የለማ ንግግር ጥሩ አደለም ግን እውነቱ ለማ ኢትዮጵያዊ ነው! (ሰርፀ ደስታ)

እስካሁን ላማን ተችቼ አላውቅም፡፡ በእርግጥም አሁን ላለው ለውጥ ከለማ በላይ አስተዋጾ አለኝ የሚል ካለ ፈጣሪ ብቻ ነው ባይ ነኝ፡፡ እሱንም ለዚህ ተግባር የላከው መስሎ ስለሚሰማኝ፡፡ ይሄ እውነት ነው! እውነትነቱም ይቀትላል፡፡ ሰሞኑን ከቤቶች ማፍረስና ከአዲስ አበባ ጋር በተገናኘ ያው የተለመደው የዘረኛ ፖለቲካ ተፋፍሟል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለማ ከዚህ በፊት በቤተመንግስት የኦሮሚያ ባለስልጣናትን ሰብስቦ ሲያናግር ከሱማሌና ኦሮሚያ ድንበር የተፈናቀሉትን የከተሞችን ሕዝብ ብዛት ተዋጽኦ ለመቀየር አልመለስናቸውም አይነት ንግግር በስፋት እየተዛመተ ነው፡፡ ለማ እዚህ ጋር ስህትት ተናግሯል በዚህ ምንም መከራከሪያ አላቀርብም፡፡ ከእሱም የማይጠበቅ ነው፡፡ ይሄ ማለት ግን ለማ ያለበትን ጫና ዘንግቼ አደለም፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና ብዙ ተማርኩ የሚለው ችግር አለ፡፡ ላለፉት 28 ዓመት ምን እለባትም ከ1960ዎቹ ጀምሮ ኦሮሞን ከመሠረታዊ ትርክት በማውጣት በጥላቻና ዘረኝነት ጠልፎ በመጣል ሌላውን እንደፈለጉ ለመዘወር ኦሮሞንም ጠባብ እያሉ ለማሸማቀቅ በሚመች ሁኔታ ነው የተሰራው፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቁ የሴራው አስፈጻሚ ኦሮሞ ነኝ የሚለው የተማረውና በፖለቲካ ውስጥ እሳተፋለሁ የሚለው ነው፡፡ እና ለማ እንደ ኢትዮጵያዊ እስካሁን የመጣባቸው ድፍረቶችና ያለፈባቸው መንገዶች እጅግ ፈታኝ ነበሩ አሁንም ናቸው፡፡ ኦሮሚያን ከን አሮሞቲ እያለ እያሰበ ያለ ከምሁር እስከ ተራ ሰው ነው የሚመሩት፡፡ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች ሌሎች ከእኛ ይውጡ የብዙ አክቲቪስት ነን የሚሉ መፈክር ነው፡፡ ይሄው መርዘኛ ንግግራቸው ወደ እርግማን ተቀየረ መሠለኝ ከኦሮሚያ ይውጣ እያሉ ሲያቅራሩ ወደ አንድ ሚሊየን የተጠጋ ኦሮሞን ደግሞ ከእኛ አገርና ሰፈር ውጡ ተባለ፡፡  በመሠረቱ አንድን ቦታ የእኔ ብሔር ነውና ሌላው ይውጣ ማለት ከዘረኝነትም ያለፈ እጅግ የከፋ እርግማናዊ የአእምሮ ዝቅጠት ነው፡፡  ይሄው እርግማናዊ አስተሳሰብ በብዙ ኦሮሞ ውስጥ ዘልቋል፡፡   ከዘመናት ኦሮሚያን ከን ኦሮሞቲ ከመለው አሁን ላይ ደግሞ ግብግቡ አዲስ አበባ ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ይላል፡፡ ምን ማለቱ እንደሆነ እንኳን ለማሰብ ምንም ተዘግቶበታል፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ባለ ቁጥር ግን ምን ያህል የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ እያራቀውና ወያኔ ለዘመናት ጠባብ እያለች ራሷ የፈጠረቻቸውን ጭንቅላቶች እንደማሳያ ስታቀርብ የነበረውን እውነትነት እየመሰከረ ነው፡፡

እንግዲህ ለማ በዚህ ሁሉ ምንም አመክንዮዋዊ አስተሳሰብን ለማሰብ ለተቸገሩ ሁሉ ትንሽ ያለሳለሰ መስሎት ነበር እንደእውነቱ አዲ አበባ ውስጥ 6000 ኦሮሞ ማስገባቱን እንደ አስተዋጽኦ እንዲያዩለት የሞከረው፡፡ የኦሮሞን ቁጥር በከተማ ለመጨመር ታስቦ ያለው ግን እንደው ማሟሟቂያ ካለሆነች ለ5ሚሊየን ሕዝብ 6000 ምን ማለት እንደሆነ ማሰብ በቂ ነው፡፡ ለማንኛውም ለማ በዚህ መልኩ የተናገረው ለዘረኞቹ ማረገቢያ የሆነ መስሎት ካለሆነ ስህተት ነው፡፡ ዘረኞቹንም የበለጠ ጭራሽ የዚህን አይነት ሴራ እንዲያስቡ ነው የሚያደርገው፡፡ አዝናለሁ! በግልጽ መናገር ስላለብኝ ነው፡፡ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ እግዚአብሔርን (እውነትን) ለማስብ በአልፈለጉት መጠኝ የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው የፈላስፋው የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ሁሌም ይገርመኛል፡፡ ኦሮሞ በዚህች አገር በስልጣንም በሌላም ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ እውነቱን ሁሉ ክደው ዛሬ ምንም ድርሻ የሌለው በጭቅጭቅና በአልቃሻነት ሲከፋም ሌሎችን በመጥላት ላይ የተመሰረት ፖለቲካ ላይ እንዲቆም ስለተደረገ ከብዙ አገራዊ ተሳትፎው እየወጣ ነው፡፡ ይሄ ለብዙ ኦሮሞ እየታየው አደለም፡፡ ዛሬ በኦሮሞ ሥም ይባልና ለሆኑ ሰዎች መጠቀሚያ በሚሆን መልኩ እንጂ አገራዊ ድርሻና አስተዋጽኦ በሚኖርበት መልኩ ያለው የኦሮሞ ተሳትፎ እየወረደ ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ በስፖርታዊና ሌሎች እርስ በእርስ እየተጋሩት በአሉት የማህበራዊ ተሳትፎ እንኳን ተሳታፊ እየሆነ አደለም፡፡ ኦሮሚያ ትልቅ ግዛት ነው፡፡ በእግር ኳስ ክልብ እንኳን  የመሳተፉ ድርሻ አናሳ ነው፡፡ አዳማና ሰበታ ከነማ በቀር ከእነጭርሱ ከሌላ ቦታ እንደውም የለም፡፡ ከተሞች ኦሮሚያ ውስጥ እድገታቸው ከሌሎች አንጻር ጥሩ አደለም፡፡ ብዙዎች በኢነቨስትመንት ሥም ኦሮሚያ ገብተው ነበር፡፡ አሁን ላይ ኦሮሚያ ለራሱ ለኦሮሞው ሳይቀር የትልልቅ ኢንቨስተመንት ሥጋት እየሆነ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር የሚለካው ቦሮሞነት ስለሆነ በብዙ እየወረደ ያለ ክልል ነው፡፡ ኦሮሞን ከሁሉም አወሳኝ ሕዝብ እንዲጋጭ የሚያደርግ ስነልቦታ ስለተዘራበት ከጎረቤቶቹም ሠላም አደለም፡፡ ወያኔ ትልቁ ጉልበቷ በጥቅማጥቅምና በዘረኝነት ያደነዘዘቻቸው የኦሮሞ ተወላጅ ነን የሚል እንጂ ትግራይ አደለም፡፡  ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ለማውጣት ያለተሰራ ሴራ የለም፡፡ ለዚህ ሴራ ዋነኛ ተሳታፊ የወያኔ ቅጥር የሆኑና ለሆድ ያደሩ የሕዝብ ጉዳይ ምንም የማይመስላቸው ኦሮሞ ነን የሚሉ ናቸው፡፡

ዛሬ ላይ ሰከን ያለ የኦሮሞ ምሁር ማንም አይሰማውም፡፡ የኦሮሞ ምሁረነትህን ለማረጋገጥ ከኦሮሞ ውጭ በተለይ አማራ የተባለውን በደንብ መጥላት ግድ ይልሀል፡፡ ጥላቻና ዘረኝነት ከሌለበት ለኦሮሞ ፖለቲካ ዋጋ የለውም፡፡ ከዚህ የወጣ አመክንዮዋዊ አመለካከት ከአለህ የዘር ማንዘርህ በደም ኦሮሞ መሆን ዋጋ የለውም፡፡ በቅርቡ በኢንግላንድ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነው ዶ/ር አወል አሎ የእነ ጀዋርን አላሙዲን መታሰር አለባቸው ጩሀኸ ሎጂካል አደለም፡፡ አላሙዲን እንደ ባለሀብት ያጠፉት ጥፋት ቢኖርም  ብዙ አስተዋጾ አድርገዋል በማለቱ ኦሮሞ ሁሉ ተገልብጦ ጦርነት የከፈተበት ነበር የሚመስለው፡፡ ችግሩ እንግዲህ እንዲህ ነው፡፡ አወል ከጀዋር በብዙ እጥፍ በእውቀት ይበልጣል፡፡ አወል ኢንተርናሽናል ደረጃን የጠበቀ አስተሳሰብ ነው ያለው፡፡ በእርግጥም በምሁርነት ብቃቱ ነው ሊያውም በኢንግሊዝ አገር የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው፡፡ አወል የበኩልን ድርሻ ለማበርከት ብዙ መልካም የሆኑ ጅማሮወችን ጀምሮ ነበር፡፡ እንደምሁርነቱም ሁሉንም ለማካተትን ውይይት መድረክ እየፈጠረ ሲያወያይ ነበር፡፡ በስድብና፣ ጥላቻ ዘረኝነት የለከፈ ጭንቅላት በአወል አስተሳስብ ሊሳብ ይቅርና ጭራሽ እንደጠላት ነው የሚቆጠረው፡፡ ከሌሎች ጋር መነጋገር ይችላላ፡፡  ጉዳዩ ግን እንዲህ ነው፡፡ አብዛኛው የኦሮሞን ፖለቲካ የሚመራው የወለጋ ጸረ-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የተሰበከ ፖለቲከኛ ነው፡፡ ኦሮሞን እንደመሳሪያ እየተጠቀመበት ያለው የሄው የዚህ አካባቢ ዘረኛ አስተሳሰብን ለማስፋፋት የሚሰራው ቡድን ነው፡፡ የሚገርመው ከኢለባቡር ጀምሮ እስከ ቦረና ሀረር ምናምን ብትሄዱ የኦሮሞ በፖለቲካም ሆነ በሥልጣን ያለው አስተዋጾ የለም ቢባል ይሻላል፡፡ ድንገት አልፈው ዘልቀው ከገቡ በአስተሳሰባቸው በድንብ ይለያሉ፡፡ ከሌላው ጋር ለመሆን በሚያደርጉት ጥረት፡፡ በአለፈው 28ዓመት ኦሮሚያን እየተፈራረቀ ሲፈነጭበት የነበረው የወለጋና አርሲ ቡድን ነበር፡፡ እነሱ ይኖራሉ ሕዝብ መከራውን ያያል፡፡ ከዚህ ውጭ ለቦረና ማን ያስብለታል፡፡ በኦሮሞነት ይጠቀሙበታል እንጂ፣ ለሐረር ማን ያስብለታለ ገበያቸው የሆነው የኦሮሞ ጽንፈኝነትን ይለማመዱበታል እንጂ፡፡

ይሄ በኦሮሞ ያለው ችግር ነው፡፡ አሁን አሁን አማራም እየተቀላቀለው ነው፡፡ ትግራይ የወያኔ ወሮበላ ከላዩ እስከሚወገድለት ነው፡፡ በአንጻሩ በሱማሌ በአጭር ጊዜ ትልልቅ ለውጥ እየመጣ ይመስላል፡፡ ሱማሌ ዛሬ በክልላቸውን ማንም እንደፈለገው መንቀሳቀስ ስጋት የለበትም እየሉ ነው፡፡ በአገር አስተዋጽኦ የነበራቸውን ታሪክ እያጎሉትና እያወጡት ነው፡፡ መልካም ነው፡፡ እነዚህ በትልልቅ ክልል ያሉ ሁለቱ ክልሎች ግን መፍረስ አለባቸው አማራና ኦሮሚያ፡፡ ቦረና ራሱን ችሎ የፌደራል ስቴት ለመሆን ምንም አያንሰውም፡፡ ከአልሆነ ግን ከአቅራቢያው ባሌና አርሲ ጋር፡፡ ከዛ ዘር ምናምን ሳይል ሁሉም የዛ ተወላጅ ለተወለደበት ይሰራል፡፡ በቦረና ጉዳይ ወለጋ አይወስንም ያኔ፡፡ አማራ እንደ ድሮው በጎጃምና ጎንደርነቱ ይበተን፡፡ ሸዋ የሁላችንም ማዕከልና የኢትዮጵያነት ማሳያ ሆኑ የብዝያ ቋንቋ፣ ባህልና ኢትዮጵያዊነት የሚታይበት መንግስት ሆኖ ይመስረት፡፡ ያኔ አዲስ አበባ የእኔ የእኔ ማለት አይደፈርም፡፡

እንግዲህ ለማ እዚህ ያደረሰው ሂደት ወደዛው (ኢትዮጵያን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ክፍለ አገራት) እንደሆነ በተግባር እናውቀዋለን፡፡ የወለጋው ፊንፊኔም ከባኮ አያለፍም፡፡ አዲስ አበባ በሸገርነቷና በአዲስ አበባነቷ ትቀጥላለች፡፡ እውነቱን ለማታውቁ ሸገር የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው የሸዋ ኦሮሞ አዲ አበባን የሚጠራበት ሥም ነው፡፡ አንድን ቦታ የእኔ ብሄር ነው ብሎ መናገር ወንጀል እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ዛሬ ስለተለማመደው ዘረኝነት ምን እንደሆነ ተዘንግቶታል፡፡ ቆይቶ ግን ሁሉም እንዲገባው ይደረጋል፡፡ እነ ለማ ከማይመጥናችሁ የሰፈር አስተሳሰብ ተጠበቁ በአለፈው አብይ ወታደሮች ቤተመንግስት በገቡ ጊዜ ከሱሉልታ ሰው እየመጣ ነበር ያለውን ንግግር አስታውሱ፡፡ አንዳንዴ ትሳሳታለህ፡፡ እያንዳንዱ ቃሉ አየር ላይ የሚውል ሰው ደግሞ ችግር ነው፡፡ ግን በመሠረታዊ አስተሳሰብ ለማም ሆነ አብይ ጋር ምንም ጥርጣሬ የለኝም፡፡

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ነች፡፡ ይሄንን ነው እየተሰራ ያለው! ይሄ ሳይገባችሁ በኋላ ትቸገራላችሁ፡፡ ሰሞን በዋልታ ፕ/ሮ መረራን ያነጋገረው ጋዜጠኛ ነገር እጅግ አሳፋሪ ነበር፡፡ ፕ/ሩን አዲስ አበባ የማን ነች ብሎ ሙጭጭ ከማለቱም በላይ ጭራሽ ለምሻሌ ቢሾፍቱ የኦሮሞ ነው ብሎ አረፈው፡፡ ልብ በሉ ምን ያህል እንደተጎዳን፡፡ ቢሾፍቱን ለኦሮሞ ማን ሰጠው?  እንግዲህ በጋዘጤኛው አስተሳሰብ ቢሾፍቱ የኦሮሞ ነች አዲስ አበባ ደግሞ የኦሮሞ ልትሆን አትችልም አይነት ነው፡፡ ይገርማል! ለማንኛውም ማሰብ እንጀምር!

አመሰግናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን  ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

1 COMMENT

  1. ወንድም አንተ ነገሩ ገብቶሀል:: የአክራሪ ኦሮሞዎች አቅዋም ሊገርመን አይችልም :: የለማ ኢትዮጵያዊነት ይጎረብጣቸዋል:: የሚገርመው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚምሉ የፖለቲካ ደላላዎች ናቸው ግራ የሚያጋቡት::አርቀው ስለማያስቡ ይመስላቸዋል ለማን ከአክራሪ ኦሮሞዎች ጋር ካጋጩት ቤተመንግስት ወለል ብሎ ይከፈትላቸዋል:: ሀይል የላቸውም ታዲያ ኦሮሞና የፈረደበት አማራ ሲጋጭላቸው በመሀል አማራጭ ሆነው ይቀርባሉ:: አማራ ደግሞ እንዳይደራጅ ስም አጥፊዎቹ በመጀመርያ እነሱ ናቸው:: ይህቺ ሀገር ስንት ጉድ ተሸክማለች!

    ለማ መገርሳ ሰው ስለሆነ ስህተት ሊናገር ይችላል:: አግባብ ባለው መልክ መቃወም ያስኬዳል ኢትዮጵያዊነቱን ማንም ሊሰጠው ወይንም ሊቀማው አይችልም:: እራሳቸውን አሳብጠው የህዝብ ተወካይ አድርገው ህዝብን ለማጋጨት የሚቃዡ ጋዜጠኛ ተብዬዎች ነገሮች እየስከኑ ሲሄዱ ባዷቸውን ይቀራሉ:: እሁን በቅርብ የራስ መኮንን ሀውልት ሀረር ከተማ ፈረሰ:: ታድያ ዜናውን የሰማሁት አንድ ሰው መኪና ሲያዞር በስህተት እንደገጨና እንደተቆጨ ነው::የከተማ አስተዳደሩም እንደሚያሰራው ተዘግቧል::

    ለወሬ ችኩሉ አቻምየለህ አጣሞ ኦነግ እንዳፈረሰው አቀረበ:: ኦነግን እንደፈለገ ይስደባቸው:: ሆኖም ያልሆነውን ትረካ ፈጥሮ ህዝብን የሚያጋጭ ማቅረብ መብት የለውም:: ራስ መኮንን ጉዲሳ የሸዋ የሸኖ አካባቢ ኦሮሞ ነበሩ::

    በእነ ለማ ትግል ነው እስክንድር ዛሬ በነፃነት የሚፅፈው::የአዲስ አበቤዎችን አርበኝነት ከ 2015 ጀምሮ አይተናል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.