ዲሞግራፊውን ስለመቀየር… (ሚኪያስ ጥላሁን)

 1. ትናንት «ርዕዮት ሚዲያ» ባሰራጨው ቪዲዮ ላይ አቶ ለማ መገርሳ ስለ«ከተሜ ፖለቲክስ»ና ዲሞግራፊ አንስቶ ተናግሮ ነበር። ዓላማው ኦሮሞን በገፍ አስፍሮ፣ ሌላው እንዲዋጥ ማድረግ ሲሆን፣ ቀጣዩ ምርጫ የዓላማው መዳረሻ እንደሚሆን ተገምቷል። በአቶ ለማ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የኦሮሞ ዘረኞችም የተቆሰቆሰ ዓላማ እንደሆነ በግልፅ – በአደባባይ ያዬነው ሃቅ ነው። አቶ ለማ ወሬውን ዕውነት መሆኑን በመጨረሻ አረጋግጦልናል።
 2. ኦሮሞን ወደ አዲስ አበባ ለማስፈር በርካታ ሰበቦች ተሳብበዋል። «ዋዜማ» ራዲዮ የቅርብ ምንጮቿን ጠቅሳ እንደዘገበችው፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮዬ ፈጬና ሌሎች አካባቢዎች በርካታ የብሎኬት ቤቶች እየተገነቡ ነው። ቤቶቹ ባለፈው ዓመት ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ኦሮሞዎች የሚሰጡ ናቸው። በተጓዳኝም፣ ዘረኛው ታከለ ኡማ ለበርካታ ኦሮሞዎች መታወቂያ እያደለ ነው። በቅርቡ ተማራኪ የኦነግ አባላትን በሺህዎች ሄክታር ላይ አስፍሮ ለማኖርም ታስቧል። አዲስ አበባን ለመያዝ «ጊዜው አሁን ነው!» ያሉት ዘረኞቹ፣ መጪውን ምርጫ ጠቅልለው በማሸነፍ፣ የ«ፊንፊኔ»ን ንግስና ለማረጋገጥ ደፋ ቀና እያሉ ነው።
 3. ከለማ መገርሳ በላይ ዙፋኑ ላይ ያለው አብይ አህመድም ቢሆን፣ የዕቅዱ አስተናባሪና ሽፋን ሰጪ መሆኑን ባገኘው መድረክ ላይ አስመስክሯል። ከሳምንታት በፊት ከለገጣፎ አማርኛ የሚናገሩ ነዋሪዎችን መንጥረው በማውጣት፣ ቤታቸውን አፍርሰው ለጎዳና ኑሮ ከዳረጉ በኋላ፣ አብይ ወቀሳው ሲበዛበት፣ «አላውቅም!» ብሎ ክዷል። አብይ ጃዋርንና ዳውድ «እሹሩሩ!» ማለቱ ሲገመገም፣ የእነርሱ ዕቅድ ተካፋይነቱን አረጋግጦ፣ አዲስ አበቤን ዝብርቅርቁን አስወጥቶ የመምታት አቅድ አለው። በኦሮምኛ ንግግሮቹ ላይ መታዘብ ይቻላል። ለታከለ ኡማ እነዳውድን እንዲቀልብ በርካታ ገንዘብ ፈሰስ አስደርጎለታል። አብይ እንዲህ የሚለፋው፣ የህዝብ ምጥጥኑን (ዴሞግራፊውን) አዛብቶ አዲስ አበባን የኦሮሞ ዘረኞች ምርኮኛ ለማስደረግ ነው።
 4. ሚዲያዎችም የእዚሁ ሴራ ሁነኛ ተባባሪዎች ናቸው።ከፊትአውራሪዎቹ OMN ጀምሮ የሃሳብ ተጋሪዎቹ እንጭጭ ሚዲያዎች ድረስ «ፊንፊኔ» የሚለውን ተረት-ተረታማ ቃል በማስጮኽ፣ «ሰፋሪዎች ናችሁ!»ን ለሰፊው አዲስ አበቤ በማስነዛት፣ ዛቻ ቀረሽ ዘፈኖችን በመልቀቅ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው። ትንሹ ሚሊን ኮሊንስ የሆነው OMN ከታሪክ ጋር የተጣሉ ትንታኔዎችን ለአድማጮቹ – ለዕውቀት-አጠር «ቄሮ»ዎቹ በማስሰማት አደገኛ ቦንብ በየተከታዮቻቸው ልብ ዘንድ እየቀበረ ነው። ዲሞግራፊው እንዲቀየርም እየወተወተ ነው። ባለፈው ሳምንት የለገጣፎዋን ዘረኛ ከንቲባ ቃለ-መጠይቅ በማድረግ፣ እርጉም ሃሳቧን ያስደመጠን ይኸው ሚዲያ ነው። ውጊያው በዘረፈ-ብዙ ቀጣናዎች የሚደረግ ነው፣ እየተደረገም ነው – ዲሞግራፊክ ዝነቃው።
 5. የተደማሪ ፓርቲዎች ዝምታም ያስተዛዝባል። «ለአዲስ አበቤ መብት አታገላለሁ!» ያለው ግንቦት 7፣ የወረት መግለጫ በማውጣት፣ የዝነቃውና የፍርሻው ተባባሪነቱን አሳይቷል። ዶ/ር ብርሃኑ ከታከለ ኡማ ጋር ግንኙነት ማብዛቱ፣ የአብይን ደጀ-ሰላም በሳምንት ሶስቴ መሳለሙ፤ ለእርሱም – ለጓደኞቹም – ለደጋፊዎቹም የይሉኝታ ገመድ ሆኖ አስሯቸዋል። «እናራምደዋለን!» የሚሉት የዜግነት ፖለቲካ ለዜጎች ዴሞግራፊያዊ ነፃነትና የመኖር መብት እንደማይቆም ተረድተናል። ለአዲስ አበቤ ያላቸውንም ንቀት አስመልክተውናል። በ’ርግጥ፣ መግለጫ ማውጣት፣ ትንሿ ስራ ነበረች – ችግር ማሳወቅም እንደዛው። ግን የጀመሩት የእፍታ ፍቅር አፋቸውንና ብዕራቸውን ለጎመባቸው፤ ራሳቸውንም አስገመቱ፣ አዋረዱ። የዴሞግራፊ ቅይጣው ደጋፊ ሆኑ።
 6. ለማጠቃለል፣ በአሁኑ ወቅት ለአዲስ አበባና አዲስ አበቤ የሚጠቅመው ራሱን ከግንቦት 7 «ላም አለኝ በሰማይ!» ወሬ አላቅቆ፣ የታከለ ኡማንና የበላዩን – የአብይ አህመድን አስተዳደር በፅኑ መታገል ብቻ ነው። ለመታገል መደራጀት ወሳኝ ነጥብ ነውና በአዲስ አበቤነቱ የማይደራደር ፅኑ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁሞ፣ ከዚህ በፊት ያልተተገበሩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን በተጠና መልኩ መከወን አለበት። ምሁራን ሃሳብ በማዋጣትና ታክቲክና ስትራቴጂ በመቀየስ መታገል አለባቸው። የዲሞግራፊው ዝብረቃው ከቀጠለ፣ አዲስ አበባ እንደወልቃይት መሆኗ አይቀርምና ይታሰብበት!

4 COMMENTS

 1. What is wrong with it if we resettle the Oromo in Finfinne and its surrounding. Shall we ask for a permission from the offspring of the ex-neftengas?  You are poor and stupid. Today you are not in the Menilik’s era. No inch of the Oromia’s soil will be given to the greediness. Your milcious tactics will not work any more, not only in Oromia, but also all over Ethiopia.The Oromo people needs no permission from anybody to resettle the Oromo within the territories of Oromia. Also we will not send our kids and elders to beg you and resettle them in Bahir Dar or Gonder. 

  Since 1991 more than 3 million Oromos were pushed out of  Finfinne and its surrounding in 4 directions. They were also robbed off their land & were made strangers in the same city. Now can you say why you don’t question that as a demographic engineering angaist the Oromo but this one is against you?

  Why do you cry always loudly? Why do you misuse the hospitality of the Oromo? We have been hosting and treating all ethinc groups from different  parts of Ethiopia all over Oromia equally with love and respect. The other Ethiopians are very thankful for our heartfelt hospitality and empathy. But you have no the terminologies of thankfulness, appreciation, gratefulness, recognition and valuations in your culture and vocabulary. You are just possessed by the spirit of greediness and egocentricity like tapeworms. In simple language you are inhuman. The racists are aways like snows. They can be dissolved with a minimum heat.  That is why the ideologies of the Apartheid, Nazi and segregation were eradicated. Likewise the ideologies of the ultra nationalists in Ethiopia will be eroded soon. Watch out!

  The Oromo and other subjugated peoples of Ethiopia have been fighting such backward mentalities and ideologies. Our fighting will be continued until not only the villages and towns, but also all languages  and cultures will be free and flourished. Period!

  Finally, there is no wonder that the Parasites cannot understand mutual understanding and benefits. They are very selfish and self-centered. They want to have everything alone. First of all, they want to dehydrate their hosts step by step. Finally, they try to kill their hosts if they can. That is what we have been witnessing in Ethiopia in the last 140 years. Human parasites.

 2. ዶ/ር ለማ ያንን ንግግር ያደርጉት ወራቶች በፊት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ያፈነገጠውን ኦነግን ለመመለስ ለኦሮሞ ሽማግሌዎችና ተወካዮች ሲሆን ባብዛኛው ደጋግመው ያተኮሩት ህዝቡ በተለይ የተፈናቅሉት ኦሮሞዎች ከተሜነትን እንዲለማመዱ በቅንነት ያቀረቡት ነው:: ስለዲሞግራፊም በጥቂቱ ተነስቷል ግን ይህ ርእዮት ተብዬው መዝዞ ያተኮረው የዲሞግራፊውን ጉዳይ በአሉታዊ መልኩ ሲሆን ይህን የከረመ ንግግር ከወቅቱ የለገጣፎ ትኩሳት ጋር ማቅረቡም ለትኩረት ፍጆታ ወይም ለተለመደው የሚዲያ ክፉ የማባላት ሴራ ነው::

 3. የአቶ ለማ ንግግር እንዲያውም ጉዳዩን አስከፊ የሚያደርገው ፣ከበፊት የታቀደው አሁን ስራ ላይ በመዋሉ ነው።የዘር ስብጥር (ዴሞግራፊ) አሁን ባለንበት ኢትዮጵያ ፣በተለይ አዲስ አበባን በተመለከተና በተያዘው የልዩ ጥቅም ጫጫታ ፣ለምርጫው ከአሁኑ የተያዘው እሩጫ፣ ተፅእኖ የለውም ብሎ ማሰብ ፣የፓለቲካን ሀ ሁን አለመገንዘብ ነው።
  ይህ ካልሆነ ታድያ የመሪዎች ብሎም አጋር የኦሮሞ ድርጅቶች የሚያወጡት መግለጫዎች በምን ላይ ተንተርሰው ነው።
  የሰለጠነው ዓለም ይሄን በአፍሪቃ የሚካሄደውን ዘር ነክ መጨፋጨፍን በመሳለቅ ብቻ ሳይሆን በማጨብጨብ ያጅቡታል። ከሌላው ሐገራት የዘር መባላት አለመማራችን ገና ብዙ ያስከፍለናል። ማን ይነካኛል ብሎ ደረቱን የነፋው ህወሓት አሁን እንደአይጥ ተንሿኳል። የሚያሳዝነው የአሁኖቹ ዘረኞች ከቅርቡ ታሪካችን አለመማራቸው ነው።
  ድሮም ተብሏል “ቀን የወጣለት ቅል ድንጋይ ይሰብራል ” ። ውጤቱ ከአሁኑ ይታወቃል።

 4. ገመዳ
  በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች ከቦታቸው በሚፈናቀሉበት ወቅት ተመልሰው መስፈር ያለባቸው ይኖሩበት በነበረው ስፋራ መሆን ይገባዋል። ይህም ለህብረተስቡ ክፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል። በህዝቦችም መካከል የተፈጠረወውን ችግር ለመቅረፍ እና በመካከላቸው የተፈጥረውን ቆርሾ ለማከም ይርዳል። ይህ ሳይንሳዊ አቅ ነው። ስህተቱ የሚጀምረውም አንድ በስልጣን ላይ ያለ የመንግስት አካል ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲል ህዝቦችን ያለፍላጉታቸው እና ይለፍቃዳቸው በማይፈልጉበት ቦታ ላይ ማስፈርሩ ላይ ነው። ኦቦ ለማ ሲናገሩ ስምተህ ከሆነ ‘’ ለምነን በአባ ገዳዎች አስለምነን በአዲስ አበባ ዞሪያ አስፍረናቸዋል ፣ ምክንያቱም ለከተማ ፖለቲካ / Urban Politics ስለሚጠቅመን ህዝቡን በአዲስ አካባቢ በማያወቀው አዲስ ስፋራ ሂዱ ለመልመድ ግዜ ቢወስድበትም …………‘’
  ውንድሜ ፖለቲካ የሚሰራው የህዝብን አሰፋፈር / Demography በመቀየር አይደለም ። ፖለቲካ የአሳብ የበላይነት ነው። የአዲስ አበባን ህዝብ ጨምሮ የመላው ኢትዩጲያውያንን ልብ የሚገዛ አሳብ አምጡና ህዝብ ይምረጣቹ። ስልጣን ስለተያዘ ህዝብን እንደፈለገህ በተልካሻ ምክንያቶች ለዘመናት ከኖረበት ቦታ እያባረርክ ፣ አያፈናቀልክ እና አያሰፈርክ ፖለቲካን መስራት አትችልም። ይህ ወንጀል ነው።
  በእኛ ኦሮሚያ ምን አገባችሁ ? ለምትለው ኦሮሚያ ወይም ፊንፊኔ ብሎ ሰይሞ ቦታ የሰጣችሁ ውያኔ ነው። ከዚያ በፊት የምናውቀው ኦሮሞ ( ችግሮች አንዳሉ) ኢትዩጲያ በምትባል አገር የሚኖር ፣ የተከበረ እና አቃፊ ህዝብ አንደነበር እና ዛሬም እንደዚያው አንደሆነ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ለሀገሩ ከማንም በላይ የሰራ አራሱን በኢትዮያዊነት አንጂ እንደ አንተ አይነት ጅሎች እንደሚያስቡት በመጥበብን እና በማነስ ፣ በጎጠኝነት እና በጎሰኝነት እራሱን አሳንሶ እና አዋርዶ መኖርን አይፈልግም። የኦሮሞ ህዝብ እናንተ በስራችሁለት ካርታ ተከልሉ የሚቀመጥ ህዝብ እይደለም ። ከምህራብ እሰከ ምስራቅ ፣ ከስሜን እስከ ደቡብ የሚገኘው የኢትዩጵያ ምደር የኦሮሞ እና የሌሎች ወንድሞቹ እና እህቶቹ ምድር ነው። ያሉበትን ችግሮች ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር አብሮ በመኖር እና በመካከር በመፍታት አብሮነቱን ያጠነክራል።
  ወንድማዊ ምክር ፡ አባክህ ሰው ሆን ። ሰውን በቋንቋው ፣ በዘሩ ፣ በማንነቱ ሳይሆን ሰው በመሆኑ ብቻ ለመቀበል አቅሙ ይኑርህ ። አንደ ሰለጠነ ሰው አስብ ። በእኛ ኦሮሚያ ምን አገባቹ አትበል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዩጵያ ምድር ላይ ለሚደረገው ነገር ይመለከተዋል። ትላንት የኦሮሞ ህዝብ እንዲ እና እንዲህ ተደርጓል በማለት ቁስል ከማከከ እና ከማልቀስ እና ከማስለቀስ ወጥተህ ያህ ታሪክ በሰው ዘር ላይ በድጋሚ አንዳይደገም አሳብ አቀብል። ሰው አሳቡን ስለገለጸ ከሰውነት አወርደህ እንደ አንሰሳ አትቁጠርው። ሰውን አትጥላ። በዘረኝነት ታውረህ የሰውን ልጅ አሳንሰህ አትይ። ትላንትና ዘረኞች የእኔን ዘር አሳንሰው ያዩት ነበር የሚል አንደ አንተ አይነቱ ሰው አንዴት ዛሬ የአኔ እና የኔ ብቻ ማለት ይጀምራል።
  አንድ ነገር ልንገርህ እና ላብቃ። አዋሳም ፣ መቀሌም፣ ባህር ዳርም እና ሌሎችም ከተሞች የመላ ኢትዩጲያ ህዝቦች ከተሞች ናቸው። አንተ አልፈልገም ብትልም የአንተም ናቸው። አዲስ አበባም / ፊንፊኔም የአንተም ፣ የአኔም የሁላችንም ናት። መሬቱ ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ጭምር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.