ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለአዲስ አበባ ወንዝ ዳር ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት አዘጋጁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአዲስ አበባ ወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት አዘጋጁ።

ለእራት ምሽት ዲፕሎማቶች፣ የኩባንያ ስራ አስኪያጆች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እና ሎሎች አካላት እንዲሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።

የእራት ምሽቱ ለሸገር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር በሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱ ነው የተነገረው።

ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ጥሪም አዲስ አበባን ንፁህና አረንጓዴ ለማድረግ ተሳትፏችሁ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ያስችላል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፋችሁ ይህን ታላቅ አላማ ስኬታማ በማድረግ የመዲናዋን ነዋሪዎች አኗኗር ለመቀየር ወሳኝ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

በአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ የምታደርጉት ተሳትፎ ለቀጣይ ትውልድ ውብ ከተማን ለማስተላፍ በዋጋ የማይተመን ነው በማለት ገልፀዋል።

በዚህ የእራት ምሽት አንድ እራትን 5 ሚሊየን ብር ለመሸጥ ዋጋ ተቆርጦለታል።

የአዲስ አበባን ዋና ዋና ወንዞች ተፋሰስ ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

——————————————–

የአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማትን ለመደገፍ የቻይና መንግስት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማትን ለመደገፍ የቻይና መንግስት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

ለዚህም የቻይና መንግስት የባለሞያ ልዑካን ቡድን ከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት በገንዘብ እና የቴክኒክ ዕገዛ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር ውይይት አድርጓል።

በዚህ መሰረትም የቴክኒክ ቡድኑ የቻይና መንግስት ፕሮጀክቱን የሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ጥናት እንደሚያደርግ የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የአዲስ አበባን ዋና ዋና ወንዞች ተፋሰስ ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው።

አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ፥ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል።
ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

FBC

2 COMMENTS

  1. ህዝብ ከቀየው እየተፈናቀለ የወንዝ ዳር ግንባታ ምን የሚሉት ፕሮጀክት ነው? ዶር አብይ የኢትዮጵያን ህዝብ ያውቃል ብዬ አስቤ ነበር። ለካ ህዝቡን አያቀውም፥ የህዝቡን ጉድለት አያውቀውም፥ የህዝቡን ኑሮ ደረጃ አያውቀውም። ህዝብ ውሃ ለማግኘት ጀርካን ይዞ ከሰፈር ሰፈር ሲዞር እርሱ በጀርባቸው ውሃ ተሸክመው በዚያ መንገድ እንዲሄዱ ነው እንደ መንገድ የሚገነባው? ሰላም አጥቶ በስጋት ኑሮውን ለሚገፋው ህዝብ ዋስትና ሳይሰጥ፥ በአዲስ አበባ መብራት ያጣው ስንት እያለ የወንዝ ዳር መዝናኛ? እባክህ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ሥራበት። ኦሮሞ ብቻውን አይደለም የተጎዳው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ ያልተጎዳ፥ ያልተዘረፈ፥ መብቱን ያልተነፈገ ማን ነው? እኔ ግራ የሚገባኝ ኢትዮጵያዊነት ኦሮሞን ማስቀደም ነው እንዴ?

  2. @ T. Goshu

    The people have to wake up, make demands and go to the streets and fight.

    Abiy is no longer trusted, he is tribalist and anti-Ethiopian.

    He cheated the people by preaching Ethiopiawinet, but the event in Legetafo, hiring policies and other examples exposed the true face of Abiy.

    Now the people should demand his resignation.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.