አማራ ሆይ! ሰው እንሰሳ ነው!በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

“እግዚአብሔርም ..ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” አለና እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረው፡፡ ዘፍ ፩፡ ፳፮-፳፯. ይህ መለኮታዊ ቃል አማራ ክስድስት ሺ ዘመናት በላይ ኑሮህን የመራህበት ቃል ነው፡፡ በዚህ ቃል መሰረትም ሁለት እጅ፣ ሁለት እግር፣ ሰላሳ ሁለት ጥርስና እሚናገር ምላስ ያለውን ሁሉ እንደ ሰው በመቁጠርና በሰው አካልም “እግዚአብሔር አለ” እያልክ ለብዙ ሺ ዓመታት ለአደጋ ስትጋለጥ ኖረሃል፡፡ በዚህ ዓለምን ሰይጣን በሚያስተዳድርበት ዘመን ሳይቀር “ሰውን እግዚአብሔር ባምሳሉ ፈጠረው!” እያልክ እንደ እብራውያን የመሰደድና እንደ አረማውያን የመጥፋት አደጋ ተደቅኖብሃል፡፡

ተንኮልና ደባ ሸርቦ የመጣውን ሰው መሳይ ፍጡር ሁሉ የእግዚአብሔር እንግዳ እየመሰለህ ለለበጣ “ቤተ-ለእቦሳ!” ሲልህ “እምቦሳ እሰር” እያልክ ተቀብለህ ምርጥ ምርጡን እያበላህና ከአልጋህ እያስተኛህ ያሳደርከው እንግዳህ ሲያሰቃይህና ጦርነት ሲከፍትብህ ኖረሃል፡፡ ጦርነት ከፍቶብህ ያስጨነከው ጣልያን “በማርያም ይዤሃለሁ!” እያለ ማተብህን እንደ ድክመት ቆጥሮ ሊያታልልህ ሞክሯል፡፡ እንደ ጣልያን ሁሉ የጣሊያን ትርጁማንና እንቁላል ቀቃይ ልጆች ይኸንን መለኮታዊ ባህልህን እንደ ድክመት ቆጥረው ከቤትህ እየበሉና እያደሩ አንዳንድ የተረገሙ ልጆችህን በሆዳቸው ገዝተው አንተን የሚጠልፍ ወጥመድ ዘርግተው ዛሬ ካለህበት መቀመቅ ዶለውሃል፡፡ በእንግድነት ተቀብለህ ከምግብህ፣ ከመጠጥህና ከጥበብህ ያካፈልካቸው እርጉሞች በአያቶችህ ደም በከበረችዋ አገርህ “ሰፋሪን አባር” እያሉ የጎዳና ተዳዳሪ አድርገውሃል፡፡

አማራ ሆይ! በምድር ያለው ሕዝብ እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረው ቢሆን ኖሮ እንኳን ክልል የአገርና የአሀጉርስ ድንበር ይኖር ነበር ወይ? ዛሬም “ሰው”ን ሁሉ እግዚአብሔር በአምሳሉ ፈጠረው በሚል ፍች የሌለው ህልም እየዳከርክ ነወይ? እግዚአብሔር አይምሮ የሰጠን ሰው የሆነውን ሰው ታልሆነው፣ ክፉውን ከደጉ እንድንለይ አይደለም ወይ? እና ይኸ የሰላሳ ዓመታት መከራህም እግዚአብሔር በአምሳሉ ያልፈጠራቸው ሰዎች እንዳሉ አላስተማረህም ወይ?

“የአማራና ኦርቶዶክስ ቋንጃ ተሰብሯል!” የሚል አረመኔ አጋንንት እንጅ እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ? በበደኖ ባለቤቷን ገለውና አስራ ሶስት ልጆቿ እያሉ የአርባ ዘጠኝ ዓመት እናትን ተሰልፈው በየተራ የሚደፍሩ ከሃምሳ በላይ ታጣቂዎች እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ? ልጆችህን ከነነፍሳቸው ከፈላ ወደ ቀዝቃዛ ውሃ እየከተተ እንደ ዶሮ የሚገሸልጥ፣ በብልታቸው የሞላ ኮዳ እያንጠለጠለ እግዚአብሔር የፈቀደውን ዘር እንደ ኩራዝ እሚያጠፋ፣ ዓይናቸው እያየ ህብለ- ሰረሰራቸውን እየቆረጠ ሽባ የሚያደርግና እግርን እሚቆርጥ፣ በቁማቸው ዓይናቸውን መንቅሮ እንደ ድንች እሚያወጣ ጭራቅ ዲያብሎስ እንጅ እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ? ቤታቸውን በግኒደር እንደ ቋጥኝ ፈንቅለው ሴት ልጆችህን እንደ ፈረስ ከመስክ እንዲወልዱ የሚያደርጉ አውሬዎች ሰይጣን እንጅ እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ?

ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚለው እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በአምሳሉ ነው፡፡ “እግዚአብሔር ሰውን ባምሳሉ ፈጠረው!” ውስጠ ወይራው ሲገለጥ በእግዚአብሔር አምሳል ያልተፈጠረ ፍጡር ሰው አይደለም ማለት ነው፡፡ አማራ ችግርህ በእግዚአብሔር አምሳል ያልተፈጠረን ፍጡር እንደ ሰው መቁጠርህ ነው፡፡ የመከራህ ሁሉ መንስኤው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው በዲያብሎስ አምሳል ከተፈጠረው ሰው መለየት አለመቻልህ ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ዲያብሎስ ከፈጠረው ሰው መለየት ከቻልክ እዳው ላንተ ገብስ እንደሆነ ቱርክም፣ ግብጥም፣ ጣልያንም የሚያውቀው ነው፡፡

ዲያብሎስ በአምሳሉ የሰራው ሰው ጉልበት ሲያገኝ በመንጋጋው ሰው እሚግጥ አውሬ ጉልበት ሲያጣ ደሞ በፊት ጥርሱ ሳር እሚግጥ እንሰሳ ነው፡፡ ሳይንስም ሰውን እሚያውቀው በእንሰሳነቱ ነው፡፡ የሳይንሱ ሰው እንደ ጅብ ካሉ እንሰሳት እሚለየው ለህሊናና ለይሉኝታ የሚታዘዝ እውቀትና ጥበብ ስላለው ነው፡፡ ህሊናና ይሉኝታ የሌለው ሰው ሲጎለብት አውሬ ሲደክም ከብት እሚሆን እንሰሳ ነው፡፡

አማራ ሆይ! እየኖርክ ያለኸው ይህ ሲጠግብ አውሬ ሲደክም ደሞ ከበት የሚሆን እንሰሳ በሚገዛት ዓለም ነው፡፡ በዚች ዲያብሎስ በአምሳሉ በሰራው አውሬ በሚቆጣጠራት ዓለም እግዚአብሔር በአምሳሉ የሰራው ሰው ሆኖ መገኘት እሚጠቅምህ ምናልባትም በሰማይ ቤት ብቻ ነው፡፡ ይህ አጉል ብጽዕና በምድር የሚያስከትለው መጥፋትን ነው፡፡ በዚህ አጉል ብጽዕና ተሸፍነህ ዲያብሎስ በአምሳሉ የሰራውን ሁሉ እንደሰው መቁጠር ከቀጠልክ እንደ ጀመርከው ሳስተህ ሳስተህ እንደ በራ ማለቅህ ነው፡፡

አማራ ሆይ! ተማለቅ የምትተርፈው ዓለም በዲያብሎስ “አምላክነት”ና በአውሬዎች አዳኝነት የምትገዛ መሆኗን ተገንዝበህ ዲያብሎስን በፀበል አውሬንም በነፍጥ ተመከትክ ብቻ ነው፡፡ አውሬ አፉን እንደ ሰማይ ቦርግዶ፣ አቀንጣጤውን እንደ ጦር አስልቶ፣ ጥፍሩን እንደ ወስፌ አሹሎ ከጭራቅ ከፍቶ ሲመጣብህ በውይይት፣ በምክክር፣ በእርቅና በፍቅር ለመመለስ መጃጃል ፈጣሪንም መፈታተን ነው፡፡ ፈጣሪ ለእባብ እንዳዘዘው ከአውሬ መግባባት እምትችለው አውሬ በሚገባው ቋንቋ ብቻ ነው፡፡

አማራ ሆይ! ድክመትህን ደጋግመህ አጢነው! ትልቁ ድክመትህ “እግዚአብሔር ሰውን ባምሳሉ ፈጠረው” እያልክ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ዲያብሎስ ከፈጠረው ሰው አለመለየትህ ነው፡፡ ይህ ድክመትህ የሚጠገነው እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ዲያብሎስ ከፈጠረው ሰው ለመለየት ዓይንህን እንደ ባውዛ ያበራህ እለት ነው፡፡ ድክመትህን ጠግነህ እንደ እብራውያን ከመሰደድ፣ እንደ አረማያንም ከመጥፋት የምትድነው ዲያብሎስን “ቿ!” አርገህ በፀበል ስታጠነፍገው አውሬንም “ዘራፍ!” ብለህ በሚገባው ቋንቋ ሰምና ወርቅ ስታናግረው ነው፡፡

አማራ ሆይ! አትዘንጋ! የዛሬ ሰው ሲጎለብት በመንጋጋው ሰው እሚግጥ አውሬ ሲደክም ደሞ በፊት ጥርሱ ሳር እሚግጥ እንሰሳ ነው! ሲጠቃለል የዛሬ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ያልተፈጠረ እንሰሳ ነው! ህልውናህና ክብርህ እሚከበረውም  ይኸንን ከተገነዘብክ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

መጋቢት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

 

5 COMMENTS

 1. አዎ!! ወገን በላይነህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ መነሻችን አሁን ነው። ነገን ከጠበቅን ተነገወዲያን ሳናይ ያጠፉናል።
  እውነት ነው ወገን በላይነህ!!! አውሬ ማሳደድ ከጀመረ ሳይበላ አይለቅም ። በመሆኑም ፣ አማራው አውሬዎቹን በቋንቋቸው አናግሮ ወደ ከብትነት መመለስ ይኖርበታል ። ይሄንን ፈጣሪም ከእኛ እንደሚጠበቅ አምናለሁ። አለበለዚያ ቱርኮች በአረማውያን ላይ ያደረሱትን ዓይነት ጥፋት ይደርስብናል ።
  ለአማራ ልሂቃን!!!
  ዲያብሎስን ለማርከስ የሚደረገውን ድግምት አፍላቂ እናንተ ነበራችሁ ። ግን ብዙዎቻችሁ ፈስታችሁታል።
  በመሆኑም ዲያብሎስ የሱ ተገዢ አድርጎናል። ስለዚህ አማራውን የሚያድኑትን ድግምት እየረጫችሁ አማራውን ከዲያብሎስ አላቁት ።

  ድኩላ ይመስል እያሳደዱን፣
  ገንጥለው ሊበሉን ሲጠራሩብን፣
  ጉብ እንበልባቸው አውሬ ካረጉን።

 2. እዚያ ስፈር በሜንጫ በገጀራ በዱላ በስነልቡና ፕሮፓጋንዳ ተነሳ እዚህ ሰፈር አውሬ ተንሳብህ በምታውቅበት ልማድ አሳየው ጎራዴም አለን የሚሉ ቅስቀሳዎች በብዙ መከራ ላላፈው ህዝባችን የሚበጅ አይደለም:: ሌላ እልቂት ሌላ ደም መፋሰስ ሌላ መሰደድ ለማንም የስው ዘር አልመኝም:: ስለዚህ ዶ/ር አብይ ለአዲሱ የአማራ ክልል ተሿሚ ዶር አምባቸው ያለውን ምክር ተቀብለን ጥላቻውን በርስበርስ ጉብኝት በይቅርታ በፍቅር በመደጋገፍ ይቀየር ዘንድ እንትጋ ::ይህን መሰሉን በለው ፍለጠው አትመነው አውሬ ነው ቅስቀሳ እቃወማለሁ

 3. This is from a very sick mind! ሲጠቃለል፣ “ሰው ሁሉ አዉሬ ነው፣ አማራ ግን ሰው አይደለም!!” ነው ! ወይም፣ “እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው (አማራ) እና ዲያብሎስ የፈጠረው ሰው (ሌሎች)” አሉ። ስለዚህ ዲያብሎስ የፈጠረውን እንስሳ (ሌሎችን) አማራው ተነስ፣ ጨፍጭፍ! ነው ጥሪው! Is this person a desciple of Goebbels??

  Where are the Editors of this website ?? You are responsible for such call for violence!

 4. ክቡር አቶ ደጎሜ ሞረቴው!
  እስከአሁን በ ማነባቸው ፅሑፎች ላይ ሁሉ አማራው ሲገደል ፣ሲፈናቀል እራሱን ለመከላከል ቆርጦ መነሳቱ ሲሰማ ስለ ውይይት ፣ስለ ፍቅር ማንሳት ይጀመራል ። ውይይትና ፍቅር ከተፈለገ በሚከተለው ሁኔታ ከአማራው ጋር ማድረግ ይቻላል።
  1ኛው) ኦዴፓ ለደራ ፣ለቅምብቢት አማሮች በጠቅላላው ኦሮሚያ ውስጥ ለሚኖሩ አማሮች በቋንቋቸው እንዳይማሩ መከልከል የለበትም። ኦዴፓ የአፓርታይድ ክልላዊ መንግሥትና ተስፋፊ ክልላዊ መንግሥት ነው።
  2) ኦዴፓ አዲስ አበባ ኬኛ የሚለውን ቅዠትና አጫራሽ የተስፋፊነት አቋሙን መተው አለበት።
  3ኛ ጀዋር መሐመድ ሕዝብን ለማጨራረስ እየጣረ በመሆኑ ለፍርድ መቅረብ አለበት።
  በእነዚህ ነጥቦች ላይ ምን ታስባለህ?
  ይኸው ልህ ኦዴፓ እነዚህን ተሰፋፊነትና አፓርታይድ ይዞ ፍቅር ሊያመጣ አይችልም ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.