለ ሕገ-ወጥ ሥራን የሚያስፋፉትን እርምጃ መውሰድ ይገባል፡፡ ግንባታም ሆነ ሌላ ሥራ በሕገ-ወጥ መንገድ ከመሆኑ በፊት መከላከል ከአልሆነም እንደተፈጸመ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ይሄ ዜጎችን ለብዙ አመት አሁን በተባለው መልክ ግንባታ ሲገነቡ ያለተቆጣጠረ አስተዳደር ዛሬ ላይ ሕገወጥበሚል ማፍረስ ከፍትሕ አንጻር ራሱ ስህተት ሆኖ፡ ብዙ ወንጀሎችንም የሚጋብዝ ነው፡፡ ከጅምሩ ሕጋዊ እርምጃ ቢወሰድ ማንም ደፍሮ እንዲህ ያለ ሂደት ውስጥ አይገባም፡፡

በተረፈ በለገጣፎ ለሆነው ጉዳይ ተከታትለው ስለሁኔታው ለሕዝብ በቪኦኤ በኩል የተናገሩትን የአቶ ንጉሱ ጥላሁንን  ብስለት አድንቄያለሁ፡፡ ንጉሱ ሕዝብ ፊት ነገሮችን ለማርገብ ሲሉ የሆነውን ነገር እንኳን አቀዝቅዘውና ሠላም በሚፈጠርበት አኳኋን የሚያናገረ ሰው እንደሆነ ከበደሌው የኦነግ-ወያኔ ጥምር ሴራ ጀምሮ ስናውቀው ውስጥ ግን ሕዝብን ወክሎ እንዴት አንደሚናገር ከቀድሞው የወያኔ የወንበዴ ቡድን የሚዲያዎች ኃላፊ ጋር ግብግብ አይነት ንግግሩ ሰምተን ተደንቀናል፡፡ አዲሱ አረጋ ከኦሮሚያ ምን አልባትም ከንጉሱ ጋር በግልም ጓደኛ ናቸው አደነቀዋለሁ፡፡ ሌሎች ግን ብዙዎች ለሕዝብ አንደ አንድ ኃላፊ ሳይሆን የሚያወሩት ያው የለመድንውን የወሮበላ አነጋገር ነው፡፡ ሕዝብ ፊት ቀርቦ መደንፋትና አልፎም በሕግ ሳይቀር የሚያስጠይቅን ነገር መናገር ከአለመብሰል ይሆን ወይም በጥላቻና ዘረኝነት የታመቀ አመለካከት ሲፈነዳ ባይገባኝም ችግር አለ፡፡ በሕጉ መሠረት ከ7-15 ዓመት የሳስራል እኛ ግን ወደዛ አልሄድንም ብሎ ማለት ልክ አደለም፡፡ ሲጀምር የሕግ ሂደት የተከተለ እርምጃ ለመውሰዳቸው ራሱ እርግጠኞች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ፍርድ ቤት ሕገ-ወጥ ያላለውን እነሱ ሕገ-ወጥ ብለን ማሰር ሲገባን ባለማሰራችን ልንመሰገን ይገባል አይነት ነው ንግግራቸው፡፡ ሌላው በግልጽ በአነጋገራቸው የጥላቻና ዘረኝነት ነገር ይነበባል፡፡ ሰው ከንግግር ቶን ብዙ ያነባል፡፡

ዛሬ ከሰማኋቸው በዙዎቹን ከተናገሯቸው ቃላት ይልቅ ይንግግራቸውን ቶን ማንበብ ሌላ ነገር ያደመጥኩ መሠለኝ፡፡ እዚህ ወንጀል ውስጥ ራሳቸውም ነጻ የሆኑ አይመስለኝም፡፡ በዚህ ረገድ እንደውም የለገጣፎዋ ከንቲባ በንግግር ብትሳሳትም ነገሮችን ከአለመረዳት ከአልሆነ በቀር የተሻለ ነጻነት ያላት ይመስላል፡፡ እያደረገችም ያለቸው ምን አልባትም ከንጹህ የህግ ማስከበር ብላ ከአሰበቸው አንጻር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን በሕግ አግባብ መሥራት አለመስራቷን ጠንቅቃ ተረድታዋለች ማለት አደለም፡፡ ይሄን ከላይ ጠቅሼዋለሁ፡፡  ከዚህ በተረፈ ግን  ዜጎች-ሕጋዊ ግንባታ ገንብተውም እንኳን አስተዳደሩ ቤታቸውን አደፍረሶ እንደፈለጋችሁ ሁኑ ማለት አይችልም፡፡ ከቤተሰቡ የሚጠየቁት እንደተባለውም እሰከ 15 ዓመት ተጠይቀው ቀሪዎቹ በተለይ ሕጻናቱ መጠለያ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ የመንግስት ገዴታ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ነው መንግስት ማለት፡፡ እንደዚያ ሲሆን ለአስተዳደሩም ቤት እንደፈለጉ ተነስቶ የማፍረስን ያህል ቀላል ሂደት አይሆንለትም፡፡ ችግሩ ከመከሰቱ በፊትም ይጠነቀቃል፡፡ ለገጣፎን አስመልከቶ ነገሮች ለሕዝብ ጆሮ ቢደርሱም ችግሩ በየከተሞች እየሆነ ያለው ማሳያ ስለሆነ፡፡ መንግስት ሕግ ከአለ ቢያስብበት፡፡

በተረፈ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የተባሉ ሰው ግልብ አሳብ በሚል ሉሲ ለሠላም የሚለውን የተቹበት እይታ ተመችቶኛል፡፡ እውነት ነው! ሕዝብን በተራ ስሜት ውስጥ እየከተቱ ጨፋሪና አጫፋሪ ማድረግ ይቁም፡፡ እንዲህ ያሉ አሰራሮች የቆማርተኞች ነው፡፡  አገር የምትመራው ሕዝብን መሠረታዊ የሀገር ሥሜት እንዲኖረው በማድረግ እንጂ በተራ ቃላትና ማደንዘዣ ትኩረት ሳቢ ነገሮችን በማዘጋጀት አደለም፡፡  የአሁኑ የአሜሪካው መሪ ትረምፕ ወደ ሥልጣን የመጡት ብዙ ሕዝብ የአገር ምንነት ጉዳይ ስለገባው ነው የእነ ሂላሪን ቅብ ንግግር ስለተራደ ነው፡፡ ይሄ ለእኛም ተርፎናል!  እንደ እነ ሄለሪ የተቀባባ ማታለያ ተሳክቶላት ተመርጣ ቢሆነ የእኛም መከራ በቀጠለ ነበር፡፡ በትረምፕ ቦታ ሂላሪ ተመርጣ ቢሆን ወያኔን ማውረድ በከበደን ነበር፡፡

የአዲስ አበባ ወንዞችን ማጽዳትና ዳርቻቸውን ወደ መዝናኛ ነት መለወጥ የሚለው ሐሳብ የዶ/ር አብይ አደለም፡፡ እኔ የዚህ ሐሳብ ባለቤት ነኝ፡፡ ከአስፈለገ በ2014 የጻፍኩትን ንድፈ ሐሳብ ላቀርብ እችላለሁ፡፡ ይሄን ሐሳብ ለከተማዋ አስተዳደር ይሄው ጉዳይ የሚመለከተውን መምሪያ አቅርቤ ነበር፡፡ ሌላም ሰው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰነድ ተዘጋጅቶ እንደነበር እየተናገረ ነው፡፡ በተናጥል አንድ አይነት ሐሳብ ሊኖረን ይችላል፡፡ ቢያን ግን አብይ የዚህ ሀሳብ አመንጭ አደለም፡፡ ኢቢሲም ሆነ ሌላ ይሄ የአጫፋሪ አይነት ዘገባ ባትዘግቡ ጥሩ ነው፡፡

ዛሬ ጠ/ሚኒሰቴሩ አንድ አገራዊ ፓርቲ አንመሰርታለን ያለው አንድ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ልክ ነው ኦዴፓ ኦሮሞን እንጂ ኦሮሚያ የተባለውን ክልል አይወክልም! አዴፓም አማራን እንጂ አማራ የተባለውን ክልል አይወክልም፡፡ ይሄ ዛሬ የተባለው የለውጡ አንዱ አካል ነው፡፡ ጥሩ

ብዙ ሶሻል ሚዲያ ጃዋር መሐመድ የተባለ በሕዝብ የሚነግድ ወሮበላ አዲስ አበባን አስመልክቶ ሲደነፋ የነበረውን ጉዳይ ሰሞኑን እያራገቡት ነው፡፡ ነገሩ የሰነበተ መሰለኝ፡፡ ይሄን ወሮበላ እየሰሙ የሚጨፍሩ ራሳቸውን ባያታልሉ ጥሩ ነው፡፡ ነገሮች ወዴት እየሁዱ እንደሆነ እየገባቸው አልመሰለኝም፡፡ ግን መብታቸው ነው፡፡ ቆይተው ያዩታል፡፡ ኦዴፓ ውስጥ ብዙ የጀዋር አይነት አስተሳሰብ ያለቸው አሉ ግን ሕግና ሥርዓት ሲከበር ሁሉም ቦታውን ይይዛል፡፡

አመስግናለሁ!

ለዑል አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን

ሰርፀ ደስታ

 

3 COMMENTS

 1. የተደቀነውን የእርስ በእርስ እልቂት ለማስቆም፣ በመጀመሪያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሚያ ከተሞች ዙሪያ ያቀደውን የ ዜጎችን ማፈናቀልአና ሜዳ ላይ መጣሉን በአስቸኳይ ማቆም አለበት ። ይህን ወደ ጎን ትቶ የ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማፈናቀሉን ከገፋበትና በአዲስ አበባ ዙሪያ በማድረግ ላይ እንዳለው የኦሮሞ ተወላጆች ያልሆኑትን እያፈናቀለ ከሐረር የ ኦሮሞ ተወላጆችን በአዲስ አበባ ዙሪያ የ ሚያሰፍር ከሆነ ዘመዶቻችን ፣ወገኖቻችን በኦነግ ቅጥረኞች አና በኦዲፓ ፅንፈኞች ሜዳ ላይ ተጥለው ዝም ብለን እንደማንታረድ ወገን ጠ ላትም ይወቀው። የ16ኛው ክፍለ ዘመን እንዳይመስላችሁ ።
  በ 16ኛው ክፍለ ዘመን በተከሰተው የጋላ(ኦሮሞ) ወረራ በሲዳሞ፣ በባሌ ፣በአርሲ፣በሸዋ ወዘተ ሲፈፀም ወራሪው ጋላ፣ የነባሩን ህዝብ፣ በተለይ የአማራውን ቤቶች በማቃጠል፣ የ ወረረውን ሕዝብ በመጨፍለቅ ፣የ ወንዱንም ብልት በመቁረጥ ነበር።
  ዛሬ በ 21ኛው ክ ፍ ለ ዘመን ቅጥረኛው ኦነግና የኦዴፓ ፋሽስቶች “ሕገወጥ ቤቶችን እናፈርሳለን ” በሚል ቅጥፊያ ኦሮሞ ያልሆኑትን ወገኖች ከኦሮሚያ ከተሞች በማፈናቀል በምትካቸው የኦሮሞ ተወላጆችን ለማስፈር ነው። ይህ ለመሆኑ እንደ ማስረጃ ከአዲስ አበባ ና ዙሪያዋ ሕገወጥ ያሏቸውን አፈናቅለው ከሐረር ድረስ ኦሮሞዎችን አምጥተው በቁዋሚነት እያሰፈሩ ነው።
  ሰለዚህ
  1) የኦሮሞ ዘር ያልሆንን ኢትዮጵያዊያንና ከሌላው የተዋለዱ ኦሮሞዎችም ሆኑ በእኩልነት አብሮ በመኖር የሚያምኑ ኦሮሞዎች አንድ ላይ በመሆን የታቀደውን እኩይ ፕላን ለማክሸፍ ተባብረን እንነሳ።
  2) የኦነግ ቅጥረኞች ና የኦዲፓ ፅንፈኞች ወገኖቻችን ን አሁን ማፈናቀል የጀመሩት የኦሮሞ ያልሆኑትን ቁጥር ለመቀነስ የታሰበ እኩይ ዘዴ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ የሕዝብ ቆጠራ መካሄድ የለበትም ።
  3) በተጨማሪም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ቸው እንዳይማሩ በክልሉ ውስጥ የተከለከለ በመሆኑ በአዲስ አበባ ምን ሆነ በአማራ ክልል ወይም ሌላ ክልል በኦሮምኛ ትምህርት መሰጠቱን በጥብቅ እንቃወማለን ።ይሄ የሚያሳየው የኦነግ ቅጥረኞች ና የኦዲፓ ፅንፈኞች የ21ኛው ክፍለ ዘመነ የ ጋላ ወራሪዎች መሆናቸውን ነው።

 2. What is going on in the minds of the ultra nationalists of the Amahara. It is extreme paradox. On one side they accuse the Tigers for replacing the Amahara culture and language with the culture and language of the Tigres in Walkit. On the side they are trying to describe the Oromo language and culture as alien to Finfinne and its surrounding. They want to hear more English or Spanish instead of afaan Oromoo. They behave like a parasite. They are not thankful. They want to have everything alone. We have to search for something which may help as remedy before it will affect us extremely. Their greediness is not only limited in Ethiopian territories, but also in abroad. For example, they claimed one part of a city around Wishing DC to have alone for themselves by renaming it as little Ethiopia. 

  The Oromo and other subjugated peoples of Ethiopia have been fighting such backward mentalities and ideologies. Our fighting will be continued until not only the villages and towns, but also all languages  and cultures will be free. Period!

 3. @Assefa Belay; ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል አሉ? ድሮም በግድ የተዳፈነውን ከልክ ያለፈ የኦሮሞ ጥላቻችሁ በትንሿ ላጋጣፎ መንደር በተካሄደ የህግ ማስከበር ስራ እንደእሳተ ገሞራ ፈነዳባችሁ አይደል!! ያዉም እኮ የአማራ ቤት ብቻ አይደለም የፈረሰው።
  በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተካሄደ “የጋላ(ኦሮሞ) ወረራ ” አልነበረም። ተረቱን ግን ድሮም ሰምተነዋል! ያኔም ሆነ ዛሬ የሆነው እና እየሆነ ያለው፣ ኦሮሞዎች ጥንት ይኖሩበት ከነበረው በሰሜን በኩል በክርስቲያኑ የአበሻ አጼዎች መንግስት፣ ከምስራቅ በኩል በአዳል ሱልጣኔት በተደረጉበት ሰፊ ጥቃቶች ከተቀማጭ አርሶ አደርነት ወደ ዘላንነት እንዲቀየር ተገድዶ (forced from settled agriculture into nomadism)፣ ወደ አሁኑ ባሌ (Madda Walabu) አፈገፈገ። ጥቃቱ ማቆሚያ እንደሌለው ሲታወቅ፣ የቀረው አማራጭ አዋጭ የሆነ የጦር ስልት መቀየስ እና ጦር ማሰልጠን ሆነ (the Gadaa was militarized)። That is how they could withstand and defeat two at the time more powerful regimes armed with upto date weapons and assisted by the then supepowers (Portugal and the Ottomans, resp.) ህዝቡ ይኖርበት ከነበረው ሁሉ ተባሮ መዳ ዋላቡ ከታጨቀበት ተነስቶ የተቀማውን ቦታዎች ሲያስመልስ “ሃገሩን እንደጎርፍ አጠለቀለቁት” ተባለ። ለተረት የተፈጥሮ ህግ አይሰራም፣ ግን ሰው አንበጣ አይደለም ባንዴ ተራብቶ ሃገር የሚሞላ! ከዚህ ተነስቶ የተፈበረከው የሃበሻ ተረት ስፍር ቁጥር የለዉም። ተረቱን እንደዉነት ወስደው የሚያደነቁሩ ደግሞ ህጻናቱ ብቻ ሳይሆኑ እንከፕሮፈሰሩም ይደርሳል!
  እናም ኦሮሞዎች ድሮ ክተባረሩበት ምድር ተመለሱ እንጂ ከሌላው የቀሙት መሬት አልነበረም! አሁን የምናየዉስ የያኔውን አያስታዉስም?
  And now you proclaim: “ዝም ብለን እንደማንታረድ ወገን ጠ ላትም ይወቀው። የ16ኛው ክፍለ ዘመን እንዳይመስላችሁ !” መሰለሳ?? እና?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.