ኦሮሞ ባይተዋር የሆነበት የአደዋ ድል ታሪክ! አሳዛኝ! (ሰርፀ ደስታ)

በድሮው የአደዋ ድል አከባበር በዋናነት የኢትዮጵያን ባንዲራ የያዙ ፈረሰኞቹ ዋናው የበዓሉ ድምቀት ነበሩ፡፡ ዛሬ በሚኒሊክ አደባባይ ከሚኒሊክ በቀር ፈረሰኛ የማይታይበት በእርግጥም እንደድሮው በኢትዮጵያ ባንዲራ የተዋበ በዓል ተከብሯል፡፡ ይሄን ታሪካዊ ቀን አከባበር ሳይ በአለፉ 28 ዓመታት የዚህን ታሪክ መሠረት ደብዛ ለማጥፋት የተሰራው ሴራና ጥረት ታሰበኝ፡፡ ሐዘንም ተሰማኝ! አሁን አሁን ሁሉም ወደልቡ እየተመለሰና ወደነበረ የኢትዮጵያዊነት ማንነቱ እየከተተ ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊ ማንነት ሙልጭ ብሎ እንዲወጣ በአለ በሌላ ጉልበት ሲሰራበት የነበረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ግን አሁንም ገና ነው፡፡

የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ለማራቅ የተሰሩትን ዋና ዋናዎቹ ሴራዎች ከአደዋው ጀምሬ እስኪ ጥቂት ልጠቁም፡፡

 1. አደዋ፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ እንደምናየው ከየትኛውም ማህበረሰብ በበለጠ በአደዋው ድል ትልቅ አስተዋፅዖ የነበራቸው ዛሬ ኦሮሞ ከተባለው ማህበረሰብ የወጡ አባቶች ናቸው፡፡ ይሄን የካዱ ኦሮሞ ነን የሚሉ ዘረኛና በጥላቻ የመረቀዙ የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ለማራቅ የአደዋ አባቶቻችንን መስዋዕትነት አጣጣሉት፡፡ ዛሬ በኦሮሞ ሕዝብ እነ ገበየሁ ጎራ ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባነብሶ) ሳይሆኑ ጀግኖቹ መንደርተኞችና በዘረኝነትና ጥላቻ እየበከሉት የአስተሳሰብ ባሪያ ያደረጉት ናቸው፡፡ ዛሬ ለኦሮሞ ሕዝብ የአደዋን ድል ማክበር የውርደት ያህል ነው የሚሰማው፡፡ በየአመቱ በዓሉ በተከበረ ቁጥር በመርዘኛ ታሪክ ሲመረዝ ይውላል፡፡ የአደዋው ድል ታላላቅ ጀግኖቹን ያፈራው ጎበና የኦሮሞ ጠላት ነው፡፡ የአደዋው ድል መሪ ሚኒሊክ ሥም ዛሬ ኦሮሞን ያስደንብረዋል ያባንነዋል፡፡ በታሪክ ኦሮሞ ከፍተኛ ልዕልናና ትልቅ የመሪነት ድርሻ የነበረው በሚኒሊክ እንደነበር እውነት ቢሆንም ዛሬ ለዛሬው ኦሮሞ ያ ታሪክ ሲዖል ሆኖ ተስሎበታል፡፡ ለዛም ነው የሚኒሊክ ሥም ሲጠራ የሚደነግጠው፡፡ የዛሬውን አደዋ የሰሩ ጀግኖች ሚኒሊክና ከሚኒሊክ ጋር የነበሩት ጀግኖች አባቶች ስለሆኑ በጠላቶቹ ትርክት ለተመረዘው ኦሮሞ ይህ በዓል ያመዋል፡፡ በዓሉ በመጣ ቁጥር የድሉን ገጽታ ለማራከስ በየአመቱ ሰዎችን የሚያነጋግረው ኦኤም ኤን የተባለው ብዙዎን ኦሮሞ የጀዋር መሀመድ አምላኪ እስከሚመስል የዳረገው የፕሮፓጋንዳ ሚዲ  በዚህ አመት ለየት ያለ አመለካከት ያለው ሰው ጋብዞ ተመለከትሁ፡፡ ግለሰቡ በታሪክ ያላችው ግንዛቤ አልፎም አጠቃላይ በኢትዮጵያዊነት የሚኮሩ ናቸው፡፡ ሆኖም ጠያቂ ጋዜጠኛ ሆና የቀረበቸውን ልጅ ሳይ እጅግ አዘንኩ፡፡ ተጠያቂው ስለኢትዮጵያዊነት ሊናገሩና ኦሮሞ እንዴት በኢትዮጵያዊነት ታሪክ ድርሻ እንደነበረው ሊያብራሩ ይሞክራሉ፡፡ ልጅቱ ስትሞላ ያደገችበትን ትርክት እንዲነግሯት መከራ ታያለች፡፡ ሚኒሊክን ከአደዋ ድል ለመለያየት አለኝ የምትለውንና በአደዋ ላይ አሉታዊ ተጽኖ ይኖራቸዋል ብላ ያሰባቻቸውን ለሚዲያው ለማበርከት የበኩሏን ሞከረች፡፡ ተጠያቂው ቀዝቀዝ ብለውም ቢሆን እውነቱን ሊክዱላት ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ይልቁንም ራሳቸውንም ሆነ መላውን ኢትዮጵያ በኦሮሞ ዘንድ እንዲጠላ የተደረገውን የሐበሻነት ስያሜ እየተጠቀሙ ማብራራት ቀጠሉ፡፡ ለዛሬው የኦሮሞ ዘረኛ ፖለቲካ ሰለባ ለሆኑት ኦሮሞዎች ሐበሻ ማለት ሌላው የሚያስበረግጋቸው ድምጽ ነው፡፡ ከራስህ ጋር ስትጣላ ሁሉም የሚያስፈራ ይሆንብሀል፡፡
 2. ኢትዮጵያ፡ ብዙ በዘረኞቹና ሴረኞቹ ኦሮሞ ነን የሚሉና አጋሮቻቸው መርዘኛ ትርክት ሰለባ የሆነው ኦሮሞ እንዲጠላው የተደረገው ሌላው ራሷ የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ይሄም ከላይ ከተነሳው የአደዋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ ጉልህ ድርሻ የነበራቸው ሚኒሊክና ጎበና አልፎም ሌሎች ብዙ አባቶች በኦሮሞ ዘንድ ማስፈራሪያ እስከሚሆኑ ድረስ እንዲጠሉ ትልቅ የሐሰት ትርክት በመስራት በብዙ ሕዝብ ስነልቦና ጥላቻ እንዲሰማው ተደርጓል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ኦሮሞ ሆኖ ኢትዮጵያዊነቱን እንደልቡ በኩራት መናገር የሚችለው ጥቂት ነበር፡፡ ቆይቶ በቅርብ በመጣው ለውጥ ይልቁንም የለማ የኢትዮጵያዊነትን ዘመቻ ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያዊነት ስሜት ተመልሰው ቢገቡም አሁንም የ27ዓመቱ ሐሰተኛ ትርክት ሙሉ በሙሉ የስነልቦና ነጻነት ሊሰጣቸው አልቻለም፡፡ እስካሁንም ግን ኢትዮጵያዊ ነን ለማለት የልቻሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ግን ቀደም ባለው ጊዜ ብዙ ኦሮሞ ዜግነቱን ሲጠየቅ ኦሮሚያ እንደሚለው ዘመን አደለም፡፡ እንግዲህ ኦሮሞን ከገዛ አገሩ አስወጥቶ ኦሮሚያ በሚባል የቅዠት ሀገር ስደተኛ ያደረገው በፕሮፓጋንዳ የተፈጠረበት ስነልቦናው እንጂ በአካል ተሰዶ አልነበረም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ኦሮሞ ምንም ድርሻ የለውም ብለው ከኢትዮጵያዊነት የለዩት ሴረኞቹ ዛሬም ይነግዱበታል፡፡ አሁንም ይቀራል፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያዊነት አልፎም የአፍሪካም ልዩ ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዞ መገኘት በሀሰት ትርክት ስነልቦናቸው ለተጎዳና የሴረኞቹ የአስተሳሰብ ባሪያ ለሆኑት ብዙዎች ከምንም በላይ ውርደት ነው፡፡ በሌሎም ኢትዮጵያውያን ላይ በኦሮሞ የተደረገው ከኢትዮጵያዊነት ማግለል ሴራ ተሰርቷለ፡፡ እንደ ኦሮሞ ግን አልነበረም፡፡ ዛሬ ሌሎች በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያዊነታቸውን እያጠነከሩ ነው፡፡ አፋር ከድሮው ጀምሮ እንኳን ሰው ግመሌቼም የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቋታል ባይ ነው፡፡ ለሱማሌም የኢትዮጵያ ባንዲራ ምልክቱ ነው የአሁን የሱማሌ አካሄድ ግን በታሪክ የተፈጠረውን የሴረኞችን ትርክት በእውነተኛው ትርክት መተካት በይበልጥም ደግሞ ከሱማሌ ማህበረሰብ ሆነው ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጉልህ ድርሻ የነበራቸውን ግለሰቦች ታሪክ ወደፊት በማምጣት የኢትዮጵያዊ የአገር ባለቤትነት ድርሻን ማጉላት ነው፡፡ መልካም የሚባል ነው፡፡
 3. የፊደል መቀየር፡ የኦሮሞ ከግዕዝ ወደ ላቲን ፊደል መቀየር ከዚህ በፊት ብዙ ምሁራን ተከራክረውበታል፡፡ እውነታው ግን የግዕዝ ፊደል ለኦሮምኛ ቋንቋ ምቹ ያለመሆን ሳይሆን ሴረኞቹ ከኢትዮጵያና እነሱ ሐበሻ ከሚሉት ሕዝብ ለማራቅ ሆን ብለው ያደረጉት ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ የግዕዝ ፊደል አዳዲሰ ምልክቶችም ለመፍጠር ሆነ ብዙ ድምፆችን ለማካትት ከየትኛውም ፊደል በተለየ የተሳካለት ነበር፡፡ የኦሮሞን ቃላት የሚወክሉ ፊደላት ቢጎድሉት እንኳን አዲስ ምልክትን መጨመር ቀላል ነበር፡፡ ለምሳሌ መቀሌ የመጻፍበት ቀ በግዕዝ ፊደል ውስጥ አልነበረም፡፡ የላቲን ፊደል ለብዙ ቋንቋዎች መገልገያ ቢሆንም እንደወረደ አደለም እንደየቋንቋው የሚጨመሩ ሌሎች ምልክቶችና አልፎም ራሳቸውን የቻሉ ፊደሎች አሉ፡፡ ግዕዝ እንደ አማርኛ አልነበረም፡፡ እጅግ የበለጸገ የቃላት ብዛት ነበረው፡፡ ፊደላቶቹም ለዛ የተዘጋጁ በመሆናቸው ብዙ ድምጾችን እንዲያካትቱ ነው፡፡ ዛሬ ላይ በአማርኛ አንድ አይነት ድምጽ የሚመስሉት የእነ ሀ አ፣ ሰ ዘሮች የተለያየ ድምጽ ነበራቻ፡፡ ለምሳሌ “ሰረቀ” ና “ሠረቀ” እዩ ሲነበቡም ትርጉማቸውም ፍጹም የተለያየ ነው፡፡ ዐ እና አ ድምጻቸው ሳይቀር በግዕዝ የተለያየ ነው፡፡ በአማርኛ ይሄ የለም፡፡ ከዚህ በተረፈ አዳዲስ ፊደላት መጨመር በግዕዝ ቀላል ነው፡፡ አንዴ የመሰረታዊ ድምጹን ፊደል ከተቀረጸ አባዥ ድምጾችን በቀላሉ ይ ቀረጻሉ፡፡ ለምሳሌ ፐ፣ ቨ የመሳሰሉ ፊደላትንና ዘሮቻቸውን የሚጠቀሙ ቃላት በግዕዝ  የሉም እነዚህ ፊደላት የገቡት አንዳንድ የውጭ ቃላትን በግዕዝ ፊደል ለመጻፍ ነው፡፡ በኦሮምኛ ዛሬ dh በሚል ፊደላት የተተካው ድምጽ በግዕዝ ፊደል ተቀርጾለት ነበር ግን በምን ምክነያት እንደሆነ ባይገባኝም እስካሁንም የግዕዝ ፊደል ሶፍትዌር አዘጋጆች ይሄን ፊደል አላካተቱትም፡፡ አስናለሁ፡፡ ምን አልባት አታካቱ ተብለው ይሆን? በዚህ መልኩ ግን ግዕዝን ለኦሮምኛም ሆነ ሌሎች ቋንቋዎች መጠቀም ቀላሉና የራስ በሆነው መመካት ጭምር ነበር፡፡ በዋናነት በኦሮሞ የተጀመረው የፊደል መቀየር ሌሎችም የሄንኑ እንዲከተሉ ተደርጓል፡፡ወደፊት ግን ግዕዝ በአፍሪካ ደረጃ ፊደላችን ይሁን የሚል አስተሳሰብ ሊነሳ እንደሚችል አስባለሁ፡፡ ያኔ ኦሮሞ የግዕዝ ፊደልን ለመጠቀም አንዳዲስ አንግዳ ሊሆን ነው፡፡ ይሄ አይሆንም ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል ሊሆን የሚችልባቸው ብዙ ምክነያቶች እየታዩ ስለሆነ፡፡ ዛሬ ላይመስል ይችላል ግን ቆይተን እናየዋለን፡፡
 4. ሐበሻዊነት፡- ሌላው ኦሮሞ እንዲጠየፈው የሆነው ከላይ የጠቆምኩት ሐበሻዊነት ነው፡፡ ሐበሻዊነት በእርግጥም የዘር መለያ ነው፡፡ ሐበሻ የሚባለው ማሕበረሰብ ከሌሎች ዓለም ላይ ከአሉት ማሕበረሰብ የሚለይበት በሕብረ ቀለምነቱ ነው፡፡ ሐበሽ ማለት ድብልቅ ሕዝብ ነውና፡፡ ይሄን ታላቁ መጻፍም የኢትዮጵያና የፉጥ (ሊቢያ) ድብልቅ ሕዝብ ሲል ይጠቅሰዋል፡፡ ለማንኛውም ሐበሻ የሚባለው ሕዝብ ዘሬ በሳይንስ ግልጽ ሆኖ ያለ የተለየ የዘር ግንድ ያለው ለሳይንስም ለየት ያለ ግብዓት የሆነ ነው፡፡ ሐበሻ ከሶስት ዋና ዋና የዘር ግንዶች የሚመጣ ነው፡፡ የጥንታውያን ሌቫንት (ለመጀመሪያ ጊዜ እርሻን የፈለሰፉ የሶሪያና አካባቢው)፣ የአሪ (አሪ ማህበረሰብ ውስጥ ዛሬም የዚህ ዘር ግንድ ነጹሁ አለ)፣ ከማሳይ ከሚባለው ኬኒያ ውስጥ ከሚኖረው ሕዝብ ጋር በሰፊው የምንጋራው አንድ ሌላ ኢትዮጵያና አካባቢው ያለ የዘር ግንድ ነው፡፡ እነዚህ ሶስት የዘር ግንዶች ከ99 በመቶ በላይ የሆነውን የዘር ድርሻ በመያዝ የአብዛናው ኢትዮጵያ፣ ሱማሌ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን የመሳሰሉ በአካልም የሚመሳሰሉት ሕዝቦችን የሚወከሉት ዘሮች ናቸው፡፡ እንግዲህ ሐበሻ የሚባለው ህዝብ ይሄ ነው፡፡ የሚገርመው ይሄ ሕዝብ እነዚህ ሶስት የዘር ግንዶች በጋራ ሲጋራ ከሌሎች አፍሪካውያን ጋር ያለው ዘር ትስስር ሳይቀር የተለየ ነው፡፡ ሶሶስቱም የዘር ግንዶች በሌሎች አፍሪካውያን ዘር ውስጥ እምብዛም አይታዩም፡፡ ከላይ እንደጠቆምኩት ማሳይ በብዛት አንደኛውን ኢትዮጵያዊ መሠረት ያለውን የዘር ግንደና(ከ70 በመቶ በላይ ለማሳይ ይሄ የዘር ግንደ ነው) የሌቫንቱን(በጥቂቱ) ይጋራናል፡፡  ሆኖም ግን ብዙ ኢትዮጵያውያን ዘልቀው እስከ ደቡብ አፍሪካ እንደሄዱ የሚያሳይ ይሄንኑ ከላይ የጠቀስኳቸውን ዘር ግነዶች በደማቸው የየዙ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ታንዛንያ ውስጥ በብዛት አሉ፡፡ ወደፊት ማንነትን ፍለጋ መነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡ ሐበሻ ዘር ነው፡፡ ነገድ ነው፡፡ በኦሮሞ አማራ ትግሬ ሱማሌ አፋር መካከል አንድም ልዩነት የለም፡፡ አማራ ሐበሻ ሆኖ ኦሮሞ ሐበሻ የማይሆንበት ተፈጥሮአው እውነት የለም፡፡ ሐበሻነት ተፈጥሮዋዊ እውነት እንጂ ባሕልም ቋንቋም አደለም፡፡ ይሄን ጉዳይ ደጋግሜ አንስቼዋለሁ፡፡ የሚገባው ቢኖር እውነቱ ይሄ ነው፡፡ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ያመቸናል ያሉ ነበሩ ኦሮሞን ከሐበሻዊነት አውጥተው አሁንም በገዛ የደም ማንነቱ ሳይቀር ባይተዋር ያረጉትና ሐበሻ የሚለውን ቃል ራሱ እንዲጸየፈው የሚያደርግን ስነልቦና የፈጠሩበት፡፡
 5. የኢትዮጵያ ባንዲራ፡ ከላይ አንስቼዋለሁ ግን ጉዳዩ በራሱ ትልቅ የስነልቦና ችግር ስለሆነ ነው፡፡ ዛሬ ለብዙ ኦሮሞ ድሮ አባቶቹ የነጻነት አርማ አድርገው ሲዋደቁላት ለነበረች አገር ምልክት አድርገው ያቆዩትን ባንዲራ ማስጣል ትልቁ የሴረኞቹ ድል ነበር፡፡ አሁን ለብዙ ኦሮሞ የኢትዮጵያ ባንዲራን ሲያይ ይነዝረዋል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ በዚህም ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከሚጋሩት እውነት ወጥቶ በራሱ ጊዜ የሥነልቦና ቀውስ ውስጥ ገብቶ እናየዋለን፡፡ አደዋ በሉት ሌላ ሴረኞቹ አሁን የፈጠሩበትን የስነልቦና ቀውስ እስከሚያመጡበት ጊዜ ድረስ ከሌሎች በተለየ የኢትዮጵያ ባንዲራ ለኦሮሞ ጌጡ ነበር፡፡ በቅርብ አብይ ተመርጦ አምቦ በሄደ ጊዜ ሊያውም ባለኮከቡን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራወን ይዘው የወጡ ፈረሰኞች በመታየታቸው በኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ አራማጆች ዘንድ ምን ያህል ውግዘት እንዳስከተለና ፈረሰኞቹንም ለማሸማቀቅ ምን ያህል ፕሮፓጋንዳ እንደተሰራ አይተናል፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ግራ ገብቶታል፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነው ራሱ ኦሮሞ ከሆነ የኢትዮጵያን ባንዲራ መያዝ ቢፈልግ እነኳን የሚደርስበትን ውግዘትና የሥነ ልቦና ጫና በመፍራት አይዝም፣ የኦነግን እንዳይዝ በብዙዎች ኦነግ የወሮበላ ቡድን እንደሆነ ይታወቃል፣ የኦፒዲኦን አንዳይዝ ኦነጋውያን ይነሱበታል ብቻ ምን አለፋችሁ ይሄ አንዱና ትልቁ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የስነልቦና ቀውስ የፈጠረ ነው፡፡

እንግዲህ ከእውነትና ከማንነት ጋር ተጣልቶ ነጻና ሠላም ሆኖ መኖር ከየት ይመጣል? ዛሬ ላይ ብዙ ኦሮሞ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጋር የተያያዙ ታሪካዊና ተፈጥቶአዊ እውነቶችን እንዲክድና ከማንነቱ ውጭ በሆነ የስነልቦና አስተሳሰብ ስለሚኖር በኢትዮጵያውያን ምድር የሚሆነውን ሁሉ እንደልቡ በባለቤትነት ለመጋራት አልቻለም፡፡ በሚኒሊክ አገር እየኖረ ሚኒሊክ የሚለው ቃል በተጠራ ቁጥር ስቅጥጥ እያለው ይኖራል፡፡ በኢትዮጵያ እየኖረ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ ባህልና አስተሳሰቦች አንዲሁም የኢትዮጵያዊነት ምልከቱ ባንዲራው ሳይቀር የሚያስበረግገው ኦሮሞ ቀላል አደለም፡፡ ሐበሻ ነኝ ማለት ለብዙ ኦሮሞ ያሳፍረዋል ብቻም ሳይሆን ሐበሻ በለው የነገሩትን ሌሎችንም እጅግ በካፋ ጥላቻና ዘረኝነት ነው የሚያየው፡፡ አሁንም ከዚህ የስነልቦና ቀውስ ለመመለስ ከመሞክር ይልቅ  ሌላ ተጨማሪ ከማንነቱ የሚያወጣውን ትርክት አቀንቃኝ እየሆነ እንዲቀጥል በአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ ከተው የሚነግዱበት በአለ በሌላ ጉልበታቸው እየሰሩበት ነው፡፡   እንግዲሀ በዋናነት ከራሱ በወጡ ኦሮሞ ነን በሚል ኦሮሞን የአስተሳሰብ ባሪያቸው ያደረጉትን እየተከተለ ብዙ የራሱ የሆኑትን እውነተኛ ማንነኖችና የባለቤትነት ድርሻ አልፎም ከዘር ማንነቱ እራሱን በስነልቦና በማግለል በባይተዋርነት እንዲኖር ብዙ ኦሮሞ ግድ ሆኖበታል፡፡  የራሱን አደዋን፣ የራሱን ጀግኖች አባቶች ገድል፣ አባቶቹ ሰርተውና ጠብቀው ያኖሯትን አገር ታሪክ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኩራትና በደስታ እየዘከረው ለብዙ ኦሮሞ ግን የሚያሸማቅቀው ሆኗል፡፡ የሚገርም ነው! ይሄን ማስተዋል እንዴት ተሳነን? አሁንም እላለሁ በኢትዮጵያዊነታችሁና አባቶቻችሁ በሰሩት ታሪካዊ ገድል የምታምኑና የምትኮሩ ከዚሁ ማህበረሰብ የወጣችሁ ሁሉ ይሄን ታሪክ ወደ እውነቱ በመቀየርና ኦሮሞን ሁሉ ወደ ክብሩ እንድትመልሱት መሥራትን እጠይቃችኋለሁ፡፡ ጉዳዩ የፍትህም የዲሞክራሲም ሳይሆን እጅግ ሕዝብን የሚያዋርድና በስነልቦና ከሌሎች ባይተዋር የራሳቸው ንግድ መጠቀሚያ ያደረጉት የሴረኞች ሴራ ነው፡፡

ከላይ እንደጠቆምኩት ዛሬ ለብዙ ኦሮሞ ጀግና የለውም! ጀግና አድርጎ እንዲያምን የተደረግው ዛሬም እየነገዱበት ያሉትን ነው! ዛሬ ለብዙ ኦሮሞ ምሁር የለውም ምሁር ብሎ እንዲቀበል የተደረገው ራሳቸውን ትልቅ በማድረግ የስነልቦናና አስተሳሰብ ዘመቻ የከፈቱበትን ተራ ወሮበሎችን ነው፡፡  ዛሬም ከሌሎች በተለየ በጭቆናና በበታችነት ስነልቦና እያኖሩት ነጻ አውጭህ ነን በሚል እየነገዱበት ነው፡፡ ቢያንስ ለ50 ዓመት ተነገደበት፡፡ ይሄን ማስተዋል ሳንችል በዚሁ ከቀጠለ ዛሬ በቁጥር በዝቶ የምናየው ሕዝብ በቁጥርም እንደሚወርድ አትጠራጠሩ፡፡  ኢትዮጵያዊ መሠረት ላይ ከአልታነጸ በኢትዮጵያ ምድር እየኖሩ ከስነልቦና የበታችነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሚኒሊክን እየፈሩ በሚኒሊክ አገር ሠላም አግኝቶ መኖር አይቻልም፡፡ ሚኒሊክ ከሸዋ እስከቦና ዛሬም ድረስ የሚታዩ የኦሮሞ እሴቶች እንዲቀሩ ያደረጉ ጭርሱንም የኦሮሞ መሪ በሚያስብል መልኩ የመሩ ታላቅ ንጉስ ናቸው፡፡ ሚኒሊክ ባይኖሩ ዛሬ ገዳ እያለ የሚያቅራራ ይቅርና ገዳ የሚለውን ሥም ራሱ የሚያውቅ ባልኖረ ነበር፡፡ ሚኒሊክ በኬኒያ ተቆርጠው እንደቀሩ ኦሮሞዎች ሥርዓታቸውን ሁሉ አጥፍቶ የነጭ ታሪክን የፈጠሩለት እንጊሊዞች ሳይሆን ቦረናን በገዳ ሥርዓት እንዲተዳደር በቀጥታ ገዳን የቦረና አስተዳደራዊ መንግስታዊ መዋቅር በማድረጋቸው ነው ዛሬ ድረስ የቆየው፡፡ የኦሮሞ የተባሉ ዛሬም ድረስ የምናያቸው ባህሎች የገዳውና ሌሎች ባህላዊ እሴቶችን በመጠበቅ የቆዩት የሚኒሊክ ዋና የነበሩት ሸዋዎች እንጂ ወለጋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሐርር፣ ጂማ አደለም፡፡

ይሄን የምለው ዛሬ በሚኒሊክ ላይ ከሚነሱ የኦሮሞን ባህልና እምነት አጠፋ የሚሉ  የሐሰት ትርክቶች አንጻር እንጂ እንደእውነቱ ሰው እንደሚኖርበት ማህበረሰብና ሌሎች እውነታዎች  ባህሉም ሊቀየር ይችላል፡፡ በአርሲ፣ ባሌ፣ ጂማ፣ ሐረር አብዛኛው የአሮሞ ማሕበረሰብ የእስልምና ተከታይ በመሆኑ የእስልምናውን እምነት ባሕሎችናና አኗኗሮችን ስለሚከተል ዛሬ ጠፉብን የሚባለው ግን ያለቦታው ሚኒሊክ የሚጠሉበት ባህሎች በእነዚህ ቦታዎች የሉም፡፡ ለዚህ ምንሊክ አደሉም ምክነያቱ፡፡ ለውጥ ደግሞ የሕዝብ ሂደት ነው፡፡ ሚኒሊክን ለመክሰስ የሌለ ታሪክ ሲፈጠር ማስተዋል አእንኳን የለም፡፡ ሚኒሊክ የማንንም ሀይማኖት ባሕል አንድም ቦታ አልቀየሩም፡፡ ሰሞኑን ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ የተናገሩት አሳፋሪ ንግግርን አስታውሱ፡፡ እንደ ኃይሉ ጎንፋ ዛሬ ኃይሉ የመባላቸው ምክነያት ምኒሊክ ናቸው፡፡ በዚህ ደግሞ ሚኒሊክ እጅግ ማንነትን የሚያጠፋ ሥራ እንደሰሩ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ እኝህ ሰው የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ ኦሮሞ ማህበረሰብ ቢወለዱ ሥማቸው የኦሮሞ ይሆን ነበር ወይ ተብሎ ቢታሰብ ያለው እድል 20 በመቶም አይሆንም፡፡ በእስልምና እምነታቸውን በሚገልጽ ሁኔታ ሥማቸው ከመገርሳነት ወደ አበዱልቃዲሪነት የቀየሩም ምክናያቱ ሚኒሊክ ይሆኑ፡፡  ልብ በሉ ሕዝብ እንሚያምነው እምነት፣ በአጎራባችና አብሮ እንደሚኖረው ሌላ ሕዝብ ባሕል በሂደት ብዙ የነበሩትን ባህል በአዳዲስ ከሌሎች በሚወርሳቸው ባሕል ሊቀይር ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የመነግስት መዋቅር ደርሻ ሊኖረው ይችላል፡፡ የሚኒሊክ መንግስት ግን በአስደናቂ ሁኔታ ከዚህ አይነት ሕዝብን ከነበረበት ባህልና እምነት የመቀየር ደርጊት ፍጹም የጸዳ ነበር፡፡ ኢትዮጵያንም ዘሬ በምናየው ሕብረ ብሔራዊ ባህልና እምነት ያገኘናት የሚኒሊክ አገር በመሆኗ ነው፡፡ ይሄ የሚኒሊክ ልዩ ታሪካዊ አሰራር ነው ዘሬ ተገልብጦ እየተነገረው በሥነልቦና ራሱን የሴረኞች ባሪያ ያደረገ ትውልድ የተፈጠረው፡፡ ሚኒሊክ ብቻም አደሉም ለአልጋ ወራሽነት የመረጡት ኢያሱንም አሰድገው ዙፋናቸውን ያስረከቡት በዚህ ፍልስፍና አሳድገው ነበር፡፡ ይሄ ፍልስፍና ከዛም በፊት በነበሩ፣ ከዛም በኋላ በመጡ አልተሞከረም፡፡ ኃይለስላሴ እንደዛ አልነበሩም፣ ደርግም እኳን እንደዛ አልነበረም፡፡የወያ ወሮበላ ቡድንና ኦነጋውያን ሚኒሊክን ኢላማ ያደረጉበት ምክነያትም የሚኒሊክ ታሪክ እውነታዎች ፍጹም እነሱ ላሰቡት ሴራ አደገኛ በመሆኑ ነበር፡፡   እውነቶች በተገለጡ ቁጥ ሁሉንም ሊጠይቅ የሚችል ትውልድ እንደሚመጣ አስቡ፡፡ ያኔ በውሸት ትርክትና ስነልቦና የተገነባ ማህበረሰብ አባል መሆንን የሚፈልግ የለም፡፡ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆመው ማውረድ እንደሚያዳግት አትጠራጠሩ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር አጥንጣቸውንና ደማቸውን አፍሰው አገራችንን ጠብቀው ያስርከቡንን የጀግኖች አባቶቻችንን ወኔና መንፈስ ያድለን!

ለዕል አምላክ እግኢአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ! አሜን!

13 COMMENTS

 1. “ዛሬ በሚኒሊክ አደባባይ ከሚኒሊክ በቀር ፈረሰኛ የማይታይበት … በዓል ተከብሯል! ” ወይኔ ወይኔ! አናኛቱ ኦሮሞ ባይተዋር ሆነ!!
  1* ሃበሻና ጣልያን የአያቶቹን ሃገር በቅኝ ግዛትነት ለመቀራመት ለከፈቱት ጦርነት መታሰብያ ላይ፣ የጦርነቱ ማገዶ (cannon fodder) የነበሩ ኦሮሞዎች የልጅ ልጆች ሳይካፈሉ ቀሩና ክብርና ሞገስ ቀረባቸዉ!!
  2* በጌቶቹ ብልት አልኮራም በማለቱ ኢትዮጵያዊነትም ቀረበት!
  3* ፊደልን ትቶ ቋንቋዉን በትክክል የሚቀርጸዉን ቁቤን በመምረጡ “አፍሪካዊ ኩራት” አጣ!
  4* ከአረብያ ለፈለሱት የተሰጠውን ስም የኔ አይደለም በማለቱ “ሃበሻዊነት” ቀረበት!
  5* ድሮ አባቶቹን እና እስከዛሬ እሱንም በባርነት ደረጃ ዝቅ አድርጋው የነበረችውን የአገር ምልክት ባንዲራዬ አይደለም ማለቱ እዉነትም “ዛሬ ኦሮሞ ግራ ገብቶታል”!!
  እዉነትም “በውሸት ትርክትና ስነልቦና የተገነባ ማህበረሰብ አባል መሆንን የሚፈልግ የለም” ብሎአል ኦሮሞ!!!
  ስለዚህ ኦሮሞ “የስነልቦናና አስተሳሰብ ዘመቻ የከፈቱበትን ተራ ወሮበሎችን ” ባዶ ማስቀረቱ፣ የጀግኖች አባቶቹን ወኔና መንፈስ ታድሎአል!!
  Habesha super-hypocrites like ሰርፀ ደስታ, what are you going to do???

 2. ሁልም የሚገርመኝ ነገር ምንድነው ኣንዳንድ መርዘኛ ሰዎች ስለብዙሃኑ ኦሮሞ ሊመልሱለት ይፈልጋሉ። አንደሚመስለኝ ወይ የወያነ ሎለዎች ናቸው ወይ ደግሞ ድንጋይ ራሶች ናቸው። ኣንድ ሰው ታሞ ሃኪም ጋ ሲሄድ ሃኪሙ የሚጠይቀው በሽተኛውን አንጂ ይዞት የመጣውን ኣጃቢ ኣይደለም። ኣሁን ኣባ ጫላ ስለሚልዮን ኦሮሞ ሊመልስ መብት ማን ሰጠው? ካላበደ በስተቀር። ጸሁፉ ኣይምሮው ጤነኛ ለሆነ ሰው በቀላሉ የሚረዳውና ፖሰቲቭ ኣስተያየት ነው። ኣንዳንድ በሽተኛ ኦሮሞ ወንድሞች ግን የስነ ኣይምሮ ጠበብቶችን ቢያማክሩ ከጥላቻ በሽታ ሊፈወሱ ይችላሉ። ጠበልም ቢሞክሩ ኣይከፋም። This kind of hatred doesn’t help anyone except satan.

 3. አባ ጫላ
  ሳይንቲስቱ ዶክተር አበራ ሞላ የሰንዳፋ ኦሮሞ ተወላጅ ፊደላችንን ኮምፒተራይዝድ ያደረጉትን ሳይንሳዊ ስራዎች በዚህ መክፈቻ ቁልፍ ይመልከቱ መልሱንም እዛው ያገኙታል አጥብቀው ያጢኑት

  https://am.m.wikipedia.org/wiki/ኣበራ_ሞላ

 4. ክቡር ሰርፀ ደስታ
  ሳይንቲስቱ ዶክተር አበራ ሞላ የሰንዳፋ ኦሮሞ ተወላጅ ፊደላችንን ኮምፒተራይዝድ ያደረጉትን ሳይንሳዊ ስራዎች በዚህ መክፈቻ ቁልፍ ይመልከቱ መልሱንም እዛው ያገኙታል አጥብቀው ያጢኑት እንዲሁም የተለያዩ እውቅ የኦሮሞ ሀቀኛ ምሁራን እነ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ እነ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድን( የአጯሉ ሁንዴሳ አጎት /የቅርብ ዘመድ) እነ በአሉ ግርማ እነ ሻለቃ ሳህሌ ደጋጎ እነ ትዝታ በላቸው /V O A / እነ ብላታ ደሬሳ አመንቴ እነ ሰለሞን ደሬሳ እነ ይልማ ደሬሳ ከቀደምት አባቶች እነ አባ ገመችስ አናሲሞስ ነሲብ እነ አባ መገርሳ/አቡነ ጴጥሮስ/ እነ አባ ተየሱስ ዋቅጅራ ሰለ ኢትዮጵያ ፊደል ብቃት ጥራትና ምልዓት የፃፉትን ይመልከቱ

  https://am.m.wikipedia.org/wiki/ኣበራ_ሞላ

  LEAVE A REPLY

 5. @mootummaa; ዐይንህ ዉስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ከሌላ ሰው ዐይን ጉድፍ ለማውጣት ጣት ታሾላለህ! እኔን “ስለብዙሃኑ ኦሮሞ ሊመልስለት ይፈልጋል” ብለህ ትከሳለሕ ያንተው ወዳጅ ግን በጅምላ “ኦሮሞ ባይተዋር ሆነ!” ሲል ብዙሃኑን መሳደቡ አይታይህም! Hypocrisy ማለት ይህ ነው! ኸናንተ ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል? እንደማይቻል በሚትሞነጫችሩት ሁሉ ታሳያላችሁ፣ መልሳችሁ ደግሞ ሌላውን ትወነጅላልችሁ! አጭበርባሪዎች!!

  @Abrham kejela, ሌላው አጭበርባሪ; I have seen your irrelevant side issue type arguments more than often. It has never touched upon the central issue.And don’t list people like ፍቅሬ ቶሎሳ here, just they have Oromo names, but who have never written a single paragraph in Oromiffa to give “expert” opinion! The rest have lived during the dark ages when writing in Afaan Oromoo was punishable by law, but some of them did the best they could under the prevailing circumstances. No thanks, We refuse to learn our language, culture and history from anti-Oromos!

  Anyway, በሚኒሊክ ዘመን ለደነቆራችሁ፣ how much you ever try, Qubee will never be reversed! እርማችሁን አዉጡ!

 6. አባ ጫላ
  ሰለ ስድብህ አዝናለሁ ብዙ ስድብ አለ ግን እንደአንተ ወርጄ አልሳደብም ሳፉ ነው እውነትም You can Not Teach New Tactics To Old Dog ያሉት አሮጌ ጊዜ ያለፈበት አስተሳሰብህን ይዘህና ዛሬም ታቅፈህ ትውልዳችንን ጨለማ ዉስጥ አስቆልፈህ ያለህ አሁንም ዛሬ ያልለቀቀህ በሚኒልክ ጊዜ የደነቆርክ ይልቅ አንተ ነህ እስቲ ከዚህ በትች ሀቀኛ የኦሮሞ ምሁራን አፋን ኦሮሞን ለማሳደግና ለማፋፋት ያቀረቡትን የጋረደህን አይነ ጥላ ግለጥና ተመልከት ለማንኛውም
  ለመሆኑ የኦሮሞን
  የአቃፊነት ባህል ጉዲፈቻን ጉዲሳን ሞጋሳን ሜዴቻን ሆርማ ሆዳን ታውቀዋለህ ?ለማንኛውም ያ ቡልቱ ዱቢና ጎፍታኮ

 7. @abbaa caala,
  I wont get tired to respond to your non sense reply. The article says that the Oromo people should celebrate the Adwa victory. Because the Oromo people including my grandfather fought for the freedom of my country. He fought gladly without expecting anything from the king. My father followed his footsteps and fought for the territorial integrity of my beloved country. That is why when Adwa is celebrated, the Oromo people should wave proudly the flag they fought for. The green, yellow, and red flag is not only for Amhara, Tigre, but also belongs to me. People like you (yedil atbiya arbegnoch) open your mouth without any facts. When the egg hatches, the chick will follow anything that is moving. For the last 27 years you only know your bosses woyane propaganda and reflect their opinion. You don’t have any clue about the truth behind our arguments. This trend of hatred and hoopla will change sooner or later. All OLF/TPLF puppies will never succeed to divide our country. We fought woyane for the last decade and we’ll start our struggle once again for equality and basic human rights online and on the ground. We’ll never get weary until we see all Ethiopians treated with respect, their right to live in any area of the country respected, to use the language they preferred to speak (not someone imposed on them), freedom from discrimination, imprisonment, torture, freedom of opinion and expression, the right to work anywhere they want and the right for education etc. Just wait and see.

 8. እናመሰግናለን ሞቱማ
  እነ ጎበና ዳጬ ብሄራዊና አለም አቀፍ ጀግኖ
  ቻችን ናቸው ዶክተር ብርሃነምስቀል አበበ ስኜ አሁን የፃፈውን ይመልከቱ

 9. @mootummaa; “The article says that the Oromo people should celebrate the Adwa victory.” Adwa may be worth celebrating for galtuus like you! But not for an an Oromo proud of his Oromoness! Here is why, unless you still say telling the truth divides the country. በዉሸት እንኳን ሃገር፣ አጥርም አይገነባም!

  The victory at Adwa may have served as a symbol of victory of the black race over white colonialists. But within Ethiopia, it has masked the fact that Ethiopia itself was a colonial power. The battle at Adwa in fact was a fight between two colonialists scrambling for African territories, Italy to gain more colonial land including the home territory of Minilik, and Minilik defending his home turf and his colonies in the south.

  Abyssinian under Menelik was the only black power to take part in the colonial scramble. Menelik clearly expressed motives of his conquests in a letter dated 10th April 1891 to the European powers meeting in the infamous Berlin Conference (to partition Africa) in which he stated: “I have no intention of being an indifferent onlooker if the distant powers have the idea of dividing up Africa for Ethiopia has been for more than fourteen centuries an island of Christians in the middle of the sea of pagans.”

  Thus, “…Menelik claimed a place among the colonial powers for his Ethiopia which became the only African colonial power the Europeans hesitatingly recognized. The weapons Menelik used to conquer the areas in the south and later to defend against the Italian invasion [of 1896] came from Europe.” see Pausewang, S., “A new world order for third world peasants?” in Adedej, A. et al (eds.) “Africa within the world”, Zed books, London, 1993.

  A paper presented to the League of Nations in 1935 under the title “Domination of the Negus over Non-Abyssinian Populations” described the indescribable agony of the conquered peoples as follows:
  “The Abyssinian domination in the conquered countries takes concrete form in the slave trade and the so-called gebbar system. The slave trade … is due not only to a desire for gain, but also to the idea, deep-rooted in the Abyssinians’ mind, that their victories have left them absolute masters of populations which, in their eyes, are no more than human cattle.

  The gebbar system is a form of slavery, and is regarded as such by European writers and travelers. In each of the countries conquered and annexed by Abyssinia, a body of Abyssinian troops is stationed, comprising the soldiers themselves and their families. The inhabitants of the conquered country are registered in families by the Abyssinian chiefs, and to every family of Abyssinians settled in the country there is assigned one or more families of the conquered as gebbar. The gebbar family is obliged to support the Abyssinian family; it gives that family its own lands, builds and maintains the huts in which it lives, cultivate the fields, grazes the cattle, and carries out every kind of work and performs all possible services for the Abyssinian family. All this is done without any remuneration, merely in token of the perpetual servitude resulting from the defeat sustained thirty years ago.” in: Ethiopia: land of slavery & brutality – League of Nations, Geneva 1935, Official No. C.340.M.171.1935.VII.

  ስለዚህ፣
  ልክ ነጮቹ የቀይ ህንዶችን ህዝብ እስክ 90% እንደቀነሱት፣ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች በአውስትራሊያ ነባር ህዝቦች ላይ አሰቃቂ ግፍና ዕልቂት እንደፈጸሙት፣ እዚሁ አፍሪካ ኮንጎ (ዛዬር) ውስጥ የቤልጂዬም ግዢዎች 10 ሚሊዮን ጥቁሮችን እንደጨፈጨፉት ሁሉ
  ሚኒሊክም በጦርነትና በባርያ ፍንገላ ሰበብ የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር ከ10 ወደ 5 ሚሊዮን እንዲያሽቆለቁል፣ ይባስ የካፍቾ እና የዎላይታ የመሳሰሉት ህዝቦች ቁጥር በ2/3ኛ እንዲቀንስ አድርጎአል !!

  All these are recorded facts. Surely, it is a blasphemy to those worshiping Minilik. But, for the sake of those black Africans that perished or suffered the agony of colonialism and enslavement in Ethiopia as well, the truth must be told!

 10. አባ ጫላ
  ታዲያ መፍትሄውን ምንም አልተናገርክ
  እሺ መፍትሄው እንደምትሉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ማፈናቀልና በርትቶ መፍጀት ነው?

 11. ጨለምተኛ ምንም መፍትሄ አላቀረብክም
  ያው ዘላለም እንደምትሉት ሌላውን ህዝብ መጨፍጨፍ ነዋ

 12. #Ethiopia
  ኦሮምኛ በራሳችን በኢትዮጵያ ፊደል እንማር (ምንጭ: #Sena Tube.com)

  1 ኤሳ – የት
  2 ዮም – መቼ
  3 ኤኙፊ – ለማን
  4 ሲፍ – ላንተ / ላንቺ /
  5 ማሊፍ – ለምን
  6 ከም – የትኛው
  7 ቦሩ – ነገ
  8 ዲማ – ቀይ
  9 አዲ – ነጭ
  10 ጉራቻ – ጥቁር
  11 ማገሪሳ አርንጒዴ
  12 አባ – አባት
  13 ሙጫ – ልጅ
  14 ኢጆሌ – ልጆች
  15 ዳኢማ – ህፃን
  16 መና – ቤት
  17 ሲ – አንተ
  18 መቃ – ስም
  19 ፊራ – ዘመድ
  20 ማቲ – ቤተሰብ
  21 ከና – ይህ
  22 ሰን – ያኛው
  23 አስ – እዚህ
  24 አች – እዛ
  25 – ኬ – ያንተ
  26 ኪያ – የኔ
  27 ሲገሌ – ገባህ
  28 ኛታ – ምግብ
  29 መና ኛታ – ምግብ ቤት
  30 ሲሬ – አልጋ
  31 ሲሬን ጅራ – አልጋ አለ
  32 ቢሻን – ወሃ
  33 – ጪስ – ተኛ
  34 ለጋ – ወንዝ
  35 ባዬ . ሄዱ – ብዙ
  36 ጋሪ . ደንሳ . ሚሻ – ጥሩ
  37 – ኡመታ – ህዝብ
  38 ኮቱ – ና
  39 ዴም – ሂድ
  40 – ከሌሳ – ትናንት
  41 በልበላ – በር
  42 ኢብሳ – መብራት
  43 ኢፋ – ብረሃን
  44 – ከራ መንገድ
  45 ቦላ – ጉድጓ

 13. ይህ የሰንዳፋ ተውላጅ ሳይንቲስት አበራ ሞላ ፊደላችንን በአለም አቀፍ ደረጃ ዩኒ ኮድ ማለትም ዩኒቨርሳል ኮድ ደረጃ በማስገባትና በማዘመን ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ኮምፒተርና ሞባይል ፎን እንዳበቃው ተመልከቱ
  ዶ/ር ኣበራ ሞላ ዓማርኛ ዊኪፔዲያ
  Dr. Aberra Molla Amharic Wikipedia
  https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB_%E1%88%9E%E1%88%8B

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.