አብይ አገራችነን ለአሸባሪ ወሮበሎች እያመቻቸ ነው? (ስርፀ ደስታ)

ዛሬ በሁኔታዎች አዝኛለሁ፡፡ ነገሮች እየተናገርን ሲበላሹ በጣም ያሳዝናል!

  • አብይ እየቆመርክ ነው? የመንግስት ባሕሪ ያለው አስተዳደር ከማጽናት ይልቅ የወሮበሎች ሽፋን ሆነሀል፡፡ የተዘፈነልህ ያህል ብትሰራ በተሻለህ ነበር፡፡
  • በኦሮሞነት ባሌና ከወለጋ አዲስ አበባ ላይ ለሚሆነው እኔ ነኝ ወሳኙ እያለና ይሄን አስተሳሰብ በየቀኑ ሕዝብ ውስጥ እየዞሩ በመንግስት ገንዘብ የሚያሰራጩትን ከለላ ሆነህ የኢትዮጵያውያን መሪ መሆን አትችልም፡፡ ደግፈንሀል፣ ተዘፍኖልሀል፡፡
  • የኦሮሞን ገበሬ በዋናነት ያፈናቀለው ኦሮሞ የሚያስተዳድራቸው ከተሞች እነ ቡራዩ፣ ገላን፣ ዱከምና የመሳሰሉት እንደሆነ እየታወቀ የገበሬ መፈናቀል ከአዲስ አበባ ጋር ብቻ በማያያዝ የኦሮሞን የዘረኛና ጥላቻ ፖለቲካ በማሰራጨት በጉልበት የፈለግንውን ማረግ እንችላን እየተባለ እንደሆነ ሁሉም ልብ ሊል ይገባል፡፡
  • የተፈናቀሉ ሚስኪን ገበሬዎች የሚጠቀማቸው በእርግትም አስተማማኝ ካሳ እንጂ የወሮበላ ድንፋታ የእነሱን ጥቀም ለመቀማት እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡
  • ኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል ከአለባት ሸዋን ራሱን የቻለ መንግስት ማረግ ግድ ነው፡፡ ወደድክም ጠላህም ፊንፊኔ የኦሮሞ ነች የሚለው ወሮበላ አስተሳሰብን እነ አብይ ማስቆም ከአልቻሉ አዲስ አበባም ሆነች ራሱ ሸዋ እንደ አገር የሚመለከታቸው ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ሰሞኑን አዲስ አበባ የሚለው ሥም እነ አብይ ሸገር በሚል መተካታቸው ለእነሱ ሴራ ቢሆንም ለእኛ ግን በእርግጥም ሸገር የአዲስ አበባ ሌላኛው ሥም ነው፡፡ ፊንፊኔ የሚሉት የኦሮሞ ዘረኝነትን የሚያስፋፉት ወለጋዎች ናቸው፡፡ ሸዋ መንግስት ሲሆን ከተማችንን ሸገር- አዲስ አባ፣ አዱገነት እንደወደድን እንጠራለን፡፡ እኔ አብይ በሚሰሩት ሸፍጥ ግን አደለም፡፡ በረራ ምናምን የምትሉ አያገባችሁም፡፡
  • የኦሮሞ አክራሪ የፖቲካ አስተሳሰብ ብዙ ሕዝቦችንና ቦታዎችን ታሪካቻውንና ማንነታቸውን ለማጥፋት ነው፡፡ ለምሳሌ ዝዋይን ባቱ ያለው ከዜይ ሕዝብ ቀምቶ ነው፡፡ ብዙ ታሪካዊ ቦታዎችንም እንዲሁ ሞክረዋል፡፡

ከመጀመሪያው ጀምሮ ብዙ ያልን ሰዎች አለን፡፡ ግን ማን ይሰማል? በግልጽ እየታየም ችግሩን ከመፍታት ይልቅ በማስተባበያ ለማቆየት ለአገር አፍራሽና አሸባሪ ቡድኖች ሽፋን በመስጠት ዛሬም የአብይ አስተዳደር ለሕዝብ አሳቢነቱን ይነግረናል፡፡ እስካሁን ድረስ ብዙ ደግፈናል፡፡ አብይ እያጭበረበረ ነው ብለው የሚቃወሙ ቢኖሩም ብዙዎች ግን ብዙ ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ ብዙም ዘፈኑለት ብዙም ወደዱት፡፡ እሱ ብዙ ሰራሁ ባይ ነው፡፡ በእርግጥም ትልልቅ ክንዋኔዎች ተከናውነዋል፡፡ ከእነዚህ ክንዋኔዎች ዋናው የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ ሲሆን ለዚህ ግን ሌሎች ትልቅ አስተዋጾ እንዳደረጉ አይነገርም፡፡ አብይ ራሱን በከፍተኛ ደረጃ እያስተዋወቀ በየቦታው መዞር ትልቁ ስኬቱ ነው፡፡ ስኬት ከተባለ፡፡ እንደመንግስት ግን እየሠራ እንዳልሆነ በብዙ ነገሮች እያየን ነው፡፡ ሕግና ሥርዓትን እንደመንግስት ከማቆም ይልቅ የመንግስትን ስልጣንና መንበር የራሱ ማስተዋወቂያ እያደረገው እንደሆነ ነው እየተሰማኝ ያለው፡፡ በቀደም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የተባሉ ሰው የሉሲን ለሰላም ጉዞን የተቹበትን ንባብ ሳነብ እውነትም አብይ ከዛ ያለፈ የመንግስትነት ባሕሪ እንደሌለው ተሰማኝ፡፡

ሰሞኑን እየሆነ ያለው ነገሮችን ግልጽ እያረገ የመጣ ይመስላል፡፡ የአዲስ አበባ ኮንደሚኒየምን ተከትሎ እየታየ ያለው ችግሩ የኮንደሚኒየሙ ጉዳይ ሳይሆን ከበፊት ጀምረን ስንንናገር የነበረው ጉዳይ ነው፡፡ ሕግ ከታሰበ ኮንደሚኒየሙ ሕገ ወጥ ግንባታ መሆኑ ነው፡፡ ሰሞኑን በለገጣፎና ለገዳዲ ቤታቸውን ሕገ-ወጥ በማለት በማፍረስ የጀመረው የኦሮሚያ አስተዳደር አሁንም እዚህ ጋር ሌላ ቁማር ጀምሯል፡፡ በእርግጥም ይሄ ኮንደሚኒየም ከአለኦሮሚያ መንግስት ፍቃድ በክልሉ ውስጥ ሲሰራ ያለፍቃዴ ነው ቢል አይገርመንም፡፡ ከዛም በኋላ ስለዚህ ነገር አልተወራም፡፡ ዛሬ ለሰዎች ቤቶች መታደል ሲጀምሩ ግን ኦሮሚያ ውስጥ ተሰርቷልና የአዲስ እጣ የደረሳቸው ቤቱን አይወስዱም ነው አለ፡፡

ይሄ ይሁን እኔ ግን ከበፊቱም ስናገር የነበረው ዛሬም ኮንደሚኒየምን ምክነያት በሚል ኦሮሚያን በሙሉ ያጥለቀለቀው ጩኸት ነው ትኩረቴን የሳበው፡፡ ሕግና መንግስት በአለበት ይሄ ሊሆን ባልቻለ፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ የፈጠረው መርዛማ አስተሳሰብ በዋናነት ብዙውን የኦሮሞ በተለይም ወጣት ትውልድ ከሎጂካል አስተሳሰብ ያመከነና ለወደፊትም በራሱ ላይ ችግር እያመጣ ነው፡፡ ስለ አዲስ አበባ ወይም አዲስ አበባ ዙሪያ ስላለ ጉዳይ በኦሮሞ ሥም ባሌና ወለጋ ዘረኝነትና ጥላቻ ያደለበው ወሮበላነት ከአልሆነ በምን መስፈርትና ሒሳብ እንደሚያገባው አላውቅም፡፡ የኦሮሞ ገበሬዎች ተፈናቀሉ የኦሮሞ መሬት ተወሰደ ወዘተ … የለመድናቸው ቁማሮች ናቸው፡፡ የኦሮሞን ገበሬ ያፈነቀለው ይሄ በየቦታው ሴራ የሚዶልተውን ጨምሮ በዋናነት ኦሮሚያን አስተዳድራለሁ የሚለው የኦሮሞ መንግስት ነው፡፡ የኦሮሞ መንግስት የምለው ወድጄን አደለም፡፡ በግልጽ ስለሆነ ነው፡፡

ከዚህ በፊትም አንስቼው ነበር አሁንም እደግመዋለሁ፡፡ ብዙ ገበሬ የተፈናቀለው የኦሮሞ መንግስት ከሚያስተዳድራቸው ከቡራዩ፣ ዱከም ገላንና ሰሞኑን ሌሎችን ገንዘባቸውን ወስደው መሬት ከሸጡላቸው በኋላ አሁን ዲሞግራፊ ለመቀየር በሚል ሴራ ቤታቸውን እያፈረሱባቸው ከአለው ለገጣፎ ከተባለውና መሠል አዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ በዙሪያዋ ከአሉት የእነ ለማ መንግስት ከሚያስተዳድራቸው ከተሞች አንጻር ትንሽ ገበሬዎችን ነው ያፈናቀለችው፡፡ ትንሽ ማለት ግን በንጽጽር ነው፡፡ ገላን እኮ ዛሬ ከተማ የሆነው ከጥቂት አመታት በፊት ቅልጥ ያለ የጤፍ ምድር ነበር፡፡ ለማንኛውም በእርግጥም የአዲስ አበባው ኮንደሚኒየም አልፎ በእነ ለማ አገር መሠራቱ ስህተት ነው፡፡ አሁን ከሀረር አፈናቀሎ ላመጣቸው ተፈናቃዮች ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ነገሩ እየገባን ያለው አሁን ነው፡፡

ያም ሆኖ የአርቲስቶቹ ደግሞ እዛ ሄዶ ማቡካት ሌላው ድራማ ነው ያልገባኝ፡፡ አብይ አገርን እንደመንግስት መምራት ሳይሆን ይታያሉ በሚላቸው ሰዎች እያደናገረ በመሪነቱ ቦታ ተቀምጦ እየተዝናና ነው፡፡ አዝነለሁ! ሰሞኑን የአዲስ አበባን ወንዞችና ተፋሰሳቸውን ለመዝናኛ ለመዋል በሚል የ28 ቢሊየን ብር ፕሮጄክት እያስተዋወቀን ነው፡፡ ይሄን ሐሳብ ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ እኔ አቅጄው የነበረና ለከተማው ይሄው ጉዳይ ለሚመለከተው አቅርቤ ነበር፡፡ ሥራው ሙያን እውቀት የሚጠይቅ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ ሲጀምርም በውል በተጠና ዲዛይነሮች፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሙያዎችና ኢንጂነሮችን እውቀት የሚተይቅ ነው፡፡ አጅሬው የአገር አርቲስት ሰብስቦ በፕሮጄክቱ በማሳተፍ ነው እሰራዋለሁ ብሎ እያጃጃለን ያለው፡፡ ጉዳዩ ልክ እንደ ግድቡ ነው፡፡ ሟቹ የወያኔ ቡድን መሪ ድንገት ተንስቶ የአባይን ግድብ እንገነባለን ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አስቦረቀው፡፡ የአባይንም ግድብ መገንባት ሐሳብ የእሱ አደረገው፡፡ ይሄኛውም እንደዛው ነው ያደረገው፡፡ ኢቲቪ በዶ/ር አብይ የሐሳብ አመንጪነት ሲል ሐሳቡን ያመነጩት ሊታዘቡ እንደሚችሉ ሳይሆን የአብይን ዝና ከፍ ለማድረግ ነበር፡፡ ያኛውም ከኃይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ የመሠረተ ድንጋይ ሳይቀር የቆመለትን ሐሳብ ነው የሐሳብ አመንጪ የሆነበት፡፡ ሰሞኑን እነዛው ኢንጂነር አርቲስት፣ ፖለቲከኞች፣ ሕዝብ አስተዳዳሪዎች ኮንዶሚኒያም እንዴት እንደሚሰጥ ሲነግሩን ነበር፡፡ ቁማሩ እነሱ ተልከው ነው፡፡ ይሄው ሐሳብ ነበር በሁሉም ቦታ ሲነገር የቆየው፡፡ ግን ይሄ አሁን ገበያ ሊሆን የሚገባው ጉዳይ ነበር? ታከለም ልክ ለገበሬዎች ልዩ ነገር እንዳደረገ ሲናገር ነበር፡፡ እውነቱ ለገበሬዎች ከወሬው ያለፈ የሚደረሳቸው የለም፡፡ ሁሌም እየሆነ ያው ይሄ ነው፡፡ በተለይ ኦሮሚያ በኦሮሞ ሥም ስለሚታሰብ ኦሮሚያን ከንኦሮሞቲ የሚሉት እንጂ ሚስኪን ገበሬው በኦሮሞነት ሥም ከሚሰጠው ኮታ ምንም ድርሻ የለውም፡፡ ኦሮሚያን ከንኦሮሞቲ የሚሉት ወሮበሎች ይቀሙታል፡፡ አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ ሚስኪኑን ገበሬ ዜና ይሠሩበታል ራሳቸውን ያስተዋውቁበታል፡፡ ብቻ ይሄ ነው ቁማሩ፡፡ ለሚስኪኑ ገበሬማ ማን ሰው ብሎ ቆጥሮት፡፡

ሕገወጥነትን በመሪነት እየከወኑት ሕግ እናስከብራለን ይባላል፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ችግር አለ ብለን ነበር፡፡ ኦነግን ሊዋጋ የሄደውን ሠራዊት ሽምግልና በሚል እንዳይጎዳባቸው ሲቆምሩ የነበሩት ሰው ሲገድል ባንክ ሲዘርፍ ትንፍሽ ሲሉ አልተሰሙም ነበር፡፡ ይባስ ተብሎ የዚሁ ቁማር ዋና በየቦታው እየሄደ ሕዝብን ከሕዝብ እያጋጨ ያለው ወሮበላ ግለሰብ መሆኑ ነው፡፡ በመንግስት ገንዘብ ሽማግሌ ነን በሚል እየዞሮ ሲያደራጁት የቆዩት ነው ዛሬ ዶላ ይዞ አደባባይ እየወጣ የምናየው፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ ይሄን ችግር እንዲየስቆም ለአብይ ተነግሮታል፡፡ ዛሬ ብዙ ቦታ ብዙ ሕዝብ በኦነጋውያን ምክነያት እየተሰቃየ ነው፡፡ ጌዲዮ በሺዎች ተፈናቅለዋል፡፡ እነሱ የሚጠይቅ ስለሌላቸው የአብይ መንግሰት አያስታውሳቸውም፡፡ ለነገሩ ለገጣፎም የሕዝብ ቤት አፍርሰው ዜጎችን ሜዳ ላይ የበተኑትን አልሰማሁም ብሏል፡፡ ሰምቶስ ምን አረገ?

ችግር አለ፡፡ ችሀግሩ ደግሞ ከላይ ጀምሮ ነው፡፡ አውን አገርና ሕዝብ ቢታሰብ ወሮበሎችን በአገሪቱ አሰማርቶ ሕዝብን ከሕዝብ ማጋጨትና ማሸበርን ቁማር ባልተጫወተ፡፡ ኮንደሚኒየም አሁን የሚታደለው ግን ያችው የተለመደችው የወያኔ ስልት መሆኗ ነው፡፡ ምርቻ ምናምን ሲመጣ ሲመጣ ነበር ወያኔ ሕዝቡን ጮቤ የሚያስረግጠው፡፡ እነ አብይም ከአሳዳጊዎቻቸው የተማሩትን ነው?

ሌላው የለማ የሚኒሶታን ቆንሲላ ከፋች መሆን ከአገራዊ አሰራር አንጻር ስህተት ነው ያሉ ብዙ ውርጅብኝ ሲወርድባቸው አየሁ፡፡ እውነታው ለማ እንደተባለው የአንድን አገር ኮነሲላ መክፈት ልክ አልነበረም፡፡ ምልከታቸው በኦሮሞነት እንደሆነ ግልጽ የሆነበት ክስተት ነው፡፡ አብራ የነበረችው ብርቱካን ብትከፍት የተሻለ በሆነ፡፡ አገር፣ መንግስት ማለት ፕሮቶኮሎ ግን ይገባቸዋል እነዚህ ሰዎች?

እንዲህ በአለ ቁማር አገር አይመራም መንግስትም  አይጸናም፡፡ አገር መንግስት ይፈልጋል፡፡ ሳይቃጥል በቅተል ብለናል፡፡ ብዙ የኦሮሞነት አቀንቃኞች ለዘብተና ናቸው የተባሉት ሳይቀር ሰሞኑን እየደነፉ ነው፡፡ አርማጌዶን፣ አንቀጽ 39ን እንጠቀማለን ምናምን፡፡ ከዚህ በኋላ ለእነሱ ማባበል አያስፈልገም፡፡ ሁሉም በየአለበት ራሱን ይጠብቅ፡፡ አንቀጽ 39ን ተጠቅሞ ኦሮሚያ የሚባለው ክልል ከኢትዮጵያ ቢለይ እኔም እደግፋለሁ፡፡ ዛሬ እንዲህ ከሥርዓት ውጭ የሚደነፋው ስርዓት አክባሪ ዜጎች በሠሩት አገር ነው፡፡ ኦሮሚያ እንደ አገር ቢገነጠል የደቡብ ሱዳንን ያህል እንኳን  ቀን አይጠብቅም፡፡ ሲጀምር ኦነጋውያን አገርና ሕዝብን ማፍረስ እንጂ አንድም ቀበሌ በኃላፊነት ማስተዳደር እንደማይችሉም እንደማይፈልጉም ግልጽ ነው፡፡ ከጅምሩም ይሄው ነው አለማቸው፡፡ አገር መሥርተው እንደማይቆሙ ያውቁታል ግን እንዲህ ያለ ኃላፊነት እንደፈለጋቸው እየቆመሩ መኖሩን ነው፡፡

ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ ግን ሸዋን በቁጥጥርህ ሥር አድርግ፡፡ ሸዋ የአባቶቻችን ማዕል ነው! ሁሉም ሸዋ ላይ አለ፡፡ ወሮበሎችን ከዚህ መንጥሮ አውጥቶ የራሱን ግዛት መመስረት ግድ ይላል፡፡ ያኔ የኢትዮጵያ መንግስትም መንግስት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በሸዋ ገበሬ ኦሮሞ ነኝ በሚል መነገድ ከዚህ በኋላ ሊቆም ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የዜጎች መብት ሙሉ በሙሉ የሚከበርበት የሸዋ መንግስት ግድ ነው!

ልዑል እግዚአብሔር አገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቃል! አሜን!

ስርፀ ደስታ

 

 

2 COMMENTS

  1. የሰሞኑን የፖለቲካ ትኩሳትን በሃገራችን ለተጀመረው በጎ ለውጥ መሪዎች መንቀፊያ ማድረግ የሚያሳዝንም የሚያሳፍርም ነው:: የከተሞች ህዝብ የመኖሪያ ቤት ችግር በሃገራችንና በተመሳሳይ ሃገሮች የከፋ ሲሆን ጨቁዋኝ መንግስታት ከአጼ እስከ ወያኔ ደሃ ገበሬዎችን በማፈናቀል መዝባሪ ባለስልጣኖችና ደላሎቹ የቅንጦት ኑሮ የበዙ ትልልቅ ቤቶችና ቦታዎች ለራሳቸውና ለዘመዶቻቸው ሲያካብቱ ብዙሃኑ ህዝብ በሰቆቃ መኖሩ የሚታወቅ ነው ይህንን ለመቅረፍ የዶር ኣአብይ መንግስት ከገቢዎች ሚስንትር ጀምሮ የሚሰራውን ታምራዊ ስራ የማያይ አይን ይማር ከማለት ሌላ ምን ይባላል? የሰሞኑ የጩፌ የቤቶች ማደል የተሻለ ቢሆንም ቤቶቹ የተሰሩት በወቅቱ ኦሮሚያ ተብሎ በሚታወቀው መስተዳደር ስለሆነ በዚያ መሰረት ሙሉ ስልጣኑ የኦሮሚያ ክልል መሆኑን ያለምንም የሰውና የንብረት ጥፋት የተቃወሙትን በመስማት ክልሉ ስያውቀው የማይቀረውን አላውቅም ብሎ ለህዝቡ መወገኑ ያለው ብቸኛ አማራጭ ነው:: ለወደፊቱ ግን ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሃገሮች ችግሩን የፈቱበትን በምክክር ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ መከወን ይገባናል:: ከዚህ ውጭ ግን አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የህዝቡን ስሜት በመጠበቅ የማረጋጋቱን የጥበብ ስራ በማጣመም የዶ/ር አብይን የለውጥ ራእይ ማጥላላት ማንነትን ያሳያልና ነቃፊዎች በአግባቡ መንቀፍን ሚዛናዊ መሆንን ህዝቦችን መብትና ማንነትን ማክበርን ተማሩ::

    ሃሰት ዜና ባቀረቡ ቁጥር የሚቀሉ ሚዲያ ተብዬ ማፈሪያ ናቸው::መጀመሪያ ቄሮዎች(ወጣቶቹ) ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ምንም የሰውና የንብረት ጉዳት ኣልተከሰተም:: የያዙት ገጀራ ሳይሆን ዱላ የኦሮሞ ምልክት ነው::ባለጌዎች ኦዱ (ዜና) ሲቀርብ ድሮ ኦሮሞና ዱላው ያሉት ስድነትም ቢሆን ታሪክ ነው:: ከዚህ በተረፈ የመኖሪያ ቤቶች ችግር ያለባቸው ትልልቅ ከተሞች ተመሳሳይ ችግር በከተማ ዙሪያ ባሉ ቦታዎች ያደርጋሉ ከአፍሪካ ሩዋንዳ ምሳሌ ስትሆን የሃገራችን የወያኔ ክፉ ማካለል ይህን ለመተግበር ያስቸግራል::ቤቶቹ የተሰሩበት ስፍራ የኦሮሚያ ክልል ተብሎ ባለው ህግ የሚታወቅ ስለሆነ የኦሮሚያ ማንነትን ለሚያምኑበት ይህን መቃወም ህገ መንግስታዊ መብት ነው::ሆኖም ግን የመኖሪያ ቤት ችግር ክፉኛ ላለባቸው ወገኖቻችን በምክክር ያለውን የመስተዳደሮች መብት በመጠበቅ ቢደረግ ለሁሉ ይበጃል::የኦሮሚያ ሃላፊዎች ሳያውቁ ግንባታው አልቀጠለም::በምክክር ቢደረግም ወያኔ ባበላሸው የጎሳ ፌደራሊዝም ህግ ቤቶቹን ማስተዳደር ያለበት የኦሮሚያ መስተዳደር መሆን እነደሚገባው አክትቪስቶቹ ከውጭም ከውስጥም ባደርጉት ትግል የኦሮሚያ ክልል ጉዳዪን ለማርገብ ከዚህ የተሻለ አማራጭ የለውም::አመቺ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታና እደላ በህዝብ ከተጨናነቁ ከተሞች ወጣ ብሎ መገንባት በሌሎቹ ሃገሮች በሩዋንዳ በህንድ ይካሄዳል ለብዙ ዜጎችም ጥሩ ቤት ያጎናጽፋል:: ውዝግቡ ተወግዶ በመኖሪያ ቤት ችግር የተጎዱ ወገኖቻችን የሚደገፉበትን ቀን በጸሎት ናፍቃለሁ::

  2. “የደንበጫው ተወላጅ እስክንድር ነጋ ስለ ፊንፍኔ ባለቤትንት ለመምከር ከአባይ ማዶ የባህርዳር ተወላጆችን ዛሬ በተለያዩ መኪናዎች ይዘው ገብተዋል::” haha

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.