‹‹አድዋ ኬኛ!›› – ዘላቂ ነው ወይ? (ሚኪያስ ጥላሁን)

ሀ. አድዋ – በዓለም ታሪክ ውስጥ ወፍራም ቦታ አላት፤ የጥቁር ህዝብ ጠንካራ ክንድ የነጭን ዕብሪተኛ ልብ ልክ ያስገባበት የጦር አውድማ የነበረው፣ በዚህች ተራራማና ሙቀት-ዘለቅ አካባቢ ነበር፡፡ ድሉ ለኢትዮጵያውያን አልፎ፣ መላ ጥቁር ህዝቦችን ያቀናጀ ድንቅ የአንድነት መንፈስ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ልጆች አይበገሬነት ተረጋግጦበታል፤ ጦርን መስበቅ የማያቅተው ወኔያም ህዝብ መሆኑንም ጨምሮ፡፡ ከድል በላይ ወደ መንፈስነት የተሻገረ ረቂቅ ዕሳቤ ‹‹ነው!›› ብለን መደምደም እንችላለን፡፡

ለ. የድል በዓሉ ከአጤ ምኒልክ ዘመነ-መንግስት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሲከበር ዘልቋል፡፡ የአጤ ኃይለስላሴ ስርዓትና የደርግ መንግስት ኢትዮጵያዊ በዓልነቱን ሳይበርዙ ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡ ኢህአዴግ አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት ሲገባ ግን ሆን ተብሎ የዘረኞቹ ጭዳ እንዲሆን ተደረገ፡፡ ‹‹የነፍጠኞችና የደርግ ርዝራዦች በዓል ነው!›› እስከመባልም ተደረሰ፡፡ ኦነግና ቡችሎቹ ‹‹ድሉ የኦሮሞ ህዝብ ድል አይደለም!›› የሚል ደከመ አመክንዮ አመጡ፡፡

ሐ. ዘረኞቹ ትናንት ‹‹አይወክለንም!›› ብለው የጣሉትን በዓል፣ ዛሬ 360 ዲግሪ ተሸከርክረው ‹‹አድዋ ኬኛ!›› ብለው አንስተው ማክበር ጀመሩ፡፡ ምክንያታቸው ሌላ ሊሆን ይችላል፡፡ ለእኔ ግን ‹‹አድዋ ኬኛ!›› ሲባል፣ እምዬ ምኒልክን የታሪክ ትቢያ ውስጥ ጥለው፣ ‹‹ደሜ ናቸው!›› ብለው የሚያስቧቸውን የጦር አበጋዞችን ብቻ ማዘከር ማለት ነው፡፡ ‹‹አድዋ ኬኛ!›› – ፖለቲካዊ ግልበጣም ይመስለኛል፡፡ በ‹‹አድዋ ኬኛ!›› ጭምብል የኦነግን የጥንብ-አንሳ ፖለቲካ ለመፈፀም የታቀደ ነው፡፡ ባልቻ አባ ነፍሶን ብቻ ነጥሎ፣ ‹‹ጀግናዬ!›› ማለትና ምኒልክን ከጦር አውድማው ላይ እንደሌሉ ቆጥሮ መካድ፤ የአነግ ርካሽ ፖለቲካ ነው፡፡ እኔ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ የግላቸውን ድርሻ ለጦርነቱ ያዋሉ ግለሰብ ‹‹ናቸው!›› ብዬ አስባለሁ፤ ኢትዮጵያዊም ናቸው፡፡ ግን እርሳቸውን ብቻ ለይቶ ለፖለቲካዊ ዝከራ ብቻ መጠቅም ታሪክን የመበረዝ ወንጀል ወይም በእንግሊዝኛ historical revisionism ነው፡፡ ለዚህም ነው – ‹‹አድዋ ኬኛ!›› ከቅን ልብ ያልመነጨ የመርዛሞች ፖለቲካ ድምር ውጤት ‹‹ነው!›› የምለው፡፡

መ. ‹‹አድዋ ኬኛ!›› – ዘላቂነት የለውም፡፡ የአንድ ሰሞን ሆይ-ሆይታ ነው፡፡ የኦሮሞ ዘረኞች ለአንድ ቀን የአንድነት አስተሳሰብ አቀንቃኝ ይሆኑና ነገ ወደ ጎሬያቸው ይመለሳሉ፡፡ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ስለሆኑ፣ ሃሳባቸው በሙሉ በጠባብ የዘር ኬላ የታጠረ ነው፡፡ ከአዕምሯቸው ‹‹አድዋ ኬኛ!›› ቢፈልቅ በቅንነት አይደለም፡፡ በቅንነት ቢታሰብማ፣ እምዬ ምኒልክ – የጦሩ አዝማች ንጉሠ-ነገሥት – ይታሰቡ፣ በበጎ ይጠቀሱ፣ ይሞገሱ ነበር – በአበረከቱት አበርክቶ ምክንያት፡፡ ‹‹አድዋ ኬኛ!›› ግን ይህንን አልፈለገም፡፡ ‹‹አድዋ ኬኛ!›› – የቀናት ጋብቻ ነው፡፡ ከየካቲት 23 በኋላ ይፈርሳል፡፡

ምኒልክ እና ጣይቱ በአድዋ!

2 thoughts on “‹‹አድዋ ኬኛ!›› – ዘላቂ ነው ወይ? (ሚኪያስ ጥላሁን)

  1. ‹‹አድዋ ኬኛ ሚቲ!››
    ባርያ ጌታ አይመርጥም! ጣሊያን አድዋ ላይ ተሸነፈና ባርነቱ ቀረልን? ባባት ቅማያቶታችን ቀዬ ገባር ተብሎ ከባርያ በታች መጨቆን ቀረ? ጣልያን ቢመጣስ ኖሮ ከዚያ በላይ ኢሰብዐዊ አገዛዝ ያመጣ ነበር?
    Osoo beeknu huuba wajjin nyanne, jette sareen. ዘረኛ ነጮች እንኳን በጥቁሮች ተሸነፉ ለማለት ብለን ነው እንጂ፣ ከነጮቹ የባሱ ዘረኞች በባርነት አገዛዝ ስር እንዳማቀቁን አልጠፋንምና ስለ አድዋ ድላችሁ ከኛ ጋር ደንሱ እንዳትሉን አደራ! እነ አኖሌን ያስታዉሰናልና!

  2. <<ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅኔ በላይ ታሪክ ነው የሚዘረፈው። ታድያ ታሪክ ሲዘረፍ ሰሙም፣ ስሙም ፣ማንነቱም፣ ወርቁም አይቀራቸውም። ለምሳሌ የአድዋን ድል አከባበር አስተውሉ። የኦሮሞ ፈረሰኞች ለድሉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ብዙ ተፅፏል። የድሉ ትላልቅ ፊታውራሪ ጀግኖችም ኦሮሞዎች ነበሩበት። ይህ ውለታ ተዘንግቶ ግን ኦሮሞ በአገሩ ጭሰኛ እንዲሆን ተፈረደበት፣ ቋንቋውን እንዳይናገር፣ ስሙን እንዲቀይር፣ የአገሬው ስም ሳይጥማቸው ሲቀር ወደ አማርኛና አይሁድ ስም እንዲቀየር፣ መሬቱን ወረውት ማንነቱን ነጥቀውት ካበቁ በኋላ "የአድዋን ድል ና አክብር" ይሉታል። በነገራችን ላይ አድዋ ላይ የተዋደቁት የኦሮሞ ጀግኖች እንደገና ቢነሱ ኦነግ ነው የሚሆኑት፣ ወጣት ቢሆኑ የነፃነት ትንታጎቹ ቄሮ ነው የሚሆኑት። ጀግናው ታደሰ ብሩ ትልቅ ምስክር ነው። ኦሮሞን "አድዋን አከብር" አትበሉት፣ እንቅልፍ ማስያዣ ነውና። ኦሮሞ አድዋን ሲያስብ "ምን አይነት ኢትዮጵያ ነች የተፈጠረችው?" በሚል ጥያቄ ነው። ለኦሮሞ በራሱ ምድር ላይ መታወቂያ ተሰጠው ተብሎ ተቃውሞ የሚነሳባት ኢትዮጵያን ለመስራት አይደለም አድዋ ሄዶ የተዋደቀው። እሱ አይደለም ከብቶቹ ለሆራ የሚሰማሩበት ፊንፊኔ እሱን የምትጠየፍበት ከተማ ለመገንባት አይደለም አድዋ ድረስ ተጉዞ የተዋጋው። ኦሮሞ አድዋን ያስታውሳል። የሚያሳታውሰው ግን ያልተወራረደ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ስላለው ነው። Kanuma.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.