አዴፓ እጅግ ፈዟል 2.0! (ተሰማ እውነቱ)

ክቡር ፕሬዚዳንት አምባቸው መኮንን ሲሳይ
መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ::
1. አዴፓ ንና ኦዴፓን ለመለያየት ህውሀት ያገኘውን ክፍተት በሙሉ በመጠቀም እየተረባረቡ ነው:: ለዚህም ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ደላላዎች በፊታውራሪነት እያገለገሉ ነው:: አዴፓ ይህን ክፍተት በንቃት መከታተልና ማምከን አለበት::ህውሀት እጅግ ብዙ ሺ ዲጂታል ወያኔዎችን ለዚህ ስራ መድቧል:: የወያኔ አማራ ቡድንና ወያኔ ኦሮሞ የፌስቡክ አርበኞች እውነተኛውን የአማራ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብን ለመለያየት ስራቸው አድርገው ይዘውታል:: የአማርኛን ቋንቋ ለአማራው ህዝብ ማጥቂያ እየተጠቀሙበት ነው:: አዴፓ እጅግ ፈዟል :: የራሱ የፌስቡክ ተመጣጣኝ ሰራዊት ማሰለፍ ይኖርበታል::
2. አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች የዶክተር ዐቢይ ኢትዮጵያዊነት እጅግ ይጎረብጣቸዋል:: አማራው ከምንጊዜም በላይ ኢትዮጵያዊነት ከሚያስቀድሙ የኦዴፓ አመራርና የኦሮሞ ህዝብ ጋር ስልታዊ መቀራረብንና ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ ነው::ከኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ በሸዋ እንደ አማራና ኦሮሞ የተቀላቀለ ህዝብ የለም::ወያኔ 27 አመታት የቆየው ይህን ሀይል ስለበታተነ ነው::አዴፓ ይህን ታሪካዊ የለውጥ እድል በመጠቀም የሸዋ አማራን እጅግ ማጠናከር የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጎላ ነው:: አዴፓ ወያኔ በከለለት አባይ ማዶ እራሱን ተከርችፎ እንዳይቀር:: አማራ የአስትዳደር ወሰን እንጂ እንደ ህዝብ ክልል የለውም::
3. ለአማራ ህዝብ ከኦሮሞና ትግራይ ህዝብ ባልተናነሰ የደቡብ የጉራጌ የ ጋሞ ከፋና ሀድያና የቤንሻንጉልና የአፋር ህዝብ እጅግ ይቀርበዋል:: አዴፓ የግኑኝነት ሰንሰለቱን ማስፋት ያስፈልገዋል::
4. በዶክተር አምባቸው አመራር አ ብ ን ከአዴፓ ጋር በጋራ የማይሰራበት ምክንያት አይታየኝም:: አማራው በአንድነት የሚቆምበት ወቅቱ ቢኖር አሁን ነው:: አዴፓ በአማራ ክልል አ ብን በመላው ኢትዮጵያ ያለውን አማራ ያደራጅ:: ድርጅት ሀይል ነው:: የተደራጀ ህዝብ አይፈናቀልም አይደፈጠጥም:;
5. ዳር ቆመው ለአማራ ህዝብ ምንም የሚረባ ነገር ያላደረጉ ተቃዋሚ የአማራ ምሁራንን ልክ አቶ ደመቀ ከወራት በፊት እንደሰበሰበው የውይይት መድረክ በመክፈት አማራው በሀገራችን አንድነት ላይ የሚኖረውን ተሳትፎ ማመቻቸት እነዚህም ወገኖች የድርጅቱ አካልና አጋዥ እንዲሆኑ ማሳተፍ ከአዴፓ ይጠበቃል::
6. የአዲስ አበባ ጉዳይ አዴፓን እንደ ኢህአዴግ እንደ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ከሁሉም በላይ እንደ አማራ ድርጅት የአዲስ አበባ ሁኔታ ይመለከተዋል: እንደሚታየው የአዴፓ በአዲስ አበባ ተወካይ ተመልካች እንጂ ተፅእኖ ፈጣሪ አይደለም:: አዴፓ እንደ አቶ ዮሀንስ ጏንጉል ያለ አመራር በቦታው ቢያስቀምጥ ተመጣጣኝ የሀይል አሰላለፍ ይኖራል::ከ12 አመታት በአዲስ አበባ በተደረገው የወያኔ የህዝብ ቆጠራ አማራ 56%  ኦሮሞ 19% ጉራጌ 16.3% ትግሬ 5.2% ስልጤ 2.9% ቀሪዎቹ .5% ናቸው:: ይህን ሀቅ መሸሽ አይቻልም::ይዋል ይደር እንጂ ዶክተር ዐቢይ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያዊነት ከአክራሪ ኦሮሞ ልሂቃን ጋር ፊት ለፊት እንደሚጋጭ የታወቀ ነው::አዴፓ የአማራ  ህዝብ ድምፅ እንዲሰማ ማስተባበር ታሪካዊ ሀላፊነት አለበት::
 
7. በኮንዶሚኒየም ዙሪያ በተነሳው መናቆር ዶክተር ዐቢይ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ የአስተዳደር ወሰን እንዲመክሩ 8 አባላትን ያካተተ ኮሚቴ አዋቅሯል:: ከነዚህም ታከለ ኡማን ጨምሮ 4 የኦሮሞ ዲሞክራቲክ 2 የደቡብ ህዝቦች 1 የአዴፓ ና 1 የህውሀት ተወካይ ተሹመዋል:: የአዲስ አበባን የአስተዳደር ወሰን የሚወስነው ኦዴፓ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶታል:: ይህ የባሰ ግጭት ፈጣሪ እንጂ የሚያስማማ አይሆንም:: የአዲስ አበባ ህዝብ 75% በላይ አማርኛ ተናጋሪ በብሄር አስተዋፅኦም ከ56 % በላይ አማራ ነው::እንዴት ይህ ህዝብ በአንድ ተወካይ ብቻ ይወሰናል? የአዴፓን መፍዘዝ ከዚህ የበለጠ ማሳያ የለም::በአዲስ አበባ ጉዳይ አዴፓ ከኦዴፓና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ፊት ለፊት በግልፅ መወያየት ይኖርበታል::
9. ከህውሀት የሚደረጉ ማንኛውንም የጦርነት ትንኮሳ ሰለባ ላለመሆን አዴፓ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል:: ጦርነቱን የሚፈልገው የትግራይ ህዝብ ሳይሆን በኢትዮጵያ በወንጀል የሚፈለጉ ኮንትሮባንዲስትና የሰብአዊ መብት የጣሱ ሰዎች ናቸው:: የፌዴራል መንግስት ጉልበት አግኝቶ እነዚህን ሰዎች ለፍርድ ሲያቀርብ የጦርነቱ ድባብም አብሮ ያከትማል::
መልካም የስራ ዘመን! አማራው ከአሁን በሗላ አንገቱን የሚደፋበት ዘመን አብቅቷል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.