አማራ ከጅብ መንጋጋ ተላቆ ከእስስት አፍ ገብቷል! (በላይነህ አባተ)

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

አብዛኛው ሕዝብ እስስትን እሚያውቀው መልኩን በመቀያየር ባህሪው ነው፡፡ የሚደንቀው ግን የምላሱ ኃይል ነው፡፡
የእስስት ምላስ እርዝማኔ የእስስቱን እርዝመት ወይም ሁለት እጥፍ ሊሆን ይችላል፡፡ የእስስት ምላስ እስስት የሚመገባቸውን እንደ ሸረሪት ያሉ ነፍሳት ለማያዝ ከኤፍ 16 ጀት አምስት እጥፍ በበለጠ ፍጥነት ይስፈነጠራል፡፡ ተስፈንጥሮ ነፍሳቱን እንደያዘም እንደ ሙጫ እሚያጣብቅ ምራቅ ተገድቦ እንደቆየ ቦይ ይተፋል፡፡ ይህ ሙጫ ምራቅም በምላስ የተወጋውን ነፍሳት ባለበት ያገግረዋል፡፡ ነፍሳቱ ሲገግርም እስስቱ በምላሱ ጠቅሎ ወደ አፉ ያስገባዋል*፡፡
“ወንድማማችነትና ኢትዮጵያ!” እያለ አማራ በአሐዝና በቃላት ተገልጾ እማያልቅ ግፍ ዛሬም እየተፈፀመበት ይገኛል፡፡ አማራ በደደቢት መመሪያ በአካል፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ኑሮ እየጎዳ ለሩብ ክፍለ-ዘመን ሊያጠፋው ከጣረው የጅብ መንጋጋ ሲላቀቅ ከአቢይና ለማ እስስት አፍ ሰተት ብሎ ገብቷል፡፡ ይህ አማራን የዋጠው እስስት ቡድን እንደ እንሰሳዋ እስስት በየሄደበት መልኩን ይቀይራል፡፡ ባህርዳርና ጎንደር ሲበር ጃኖን፣ ደብረ ብርሃን ጎራ ሲል በርኖስን ይለብሳል፡፡ ወደ ደቡብ ሲንከባለልም ኮባ ያነሳል፡፡ በዚህ መልክ ቆዳውን ከአካባቢው እያመሳሰለ እስስትነቱን ይደብቃል፡፡
ይህ እስስት ቡድን እስስትነቱን ደብቆ ኢትዮጵያ በደሙ፣ በአጥንቱና በነፍሱ የተዋኻደችውን ትሉል አማራ ሲያገኝ ምራቁ ጠብ ይልና የስብከት ምላሱን በጀት ፍጥነት ከልቡና ከአንጀቱ ይተክልበታል፡፡ ከልቡና ከአንጀቱ በተከለው ምላሱም “ኢትዮጵያ ሱስ ናት! ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞትም ኢትዮጵያዊ!” የሚል የምራቅ ሙጫ ይተፋበታል፡፡ ይህ ሙጫ የተጣበቀበት አማራም በሙጫው አልኮል ሰክሮ እየዘለለ ያጨበጨብና ስካሩ ሲታገሰው ባለበት ፈዞ ይቀራል፡፡
አቢይና ለማ የሚባሉ እስስቶች ምላሳቸውን በጀት ፍጥነት እየዘረጉና የሙጫ ምራቃቸውን እየተፉ በዋሽንግተን ዲሲ ስንቱን ቂላቂል በጉልበቱ አስኪደው ተንበርክኮ እንደ ምርኮኛ እግራቸውን እንዲስም አድርገውታል! በሚኒሶታና በአውሮጳም ስንቱን ዘልዛላ ተንበርክኮ ውዳሴ አቢይን እንዲደግምና ገድለ-ለማን እንዲተርክ አድርገውታል!
ይኸንን በእምብርክክ የሚያስኬድ፣ እግር የሚያስም፣ ውዳሴ አቢይን የሚያስደግምና ገድለ-ለማን የሚያስተርክ ሙጫ ዘልዛላውና መንጋው “ፍቅር ያሸንፋል” ብሎ ይጠራዋል፡፡ ዘልዛሌዋ! እነዚህ እስስቶች ፍቅር ቢያውቁ ኖሮ በፈላ ውሀ ለሚቀቅል፣ በብልት ውሀ ለሚያንጠለጥል፣ ጥፍር ለሚነቅል፣ ዓይን ለሚያወጣ፣ እግርን ለሚቆርጥ፣ ህጻናት ለሚገል፣ አገርን በአጽሟ ለሚያስቀር ዘራፊ በካድሬነት፣ በጆሮ ጠቢነትና በሎሌነት ከሃያ ዓመታት በላይ ያገለግሉ ኖሯል?
የአቢይና ለማ እስስት ቡድን ስንቱን ቦርጫምና ደንደሳም ተቃዋዊ ከአውሮፓና ከአሜሪካ “ኢሀዴግ ይውደም” የሚለውን መፈክሩን አስትቶ፤ በሙጫ ምራቁ አገርሮና ሬሳ አስመስሎ በተስፈንጣሪ ምላሱ እየሳበ ወደ አፉ አስገብቶታል፡፡ ይህ እሬሳ ተቃዋሚ ቡድን ድሮ ሁለት ጋዜጠኛ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ሰልፍ ይወጣ እንዳልነበረ ሁሉ ዛሬ በእስስት ሙጫ ተጨማዶ ወደ እስስቶች አቢይና ለማ አፍ ስለገባ ከመተከል፣ አሶሳና ኢሉባቦር ሕዝብ ንብረቱን እየተቀማ ሲሰደድ ትንፋሹ ጠፍቷል፡፡ ጎንደር ሲቃጠልና በአስር ሺዎች ሕዝብ በገዛ ቅየው ስደተኛ ሲሆን የድንጋይ ያህል እንኳ ድምፅ ማሰማት ተስኖታል፡፡ ቡራዩ የዘር ማጥፋት፤ ለገጣፎ የዘር ማጥራት ወንጀል ሲፈጠም፣ አዲስ አበባም የዘር ምህንድስና ወንጀል ሲጧጧፍ ምስጥ እንደ ቆፈረው አፈር ከአቢይና ለማ አፍ ኮይሶ ጉሊት ሆኖ ተጎልቷል፡፡
አማራ ሆይ! “ከሁሉም በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ”ን እየዘመርክ የጅቡንም የእስስቱንም ትክክለኛ ኢላማ ማወቅ ተስኖሃል፡፡ የጅቡም ሆነ የእስስቱ ኢላማ ኢትዮጵያ ሳትሆን አንተ መሆንህን ማወቅ አቅቶሃል፡፡ ዘርህ የመከነው፣ ዓይንህ የጠፋው፣ ህብለሰረሰርህ የተቆረጠው፣ ቆዳህ የተፋቀው የኢትዮጵያ ሳይሆን ያንተ ነው፡፡ አያቶችህ በደማቸውን ካስከበሩት ሃረርጌ፣ አርሲ፣ ሲዳሞ፣ ከፋ፣ ኢሉባቦር፣ ወለጋና ለገጣፎ ቤትህ እየፈረሰና በእሳት እየተቃጠለ እንደ ወፍ የተባረርከው አንተ እንጅ “የብሔር ብሔረሰቦች አገር” ኢትዮጵያ አለመሆኗን እንዴት አጣሃው? አንተ እስከሌለህ ወይም ያለ ተፈጥሮህና ታሪክህ አንገትህን ደፍተህ እስከኖርክ ድረስ ኢትዮጵያ ለእነሱ የጫት ሱስ መሆኗን መገንዘብ እንዴት አቃተህ? ቆራጪና ፈላጭ እስከሆኑ ድረስ እንኳን ኢትዮጵያን አፍሪካንስ አንድ አርጎ መጋጥ የማይጠሉ መሆናቸውን ማጤን እንዴት ዳገት ሆነብህ? ያለተጋሪ ለመጋጥ ተኩላዎችን ሲያባርሩ የኢትዮጵያን ጀበና የሰበሩት ጅቦችስ ብቻቸውን በጋጡበት ሰዓት የቀረችዋ ኢትዮጵያ ትበተን ሲሉ መቼ ሰማህ? እና አሁንም ጠባቸው ከአንተ እንጅ ከኢትዮጵያ እንዳልሆነ ትጠራጠራለህ?
አማራ ሆይ! ወደ አንተ ሲመጡ ጃኖ እየለበሱ አንተን ለመምሰል በሚጥሩ፣ ዳሩ ግን አድብተው ምላሳቸውን በጀት ፍጥነት ባንተ እንደ ጦር በሚቀስሩ፣ ምላሳቸውን ቀስረውም “ኢትዮጵያ ሱስ ናት! ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያዊ” በሚባል አደገኛ ሙጫ እንደ ቆርበት በሚያጨማድዱ፣ አጨማደውም ከአፋቸው አስገብተው ሊውጡህ በተዘጋጁ እስስቶች አፍ ገብተሃል፡፡ ሳይውጡህ እንደ አያቶችህ “ሞገደኛው!” ብለህ ባስቸኳይ መውጣት ይኖርብሃል!
* ይኸንን ይመልከቱ https://www.futurity.org/chameleon-tongue-speed-1083272/
የካቲት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

2 COMMENTS

 1. የፌደራሊዝምና ከተሜነት(Urbanization) እውነቶች በክፋት ሲዝመትባቸው -በዲጎኔ ሞረቴው- አሜሪካ
  በሃገራችን ኢትዮጲያ ለዘመናት የነበረውን ፖለቲካዊና መንግስታዊ ጽልመት ፈጣሪ የቀየረባቸው መልካም መሪዎች መታየታቸውን ከሊቅ እስከደቂቅ ከጳጳስ ደቀመዝሙር እስከኢማም ሙሻዘር በመመስከር ላይ ናቸው:: ሆኖም ግን ይህንን ለውጥ በጥቅምና ህልውናቸው ከመጣባቸው አንስቶ የለውጡን ዜናዎች ለትኩረት ፈላጊነት የሚጠቀሙ ጭምር በሂደት የሚታዩትን ጠቃሚ እውነቶች በየወቅቱ ከሚነሱ ትኩሳቶች ጋር በማያያዝ ያለመረጋጋት ያለመተማመን የሚፈጥሩ መኖራቸውን የሚረሱ ከታሪክ የማይማሩ ናቸው::
  የፍልስፍናናን ስነመለከት አዋቂው ቅዱስ አውግስቲን የተናገረው ለዚህ ጥሩ ገላጭ ነው::“We are too weak to discover the truth by reason alone” እውነትን በምርምር (አመክንዮ) ብቻ ለመረዳት በጣም ደካሞች ነን::
  ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌላ የሚበጀውን እውነት በውስን አእምሯቸው በሚገምቱት ምክንያት ብቻ ሊረዱት በጣም ደካሞች ናቸው:: ምክንያቱም ስጋ ለባሹ በምርምር በጎ ነገሮችን ለዚህች ምድር ቢያስገኝም ቅንነትን ከፈጣሪ ካልታደለ ዘወተር በጥርጣሬ ለራሱ እውነት በሚመስለው ሃስት ራሱንም ሌላውንም ይበክላል ያላስፈላጊ ጥላቻ ይዘራል ወይም የቀደመ ጥላቻን ይቀስቅሳል ያስፋፋል::
  ጸሃፊው በዘመነ ደርግ በኮሌጅ ሳለ በVilagization በጣም የተጎዱና በህዝብ ብዛት የተፈጥሮ ሃብታቸው የተመናመነ ወገኖችን በተበታተነ ስፍራ የሚኖሩትን በአንድ አካባቢ በማስፈር ለመሰረታዊ ፍላጎቶች አቅርቦት የተመቸውን በተፈጥሮ ወደተሻሉ ስፍራዎች በመንግስት አስገዳጅነት ይሰፍሩ ነበር:: ሆኖም ግን በወቅቱ ውዝግቦች ተነስተው የጦፈ ውይይት በዚያ ዘመን ሳይቀር ሳይፈሩ በሚሞግቱ ሲቀርቡ ነበር:: በምክንያት ብቻ ቅንነት በሌለበት በሚደረግ ጥረት እውነቱ ሳይደረስበት አመታት ሲያልፉ ቆይቶ በተደረጉት ስራዎች ኑሯቸው ተሻሽሎ በዚህ ዘመን ለምስክርነት የበቁትን ለመስማት ሲበቃ በሌላው ወገን ተቃውሞ የቀረበበት ስጋትም በመታየት በመፈናቀል ሰዎች መጎዳታቸውን ከሚዲያ ተሰምቷል:: በዚያ ዘመን በተግባር ይውል ዘንድ የተዘመተበት ቪሌጃይዜሽን በብዙ ምክክር በፈቃደኛነት ተነሺዎቹም ሆነ ተቀባዮቹ ማህበርሰሰቦች በመስማማት ቢያደርጉት ኖሮ የመስራት የዳበረ ታሪካዊ ልምድ ያለው የህብረተሰባችን ክፍል ለዘመናት ከተጎሳቆሉ ስፍራዎች በመነሳት በተፈጥሮ በታደሉ ስፍራዎች ያለውን መልካም ሁኔታ በመጠቀም ለሀገራችን ትልቅ በረከት ለሁሉም በሚመች መልክ ባፈራን ነበር::
  ዛሬም የለውጡ መሪዎች በብሄር የተደራጁ ፓርቲዎች ወደሃገራዊነት ካላደጉ በብሄርና ዘር ስም ሃገር የመም ራቱ ሃሳብ ሊተገበር የማይችለውን ያሳሰቡትን ለብዙ ሃገሮች ታላላቆቹ አሜሪካና ጀርመን ለኣፍሪካና እስያ ሃገሮች ናይጀሪያ ፊሊፒንስና ኬንያ ለተመሳሳይ ችግሮች መፍትሄ የሆነውን የፌድራል ሲስተም ከወያኔ የጎሳና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ብቸኛው ስንኩል ፌደራል ተብዬ ሽንፈት ውድቀትጋር ማያያዛቸውና ፌደራሊስም በገዥው ፓርቲ ተሰረዘ ማለታቸው ብለው ማሳታቸውን ሳይ ብርቱካን መስሏቸው እምቧይ የገመጡትን የልጅነቴን ዘመን አብሮ አደጎቼና ያስታውሰኛል::
  በተመሳሳይ መልኩ ዶ/ር ለማ መገርሳ አኩራፊ የፖለቲካ ድርጅትች ወደሰላሙ ሂደት ይመለሱ ዘንድ በቅንነት ከወራቶች በፊት ያቀረቡትን የከተሜነት (Urbaniztion) በጎ ሃሳብ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉትን ወደኣአዲስ አበባና አካባቢው ይሰፍሩ ዘንድ የተደረገውን ተገቢ ድጋፍ ከሰሞኑ የለገጣፎ እኩይ ድርጊት ራሳቸው ዶ/ር ለማ ለጥፋቱ ተጠያቂው የአካባቢው መስተዳደር መሆኑን የገለጹበት እያለ የቆየውን ዜና ተርጉመው በሌላ ኣውደህሳብ ላይ የቀረበ ደጋግመው የከተሜነት (Urbanization) ጥቅም የገለጹበትን የአንድ ብሄር መስፋፋትና የበላይነትን በመንግስት ስልጣን መጠቀም አስመስሎ ሰሞኑን ሲሰራጭ በጣም ያሳፍራል:: ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ውገኖቻችን በጎረቤት በጅቡቲ በኬንያ በርህራሄ በፍቅር ሲቀበሏቸው ማናችንም ስደተኞች ባለንበት ሃገር በፖለቲካ ይሁን በኢኮኖሚ በረደሰብን የተፈናቀልን የተሰደድን የተቀበሉንን ማነጻጸር ያቅተን ዳያስፖራዎች የዚህ የክፉ አሳች ፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆናችን ያሳዝናል::
  ስለዚህ መገናኛ ብዙሃን ለሰላምና መረጋገት ለሰው ልጆች በጎነት የተፈጠረና የሚሰራውን ያህል ይህን መስሉን የበጎ ለውጥ ሂደት መሪዎችን ሃሳብ ከሁነታው በማጣረስ ማቅረብ ማሳት ይቆም ዘንድ በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የቀረቡትን ሁሉ ከማግበስበስ በመርህ ጥያቄዎ መቼ ለምን እንዴት ማን ምን ብለን ዜናውን እንፈትሽ ዘንድ አሳስባለሁ::

 2. What is wrong with it if we resettle the Oromo in Finfinne and its surrounding. Shall we ask for a permission from the offspring of the ex-neftengas?  You are poor and stupid. Today you are not in the Menilik’s era. No inch of the Oromia’s soil will be given to the greediness. Your milcious tactics will not work any more, not only in Oromia, but also all over Ethiopia.The Oromo people needs no permission from anybody to resettle the Oromo within the territories of Oromia. Also we will not send our kids and elders to beg you and resettle them in Bahir Dar or Gonder. 

  Since 1991 more than 3 million Oromos were pushed out of  Finfinne and its surrounding in 4 directions. They were also robbed off their land & were made strangers in the same city. Now can you say why you don’t question that as a demographic engineering angaist the Oromo but this one is against you?

  Why do you cry always loudly? Why do you misuse the hospitality of the Oromo? We have been hosting and treating all ethinc groups from different  parts of Ethiopia all over Oromia equally with love and respect. The other Ethiopians are very thankful for our heartfelt hospitality and empathy. But you have no the terminologies of thankfulness, appreciation, gratefulness, recognition and valuations in your culture and vocabulary. You are just possessed by the spirit of greediness and egocentricity like tapeworms. In simple language you are inhuman. The racists are aways like snows. They can be dissolved with a minimum heat.  That is why the ideologies of the Apartheid, Nazi and segregation were eradicated. Likewise the ideologies of the ultra nationalists in Ethiopia will be eroded soon. Watch out!

  The Oromo and other subjugated peoples of Ethiopia have been fighting such backward mentalities and ideologies. Our fighting will be continued until not only the villages and towns, but also all languages  and cultures will be free and flourished. Period!

  Finally, there is  no wonder that the Parasites cannot understand mutual understanding and benefits. They are very selfish and self-centered. They want to have everything alone. First of all, they want to dehydrate their hosts step by step. Finally, they try to kill their hosts if they can. That is what we have been witnessing in Ethiopia in the last 140 years. Human parasites.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.