እስኪ ለአዲሱ የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ሞራ እንግለጥላቸው (አሰፋ በድሉ)

ሞራ ገለጣ ምንድን ነው? በሲዳማ ባህል በብሄረሰቡ በዘመን መለወጫ ወቅት ከብት ይታረድና አባቶች ሞራ ያነባሉ፡፡ስለ መጪው ጊዜ፡፡የሞራን ቃል የተዋስሁት ከምወደው ጸሐፊ ዶ/ር በዱሉ ዋቅጅራ ነው፡፡በተለይ ልጄ ዕድሩ ነው አገርሽ የሚለው ግጥሙን እወድለታለሁ ፡፡ሞራ ገለጣውን ከመጀመሬ በፊት ዶ/ር አምባቸውን እንኳን ደስ አለወት ለማለት ዕወዳለሁ፡፡መልካምም የአመራር ዘመን እመኝልወታለሁ፡፡አቶ ገዱን በእኔ የግል አቆጣጠር የመጀመሪያው የአማራ የክልል ፕሬዘዳንት ናቸው፡፡ምስጋናየ ይድረሰወት፡፡ ትግራይ የመሸገው ወንበዴው ክፍል አምርሮ እንደሚጠላወት፤እንዳስጠላወትም አውቃለሁ፡፡ጨለማ ከብርሃን ህብረት የለውም፡፡ቀና ከጠማማ ዝምድና የለውም፡፡በዚህ አይደነቁ፡፡የሰሩት ስራ ጉልህ ነው፡፡በእነሱ አነጋገር ልገለጸውና ህዛባችንን ጠርንፈውት ነበር፡፡በእርሶ ጊዜ ነው የተፈታነው፡፡ምናልባት እንዳንዶቻችን በግል ነጻነታችንን ሳናስደፍር ቆይተን ሊሆን ይችላል ግን ተዋርደው የአዋረዱን ነበሩ፡፡ሞራውን ከዚህ ልቀጥል…የጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይን፤ም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀን፤የቀድሞ የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት የአቶ ገዱን፤እንዲሁም የዶ/ር አምባቸውን የበዓለ ሲመትን ንግግር ለሞራ ገለጣየ ተጠቅሜአለሁ፡፡

መጀመሪያ ከፊት ከሚጠብቆት 2 እሳቶች ልጀምር፡፡ አማራን ለማሰባበሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ምቹ ጊዜ ይጠብቀወታል!!!

1ኛ. በመጀመሪያ ክቡር ፕሬዘዳንት ከደደቢት ሴራ ራስወን ይጠብቁ

በዚህ ጉዳይ ጠንቃቃ ካልሆኑ ከአማራ ህዝቦች ጋር ይጣላሉ፡፡የሚገርመው ሴራው የጀመረው የተሾሙ ዕለት ነው፡፡ይኽውም በዶ/ር አብይ አማካኝነት በኩል የተነገረው ዶ/ር ደብረጺዮን በበአለ ሲመትወ ዕለት መገኘት ፍላጎታቸው እንደ ነበረ፡፡ማን ይሙት ከልባቸው ነው? ታዲያ ከጠ/ሚ/ሩ ጋር አብረው ለምን አይመጡም ነበር? ዶ/ር አብይ ዋሽቶ ለማቀራረብ መሰለኝ፡፡ይሄ ሸፍጥ እኮ ነው ያጣላን፡፡የደስታ መግለጫና የጉብኝት ግብዣም ቀርቦሎታል፡፡ወሰን የለም፤ኮሪደሩን በጋራ ማልማት ነው ይላሉ፡አያይዘውም፡፡ወሰን ላይ የአከማቹት ጦር ታዲያ ዝንጀሮ እየጠበቀ ነው፡፡ዶ/ር ደብረጺወን በሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ከገዱ ጋር ተገናኝቶ የሰራው ድራማ የቅርቡ ነው፡፡ ገዱ ቃሌ ፊርማየ አለ፤እሱም ተመሳሳይ ንግግር አድርጎ፤ከሶስት ቀን በኋላ ይመስለኛል የጥምቀት ዕለት በሙሉ የትግራይን ሰው የራያ ልብስ አልብሶ ሲያስጨፍር ነበር፡፡የራያ ፖለቲካ፡፡ከመሃል አገር ለስብሰባ የሄደውን ተሰብሳቢ ሁሉ የራያ ልብስ ማልበስ እንደ ስትራቴጂ ተይዞ ነበር፡፡ሃይማኖትንም ለፖለቲካ መጠቀም በደደቢት ነውር አይደለም፡፡የዘቀጠ የሞራል ደረጃ ነው፡፡ምናልባት ዶ/ር አምባቸው እርሶም ጉብኝቱን ተቀብለው ከአቀኑ፤ባክህ የትግራይ ባህላዊ ልብስ ልበስልን ብለው በአልተዘጋጁበት እንደ ድንገት የራያ ልብስ አልብሰው፤አስጨፍረው፤በካሜራቸው ቀርጸው ወይንም ሰፊ የአማራን መሬት ያጠቃለለውን የትግራይን  ክልል ካርታ ስጦታ ሰጥተው፤ከዚያም ስጦታችንን እንዴት አገኙት የሚል ቃለ መጠይቅ ያሰራሉ፡፡መቼም ማንም ሰው ስጦታውን አልወደድሁትም አይባልም፡፡ ከዚያም የአማራ ህዝብ እንዲያየው በአማርኛ ፐሮግራም የሚከተለውን ይሰራሉ፡፡አክራሪው ገዱ ከተነሳ ወዲህ አዲሱ የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት የሰላምና የልማት ጉብኝት በክልላችን አደረጉ፡፡ህዝቡ ሰላም ወዳድና ጦርነት የሚጠላ መሆኑን መገንዘባቸውን ገለጹ፡፡የአማራ መንግስትና ህዝብም ከትግራይ ክልል ህዝብ ብዙ ሊማር እንደሚገባው ገለጹ፡፡የክልሉ መገለጫ የሆኑትን ስጦታም እንደወደዱት ገልጸዋል፡፡ብለው ከዚያ በዲጂታል ወያናይ በኩል ፕሬዘዳቱን ከአማራ ህዝብ የመነጠልና አመኔታ የማሳጣት፤የሚያጋጭ ሴራ ለወጥኑ ይችላሉ፡፡ለማንኛውም ሞራችን ግን የነገረን ግብዣውን አክበረው ተቀብለው አዲስ ፕሬዘዳንት መሆንወን በመግለጽ አጣዳፊ ስራወች ስላሉብኝ ጉብኝቱን ማዘግየት እንደሚፈልጉ ቢገልጹ መልካም ነው፡፡እስከዚያው የወሰን አካባቢወችን ለጉብኝት እንዲያመች ያከማቹትን ጦር ቢያነሱ መልካም እንደሚሆን አያይዘው ይግለጹ፡፡የማንነትና የወሰን ጉዳይን በተመለከቱ ም/ቤቱ ጥሩ አቅጣጫ ስለ አስቀመጠ በዚያ ይመሩ፡፡አሁን ሌላ ግርግር አያስፈልግም፡፡የወሰን ኮሚሹኑም ምክረ ሃሳብ መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡ወደ አሰራር መግባት እንጂ የፖለቲካ ብሮከሮች/ሰርጂኖች ጠቃሜታቸው በዚህ ሰዓት አይታየኝም፡፡

በዚህ ጉዳይ ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ የአደረጉት ንግግር ላይ ሁለት ሞራችን ያልወዳቸውን ጉዳዮች ላንሳ፡፡ ጠ/ሚ/ሩ የአደረጉት ንግግር ሃላፊነት የመሸሽ አዝማሚያና እንደ ተለመደው ግልጽ ያልሆነና አሻሚ ነው፡፡የጦርነትን አስከፊነት ገለጹ፡፡እውነት ነው፡፡በታሪክ እንደሚያስወቅስም  እናም የዚያ አካል መሆን እንደማይፈልጉ ተናገሩ፡፡ይገርማል እሳቸው እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች አዛዥ፡፡እሳቸው ሳያዙ ጦርነት አለ እንዴ? መላ ያጣች አገር! ስለ ሌላ ሁለት አገሮች ነው የሚያወሩት? ሁለቱን ክልሎች መዳኘት የአለበት ማን ነው? በእውነት ሁለቱ ክልሎች ወደ ጦርነት አልለውም ወደ ግጭት ቢገቡ ዝም ብለው ሊለምኑ ነው እንዴ? የአገር መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ወይ አልገባቸውም ወይም እየሸሹ ነው! ጦርህን አንሳ ማለት የእሳቸው ሃላፊነት መሠለኝ፡፡አካፋን አካፋ ማለት ካቃታቸው ደግሞ እንኳን አገር ቤተሰብንም መምራት ይቸግራል፡፡ለማንኛውም በቁስል አከካ አስታከው የነገሩን ስንተረጉመው በሞራችን ህወሃትን መጫን አልፈልግም፤ቁስል አትከኩ ማለት ህወሃት ስለበደላችሁ አታንሱ፤ይህም ማለት የማንነትና የወሰን ጥያቄአችሁን ተውት፤ይቅር በሉ፡፡ወንድነነት ማለት አለመለመን ነው የሚል ስድብ አከል ንግግርም አክለዋል፡፡እንግዲያው የተሸናፊነትና የአባትን ርስት በፈቃደኝነት ሳይሆን፤በፍቅር ሳይሆን፤ በግድ፤በሃይል አሳልፎ መስጠት ከልመና የባሰ ውርደት ነው፡፡የ21ኛው ክ/ዘ/ የሰለጠነው አሜሪካዊ ዛሬ በክብሩ አይደራደርም፡፡ለራስ ክብር መስጠት ስልጡንነት ነው፡፡በዚህ መሰለኝ ጣሊያንን የመለስነው፡፡እና የጠ/ሚ/ሩ አሕያውን ፈርቶ ዳውላውን ምክር አልቀበልም ይበሉ፡፡እርሶ ቢቀበሉ እንኳን የአማራ ህዝብ አይቀበልም፡፡

እዚህ ላይ ዘመናዊው መንግስት እየቀረ ስለሚመስል ስለ አማራ ቅሬታ አፈታት ላንሳ፡፡አማራ ከመሬት ተነስቶ አይጣላም፡፡በምክንያት ነው፡፡ከትግራይ ጋር ችግር ውስጥ የከተተን ጠ/ሚ/ሩ ከራሳቸው ጓሮ ገፍተው እኛ ጓሮ የአስቀመቱት ህወሃት ነው፡፡ለምን ህወሃት ላይ ለውጥ ማምጣት አልፈለጉም፡፡ጊዜ ነው መልስ የሚሰጠን፡፡በጃዋር በኩል የመንሰማው አስተዛዛቢ ነው፡፡ይህን ጉዳይ በንቃት ይከታተሉት፡፡ከህወሃት ጋር ጸባችን ሁለት ነው፡

  • ዕኛ ባልነበርንበት የነበሩ መሪወችን መነሻ በማድረግ በቅናትና፤በተንኮል፤በምቀኝነት፤በበታችነት ስሜት የተመታ ቡድን እኛን ደሃና ከአገር መሪነት የአራቀን የአማራ ብሄር ነው ብሎ በነጭ ወረቀት በጥቁር ቀለም ጽፎ የሃሰት ክስ ይዞ ተነሳ፡፡ይህን ክሱንና ስም ማጥፋቱን በትግል ወቅትም፤አገር በመራበት ወቅትም፤ዛሬም የህይወቱ አካል  በማድረግ እየሰራው ይገኛል፡፡ በዚህም ላለፋት ግማሽ ክፍለ ዘመን የሚጠጋ ጊዜ ነቀርሳ ሆኖን አመንምኖናል፡፡
  • ለአገር ግንጠላ የተዘጋጀ ቡድን ስለሆነ እስከ ዛሬም ጊዜ ሰጠኝ ብሎ የአማራን መሬቶችና ነዋሪወችንም ጭምር በሃይ አጠቃለለ፡፡

አማራ ዝም ብሎ አይጣለም የምለው ለዚህ ነው፡፡ጭብጥ ይዞ ነው፡፡

ስለ አማራ ቅሬታ አፈታት ላንሳ፡፡ ጉዳይ ተብጥርሮ ታይቶ በዕርቅ የሚፈታው፡፡እውነት ሳይወጣ እርቅ የለም፡፡የሽማግሌ ልጅ ነኝ፡፡አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡እንደ ጉዳዩ ክብደት የተለያየ ደረጃ ሊኖረው ይችላል፡፡መጀመሪያ ሁለቱም ወገኖች የተስማሙባቸውን ሽማግሎች ይመርጣሉ፡፡ሽማግሎቹ የተጣሉትን ለየብቻ በደንብ እያስማሉ ይመረምሯቸዋል፡፡ደደቢት መሃላ ይፈራል እንዴ? መስቀል ይፈራል እንዴ ኮሚኒስት? ወደ ሽምግልናው ልመለስ፡፡ሁለቱን በጋራ ደግሞ አከራክረው፤አዋቅሰው ከሰሙ በኋላ፡፡የተጣሉትን ሰወች ራቅ ብለው እንዲቀመጡ ያደርጉና ሽማግሎቹ ማን እንዳጠፋ ለብቻቸው ይመክራሉ፤አውጥተው አውርደው፡አንድ እውነት ላይ ይደርሳሉ፡፡አንዱ ብቻ በዳይ ሊሆን ይችላል፤ሁለቱም አጥፍተው ሊሆን ይችላል፡፡ የተጣሉትን ጠርተው ያንን የደረሱበትን እውነት በመንገር ይቅር አባብለው፤የተበደለ ይካሳል፤የበደለ ይክሳል፡፡ሁለቱም ቤት ድግስ ተደግሶ በየተራ ሰፋ ያለ ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት አብሮ በመብላት እንዲሽር ይደረጋል፡፡

ከደደቢት ጋር የእርቅ ኮሚሽኑም ሆነ ሌላ በጋራ ሁለቱም ወገኖች እኩል እኩል ሽማግሎች መርጠው፤ተከራክረው፤ተዋቅሰው እውነቱ ወጥቶ ከዚያ እውነተኛ ሽማግሌ የፈረደበትን ፍርድ አማራ ቢቀበል፤ወንድምነትን ከፍ አደረገ እንጂ ውርደት አይሆንበትም፡፡ግን ደደቢቶችም እንደ ኤርትራውያን ካልበለጡ፤ካላተረፋ አይስቁም፡፡ኤርትራዊያን ድንበርና አሰብን ካላነሳህ ወንድም ነህ፤ካነሳህ ግን …ያው ሃያ ዓመት ነው፡፡የራሱን የሰጠን ማን ሊጠላው እንደሚችል አላውቅም፡፡

ለጠ/ሚሩ ስለ ቁስል አከካ ጉዳይ ደጋግመው ሲያነሱ ስለሰማሁ መንገር የምፈልገው አማራ እያከከ ያለው ከፍ ተብሎ የተገለጸው ዛሬ እያመረቀዘ ስላለ ቁስል እንጂ ስለ አለፈው አይደለም፡፡እድሜ ልኩን ከዘረ መሉ የተዋሃደ እስኪመስል ምኒልክ የሚለው የእርሶ ፓርቲ አዴፓ፤ኦነግና ህወሃት ናችሁ፡፡ይሄ አማራን አይመለከትም፡፡ቁስል አከካን ለራስወ ይውሰዱ፡፡

2ኛ፡ በአዲስ አበባ ኬኛ ጉዳይ የማያወላዳ ቁርጥ አቋም ይያዙ

ፍንፍኔ የእኔ የሚለው የሰሞኑ ነጠላ ዜማ፤ጸረ-ህገ መንግስት፤ጸረ-ህዝብ፤ጸረ-አንድነት እና የፌደራል ስርዐቱን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በዚህ ፤በእናት አገር ድርድር የለም፡፡ዛሬ በአደባባይ በህግ የማይታወቅ፤ተጠያቂነት የሌለው ቄሮ የሚባል ቡድን ከመንግስታዊው አካል ጋር እየተመጋገበ አገር በማፍረስ ላይ ይገኛል፡፡

3ኛ፡ከጠ/ሚ/ሩ ከንቱ ውዳሴና ሙገሳ፤አሻሚ/ያልጠሩ አቋሞች ይጠበቁ፤ከተቻለ ጠቅላዩን ይርዱ

ጠቅላዩ አንዱ ስልታቸው በሙገሳና ውዳሴ ሸብ ማድረግ ነው፡፡የዚህ ሰለባ ዋናው ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ነው፡፡አዲስ አበባ እንኳን ስትዘረፍ የበላው ጅብ አይሰማም፡፡ዋናው ዘረኞችን ሞጋች የነበረው ምሁርና ፖለቲካኛ እንድናጣው ሆኗል፡፡ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፤ፕ/ር አል ማርያምና ሌሎችም፡፡ስላሞገስወ ድንበሩን አይተውት፤አዲስ አበባን አይተዋት፡፡ፓርቲያቸው ፍንፍኔ ኬኛ እያለ እሳቸው ደግሞ ለሁላችን የምትበቃ አዲስ አበባ እንድትበቃ ይላሉ፡፡ነገሩማ ህገ መንግስቱ የሚለው አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስት ነበር፡፡ስልጣናቸው ሲወሰድ እንኳን እንዴት ነው? ነው እዚያም እኛው ነን ነው?

4ኛ፡ ዘመነ መሳፍንት ከፊትወ ስላለ ለዚያ ራስወን ያዘጋጁ

ጠ/ሚ/ሩ ወደ ስልጣን እንደ መጡ የወሰዷቸው ርምጃወች የመሪነት ሞገስ ያላበሷቸው፤ተደማጨነታቸውና ትዕዛዛቸው ተፈጻሚ ይሆን ነበር፡፡ግን ህወሃት ላይ የተከተሉት ፍርሃት አይሉት ጥበብ አስንቋቸዋል፤ለህግ ማቅረብ አልቻሉም፡፡ጭራሽ ባናስረውም ታስሯል የሚል አስቂኝ መልስ ለፓርላማ ሰጡ፡፡በቅርቡ ደግሞ የጃዋርና የሸኔ ቡድን ኦሮሚያንና አዲስ አበባን መቆጣጠር፤የእሳቸውም አሻሚ አቋም፤ ዳግሚዊ ሃይለ ማርያም ለመሆን የቀራቸው ጊዜ ትንሽ ነው፡፡ቀዳማዊ ሃይለ ማርያም በህዝብ ዘንድ እንደሌለ ነበር የሚቆጠረው፡፡ያው ይህ ውሳኔ የመስጠት አቅም ማነስ በተለይ ህወሃት ተመልሶ እንዲገን ሆኗል፡፡ይሄ ደግሞ አማራን ለመምታት በጃዋር እንደ ተጨማሪ አቅም እየታየ ነው፡፡ጠቅላዩ መጠቅለል አልቻሉም፡፡ሰብሳቢው መሰብሰብ አልቻሉም፡፡ስለሆነም ፌደራል ላይ እንደ ሃይለ ማርያም ጊዜ ፓወር ቫኪውምና ሽኩቻ ሊፈጠር ይችላል ይላል ሞራችን፡፡ምናልባት ወደ ኦነግ ካምፕ ቢሳቡና ደደቢትን የድርሻውን ሰጥተው ደቡብን አስፈራርተው ቢይዙ ዘመቻው ወደ አማራ ይሆናል፡፡እጅ ስጥ አልሰጥም፡፡ምን እጅ አለ የእሣት ሰደድ… ይበሉ!

5ኛ፡ አማራ ተበትኖ ይገኛልኛና ወደ ሌሎች ክልሎችም እጅወትን ይዘርጉ

በተለይ ቤንሻንጉል፤ጉምዝ፤ጋምቤላ፤አፋር፤ሶማሌ ጋር ወዳጅነትወትን ያጠናክሩ፡፡ኦሮሚያ በኦነግ እጅ ስለሆነ ለፍጥጫው ይዘጋጁ!

ይላል ሞራችን!!!

ለዕለት ጉርስ ፍላጋ ውድ ጊዜአችን ቀንሰን የምንደክመው፤ጋን በጠጠር ይደገፋል የሚለውን በማሰብ፡ሲቀጥል ህዝባችን ከፊታችን የተደገሰለት ቀላል ስላልሆነ ከጎናችሁ መቆማችንንም ለማሳየት ነው፡፡

መልካም የስራ ዘመን!!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.