ኢትዮጵያ ወይስ ኩሽ (ጌታቸው ኃይሌ)

አንድ ሰሞን “የጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በሪቨረንድ በንቲ  ቴሶ  ኡጁሉ ተጽዕኖ የኢትዮጵያን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰርዛ በኩሽ ለውጣዋለች” የሚል ወሬ ተናፍሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን አበሳጭቶ ነበር። ብዙ ተቃውሞም ተጽፏል። ይኼ ተጨማሪ ማብራሪያ ነው።

(አቅራቢ፥ ጌታቸው ኃይሌ)

ከመጀመሪያው ለመነሣት፥ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ክፍል ቅድመ ክርስቶስ፥ ሁለተኛው ክፍል ድኅረ ክርስቶስ የተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍትን የያዘ ባለ ሁለት ክፍል ትልቅ የሃይማኖት መጽሐፍ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ብሉይ ኪዳን ይባላል። ይህንን ክፍል በቋንቋቸው በዕብራይስጥ ጽፈው የሰጡን አይሁድ ናቸው። ሁለተኛው ክፍል ሐዲስ ኪዳን ይባላል። የተጻፈው  በጽርእ (በግሪክ ቋንቋ) ነው። በግሪክኛ ጽፈው የሰጡን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ናቸው። እነሱም በዘር አይሁድ ናቸው።

ብሉይ ኪዳን በመሠረቱ የአይሁድ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም፥  የክርስትና ሃይማኖት በብሉይ ኪዳን ላይ ስለተመሠረተ በክርስቲያኖቹ ብዛት ምክንያት ተፈላጊነቱ እጅግ እየበዛ ሄደ። የአይሁድ ሃይማኖትን የያሰው መጽሐፍ ምን እንዳለበት ለማወቅ ፈላጊው ስለበዛ፥ የዕብራይስጡን ብሉይ ኪዳን የግብፁ ግሪካዊ ገዢ (በጥሊሞስ ፊላዴልፎስ (285-246 ቅድመ ክርስቶስ) ዕብራይስጥና ግሪክ የሚያውቁ ሰባ (ሁለት) ሊቃናት ሰብስቦ ወደ ዓለም-አቀፉ ቋንቋ ወደ ግሪክኛ አስተረጐመው። (ሕፃኑን ኢየሱስን በቤተ መቅደስ ያቀፈው ሽማግሌው ስምዖን ከሰባ ሊቃናት አንዱ ነበር የሚል ተአምር በእኛ ዘንድ ይነገራል። ስምዖን ሲተረጕም “ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ከሚለው ከኢሳይያስ ምዕራፍ ፯ ቍጥር ፲፬ ላይ ሲደርስ፥ ድንግል እንዴት ትፀንሳለች? ምን ብየ ልተርጕመው? እያለ ሲጨነቅ፥ “ግዴለህም፥ እንደሚለው ተርጕመው። ከተጠራጠርክ እውነትነቱን ሳታይ አትሞትም” የሚል የአምላካ ተስፋ ተሰጠው። ከ250 ዓመት በላይ በሕይወት ቆይቶ፥ ጌታን ሲታቀፍ፥ “እንግዴህስ ባሪያህን እንዳዘዝከው በሰላም አሰናብተው፤ ማዳንህን ዓይኖቼ አይተዋልና” ብሎ ጸለየ።)

አሁን እንግዲህ፥ ሐዲሱም ብሉዩም በግሪክ ቋንቋ  ሊነበብ ቻለ። የምዕራቡ ቤተ ክርስቲያንም (ማለት፥ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን) በአራተኛው ምእት ዓመት ወደ ላቲን የተተረጐመውን መጽሐፍ ቅዱሷን በዓሥራ ስድስተኛው ምእት ዓመት በይፋ ተቀበለችው። የግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጐመው ከግሪኩ ቅጂ ነው። ለዚህም በቂ ማስረጃ አለ። የኢትዮጵያ ሊቃውንት፥ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ጨምሮ፥ “ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳኗን የተረጐመችው በቀጥታ ከዕብራይስጡ ነው” ይላሉ። ማስረጃቸው አስተማመኝ አይደለም።

የተመረጡት ሊቃናት ሰባ ሁለት ነበሩ። ጥሪውን ተቀብለው ከፍልስጥኤም ወደ ግብፅ ሲሄዱ ሁለቱ በመንገድ ስላረፉ፥ በርትጐማው የተሳተፉት ሰባ ነበሩ እንላለን። ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ሲተረጕሙ፥ ዕብራይስጡ ብሉይ ኪዳን ውስጥ  የሀገርና የሕዝብ ስም ሲያጋጥማቸው፥ አንዳንዱን ዕብራይስጡ ውስጥ እንዳለው ይወስዱታል። አንዳንዱን፥ ለምሳሌ እንደ “ኹሽ” እንደ “ፍልስጥኤም” ያሉ ስሞችን ደግሞ እንዳለ በመውሰድ ፈንታ፥ የግሪክ ተመሳሳይ ስም ይሰጡታል። (ለምሳሌ፥ ፍልስጤምን “ኢሎፍሊ”፥ ኩሽን “ኤይቲኦፕ” አሏቸው።)  የዕብራይስጡ “ኩሽ” የሚያመለክተው ጥቁርን ሕዝብ ነው። ታዲያ  ግሪኮች ጥቁሩን ሕዝብ የሚጠሩት “ኤይቲኦፕ” ብለው ስለሆነ፥ “ኩሽ” የሚለውን ስም “ኤይቲኦፕ” ቢሉት አይገርምም። ባጭሩ፥ ግሪኩ “ኤይቲኦፕ” የሚላቸው ዕብራይስጡ “ኩሽ” የሚላቸውን ሕዝቦች ነው። “ስልቻ” እና “ቀንቀሎ” እንደማለት ነው፤ ሁለቱ ቃላት በሚያመለክቱት በምንም አይለያዩም። እኛ ደግም፥ ከላይ እንደተናገርኩት፥ መጽሐፍ ቅዱሳችንን የተረጐምነው ከግሪኩ ስለሆነ፥ “ኤይቲኦፕ” የሚለውን “ኢትዮጵያ” አልነው። ከዕብራይስጡ ተርጕመነው ቢሆን ኖሮ ምናልባት “ኩሽ” (ኩሳ) እንለው ነበር። ፓስቶሩ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የዛሬ ስድሳ ሁለት ዓመት ባሳተሙት በግዕዝ መዝገበ ቃላታቸው ውስጥ “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም እንዴት እንደተቹት ቢያይ፥ ኢትዮጵያና ኩሽ ትርጕማቸው አንድ ሆኖ የሚያመለክቱት ኢትዮጵያንና ሱዳንን መሆኑን እንደምናስተምር ይረዳ ነበር። መጻሕፍታችንም፥ ለምሳሌ፥ EMML 5649, fol. 37v፡ “ኵሳ አቡሆሙ ለኢትዮጵያ፤ ምስራይኒ አቡሆሙ ለሰብአ ምስር” (ኩሽ የኢትዮጵያውያን አባት ነው፤ ምስራም የግብጾች አባት ነው) ይላሉ።

ጥያቄው መሆን ያለበት “የግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ‘ኢትዮጵያ’ (ኤይቲኦፕ)፥  የዕብራይስጡ ብሉይ ኪዳን ‘ኩሽ’ የሚሉት ስሞች  የሚያመለክቱት እነማንን ነው?” የሚል ነበር። መልሱ ቀላል ሆኖ ሳለ፥ አስቸጋሪ እናደርገዋለን። አንደኛ፥ እነዚህ ስሞች የሚያመለክቱት ጥቁሩን ሕዝብ ነው ብለናል። ሁለተኛ፥ በዓለም ላይ ብዙ ጥቁር ሕዝቦች ቢኖሩም፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራስያን የሚያውቋቸው ጥቁር ሕዝቦች በቅርባቸው ያሉትን ኖባውያንን (ሱዳኖችን) እና ኢትዮጵያውያንን ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ አንድ ጥቁር ሰው ከተነገረ፥ ያ ሰው ወይ ኢትዮጵያዊ ወይም ኖባዊ (ሱዳናዊ) ነው። ባጭሩ፥ ለግሪክ ደራሲዎች “ኢትዮጵያ” (ኤይቲኦፕ) የሚለው ስም የሱዳኖችና የኢትዮጵያውያን መጠሪያ ነበር።

የመጽሐፍ ቅዱሱን “ኢትዮጵያ” (ያላንዳች ማስረጃ ለኢትዮጵያ ብቻ ወይም ለሱዳን ብቻ መስጠት ስሕተት ነው። በዚያው አስተሳሰብ፥ ለዕብራይስጥ ደራሲዎች “ኩሽ” የሚለው ስም የሱዳኖችና የኢትዮጵያውያን መጠሪያ ነበር። ኩሽን ያላንዳች ማስረጃ ለኢትዮጵያ ብቻ ወይም ለሱዳን ብቻ መስጠት ወይም ለአንዱ መንሣት ስሕተት ነው። “ሱዳን” ማለት “ጥቁር፥ ኩሽ፥ ኢትዮጵያ” ማለት ነው። በትርጕሙ ከሄድን፥ እኛም “ሱዳን፥ “ጥቁር፥ ኩሽ” ነን። ኢትዮጵያነታችን በስም ነው። ግን አንድ ነገር ልብ ማለት አለብን፤ አገሩን “ኢትዮጵያ” የሚል ሕዝብ እኛ ብቻ ነን። ግሪኮች ኖባውያንን “ኢትዮጵያ” ቢሏቸውም፥ ኖባውያን ራሳቸውን እንደኛ “ኢትዮጵያ” አይሉም። ስለዚህ፥ በመሠረቱ “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም የሚያመለክተው እኛን ብቻ ሳይሆን አይቀርም ብሎ መከራከር ይቻላል። የችግሩ ምንጭ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ጥቁሩን ሁሉ በአንድ ስም መጥራታቸው ነው። ስሕተቱ በብዙ ሕዝብ ዘንድ የተለመደ ነው። ለምሳሌ፥ Franks የሚለው መጠሪያ የሚያመለክተው አንድን ነገድ ነው። እኛ ግን ነጮችን ሁሉ “ፍረንጅ” (Franks) እንላቸዋልውን።

“የጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በሪቨረንድ በንቲ  ቴሶ  ኡጁሉ ተጽዕኖ የኢትዮጵያን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰርዛ በኩሽ ለውጣዋለች” የሚለው ወሬ ስሕተት ነው። ስሕተቱ እንዲፈጠር ያደረገው  መርጋ ዮናስ ሪቨረንድ በንቲ  ቴሶ  ኡጁሉን አነጋግሮ ያወጣው ጽሑፍ ነው። (የመርጋን ጾታ ስለማላውቅ አንተ ያልኩት ስሕተት ሊሆን ይችላል)  መርጋ ጽሑፉን ሲጀምር “An Oromo pastor has taken up the mantle by translating or changing biblical words deemed erroneous” (አንድ የኦሮሞ ፓስተር [በንቲ  ቴሶ  ኡጁሉ] የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን በመተርጐም ወይም ስሕተት የመሰሉትን በመለወጥ  [የማርቲን ሉተርን] አጽፍ አነሣ) ይለዋል። ነገሥት ለተከታያቸው አልጋ እንደሚያወርሱ ነቢያት ለተከታያቸው አጽፍ ያወርሳሉ–ኤልያስ አጽፉን ለኤልሳ እንዳወረሰው። መርጋ ሪቨረንድ በንቲን እንዲህ ሲሸነግለው ሪቨረንዱም አላስተባበለም። በመቀጠል፥ እንዲህ ይላል፥ “Among the most notable changes or corrections in the new bible is the term Ethiopia, which was changed to Cush. Rev. Benti Ujulu Tesso is one of the scholars behind some of the latest changes.” (እመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዋናዎቹ ለውጦች ወይም እርማቶች መካከል የሆነው፥ [አሁን] ወደ ኩሽ የተለወጠው ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ነው። ሪቨረንድ በንቲ ቴሶ ኡጁሉ  ከለውጡ በስተጀርባ  ካሉት ምሁራን አንዱ ነው።) በለውጡ ብንስማማም ባንስማማም፥ “አንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ግሪክኛና ዕብራይስጥ የሚያብጠለጥሉ የጀርመን ሊቃውንትን አማከረ” ሲባል ማንም ኢትዮጵያዊ ሊኮራ ይገባዋል። ግን የጀርመን ሊቃውንት ብሉዩን ከዕብራይስጥ፥ ሐዲሱን ከጽርዕ (ከግሪክ) ወደ ጀርመን ቋንቋ ሲተረጕሙ እንደ በንቲ ያለ አንድ ሰሞነኛ ካህን አማከራቸው ማለት እውነትነቱ ያጠራጥራል። ምክንያቱም፥  ከመርጋ ጽሑፍ እንዳገኘነው፥ በንቲ የአንድ የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን በክህነት እያገለገለ ገና የዶክትሬቱን ድርሰት ይጽፍ የነበረ ሰው ነው። ለመመረቂያ የሚጽፈውም በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ሳይሆን፥ ግሪክኛና ዕብራይስጥ ማወቅ በማያስፈልገው “ሰማይ አምላክ ነው” በሚለው በኦሮሞ ቅድመ ክርስትና ሃይማኖት ላይ ነበር። (“Oromo Indigenous Religion and Oromo Christianity: Contradiction and Compatible.”)

ጀርመኖች ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ ጀርመንኛ እስኪተረጕምላቸው ድረስ የሚጠቀሙት በላቲኑ ቅጂ ነበር። ሉተር የተረጐመውም ሐዲሱን ከግሪክኛ ብሉዩን ከዕብራይስጥ ነበር። በንቲ ስለጀርመንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙም ስለማያውቅ ይመስለኛል፥ ማርቲን ሉተር የተረጐመው ከላቲን ነው ይላል። እርግጥ፥ የጀርመን ቤተ ክርስቲያን አሁን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሷን እንደገና ለ2017 ዓ. እ. እንዲደርስ አድርጋ ተርጕማለች። የትርጐማው ግብረ ኀይል ሊቀመንበር፥ ፕሮፌሰር ዶክተር ክሪስቶፍ ኬለር (Professor Dr. Christoph Kähler, Bishop Emeritus) በጽሑፍ እንደገለጠው፥ ጀርመኖቹ መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ትርጐማ ሲከልሱ፥ ሪቨረንድ በንቲ እንኳን የማርቲን ሉተርን አጽፍ ተጐናጽፎ በትርጐማ ሊሳተፍ ቀርቶ፥ አጠገባቸውም እንኳን አልነበረም። እንዳዲስ መተጐሙን እንኳ ያወቀው ተተርጕሞ ካለቀ በኋላ ነው።

ግን “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም እጀርመንኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመግባቱ አስደስቶታል። ታሪኩ እንዲህ ነው፤ ፕሮፌሰር ዶክተር ኬለር “እመዝገባችን ውስጥ ለሪቨረንድ በንቲ የተጻፈ አንድ ደብዳቤ አገኘሁ” ይላል። አዲሱ ትርጕም ውስጥ አንዳንድ ቦታ “ኢትዮጵያ” የሚል ስም አሁንም ስላየ፥ “ለምን ሁሉም ኩሽ አይባልም?” ብሎ (በስልክ) ጠይቆ ይሆናል። መልሱ እንጂ፥ ጥያቄው በጽሑፍ አልተገኘም። ያም ሆኖ፥ ለሪቨረንዱ የተሰጠው መልስና ሪቨረንዱ ተሰጠኝ የሚለው መልስ  የተለያዩ ናቸው። ሪቨረንዱ የሚለው ተርጓሚዎቹ መሳሳታቸውን ነግረውት የቀሩትንም “ኢትዮጵያ” የሚሉትን እናርማቸዋለን ብለው ነገሩኝ ነው። ፕሮፌሰሩ የሚለው ደግሞ፥ “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም አንዳንድ ቦታ እንዳለ የቆየው ምንጩ ግሪክኛ ስለሆነ ነው። ለምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የተገኘው የግሪክኛ ትርጕሙ ነው። ግሪኩ ያቈየውን “ኢትዮጵያን” ትተው፥ ዕብራይስጡ የሚለው ኩሽ ሳይሆን አይቀርም ብለው ያለማስረጃ “ኩሽ” አላሉትም። ሪቨረንድ በንቲ ጀርመንኛው ባይገባው ይሆናል እንጂ፥ አለዚያማ እንዴት ለመርጋ  ተቃራኒውን ይነግረዋል? ኢትዮጵያ የሚለውን ስም አንዳንድ ቦታ ያልለወጡት ለምን እንደሆነ አለማወቁ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ያለው ዕውቀት ምጥን መሆኑን ያሳያል።

ሁለተኛውና ዋናው ስሕት፥ “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም ፓስቶር በንቲ  በ “ኩሽ” አስለወጣቸው ማለቱ ነው። የጀርመን መጽሐፍ ቅዱስ  ዱሮውንም “ኢትዮጵያ” የሚል ስም አልነበረበትም። ያልነበረ አይለወጥም። የነበረውና አሁን ወደ “ኩሽ” የተቀየረው ማርቲን ሉተር ሲተረጕም Mohrenland/Mohren  ያለውን ነው። ታዲያ ሌሎቻችንስ ብንሆን የቀድሞው Mohrenland/Mohren  ሳያስቆጣን ወደ Cush/Cushite ቢለወጥ ምኑ ነው የሚስቆጣን? የማርቲን ሉተር Mohrenland/Mohren እንዳለ ቢቆይ እንመርጥ ነበር ማለት ነው? እንዲያውስ እኛ እጀርመን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እስከ ዛሬ ሳንገባ ዛሬ ምን አስገባን? ጀርመኖቹ Cush/Cushite ን የመረጡት የማርቲን ሉተር Mohrenland/Mohren ስድብ ስለመሰላቸው ማሳመራቸውነው።  የጥንቱን ስም ቢያቆዩት ይሻላል ነበር?  Cush/ Cushite የሚለው ስም ካስቈጣን፥መቈጣት ያለብን፥ Cush/ Cushite ያለውን የዕብራይስጡን ብሉይ ኪዳን ነው።

“ፈረንጆች ስማችንን ለወጡብን፤ የአንድን አገር ስም መለወጥ የሚችል የሀገሬው ሕዝብ እንጂ፥ ፈረንጅ አይደለም” የሚል ቁጣ ይሰማል። የሀገር ስም መለወጥና ለአንድ ስም አዲስ ትርጕም ማምጣት የተለያየ ነገር ነው። የሀገራችንን ስም ማንም አለወጠውም። እኛ እስከ ለወጥነው ድረስ “ኢትዮጵያ” ስትባል ትኖራለች። ሁለቱ አንድ ነገር ቢሆኑ ኖሮ THE GIDEONS የሚባሉት ፕሮቴስታንቶች በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሳቸው ውስጥ ኢትዮጵያ የሚለውን ወደ Cush ከለወጡበት ጊዜ ጀምሮ ኩሽ እንባል ነበር። ግን አልተባልንም። አንድም ፈረንጅ “ይድረስ ለኩሽ መንግሥት  ፕሬዚዴን . . .” ብሎ ሲጽፍም አላየንም። ቢልም ፖስተኛው አያደርስለትም።

ሆኖም፥ ሁለት ጥያቄዎች ማንሣት እንችላለን፤ አንደኛ፥ ዕብራይስጡ ብሉይ ኪዳን “የካም ልጆች ኩሽ፥ ሚስራይም፥ ፉጥ፥ ክናዐን ናቸው” ይላል። ይኸንን ዐረፍተ ነገር አዲሱን የጀርመን ትርጕም አዘጋጆች ምን ብለው ተረጐሙት? ስሞቹን እንዳለ ገልብጠዋቸዋል ወይስ “ምስራይም” የሚለውን ስም Ägypten (Egypt ግብፅ) ብለውታል? “ምስራይም” የሚለውን ስም እንዳለ መገልበጣቸውን ትተው እንደ ግሪኩ Ägypten ብለውት ከሆነ (ባላየውም እንዳሉት አልጠራጠርም)፥ ለምንድን ነው “ኩሽ” የሚለውን ስም እንደግሪኩ Äthiopien (Ethiopia ኢትዮጵያ) ያላሉት?

ሁለተኛ፥ ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ ጀርመንኛ ከመተርጐሙ በፊት የምዕራቡ ዓለም (ጀርመኖችን ጨምሮ) የሚጠቀመው ቩልጌት (Vulgate) በመባል በሚታወቀው  የላቲንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነበረ። ይህ የላቲን ቅጂ “ኹሽ” የሚለውን ስም ያላንዳች ማወላወል Aithiopiae እያለ ነው የተረጐመው። ኩሽ የሚለውን ስም ምዕራቡም ምሥራቁም የሚተረጕመው ኢትዮጵያ እያለ ነው። ዛሬ ምን ምክንያት ተፈጥሮ ነው ዕብራውያን ያልሆኑ ሕዝቦች (እነ አሜሪካን፥ እንግሊዝ፥ እነ ጀርመን) እኩሽ ላይ ሲደርሱ፥ ቋንቋቸውና ባህላቸው ያቆየላቸውን “ኢትዮጵያ”ን ትተው የሌላ ሕዝብ ቋንቋና ባህል ማቀፍ ያማራቸው?  የዛሬዎቹ ጀርመኖች የሉተርን መጥፎ ቃል ማረም ካስፈለጋቸው ለምን በ Äthiopien (Ethiopia ኢትዮጵያ) አላረሙትም?  “ኢትዮጵያ የሚለው ስም ጥቍሮችን ሁሉ እያመለከተ የናንተ ብቻ አደረጋችሁት” የሚሉን ከሆነ፥ እኛ ማንም ሰው አገሩን “ኢትዮጵያ” እንዳይል አልከለከልንም። ሌላም ነጥብ አለ፤ ዛሬ ኩሽ የሚባል አገር የለም። ኩሽና ኢትዮጵያ የሚሉት ስሞች የአንድ ስም ሁለት ገጾች ስለሆኑ አገራችንን ኩሽም ኢትዮጵያም ብንል ምን ያደርጋሉ? ማሳፈሪያው መፍትሔ ይህ ሳይሆን አይቀርም።

መርጋ ሪቨረንድ በንቲን፥ “በአዲሱ ትርጐማ ሌላ ምን ለውጥ ተደርጓል?” ብሎ  ቢጠይቀው፥ “ሌላውን አሁን ልነግርህ አልችልም” አለው። እውነቱን ነው፤ የማያውቀውን፥ ያልዋለበትን እንዴት ሊነግረው ይችላል?

ሦስተኛ፥ “ኢትዮጵያ የሚለው ስም ስድብ ነው” ይላል ፓስቶሩ፥ ጋላ የሚለው ስም ስድብ ነው እንደተባለው ማለት ነው። “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም ስድብ  ከሆነ፥ “ኩሽ” የሚለው ስም እንዴት ስድብ አይሆንም? እንደእውነቱ ከሆነ፥ “ኢትዮጵያ”ም ሆነ “ኩሽ” የኛ ስም ከሆነ ቅዱስ ስም ነው። አንዳንድ ሰዎች የሚሉትማ ሌላ ነው፤ “ኩሽ የኖኅ እርግማን ስላረፈበት እርጉም ነው” ይላሉ። ስድብ ማለት ይህ ነው። ኖኅ ሦስት ልጆች ነበሩት፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት። ጥፋተኛው ካም አራት ልጆች ወለደ፤ ኩሽ (ኩሳ)፣ ምስራይም (ግብፅ)፥ ፉጥ፥ ከነዓን። ቢጐዳም ባይጐዳም፥ የተረገመው ከነዓን ነው። ሌሎቹ (ኩሽ፥ ምስራይም፥ ፉጥ) አልተረገሙም።

አራተኛ፥ ሪቨረንድ በንቲ፥ “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም ወደ “ኩሽ” ቢለወጥ ፥ “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም ያገለላቸውን “ኩሽ” የሚባሉትን ኦሮሞችን ሲዳሞችን፥ . . . ያቅፋል ይላል። አለማወቅ ያመጣብን ስሕተት ነው። አገር ቤት ሄደን አንዱን የኦሮሞ ወይም የሲዳማ ገበሬ፥ “ደስ ይበልህ፤ ኢትዮጵያዊ መባልህ ቀርቶ ኩሳዊ (ኩሻዊ) ተብለሃል” ብንለው፥ እብዶች ያደርገናል እንጂ፥ ብሥራት አያደርገውም። ዕውቀቱ ካለው፥ “ኩሽ” መባልን የሚወድ ሕዝብ ካለ “ኢትዮጵያ” ቢባል አይጠላም።

ችግሩ የተፈጠው የቋንቋ ተመራማሪዎችን አስተሳሰብ ባለመረዳት ነው። ተመራማሪዎቹ፥ “ሴማዊ፥ ኩሻዊ” የሚሏቸው ቋንቋዎች አሉ። ይህ አከፋፈል የተመሠረተው በቋንቁዎቹ ላይ እንጂ፥ በተናጋሪዎቹ ዘር ላይ አይደለም። ሴማዊ ቋንቋ የሚናገሩና ኩሻዊ ቋንቋ የሚናገሩ ማለት ነው። እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሁሉ እንግሊዛዊ አይደለም። ሴማዊ ቋንቋ የሚናገሩና ኩሻዊ ቋንቋ የሚናገሩ ዘራቸው አንድ ነው። በቋንቋ “ሴማዊ” እና፥ “ኩሻዊ”፥ በዘር “ኢትዮጵያ” እና “ኩሽ” የሚያመለክቱት ያንኑ አንዱን ሕዝብ ነው። “ኩሽ የሚለው ስም በይበልጥ ያቀራርበናል” ማለት ኢትዮጵያን አንቀበልም ለሚሉ ወገኖች የተፈጠረ ፖለቲካዊ አስተዋፅኦ ነው–የሃይማኖት አስተማሪን ሳይቀር የተተናኰለ በሽታ።

አምስተኛ፥ የሀገሪቱ ስም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ Abyssinia ነበር፤ ወደ ኢትዮጵያ የተለወጠው አሁን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ነው ይላል ፓስቶሩ። አለማወቅ ካልቀረ እንደዚህ ነው። በየትኛው ዘመን ነው ኢትዮጵያ ራሷን በእንግሊዝኛ Abyssinia ትል የነበረው? የትኛው ንጉሥ ነው “እኔ እገሌ ንጉሠ ነገሥት ዘብሔረ Abyssinia” ያለ? ከ1307 እስከ 1336 ዓ.ም. በነገሠው በአፄ ዓምደ ጽዮን እንኳ ብንጀምር፥ ራሱን የሚጠራው “ንጉሠ ጽዮን፥ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ” እያለ ነበር።  የውጭ አገር ጸሐፊዎች አገራችንን Abyssinia ይሏት ነበረ። በእኛ በኩል ግን አገራችን መንግሥት ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ሰነድ የሚያመለክተው ኢትዮጵያ መባሏን ነው። ሰነዶቹ በመጻሕት ሜዳ ሁሉ ይገኛሉ። አነጋግሯቸው አታኵርፏቸው።

ስድስተኛ፥ ሐበሻ ማለት ድብልቅ ማለት ነው ይላል። ከየትኛው መዝገበ ቃላት ነው እንዲህ  ያለ ትርጕም የሚገኘው?  ወይስ ዐዋቂ መስሎ የተራ ሰው አነጋገር ከሰው ፊት ማቅረቡ ነው? ሐበሻ የነገድ ስም ነበረ። የነገድ ስም ስድብ ሊሆን አይችልም። ሁለተኛም፥ አንድ ሀገር በአንድ ነገድ ስም መጠራት በኢትዮጵያ አልተጀመረም። ምዕራባውያን Abyssinia ቢሉን መላ ኢትዮጵያን እንጂ፥ ጥቂቶቹ የሚኖሩባትን ክፍል አይደለም። ለምዕራባውያን ጸሐፊዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባል የሆነ ሁሉ (ኦሮሞ ይሁን አምኀራ፥ ጉራጌ ይሁን ከፍቾ) Abyssinian ነው።

ለማጠቃለል፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ከመተዋወቃችን በፊት ጀምሮ ሀገራችንን የምንጠራው “ኢትዮጵያ” ብለን ነው። በሌላ ስም ትጠራ ማለትም፥ ኢትዮጵያን በኩሽ መለወጥም ተንኮል ነው። ስማችንንም፥ መጽሐፍ ቅዱሳችንንም አናስነካም። ሆኖም፥  የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጐማ አይቆምም፤ ይቀጥላል። ወደ ፊትም ብዙ ዛሬ ያልታወቁ የግሪክና የዕብራይስጥ ቃላት በምርምር ብዛት ይታወቁና አዲስ ትርጐማን ያስገድዳሉ። ተቀባዩ ቋንቋም ያረጃል፤ በዛሬው ሰዎች ቋንቋ የተተረጐመ መጽሐፍ ቅዱስ ለነገ ሰዎች እንግዳ ይሆንባቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የሚቋቋመው እነዚህ ምክንያቶች አዲስ ትርጐማ ሲያስገድዱ ተዘጋጅቶ ለመገኘት ነ

5 COMMENTS

 1. መልካም ብለዋል ፕሮፈስር። በአሁኑ ዘመን ያገራችን አብዛኛው ወጣት ማለት ይቻላል ከማንበብ ይልቅ ወይ ዩቱብ መመልከት ወይ ደግሞ አንድ አነበብኩ የሚል ሰው ሲለፈልፍ ያዳምጥና እንደራሱ አድርጎ ይተነትናል። አንዳንዱማ ያልተማረውን ተምረያለሁ እያለ በድፍረት በቲቪ ሲወሸክት አይተን የለ እንዴ? ወያኔ ምስጋና ይግባውና ይህንን ድንቁርና ለ27 አመታት በሃገራችን እንዲንሰራፋ አድርጎታል። አንድ በመከላከያ ሚ/ር ክሊኒክ ውስጥ ይሰራ የነበረ ነርስ ወዳጄ የነገረኝን አስታውሳለሁ። ልጁ ጎበዝ ሰራተኛ ስለነበረ ሁሉም በሽተኞች ይወዱት ነበር። የክፍሉ አለቃ ከበሽተኞች ጋር ተመካክሮ አንድ ነገር ሊያደርጉለት አሰቡ። እንደተለመደው ጥዋት ላይ ወደ ስራ ገበታው ሲመጣ የእንኳን ደስ ያለህ ጋጋታ ሲበዛበት ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቃቸው አለቃው “ታታሪ ሰራተኛ በመሆንህ ከዛሬ ጀምረህ ዶክተር ሆነሃል” ብሎት አረፈው። ልጁም ከት ብሎ ስቆ ሃኪምነት በትምህርት እንጂ በሹመት እንደማይሆን ቢነግራቸውም በግትርነት “እኛ የፈለግነውን ማድረግ እንችላለን!” ያለውን አስታውሳለሁ። በርግጥም የፈለጉትን ሲያደርጉ 27 አመታት እንዳሳለፉ አየናቸው። ምድረ ፍልጥ ሁሉ በተገዛ ዶክትሬት ማእረግ ሲንበሸበሽ፤ ልጁን ውጭ ሃገር ልኮ በውድ ትምህርት ቤት ሲያስተምር፤ እርፍ በያዘ እጁ ጄት አበራለሁ ብሎ ሲከሰከስ፤ አንዱን ሲያስር፤ አንዱን ስያኮላሽ፡ ያንዱን ጥፍር ሲነቅል ጉድ አየን። የተማሩ ምሁራንን ከስራ ገበታቸው እያባረረ ችሎታ በሌላቸው መምህራን ሞልተው በየአመቱ ወይ ብስል ያልሆነ ወይ ጥሬ ሆኖ ለመብሰል የማይሞክር ተማሪን እያስመረቁ ተወያይቶ እንኳን አንድ ነገር ላይ መድረስ የማይቻልበት ትውልድ ላይ ደረስን። አብዛኛው የኦሮሞ ምሁራን ተብየዎች ችግር የሚመነጨው ከዚህ ምክኒያት ነው። በሚኒልክ ጊዜ የነበረ ይመስል፤ ሚኒሊክ እንዲህ አድርጎኛል እስከማለት የሚደፍር፡ አማርኛ ቁዋንቅዋን እንደጠላት የሚመለከት፤የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንደናዚ ባንድራ የሚመለከት፤ የኢትዮጵያን ስም መስማት የምይፈልግ፤ ከጎሳው ውጭ ሌላው ሰው ሰው የማይመስለው፤ ጎጠኛ አክራሪ ሚሊታንቶች እየተፈለፈሉ እያየን ነው።ይህን ነው እንግዲህ የወያኔ የ27 አመታት ሌጋሲ።

 2. Prof, ጌታቸው ሀይሌ
  ስለዚህ ሚከተሉትን ቁምነገሮች ብቻ ማየት በቂ ነው፡፡ ሌላው ዝባዝንኬ ስለሆነ አይመጥንምና ትቸዋለሁ፡፡
  1. ኢትዮጵ የሚል ቃል በትረጉም ስህተት ምክንያት የገባ እንጂ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያልነበረ መሆኑን፡
  “እኛ ደግም፥ ከላይ እንደተናገርኩት፥ መጽሐፍ ቅዱሳችንን የተረጐምነው ከግሪኩ ስለሆነ፥ “ኤይቲኦፕ” የሚለውን “ኢትዮጵያ” አልነው። ” ብለዋል፡፡
  2. በየትኛው ዘመን ነው ኢትዮጵያ ራሷን በእንግሊዝኛ Abyssinia ትል የነበረው? የትኛው ንጉሥ ነው “እኔ እገሌ ንጉሠ ነገሥት ዘብሔረ Abyssinia” ያለ? ከ1923 ጀምሮ ስለመሆኑ መልስ አዚህ ይገኛል፡፡ (https://en.wikipedia.org/wiki/Member_states_of_the_League_of_Nations#1923)
  3. “ሐበሻ ማለት … ሐበሻ የነገድ ስም ነበረ። የነገድ ስም ስድብ ሊሆን አይችልም። …አንድ ሀገር በአንድ ነገድ ስም መጠራት በኢትዮጵያ አልተጀመረም።”

  ለዚህ ነው በእናንተ የሀበሻ ነገድ ስም ላለመጠራት ነው ሌሎች ሕዝቦች (ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ ወዘተ) ሀበሻ መባል የማይፈልጉት፡፡

 3. you witnensss that sudan and Ethiopia are kush thus Ethiopia is belongs to kush already emnationed in your baibile not experts chnaged the name from ethiopia to kush as you said Bent or others fasle infromation ! you are already in cotractor in your wrtiing showed ethiopia belongs to Kush not Semtic!!! find foolish guys!!!!!!!

 4. ፕሮፌሰር ጌታቸው ታሪክና ቋንቋዎች ሙያቸው ስለሆነ ሲያስተምሩ ያምርባቸዋል። ቄስ በንቲ የጻፈውን እዚህ ይመልከቱ https://bit.ly/2XKcM99
  የፕሮፌሰር ጌታቸው ችግር ከሙያቸው አልፈው ወይም ሙያቸውን ተገን አድርገው የተንጋደደ ፖለቲካ ሲያራምዱ ነው። በዚህም ከቄስ በንቲ አይሻሉም።
  ለምሳሌ፣ በንቲን “ቄስ” ላለማለት “ሪቨረንድ” (10 ጊዜ) እና “ፓስቶር” (አንድ ጊዜ) ብለዋቸዋል። “ሪቨረንድ” እና “ፓስቶር” በአማርኛ ሲተረጎም “ቄስ” ነው። ይህን ያጡታል ማለት ያዳግታል። “ሪቨረንድ” እና “ፓስቶር” የተመረጠው፣ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ባእድ ያደርጋልና ነው፤ በንቲ እምነታቸው ባእድ ነው ነው በፕሮፌሰሩ እይታ። “የጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ሪቨረንድ በንቲ ቴሶ” ብለዋቸዋል። The Missionary Factor in Ethiopia (1996 እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  ቄስ በንቲ (እና የርሳቸውን ዓይነት ፖለቲካ አራማጆች) “ኢትዮጵያ” ላለማለት አንዴ “አቢሲኒያ” (እንደ እነ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቅኝ ገዥ ለማሰኘት) አንዴ “ኩሽ” እያሉ ይዘባርቃሉ። ችግሩ ታሪክ መሠረት ያደረገ እውነት ሲገኝ አሳባቸውን ለመለወጥ አይፈቅዱምና ነው፤ እቅዳቸውን ያጨልምባቸዋላ! የፕሮፌሰር ጌታቸው ጽሑፍ ስለ አገራችን ስያሜ በቂ መልስ ነው።
  ፕሮፌሰሩ ጽሑፋቸውን ሲጀምሩ፣ “አንድ ሰሞን “የጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በሪቨረንድ በንቲ ቴሶ ኡጁሉ ተጽዕኖ የኢትዮጵያን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰርዛ በኩሽ ለውጣዋለች” የሚል ወሬ ተናፍሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን አበሳጭቶ ነበር። ብዙ ተቃውሞም ተጽፏል። ይኼ ተጨማሪ ማብራሪያ ነው።” ብለዋል። የቋንቋ ሊቅ እንደ መሆናቸው የተጠቀሙትን ሐረጎች ልብ በሉ፣ “ወሬ ተናፍሶ” “የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን አበሳጭቶ” “ብዙ ተቃውሞ”። መመዘኛቸው “ኦርቶዶክስ” መበሳጨቱ አለመበሳጨቱ ነው። በንቲ ፈቃድ ሳይሰጠው ያፈቀደውን ማመን አይችልም የሚሉ ይመስላል። ሌላኛው፣ ቄስ በንቲ ጽሑቸውን ከለጠፉ ሁለት ዓመት ሊሆናቸው ነው። ፕሮፌሰሩ እነ እስክንድር እና ኢሳት የ”ጽንፈኛ ኦሮሞ” (አሁንማ ሲያገንኑ የከረሙትን ዐብይንና ለማን ሳይቀር) እሳት ሲለኩሱ ቤንዚን ማርከፍከፋቸው ነው። ቅድም ከሙያቸው ወጣ ሲሉ አያምርባቸውም ያልኩት ይህንን ነው። ቄስ በንቲም ያለ ሙያቸው ገብተው ዘባርቀዋል እና ሁለቱም ይታረሙ!

  ሳተናው አዘጋጆች አስተያየቴን ያትሙልኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

 5. እጅግ ብዙ ታሪክ ሲያዛቡ ኖረው ፕሮፈሰርነት ወስደው ጊዜያቸው ሲቃረብና ሁኔታዎች አፍጥጠው ሲመጡ በጥቂቱ ማስተካከል መሻት አንድም ጅልነት አልያም ኋላቀርነት ነው። ስለዚህ የአማርኛ ሰዎች (ቅይጥ ዜጎች) ስለ እማማቸው ሲሉ የቢያ አባ ኬኛን ታርክ እና የሕዝባችንን (በተለይ የኦሮሞን ሕዝብ) ክብር ሲያጎድፉና ኖረው አሁን ላይ መገለባበጥ ትርፉ ፅብት ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.