#ግፍ #ወሰቆቃ ዘ #ራያ ራዩማ፡- ክፍል ሁለት ( የኢጥዮጵያ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ጭምር ያገናዘበ)

#በራያ አከባቢ በይበልጥ ቢሆንም በአጠቃላይ በሃገሪቱ ያለው የትምህርት ሁኔታ ትውልድን የመግደል ዘመቻ እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ በተለያዩ ተጨባጭ ገጠመኞች፣የተማሪዎች፣ የወላጆች እና የምሁራን ጽሑፎችን አጣቅሸ ያቀረብኩት በራያ ህፃናት የሚደርሰውን ግፍና በደል እንዲሁም ትምህርት እንዴት የአምባገነኖች መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል #ከዶ/ር #ፀሐይ ጀምበሩ የተወሰደ ጽሑፍ በምሳሌነት አቅርቤ የጻፍኩት ጽሑፍ ስለሆነ በጥሞና #አንብቡልኝ፡፡ ለሌሎችም #አጋሩት፡፡

  • ጉዳዩ የሃገር እና ፈጣን ምላሽ የሚያሻው ጉዳይ ስለሆነ ለክቡር ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድም በእጅጉ ይመለከታል፡፡
  • በተጨማሪም ጉዳዩ የሃገር እና የትውልድ ጉዳይ ነውና ማንኛውም ማንበብ የሚችል ሁሉ ያንብበው፡፡ ያነበበም ለማያነበው ያሰማ!

#መልካም ንባብ ተመኘሁ!

ሰቆቃ 1፡- የ8ኛ ክፍል ተማሪው ተስፋ ያስቆረጠው ምክንያትና የልጁ አገላለጽ

“ቧይ! ወዲ አባዲ ሕደግዮ ግዲ! ( እዲያ! እኔ የአባዲ ልጅ ተይዋ እንግዲህ!)”

********

ላይ የተገለጠው #የምሬትና #የብስጭት አገላለፅ አንድ ምስኪን ወንድማችን በምሬትና በተስፋ መቁረጥ የተናገረው ንግግር ነው፡፡ ልጁ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ሲሆን የአካል ጉድለት (Physical impairment) ያለበት እንደልቡ በነፃነት መንቀሳቀስ የማይችል ሁለት እግሮቹ በልጅነት ልምሻ  (polio)የተጎዳ ልጅ ነው፡፡ ከዚህ የአካል ጉድለቱ በላይ የሚማረው ትምህርት ብዙ በማያውቀውና በአፍ መፍቻው ባልሆነ የትግርኛ ቋንቋ ነው፡፡ ስለሆነም እንደ ሌሎቹ ደኞቹ ተራርጦና ጠይቆ ወደቤተመጽኃፍትአገላብጦ ችግሩን በቀላሉ መፍታት የማይችል ብዙ ድጋፍና እገዛ የሚሻ ልጅ ሆኖ እያለ የስርአተ ትምህርቱ አለመዛመድ ከዕንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሆነበትና የ8ኛ ክፍል ምኒስትሪን 2 ጊዜ ወደቀ፡፡ ከዚያማ ተበሳጭቶ #“ቧይ ወዲ አባዲ ሕደግዮ ግዲ!” አለ ይባላል፡፡  ወደ አማርኛ ሲመለስም #“እድያ! እኔ የአባዲ ልጅ ተይዋ ታድያ” ማለቱ ነበር፡፡ እንግዲህ ተመልከቱ ትምህርትን ነው እንዲህ #የፎከረባት፡፡ ምን እሱ ብቻ ስንት አማርኛና በኦሮምኛ አፍ የፈቱ የራያ አላማጣ፣ የራያ አዘቦ እና የራያ ኮረም ተማሪዎች እንዲሁ ተሰቃይተዋል፡፡ ትምህርት አቋርጠው ወደ አረብ ሃገር ለመሄድ የባህርና የውቅኖስ ሲሳይ ሆነዋል፡፡ የተሻገሩትም ስንቱ ተንገላተዋል፡፡ ስንቱ ሞተዋል፡፡ ገሚሶቹም 21ኛ ክፍለ ዘመን #አንድም ህፃንና ልጅ #ከትምህርት #ገበታ #እንዳይቀር #“No child left behind schooling” ተብሎ በሚፎከርበት ዘመን ላይ ተቀምጠው ወደ አባቶቻቸው #የግብርና ሙያ ተመልሰዋል፡፡ ገበሬ መሆናቸው ባልከፋ፤ ነገር ግን የወላጆቻቸው መሬትና ይዞታ በዘመነኞቹ ተቀምተዋል፡፡ የሚያርሱት የሚያንደፋርሱት ያባቶቻቸውን ርስት አጥተዋል፡፡ የነዚህ ወጣቶች እጣ ፈንታ ውለው አድረው ተጨንቀው ተጠበው አማራጭ ሲያጡ ያው መከረኛ ጅዳ ነው፡፡ ካልሆነም ስራ ፈትቶ በ20 ዓመታቸው የወላጅ ሸክምና ተጧሪ መሆን ነው፡፡

 

#ሰቆቃ 2፡- #“የትግርኛን ቋንቋ #ተገድጀ #የዋጥኩት #ክኒን እንደሆነ ቆጠርኩት” ያለችው ተማሪ ምክንያት

************************

በተጨማሪም አንዲት በቅርብ የማውቃት ታዳጊ ልጅ እንደዚሁ እንደ #ወዲ አባዲ 2 ጊዜ 8ኛ ክፍል ወድቃለች፡፡ ልጅቱ እንኳን ለኛ ሃገር የንባብ ትምህርት አንብቦ መፈተንና የሰለጠኑትና ሮኬት የሚያመጥቁት ትምህርት እንኳ ቢሰጣት መረዳትና መስራት የምትችል በጣም ፈጣንና ምንም ጉድለት የሌለባት ልጅ ነች፡፡ ከዚህ የ8ኛ ክፍል በቋንቋ የታጀበ መሰናክል ፈተና መውደቅ በቀር በሌሎች #የህወት #ክህሎቶችና ማህበራዊ መስተጋብ[ እጅግ ፈጣን ነች፡፡ የመደጋገሟ ምክንያቱ እሷም ወላጆቿም አላወቁትም ነበር፡፡ ጉዳዩ የገባው አስተማሪዋ ግን የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ አማርኛ መሆኑ ተፅእኖ ሳያሳድርባት እንዳልቀረ ይገም   ትና ብዙ ጊዜና በተጨማሪ ድጋፍ የትግርኛ ቋንቋን እንድታጠና መከራት፡፡ ልጅትም አማራጭ ስለሌላት ይህንኑ አደረገች፡፡ አስቡት እንግዲህ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር አንድ አመት ከማሳለፍ ይልቅ ተገዳ ተማሪበት ተብሎ በተጫነባት ቋንቋ ጊዜዋን ከንቱ አባከነች፡፡ ብዙ ቢያደክማትም እንደነገሩ አድርጋ በ3ኛ ጊዜ አለፈች፡፡ በመጨረሻም ምሬቷን እንዲህ ገለጠች  አሉ፡- “ማለፉንስ አለፍኩት ነገር ግን #“የትግርኛን ቋንቋ #ተገድጀ #የዋጥኩት #ክኒን እንደሆነ ቆጠርኩት” ብላ ጓደኞቿን ነገረቻቸው፡፡”  እንግዲህ እንዴት እስከ 8ኛ ክፍል እያለፉ መጥተው እዚሁ አቃታቸው የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ የአሁኑ የኢትዮጵያችን ትምህርት እንዴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡

  1. ከ1-4ኛክፍል የነፃ መዛወር (free promotion) የሚባል ጣጣ አለ፡፡ ይወቅም አይወቅም ሁሉንም ማሳለፍ ተፈቅዷል፡፡
  2. ከ5-7ኛ ክፍል ቢሆንም ያው ተመሳሳይ ነው፡፡ አንድ የጨርቅ ኳስ ሰርቶና በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረገ የሰውነት ማጎልማሻ  የትምህርት አይነትን መስፍርትና የሚጠበቀው ክህሎት ስላማላ ማለፍ ነጥብ ያገኛል፡፡ ስእል መሳይ ወይንም የእጅ ስራ ከሰራ ነገር ሰርቶ በሄደ ቁጥር የአከባቢ ሳይንስ/ የጅኦግራፊ ትምህርት ማለፍያ ነጥብ ያገኛል፡፡ በሌሎች የትምህርት ዓይነቶችም ቢሆን  የቡድን ስራ ሰርቶና አሰርቶ ማለፍያ ነጥብ ያገኛል፡፡ ከዚህ የዘለለው ደግሞ መምህሩ እንዳይገመገምና ከስራው እንዳይባረር ለሁሉም ተማሪዎች ቦነስ ማርክ ሰጥቶ አልፋችኋል ይላቸዋል፡፡ ይሄው ነው እንግዲህ ምክንያቱ ከ1-7ኛ ክፍል የተማሪው መነዳቱ፡፡

*************************

ቀጥሎ የሚነሳው ጥያቄ 8ኛ ክፍል የሚሉት መሰናክል እንዴት መጣ የሚለው ነው

***************************

የዚህ ጉዳይ ደግሞ እንዲህ ይመስለኛል፡፡ አንደኛው ነገር እነዚህ የቡድንና የተግባር ስራዎች አለመኖራቸው ሲሆን፤ በሁለተኛነት ሊጠቀስ የሚችለውና ዋናው ምክንያት የሚመስለኝ የ8ኛ ክፍል ፈተና በፈተና አውጭ መምህራን /የፈተና ሙያተኞች ሲወጣ ቋንቋው  በአንድ አከባቢና እነሱ መሆን አለት ብለው የሚያወጡት እንኳን ለራያ ልጆች፡- በራይኛ፣ በአማርኛና በኦሮምኛ አፋቸውን ለፈቱ ቀርቶ ለመቀሌ ልጆችም እንግዳ በሆኑ ቃላትና ስነ-ቃሎች ነው ፈተናው የሚሆነው፡፡ ታዲያ ተማሪዎቹ ለትምህርቱም ለቋንቋውም ባእድ ሆኑ ማለት አይደል እንዴ? ይኸው ነው እንግዲህ ምስጢሩ፡፡

 

#እዚሁ ላይ መታወቅ ያለበት ግን የመንጃ ፈቃድና የኮብልስቶን ስራዎች መስፋፋት የትእምት (EFERT) ድርጅቶች አገልጋይ ወዛደሮችን ለመፍጠርና ለትውልድ ሳይሆን ለግልና ለተወሰኑ ባለስልጣናት ለማገልገል የሚመች ስርዓተ ትም/ት ነው የተዘጋጀው፡፡

********

#ሰቆቃ3፡- የወላጅ ሰቆቃ (#“ልጆቻችን #በዱር #መካከል #እንደቆመ #ሰው #እመለከተዋለሁ፡፡” ያሉት አባት ወግ

*******************

በራያ አዘቦ ጨርጨር- አንዲት የገጠር ቀበሌ የሚኖሩ አንድ ትልቅ አባት ያሉትን አባባል ከጻፍኩት ሁሉ ሐተታ የበለጠ ገላጭ ሆኖ አገኘሁት፡፡ እንዲህ አሉኝ “ልጄ የዘመኑ ትምህርት እኮ ከንቱ ነው፡፡ ልጆቻችን እኮ ምንም አያውቁም፡፡ ፊደል እንኳ ሳይለዩ እስከ 4ኛ ክፍል በጅምላ እየነዱ አሳልፈው ችግር ላይ ጣሏቸው፡፡ የኔ ልጅ እንደዚያ ሲሆንብኝ 2ኛ ክፍል መልሸ አስገባሁት፡፡ ምን አታከተህ ልጆቻችን #በዱር #መካከል እንደቆሙ አስተውላለሁ፡፡ መውጫ መሄጃ አጥተዋል፡፡ ወደፊት እንዳይሄዱ በምን ይለፉ ዱር ነው፡፡ ወደ ኋላ እንዳመለሱ ዱር ነው፡፡” አሉኝ፡፡

በጣም የሚገርመው ነገር ወደኋላ የመመለሱ ጉዳይ ዱር ያሉበት አገላለጽ በይበልጥ ገራሚ ነው፡፡ እንዴት መሰለላችሁ? አልቻልኩምና ተመልሸ ከታች ልጀምርና አጣርቸ/አውቄ ልለፍ ቢባል እንኳ አይፈቀድም ማለታቸው ይመስለኛል፡፡ እሳቸውንም  የመለሱላቸው በአከባቢው በጣም ተጽእኖ ፈጣሪና የሃገር ሽማግሌ በመሆናቸው ሌላ የህዝብ እምቢተኝነት እንዳያስከትልባቸው ፈርተው ነው እንጂ አይፈቀድም፡፡

በቀድሞ ጊዜ ተምረው ያቋረጡ እንዲውም ተምረው ጨርሰው ወደ ንግድና ወደ ግብርና የተሰማሩ ወላጆች  የተወሰኑ ቢኖሩም እንኳ ልጆቻቸውን ማስጠናት ቀርቶ ማመልከቻ እንኳ ጽፈው ማስገባት አልቻሉም፡፡ የተማሩ ማሃይሞች አድርገዋቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ መጻፍና ማንበብ አቀላጥፈው የሚችሉት በራሳቸው የራይኛ አገላለፅና በአማርኛ ነው፡፡

********

ታዲያ ይህ ነገር የአንዴ ክስተት ነው ወይንስ ሆን ተብሎ ታስቦበት ነው የሁላችንም ግራ መጋባትና የዘወትር ጥያቄ ነበር፡፡ ከዚኸው ጥያቄ ጋር የሚሄድልኝ አንድ ርእስና መጽሀፍ  ትዝ አለኝ፡፡ ነብሳቸውን ይማርና በእውቀታቸውና በዝናቸው ከተማሪነት እስከ መምህርነት/ የዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንትነት የሚታወቁ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና መምህር የነበሩት አሁን በመከታተል ላይ ያለሁትን የ3ኛ ድግሪየን ያስተማሩኝ ተወዳጅ አስተማሪ ዶ/ር ፀሐይ ጀንበሩ ከፃፉት #“የአንጎሌ ሁካታ (ህይወቴን ልተንትን)” የተሰኘው መጽሀፍ ውስጥ በጣም ተገርሜና ተመስጨ ያነበብኩት አንድ ርእስ ነበር፡፡ እሱም #“አደድቦ መጣል” ይላል፡፡

አዚሁ አደድቦ መጣል ከተሰኘው የዘመኑን ጉድ ፍንትው አድርጎ ከሚያሳው ጽሑፍ ቀንጨብ አድርጌ እነሆ፡-

 

ሰቆቃ 4፡- ስርዓተ – ትምህርቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በአጠቃላይ የራያ ተማሪዎች በከፋ ሁኔታ መበደላቸው

#አደድቦ መጣል (ከዶ/ር ፀሐይ ጀምበሩ መጽሃፍ የተወሰደ)—( ከማቀርበው ጉዳይ ስለተገናኘ- በምሳሌነት የቀረበ)

************

#አደድቦ መጣል በዚህ መልኩ አብራርተውታል ምሁሩ (ፀሐይ፣ 2008፣ ገፅ 295)፡-

በጸረ-ምሁርነት መንፈስ ተገፋፍቶ የትምህርቱን የተወሰነ የማይፈለግን ክፍል በመምታት ሌላው ክፍል እንዲቀጥል ማስደረግ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የታሪክ መማሪያን በመቀየር ሌሎችን መጻህፍት እንደነበሩ በማስቀጠል፡፡ ሆኖም አዲሱ ትውልድ በሁሉም ፈርጆች የማሰብና የመፍጠር አቅሙ እንዲቀንስ፣ አሮጊየው ትውልድ ደግሞ የሚያውቀውን እንዲጠራጠር እንዲያውም ከተቻለ ‘እንዲረሳ’ ለማድረግ ሚለፉበት አካሄድ ነው እንግዲህ አደድቦ መጣል (dumping down) በማለት ይጠሩታል፡፡ አደድቦ መታል በምሁራዊ ደረጃ የሚሰጥ ትምህርትን፣ ስነ-ጽሑፍን ወይም ባህልን ሆን ብሎ ማቀጨጭ እና መማደሆር ነው፡፡ አደድቦ መጣል እንደ ኢላማ ለተደረገው መስክ ዝቅ እንዲል የሚፈለግበት ደረጃ ቢለያይም ፣ በሁሉም መስክ ተጠየቃዊ አስተሳሰብን የሚያቀለል፣ የቋንቋንና መማርን ምሁራዊ ደረጃዎች ይጥላል፡፡

ልብ ይሏል እንግዲህ እላይ ካነበብነው የአደድቦ መጣል መርህና ስልት የምንረዳው በሃገራችን ለ27/8 ዓመታት የመጭውም ብዙ የተለያ ባይመስልም፤ የአደድቦ መጣል መርሆን እየተተገበረብንና እኛው አስተማሪዎችም አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው ይህንኑ ተግባር እያከናወን እንደመጣን (የመጭውም ምን ታውቆ?) እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም፡፡ የታሪክ ትምህርት በየደረጃው ከ1ኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ይሰጥ አልነበረ እንዴ! ታድያ ለምን ቀረ? የእጅ ስራ ትምህርት ይሰጥ አልነበረ! የጥበብ ትምህርት አሁን ይበረታታልን? ሰው እንደ ልቡ መጻፍና መተቸት ይችላልን? በጭራሽ እንዴት ተደርጎ! ታድያ ትውልድን አደድቦ መጣል ከዚህ ወድያ ምን ይምጣ? ታሪክን ካልተማሩና ካላወቁ፣ ጥበብን ካልሰለጠኑና ካልኖሩበት ምርምር ካላካሄዱ ምኑን ተማሩት? ከሰሩ እንጂ!

#ከዚህ በመቀጠል አስገራሚ የሆነው #ትምህርትን #አስመልክቶ #ለአምባገነኑ #መሪ #የተፃፈ #የተግባር #መመሪያ ፀሐይ (2008፣ገፅ 301-305) ያለውን ብቻ ደግሞ እንመልከት፡፡

—————————————–

#ትምህርትን አስመልክቶ #ለአምባገነኑ #መሪ የተፃፈ #የተግባር #መመሪያ

#መግብያ፡- መንግስትህ አገርህን ለመምራት ከደህንነትና ከወታደራዊ ሲስተምህ በተጨማሪ ትምህርትህን ማካሄድ  ወሳኝ  ተግባርህ ነው፡፡ የትምህርቱን ስርዓት ስትቀርጽ በአንጎልህ ውስጥ ባስቀመጥኸው ዓላማ አንፃር በጥንቃቄ መሆን አለበት፡፡  . . .  ትምህርቱን እንድታሻሽል ተጨባጭ ግፊት ገጥሞሀል፡፡  በእንደዚህ ዓይነት ጫና ወቅት መንግስታት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ለመታየት ይጥራሉ፡፡ አንተም ት/ቤቶችህን እያሻሻልህ  እንደሆነ ለማሳየት  ማቀድ ይኖርባሃል፡፡ ነገር ግን ተጠንቀቅ ጥራት ያለው ዙርያ አቀፍ ትምህርት ህብረተሰብህን ሊለውጥ የሚችል አደገኛ ኃይል ነው፡፡ በተገባ ሁኔታ የተማረ፣ ለአዳዲስ ነገሮች ጉጉ የሆነ እና በቴክኖሎጂ አቅም የተላበሰ ህዝብ ለእንዳንተ አይነቱ በሥልጣን ለረዥም ዘመናት መቆየት ለሚፈልግ መሪ አደጋ አለው፡፡ ስለዚህ ሚዛናዊነት ያለው ተግባር ፈጽም፡፡

ምንም እንኳ ባለፉት ጊዜያት በርካታ አምባገነኖች ትምህርትን የሚሉት ሁሉ አግደው ህዝባቸው መሀይም ሆኖላቸው በዘልማድ አፈር እንዲገፉ ወይም በገበሬ ማህበራት ተሰባስቦ እንዲያርስ ቢያደርጉም ፣ ይህ አካሄድ ግን ለአንተ መልካም አማራጭ አይደለም፡፡  አንተ ከነሱ የተሻልህ ስለሆንህ የምትሻቸውን ክህሎቶችንና አመለካከቶችን ህዝብህ እንዲያውቅልህ ለማድረግ ትችላለህ፡፡ ትእዛዛትህን እና በትክክል ለመከተል የሚያስተምር፣ ሽምደዳን የማስተማሪያ ዘዴ አድርጎ በተከታታይ ተማሪዎችህን የሚፈትን እና የምትፈልጋቸውን ኢንፎርሜሽኖችን ልቆ ለአንበለበለ ተማሪ እውቅና እና ሽልማት የሚሰጥ ሲስተም ከስልጣንህ ላይ ያኖርሀል፡፡ በዚህም ህዝብህ ልጆቹ ተግባር ያለው እውቀት እያገኙለት እንደሆነ አምኖ ይደሰትልሃል፡፡

—————————

­­­­­

#አደረጃጀት፡- የአገሪቱ ህጻናት ሁሉ ት/ቤት ገብተው እንዲማሩ ግዴታ አብጅ [No child left Behind]፡፡ #ህጻናት #እቤት #ከዋሉ #ከወላጆቻቸው #የማይፈለጉ #ነገሮችን #ሊቀስሙ #ይችላሉ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት ልከው አንተ ያሰብካቸውን ዝንባሌዎች፣ እሴቶችና ይዘቶችን እንዲላበሱ ካደረግህ ከወላጆቻቸው ስለምትነጥላቸው የማያስፈልጉ እሴቶችን አያሰርጹብህም፡፡ ህጻናትን በእድሜ አደራጃቸው፤ ይህም ከአቻዎቻቸው ጋር አብረው ለመስራትና ለመተባበርና ለመስራት ስለሚስችላቸው በኋላ ጊዜ #ለግዴታ #ወታደራዊ ስልጠና ስትልካቸው ተግባርህ ያቀልልሃል፡፡ ሲስተምህ #በልጆች #የግል #ችሎታና #ፍላጎት ተመስርቶ መደራጀት #የለበትም፤ አደረጃጀታቸው ከህዝብህ፣ #ከጦርህና #ከካምፓኒዎችህ ጋር የሚጣጣም ይሁን፡፡ እንደሌሎች ተማሪዎች ሁሉ ደከም የአሉ  እና ብሩህ ተማሪዎች በአንተም ት/ቤቶች ስለሚገኙ፣ አይኖችህን ከ #‘ጎበዞቹ’ ተማሪዎች ላይ አትንቀል፡፡ የአሉህ አማራጮች ጥቂት ናቸው፤ ወይ እነዚህ ጥቂት ተማሪዎች ከየት/ቤቶች አስለቅቀህ ወደ አዘጋጀሃቸው  ልዩ ት/ቤቶች ከአስገባቸው በኋላ ልዩ ስልጠና ሰጥተህ አብቃቸውና በመንግስትህ ከፍተኛ ስራ ቦታዎች መመደብ፤ አለያም መምህራን እነዚህን ጎበዝ ተማሪዎች እንዲለዩ እና ለአከባቢው ካድሬዎች እንዲስመዘግቧቸው በማስደረግ ክትትል የሚያደርግባቸው መረብ መዘርጋት፤ ከፖሊሲዎችህና ከፍልስስናህ ጋር እያደጉ ለመሆናቸው መቆጣጠር፡፡

#ስርዓተ ትምህርት፡- መንግስትህ ለመምህራን የሚሰጣቸውን ኢንፎርሜሽንና የሚያስተምሩትን ሁላ ይቆጣጠር፡፡ ስርአተ-ትምህርት በሁለት ከፍለን ልንመድበው እንችላላን – ተማሪዎች የሚማሩት በተጨባጭ የሚታየውና ትምህርት ግልጽ ስርዓተ-ትምህርት [actual curriculum] ሲሆን፣ መምህራን ለተማሪዎች የሚያስተላልፏቸው እምነቶችን፣ እሴቶችንና ዝንባሌዎችን ያዘለው ሽፍን [hidden curriculum] ነው፡፡ ግልጹን ከሪኩለም ስርአተ-ትምህርት በቀላሉ ልትቆጣጠረው ትችላለህ፡፡

#ለት/ቤቶችህ የሚሆን ስርዓተ-ትምህርት ስታዘጋጅ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አገናዝብ፡-

  • በተቻለህ አቅም ለመላ ሃገሪቱ አንድ ዓይነት ስርዓተ-ትም/ት አብጅ፡፡ በክፍሉ ሃገሩ [በየክልሉ] እና በየወረዳው የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች ለየራሳቸው እንዲስማማቸው አድርገው ስርዓተ-ትም/ቱን ለማስተካከልና ለማጣጣም የሚኖራቸው እድል በጣም ይጠብባቸዋል፡፡ ይህ አካሄድ በሁሉም የትምህርት ርእሶች ላይ ቁጥጥር እንዲኖርህ የሚያስችልህ ሲሆን የተወሰኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ለእኛና ለልጆቻችን ይበጃል እያሉ ሊጨምሯቸው ያሰቧቸውን ርእሶች ያስቀርልሃል፡፡
  • በየትምህር ዓይነቶች መካከል የማይበሳ የብረት ግርግዳ አብጅ፡፡ ተማሪዎች እያንዳንዱን የትምህርት ዓይነት ነጣጥለው አለመማራቸው አረጋግጥ፡፡ እንዲህ ካደረግህ ተማሪዎችህ የተለያዩ ነገሮች መሃከል ያለውን ዝምድና ለመገንዘብ ይቸገራሉ፡፡ በተጨማሪም በክፍል ውስጥ  የሚያጠኑት ጠለቅ ያሉ የግንዛቤ [Understanding/Comprehension]፣ የትግበራ[Application]፣የትንተና[Analysis] ግምገማ [Evaluation] አስተሳሰቦች ሳይሆኑ መሰረታዊ እውቀቶችን [Basic knowledge] ብቻ እንዲሆንልህ ያስችልሃል፡፡
  • በየጊዜው እየተሸሻሉና እየተቀየሩ ብቅ ሚሉትን ትምህርት ዓይነቶች እንዳይቀስሙ ተከላከል፡፡ በዋናዎቹ ትምህርቶች – አራቱ መደቦች፣ ሳይንስ፣ ሂሳብ፣ማንበብና መጻፍ ላይ አተኩር፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ አዲስ የተገኙ እውቀቶች  ሾልከው እንይዳገቡ ነቅተህ ተጠባበቅ፡፡
  • የስነ-ጥበብ ትምህርቶች የሰዎችን አስተሳሰብ ስለ ነፃነት፣ ስለ ውበት እና ስለ ራሳቸው ህይወት ስለሚመሩት ፣ የስነ-ጥበብ ትምህርቶችን እንዳይሰጡ አግድ፡፡
  • በተቻለህ መጠን መምህራን በየክፍለ ጊዜው ለሚያቀርቡት ትምህርት በጽሁፍ የተዘጋጁ የትም/ት ዕቅዶች እና የሚናገሩትን ሁሉ ስጣቸውና ያንን ጽሑፍ እየተከተሉ ያስተምሩ፡፡  . . .

ጽሑፉ አላለቀም መጽሐፉን ገዝታችሁ አንብቡት ብዙ ጠቃሚ የስነ ልቦናና የህይወት ተክሮ ትምህርት ታገኙበታላችሁ፡፡

በገባኝ መጠን የራሴን አስተያየትና ጽብረቃ ልጨምርበት ወደድኩ፡፡ ያምባ ገነኑ መሪ የተግባር መመርያ በሃገራችን ድፍረት አይሁንብኝ እንጂ ተተግብሯል/ እየተተገበረ ነው ባይ ነኝ፡፡ ለዚህም ማስረጃየ የሚሆኑትን ምልክቶች ልጥቀስ፡-

1ኛ.  ጎበዝ ተማሪዎቹን ትኩረት አድርግ የሚለው መመርያ እኔ በማውቀው በክልል 1/ ትግራይ ላይ ተተግብራል፡፡ ይኸውም 8ኛ ክፍል ላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን ተማሪዎች ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ቀላሚኖ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተከፍቶ ተማሪዎች ተምረዋል፡፡ ከዚሁ 2ኛ ደረጃ የሚቀበል የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ተቋም (MIT) ነው፡፡ ከዚህ ተቋም የወጡት በአብዛሃኛዎቹ የሳይንስ ተማሪዎች የመረጃ መረብ ደህንንት /ኢንሳ ገብተዋል፡፡ ታድያ ለፖለቲካ ተግባርና ጥቅም ማዋል ይህ አይደለም እንዴ? ሌላው ጎበዝ ተማሪዎቸን በተለይ አንደበተ -ርቱዕና የደረጃ ተማሪዎች የሆኑትን የድርጅት አባል ካልናችሁ ተብለው ስንት አሳራችን በልተዋል፤ ተማሪዎቹን በግድ ቢመዘግባተውም ትህነጎችን የሚጠቅምም ሆነ የሃገራቸውን ልጆች የሚጎዳ የተንኮላቸው ተጋሪ ስላልሆኑ ከዚያም አንፈልግም ስላልዋቸው እያአዘኑ ትተዋቸዋል፡፡ ሌላው በየዩኒቨርሲቲ የገቡትን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና መምህራንን የሚቆጣጠሩ የየብሄራዊ ድርጅ ተቆጣጣሪ ካድሬዎች አሉ፡፡ ይህም የተግባር መመሪያው አንዱ ስልት ነው፡፡ የትም/ት ቤቶች ርእሳነ መ/ራንና ሱፐርቫይዘሮች የፖለቲካ አባላት ምልመላ እና ማብቃት እንጂ ስለ ትም/ት ጥራት አይሰሩም፡፡ የትምህርት ጥራት እማ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ አላማው እኮ #አደድቦ #መጣል ነው፡፡

————-

2ኛ. የሰነ-ጥበብ ትምህርት እና የታሪክ ትምህርት ትኩረት እንዳይሰጠው ተደርጓል፡፡ ይህም እንደተባለው ትውልድ እንዳይነቃና ስለ ታሪኩና ስለ መብቱ እንዳይጠይቅ ነው፡፡ ብሎም እነሱ የሰሩለት የተዛባ የታሪክ ግንዛቤ ይዞ እንዲያድግ ነው፡፡ ደሞም ሆኗል፡፡ እስቲ ባሁኑ ሰዓት ሃገራዊ ታሪክ፣ የአባቶች ጀግንነትና የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ያለው ማን ነው? አልቀናል እኮ ተሰርቶብናል እኮ፡፡ ዳሩ ግን ተጨዋቾቹ የኛው አምባገነኖች ሆኑ እንጂ የመጫወቻ ሜዳው ቀያሾችና ሰሪዎቹ ግቡን እንዲመታ የሚገፋፉት ለሁላችንም ግልጽ ነው ምዕራባውያኑ ናቸው፡፡ ገብቷቸውም ይሁን ሳይገባቸው ግን ችግሩን ያባባሱት ሃገር በቀሎቹ የኛው ዜጎች ቅኝ ገዢዎቻችን (native colonialists) ናቸው፡፡

———–

3ኛ. ስርአተ ትምህርት አግባብነት እና ፍትሃዊነት (relevance & equity) እንዲኖረው ተባለ እንጂ በማያውቁት ባህልና ቋንቋ እንዲማሩ እየተደረገ ነው፡፡ ግራ እየተጋቡ በአከባቢያቸው ተቃራኒ ትርጉም እንዳላቸው ሁሉ እየታወቀ ወይም ሳይታወቅ 8ኛ ፣10ኛ እንዲሁም 12ኛ ክፍል ፈተና ይመጣል፡፡ ይህ ኢ-ፍትሃዊ  (unfair) ነው፡፡ በራያ ልጆች የሚደርሰው ኢፍትሃዊ ተግባርና በአፍ መፍቻ ቋንቋ  የመማር መብት መገታት እንመልከት፡፡ እንኳንስ #በአማርኛ እና #በኦሮምኛ አፍ ለፈቱ ህፃናት ቀርቶ ከወንዙ የግእዝ ቋንቋ  ለሚጋሩት የራይኛ ተናጋሪዎች እንኳ የሚያደናግሩ ቃላትና ምንባቦች ናቸው በፈተና የሚመጡት፡፡

—————————–

#በጣም በሚገርርው ሁኔታ #በሰንጠረዥ 1 #የቀረቡት 50 ቃላት- በቃል ፊችም ሆነ ምንባብ ቢመጡ #የትግርኛ ተናጋሪዎችም #የራይኛውን በተቃራኒው ነው የሚረዱት የራያዎቹም የትግርኛውን ፍቺ #በተቃራኒው ነው የሚረዱት፡፡

በተመሳሳይ መልኩ  #በሰንጠረዥ 2 #የተመለከቱት 100  ቃላት #10ኛ ወይም #12ኛ ክፍል የማትሪኩለሽን ፈተና ቢመጡ ከላይ እንደተገለፀው የሁለቱም ወገኖች የራሳቸው ያልሆነውን አያውቁትም፡፡

#ልብ በሉ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው በደሉና ሆን ተብሎ #አደድቦ #ለመጣል ወይም ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ የሚሰራው፡፡ በ8ኛ፣ በ10ኛ እና በ12ኛ ክፍል ፈተናዎች የሚመጣው ፈተና የትግርኛው ነው፡፡ ለምን መልሱ #ግልጽ ነው፡፡ #ትግሬዎቹ #የሚያውቁትን #ይፈተናሉ፤ ነገር ግን #በቅኝ #ግዛት ያሉት #የራያ #ልጆች #በማያውቁት/ ለዚያውም #ተቃራኒ ፍች ባላው #ይጭበረበራሉ፣ ይወድቃሉ፡፡ ታድያ ለምን የራያውን አይፈትኗቸውም፡፡ የነሱ ልጆች ይወድቃሉና እንዴት ተደርጎ፡፡ የጋራ/ጋራዊ መረዳት  (mutual intelligibility ) የለማ፡፡ ይህንን እኮ እነሱም ያውቁታል፡፡ የነሱ ተማሪዎች ሌሎች የሳይንስ /ህብረተሰብ ሳይንስ ትምህርቶችን ወጥረው ሲያጠኑ፤ በአንፃሩ ግን የኛ ተማሪዎች ከፊዚክስና ከሂሳብ ትምህርት በበለጠ ጊዜ መድበው ነው ትግርኛን የሚያጠኑት፡፡ ለምን ቢባል በክልሉ ለሚደረጉ ውድድሮች ሁሉ ትግርኛ ዝቅተኛው #“C” ማምጣት ግድ ነው፡፡

#የማውቀውን የአላማጣ ታዳጊዋ ኢትዮጵ 2ኛ ደረጃ ትም/ት ቤት ብቻ እንኳ ብወስድ ብዙ ጀግና የራያ ልጆች አዳነ ይመርና እዮብ ካሴን (ሁለቱም ከዋጃ) ጨምሮ 12ኛ ክፍል የማትርክ ፈተና በተለያየ ባች 4.00 (አራት) ነጥብ ያመጡ ሲሆን ትግርኛን ግን ተውት፡፡

ብዙ ወንድሞቻችን 10ኛ እና 12ኛ ክፍል እየጨረሱ ተስፋ በመቁረጥና በስራ አጥነት (ቃለ መጠይቁም የጽሑፍ ፈተናውም ያው እንደሚታወቀው በትግርኛ ነው) እናም አቀላጥፎ የተናገረና እንደሚፈለገው የይዘት ሳይሆን ቋንቋ አፃፃፍ የፃፈን እያስቀደሙ ስራ አጥነትን አስፋፉብን፡፡

ይህ በውነቱ ከወንጀልም ወንጀል ነው፡፡ የራያ ልጆች #የ28 ዓመትና የአሁንም ሰቆቃ ነው፡፡

=============================

ከዚህ ቀጥለው ያሉትን 2 ሰንጠረዦች (ሰንጠረዥ 1 እና 2) ብቻ በመመልከት ምን ያክል በደል በትምህርት ላይ እየደረሰ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በጥሞና ተከታተሉት/ አንብቡት፡፡ እርግጠኛ የሆንኩባቸውንና የማውቃቸውን ምንጫቸው ከግእዝ እንደሆኑ በቅንፍ () አመልክቻለሁ፡፡

ሰንጠረዥ 1.  የራይኛና የትግርኛ ቋንቋቆች ልዩነት/ ንፅፅር የአማርኛ ፍች/ ተርጉም በመስጠት ሲታይ  (ከዚህ በላይ መትቀስ ይቻላል)

ተ.ቁ ራይኛ የአማርኛ ትርጉም ትግርኛ የአማርኛ ትርጉም
1 ዓብልሉ መለሰ ዓብሊሉ በለጠ/የበላይ ሆነ
2 ምጥሪ ቂጥ ምጥሪ የሴት ብልት (እምስ)
3 እሽበል ዝምበል እሽበል ሽሽበል/ዝንብ አባርር
4 ሕማቕ ክፉ/ተንኮልኛ ሕማቕ ከሲታ/የተጎሳቆለ
5 ገረብ ወንዝ ገረብ ዛፍ
6 ዑሱብ የብልግና ስድብ (ብዳታም) ዑሱብ ቅጥረኛ
7 ሰረረ ወሲብ አደረገ/ ስሪያ ሰረረ ተሰቀለ/ወጣ
8 ፅባቐ ደግነት ፅባቐ ቁንጅና
9 ዓዲ ቤት ዓዲ ሀገር ቤት
10 ቓልቐል/ ግእዝ ቀልቀል ዳር/ ወስን/ገደል ቓልቀል/ቀልቀል ሰገራ
11 ፍታን/ ግእዝ የተሞከረ ፍታን ሰገራ
12 ምጉናፍ ቸፍቸፍ ማድረግ ም’ጉናፍ ማጋጠም/ ገጠመኝ
13 ምግላብ መሽሸ ምግላብ መጋለብ
14 ሕፈስ እፈስ/ በደምብ ብላ ሕፈስ እንቅርት
15 ሙቑር ጎምዛዛ /ጨው የበዛበት/ ሙቁር ጣፋጭ
16 ምግፃብ መላጥ/መጋጥ ምግፃብ መርጨት
17 ምሕፃር አጥር ማጠር ምሕፃር ማሳጠር/ማጠር ለቁመት-
18 አባራብሩ አስደነበረ አበራቢሩ ቀሰቀሰ/ሰራ
19 ገዝሚ/ግእዝ ጋጠጣ/መጋጠጥ ገዝሚ ጥሎሽ
20 ምግዛም መጋጠጥ ምግዛም ጥሎሽ መጣል
21 ምፅዋር/ግእዝ ሸክም/ሸክም መርዳት ምፅዋር መታገስ/መቋቋም
22 ምዝንጋዕ/ግእዝ መርሳት ምዝንጋዕ መዘግየት/መዝናናት
23 ዘንግዐዮ/ግእዝ ረሳሁት/ ዘነጋሁት ዘንግዐዮ ዘገየሁበት
24 አሕድግዎ/ግእዝ አስተወው አሕድግዎ ቀማው
25 አዳልዩ/ አድለወ ግእዝ- አድልዎ አዳላ አዳልዩ አዘጋጀ
26 አዳላይ አፈላላጊ/አድሎአዊ/የሚያዳላ አዳላይ አዘጋጅ
27 ሕራይ/ግእዝ ምራጭ ሕራይ እሺ/ይሁን
28 መብርሂ ማብሪያ መብርሂ ማብራሪያ
29 መፋለጢ መተዋወቂያ መፋለጢ አስተዋዋቂ
30 መዋጊኢ መዋጊያ መዋጊኢ አዋጊ
31 መዘናግዒ ማዘናጊያ መዘናግዒ መዝናኛ
32 አዘናግዑዎ አዘናጋው አዘናጊዑዎ አዝናናው
33 አዘናግዑ ወቕዕዎ አድብቶ/ አዘናግቶ መታው አዘናጊዑ ወቕዕዎ አዝናንቶ መታው
34 መፍርሒ ማስፈራሪያ መፍርሒ አስፈሪ
35 ስድራ ስንዝር ስድራ ቤተሰብ
36 ምትራፍ ማስተረፍ ምትራፍ መቅረት
37 ትዳልዩ ተፈልጎ ተዳልዩ

 

ተዘጋጀ
38 ተዳልዩ/እንድሒ ዳሊዩ ከፈለገ
39 ሕራይ ምራጭ ሕራይ እሺ
40 ምስጓም መጎሰጥ/መጎሸም ምስጓም መጓዝ/ወደ ፊት መሄድ
41 መምሀሪ ማስተማሪያ መምሀሪ አስተማሪ
42 ድድየው/ድየው ወድያ ነየው ወዲህ
43 ዳዳዚ/ዳዚ ወዲህ ነጀው ወድያ
44 ድየይ ዳዝይ ወድያና ወዲህ ነየው ነጀው ወድያና ወዲህ
45 ምስአና ማጣታ (እሳ) ምስአና ከኛ ጋር
46 ምስኦም ከግንድ ጋር ምስኦም ከነሱ ጋር
47 ዓምል/ዓማል የዛገ ዓምል/ዓሚል ደንበኛ
48 ወዲ ሓመይ የአማቴ ልጅ/ አማቼ ወዲ ሓሞይ ያክስቴ ልጅ
49 አርሓ/አርሒ ጊደር  አርሓ ኮርማ
50 አዕልላ/ዓልላ እልል በሉ ዓዕልላ ተጫወቱ/አውሩ

 

 

         ሰንጠረዥ2.         የትግርኛና የራይኛ ቃላት የአማርኛ ትርጉም በመስጠት ሲነጻጸር

           ትግርኛ            ራይኛ    አማርኛ                  
1.       አርሓ ሽዶን ኮርማ
2.      ነቶገ ነጎደ ፈነዳ/ነጎደ
3.      ቆትቋጥ ቑጥቛጥ ቁጥቋጦ
4.      ዳንጋ፣ ብተይ፣ ጣዕዋ- (ጣዕዋ– ከግእዝ) ሙራኽ/አጣዓ ጥጃ/እምቦሳ
5.      ተሰከመ/ ፀወረ ፆረ  (ከግእዝ) ተሸከመ
6.      ገዛ/ቤት   (ቤት— ከግእዝ)     ዓዲ ቤት
7.      ደምበ ገር በረት
8.      ምግቢ  (ከግእዝ) ጎጎ ምግብ
9.      ቀረበ (ከግእዝ) ቓረበ ቀረበ
10.     ሃመማ ጭንጫይ ዝምብ
11.      ደበናዊ ደባን ደመናማ
12.     ደበና ኮይኑ- ደብኑ ዳመነ
13.     ሃደመ ገለበ (ከግእዝ) ሸሸ
14.     ካንሾሎ/ኻንሸሎ መረባ ግቢ
15.     ተናጎጸ/ ተጓነፀ (ከግእዝ) ትጓነጸ/ትሳጎደ ተጋጨ/ ተጋፋ
16.     አኸበበ ዓኹለለ/ኻበበ አከበበ
17.     ሰዓበ ደረገ ደረሰ
18.     መመሸጢ/ጥ መሰንተር ማበጠሪያ
19.     መሸጠ ሰንተረ አበጠረ
20.    አተወ አተየ (ከግእዝ) ገባ
21.     ጽልግልግ ድንብርብር ውዝግብግብ
22.    አዕለለ አዋገዐ አዋራ/ አወጋ
23.    ዑፉን ባርማሽላ በቆሎ
24.    ተራኸበ ትጋነየ (ከግአዝ) ተገናኘ
25.    ኮስኮሰ ኾሰለ /ኾስኾሰ ኮተኮተ
26.    ኮስኳስ ዃስላ/ ኾስዃስ ኩትኳቶ
27.    ነጸገ አበየ (ከግእዝ) እምቢ አለ
28.    ዓሚቊ ጠለቓ ጥልቅ
29.    ምቁር/ጥዑም ጥዑም ጣፋጭ
30.    ጠሓለ   (ከግእዝ) ጠለቐ ጠለቀ/ሰመጠ
31.     ኮቦሮ ኻረዎ ከበሮ
32.    ጎዲም   (ከግእዝ) ጎትም ድልዱም/ ደነዝ/ስለት የሌለው
33.    ዶሮና  (ከግእዝ) አወራ አዋራ/አቧራ
34.    Echo/መቓልሕ ወለለት የገደል ማሚቶ
35.    ማዕረ (ከግእዝ) ዕርያ/ዕርይ እኩል
36.    ሞለቐ ቓንጠረ/አምለጠ አመለጠ/ሾለከ
37.    ወዲ  ወዲ ወዲ/ ጓል   ጓል  ጓል

(ሌላ ካለም   እታረማለሁ)

አወሱስ የልጅ ልጅ ልጅ

(ሌላ ካለም   እታረማለሁ)

38.    ——– አቕሐው/ ቕሐው    (ለወንድ) ቅድመ አያት
39.    ——– አቕሐት/ ቕሐት (ለሴት) ቅድመ አያት
40.    አቦሓጎ አቦ ጎይታና/ይ፣ አምሐ/ አምሐው/ምሐው (ከግእዝ) የወንድ ኤት
41.     ዓባይ አምሐት/ምሐት (ከግእዝ) የሴት አያት
42.    ጓል ጓል/ ጓል ወዲ አስማ የልጅ ልጅ
43.    ወዲ ጓል/ወዲ ወዲ አስማ የልጅ ልጅ
44.    —— አወስስ የልጅ ልጅ ልጅ
45.    ጉዕ ቃርያ ቃርያ
46.    ሓሞኽሽይ ዖጋ  (ከግእዝ) ግራጫ/ደባራ
47.    ግርፃን (ከግእዝ) ግጫን ድድ
48.    ጽምሪ/ ፀጉሪ (ከግእዝ) ጨጉሪ ጸጉር
49.    ቀምቃሚ ኻርኻሚ አስተካከለ/ ለፀጉር/
50.    ሓሰር ገለባ ጭድ
51.     አሰንባዲ አደንጋፂ (ከግእዝ) አስደንጋጭ
52.    ውዑይ (ከግእዝ) ትኩሽ/ሙዩቕ ትኩስ/ሙቅ
53.    መሃዘ ፈልሰመ ፈለሰፈ
54.    ምህዞ ፍልስምና ፈጠራ
55.    ዓቀበ (ከግእዝ) አቕመጠ/ ዓቀበት ኾነ አስቀመጠ/አቀበት ሆነ
56.    Lamb/ዕየት ላዕባ የበግ ግልገል
57.    አስካላ መሳልል መሰላል
58.    ቀላይ (ከግእዝ) ባሕሪ ሃይቅ
59.    ምፅባይ ምቅልቃል መጠበቅ
60.    ገደፈ (ከግእዝ) ሓደገ (ከ ግእዝ) ተወ
61.     ዳንጋ/እግሪ ( ከግእዝ) እግሪ እግር
62.    ምሕኹልቲ ምልሑኽቲ (ከግእዝ) ጭን
63.    Lonely/ፅምው ባሕተሎ ብቸኛ
64.    ነከየ ቓነሰ/ ሓዘ ቀነሰ/ያዘ
65.    ሳንቡእ (ከግእዝ)   ሳንባ ሳንባ
66.    ጭቃ  (ከግእዝ)   መጣቕ ጭቃ
67.    ጭቃዊ   መ’ጣቕ ጭቃማ/የጨቀየ
68.    ጭዋዳ/ ጡንቻ ችንችዋ ጡንቻ
69.    ቀረበ (ከግእዝ) ጠበቐ/ቓረበ ቀረበ
70.    ክሳድ (ከግእዝ) ኽሳድ/ስኻድ አንገት
71.     አፍንጫ ፍንጫ አፍንጫ
72.    ጁባ (ከግእዝ) ኩስ/ክስ ኪስ
73.    ስሚ መርዚ መርዝ
74.    ጻሕሊ (ከግእዝ ፃህል) ድስቲ/ጻሕሊ ድስት
75.    ድንሽ ድኚት/ድንች ድንች
76.    Pour/ከዓወ ቓድሐ/አንቆርቖረ ቀዳ/አንቆረቆረ
77.    መብጽዓ/መጽብዓ ምስዕና ስለት
78.    ተመጻብዐ ትመስዐነ ተሳለ
79.    መንጎኛ ሽማግለ ሽማግሌ
80.    Reject/ ነጸገ አበየ/ ነዝሐ እምቢ አለ/ ረጨ
81.     Relief/ምፍጓስ ምፍዋስ መፈወስ
82.    አርከበ በፅሐ/ ደረገ ደረሰ
83.    ጣዕሳ ጠጠት/ፀፀት ቁጭት/ጸጸት
84.    አልገሰ አሽቐንጠረ/ገለል አበለ አስወገደ/ከላ
85.    ለማሚ ሙጭልቕልቕት እንሽላሊት
86.    ከውሒ ኾኽሒ አለት/ቋጥኝ
87.    ናሕሲ ጥራና ጣሪያ
88.    ፎኲስ ቓልል/ ፋሽኮ/ በሽከለ ቀላል
89.    ንእሽተይ ዓፃብዕቲ- ሕንጥልጥለ ትንሻ ጣት
90.    ሳሬት ሽራርት ሸረሪት
91.     ትኪ ጡሽ/ጥሽ ጭስ
92.    አትከኸ አጠሸ አጨሰ
93.    Smart/ጎራሕ (ከግእዝ) ሞለይ/ ብልጢ/ጎራሕ ብልጥ
94.    —– መራፈዲ ቁርስ
95.    ጣዓሞት መማሸዪ ማቆያ/መቅሰስ/ማማሻ
96.    ሓምለዋይ ቖፅለያይ/ ለምለም አረንዴ/ለምለም
97.    እኹል ልክዕ/ ኹዩን በቂ/ልክ
98.    ሃንደበት ድንገት/ ድሻዓዋ ድንገት/ወድያውኑ
99.    ምሕባእ ምሽኳዕ/ምድራጭ መሰበቅ/ማድባት
100.   ፈርሲ ዳንጋ ሳርባ ባት

 

————

ይህ የትህነግ ግፍና በደል በራያ ወገኖቻችን ሲፈጸም ተባባሪ አንሆንም ብለው ከኃላፊነትና ከድርጅት አባልነት የለቀቁ የራያ የቁርጥ ቀን ልጆች ብዙ ናቸው፡፡ ለመጥቀስ ያክልም በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎችን እስከ ሚንሰትር ማዕረግ ሲሰራ የነበረው ወንድማችን ዛዲግ አብርሃ፣ በኬኒያ በዲፕሎማትነትና በውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር በልዩ ልዩ የሃላፊነት ቦታዎች ይሰራ የነበረው ድፕሎማት ወንድማችን አንዳርጉ በርሀ፣ በሳውድ ዓረብያ በዲፕሎማትነት ይሰራ የነበረው ወንድማችን ሚስባህ ሞሃመድ፣ በአምባሳደርነት ይሰራ የነበረው ወንድማችን አማባሳደር ዓሊ፣ በሶማሊያ ሞቃድሹ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የሆነው የራያ #መሆኒ ተወላጁ ወንድማችን ዳሎል አረፈ ፤ እና በኩዌት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የሆነው የራያ #ዋጃ ተወላጁ ወንድማችን አብዱልቃድር  ኩቢ ለጊዜው ከታወቁት መካከል ናቸው፡፡ ይቀጥላል!

እንህ ወንድሞች ራያነት በምንም ጥቅምና ስልጣን የማይለወጥ እና ከሁሉም የሚበልጥ መሆኑን ያውቃሉ፡፡

——————–

#ያደጉበትንና የሚያውቁትን #ባህልና ወግና  እንዲሁም #ጀግንነት እንዴት ይርሱ? በጭራሽ! እስቲ በሞቴ ቀጥሎ ያሉትን ፎቶግራፎች ብቻ በማየት #ራያነት እንዴት #እንደሚነዝር ተመልከቱት፡፡ እኛ እኮ የኢትዮጵያ ጌጦች ነን፡፡ ሁሉም ሊሳሳልን ሊያከብረንና እውቅና ሊሰጠን ይገባል፡፡

———-

#ራያነት ኩሩ ማንነት!

#ድል ለራያ ህዝብ!

#ፍትህና ሰላም ለታሰሩና በየቀኑ ለሚታፈኑት ራያዎች!

የራያa ዓዘቦ የመኾኒ  ልጅ ዲፕሎማት ዳሎል አረፈ ሌላው ነው፡፡

 

#ድባዓል ሃራሙስ ሓለይቲ ፃባ ረቡዕ ክቕይድኦ? ደይነበረ  ጋዓት ብበርበረ!

*******************

በርሀ ፋኖ ሓው ህሊ  ሃፍቱ ሓው ህሊ ማጋል ሰየ

ኻልእ ደይብል ተረፍ ራያይ ዋየ

ሰርሑ ደይምብላዕ ደይብል ሆያ ሆየ

ደአሰሩዎማ ይሓዞም ድሆየ!!!

—–

#ፍትህ ለበርሀ ትኩየና  በሺዎች የሚቆጠሩ ለታሰሩ ወንድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.