በጋራ እንቁም! የኢትዮጵያ ልዑላዊነትና የኢትዮጵያ ህዝብ ህልውና በግልጽ አደጋ ላይ ወደቀ

የካቲት 28/2011 ዓ.ም የኦሮሚያ መንግስት የሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያውያን ላይ ግልጽ ጦርነት ከማወጅ ያልተናነሰ ነው፡፡ ዝርዝር ለመዘርዘር ጊዜ የለንም፡፡አደጋ ላይ ነን ምግባችንን ከምናጣፍጥባት ተራ ጨው ጀምሮ አዲስ አበባ ላይ ጥገኛ ነን፡፡አባቶቻችን ብቻ ሳይሆኑ ዛሬም ድረስ ያለነው ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ላይ ሁሉን ነገራችንን አፍሰናል፡፡ጥርጣሬ አልነበረንም፡፡ ግን ያላሰብነው በገሃድ እየሆነ ነው፡፡በገሃድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገነባው ኮንዶሚነየም በሃይል ተያዘ፡፡የመንጋ ፍትህ፡፡ቀጥሎ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪን ከቤቱ እያስወጡ ይገቡበታል፡፡እናም ነፍሳችንን ለሸኔ በአደራ መስጠት አንችልም፡፡አሁን ኦዴፓ የሚባል ነገር የለም፤ያለው የሸኔ መንግስት ብቻ ነው፡፡በኦሮሚያ መፈንቅለ መንግስት ተካሂዷል፡፡የፌደራሉን ማትረፍ የሁላችን ኢትዮጵያውያን ወኔና አብሮ መቆም ይወስነዋል፡፡አሁን አብይን መለመን፤ለማን ተስፋ ማድረግ ያለንን ጊዜ ማባከን ብቻ ሳይሆን ዋጋ ያስከፍለናል፡፡

አንዳንዶች ጉዳዩ የአዲስ አበባ ጉዳይ ብቻ መስሏቸዋል፡፡ነገ ሁላችንም ከመከራ ከምንማር ጉዳዩ የጋራ፤ፖለሪካ፤ሃይማኖት፤ዘር ሳይለየን በጋራ መመከት የአለብን ጉዳይ ነው፡፡ወገኔ በአንድ ቀን የፈረሰ አገር የለም፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን አስቸኳይ እርምጃወች መውሰድ ግድ ይለናል

1ኛ. ቤቱ በአስቸኳይ እጣው ለወጣለቸው ኢትዮጵያውያን እንዲተላለፍ የሚዲያ ካምፔን እና ሰላማዊ ሰልፎችን እናስተባብር፡፡ ባለ ዕጣወችም ከፍተኛ ተሳትፎ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛመግለጫውን ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች መቃወምና ማውገዝ አለባቸው፡፡ምክንያቱም መግለጫው የፌደራል ስርዐቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ! ህገ መንግስቱ መሬት በህዝብና መንግስት በጋራ ባለቤትነት የተያዘ እንጂ ለተወሰነ ብሔር በባለቤትነት የተሰጠ ባለመሆኑ፡፡የአዲስ አበባም የባለቤትነት ጥያቄ በዚሁ ማዕቀፍ የሚታይ ነው፡፡በተለይ ስለ አዲስ አበባ አንቀጽ 49 የሚከተሉትን 5 ነዑስ አንቀጾች ደንግጓል፡፡

ን. አ.1. የፌደራሉ መንግስት ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ነው፡፡

ን. አ. 2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን ይኖረዋል፡፡ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል፡፡

ን. አ. 3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግስት ይሆናል፡፡

ን. አ. 5. የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት፤ወይም የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፤እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሃል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል ይላል፡፡

ታዲያ በየትኛው የህግ መሰረት ነው፡፡የፌደራሉን ርዕሰ ከተማ መንጠቅ የተፈለገው

  1. ሁሉም ተቃቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲወች መግለጫውን ማውገዝና የፌደራል ስርዐቱን የመሠረቱት አባል የክልል መንግስታት ሃላፊነታቸውን እንዲያከብሩ ጫና መፍጠር
  2. ጠ/ሚ/ር ደ/ር አብይ ጠንክረው ወጥተው አገሪቱን እንዲያድኑ፤ የአዲስ አበባን ህዝብና ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ብሄሮችን ልዩ ጥበቃ እንዲያደርጉ፤ ካልቻሉ ግን ግርዶሽ ሆነው አገር ከሚወድም እሳቸውም ወደ ስልጣን ሲመጡ እንዳሉት ስልጣናቸውን በፈቃድ ማስረከብ፤ ይህንንም እንዲያደርጉ ማህበራዊ ሚዲያ ካምፕን በውጭም በውስጥም ማካሄድ
  3. ሁሉ ነገር እየሆነ ያለው በጉልበት ስለሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ አንዱ አንዱን እንዲጠብቅ ዘመቻ፤ቅስቀሳ ማካሄድ፡፤የመከላከያና የፌደራል የጸጥታ አባላት ይህ ከመስመር የወጣ የሸኔ መንግስት እያካሄደ ያለውን አገር የማፍረስና የእርስ በርስ ጦርነት ለመቀልበስ፤ በንቃት መጠበቅ፤አሁን ያለው የፌደራል መንግስት እንደ ኦሮሚያ መንግስት ግልጽ አድሎ ካሳየ፤ቁርጥ ቀን ስለሆነ የአለቃ ትዕዛዝ ሳያስፈልግ እንደ እስፈላጊነቱና የአደጋው ደረጃ በመገምገም ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ አምላክ ኢትጵጵያዊያንን ይጠብቅ!

አሰፋ በድሉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.