ለኢትዮጲያ ና ለህዝቧ የሚበጀው ነገር   (ክፍል ፪) ከሙሉቀን ገበየው

በክፍል ፩ ፅሁፌ 27  አምታት አስክፊውን አገዛዝ በህዝቡ ሰላማዊ ትግል  መዳራሻ ላይ የአገዛዙ “የለውጥ ፈላጊ” ወገኖች የመንግስትነት መንበር መያዛቸውና፤ ማንንም በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፈውን ወይም የህዝብ ድርጅቶችን ሳይጨምሩ የሽግግሩን ሂደት እንምራልን ብለው  ለህዝቡ ትልቅ አዲስ  ስርአት እንደሚመጣ ተስፋ ሰጥተውና  የህዝብ ድጋፍ አግኝተው፤  በለውጥ ግዜ የሚደርጉ የመጀምርያ የህዝብን ብሶትና ስሜት የሚያስተነፍሱ ድርጊቶችን ቢፈጽሙም፤  ግልጽ የሆነ የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ባለመግለጻቸው (ወይም ስለ ሌላቸው) ዘላቂና መስረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንድተቸገሩ፤  የፖለቲካ ድርጅቶቻቸው የተጨማለቅ 27  አመትት ልምድና ወደ ኋላ ጉተታ፤  በተጨማሪም  ከውጭ አገር ተስባስበው በመጡ  የአዲሱን ትውልድ (ያብዛኘውን ህዝብ) የልብ ትርታ ያልተርዱና በ 60እን 70 ዎቹ  የመገዳደልና የመሽናንፍ የፖለቲካ ሴራቸውን በጎሳ ፖለቲካ ካባ አልብሰው ባሁኑ ግዜ ህዝቡንና አገራችንን እያመሱ እንድሆነ፤ “የለወጡ መሪዎችም” በነዚህ  ግለሰቦችና ድርጅቶች ውዥንብር ወስጥ ገብተው  መደረግ የነበርባቸውን ወሳኝ  ጉዳዮች፣ የከፋፍልህ ግዛው ፖሊስን መቅበርና ለ 45  አመታት በአገራችን የደርሰውን እልቂት፣ ጥፋት፣ ደም መፍሰሥ  መዝጊያ የሚሆን የይቅርታ፣ የእርቅና የህዝብ መግባብያ  መድረኮችን  በመዝንጋታቸው ወይም በማዘገይታቸው አገራችና ህዝቧ መስቀልኛ መንገድ ላይ መሆናችንን የገለጽኩ ሲሆን፤  ምንም እንኳ ለውጡ የሚጓዝበት መስምሩን  የሳተ ቢሆንም መንግዱን ለማስትካከል እድሉ አሁንም እንዳልን፤ በተልይ ሁሉም የለውጡ አካል ህዝቡንም ጨምሮ በዜግነት ላይ የተመሰረተ፣ ልዩነታችንን የሚያቻችል ስርአተ-መንግስት አስፍላጊነትንና  የሚቀነቀነውን የጎሳ ፖለቲካ አፈራሽነት የገፅኩብት ጽሁፍ ነበር።

አሁንም ቢሆን በመንግስትነት የተቀመጡ  “የለውጡ ፈላጊ” መሪዎች  በማስተዋልና ይህን ለውጥ እውን ለማድርግ የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ ነድፈው ከግብታዊ፣ ግዜ አመጣሽ አጀንዳ ላይ ከማተኮር ይልቅ በሽግግር ወቅት መደርግ ያልባቸውን ወሳኝ ውሳኔዎችን ላይ ቢያትኩሩ እንምክራለን። ህዝቡ እፍ እንትፍ ካለው አገዛዝ ስርአት ውስጥ የመጡ መሆናቸውን ሳይዘነጉ፣ ህዝቡ  ሳይመርጣጫቸው ነገር ገን በሰጡት የተስፋ ቃል ብቻ ድጋፍ የሰጣቸው መሆኑን ተገንዝበው  ዋና ተግባርቸው ህዝባችንን ሲያተራምሰን የኖረውን የከፋፍልህ ግዛ ፖሊሲን አፍርሰው በዜግነት ላይ ያተኮረ ኢትዮጵያዊ ድባብን እንዲሁም ወሳኙን የይቅርታ፣ የእርቅ እና የህዝብ መገባቢያ ስራዎች ላይ ማተኮር አለባቸው። እንዚህን ወሳኝ ስራዎች ሲፈጸሙ፣ሌሎች እንዚህን ሊከተሉ የሚችሉ አገርዊ ለውጦችን ለማስፈጸም  ቀላልና አመቺ ያድርጋሉ።

የተበደለ፣ ያዝነ፣ ቂም የያዘ ወገንና ህዝብ ከገዳዩ፣ አሳሪው ፣አሳዳጁ ጋ ተስማምቶ የሚኖርው፡ በዳዩ ይቅርታ ሲጠይቅና ከልብ ሲፀፀት፤ ፍርድም ቢደርገ ውሳኔውን ለመቀበል ሲዘጋጅ፤ ተበዳዩም በልቡ ያደረውን ቂምና የሃዘን የጨለማ ስሜት በይቅርታ ማድርግ ሲስርዘው፤ ትልቅ ሰው መሆኑና ሃዘኑንም መቅበሩን ፣ወድኋላም የማይመልስበት መሆኑን፣ ባዲስ ስሜትና መንፍስ በዳዩን ወንድሙን ይቅር ብሎ በመንፍስ-ልእልና በዳይም ተበዳይም አብረው ለመኖር ያስችላቸዋል።  ይህን ታላቅ ስራ ከፈፀምን  ቦሓላ ባልኖርንባቸው 100- 400 አመታት ተፈፀሙ ለተባሉት የታሪክ ክስተቶች  በፕሮፕጋንዳ ተከሽኖና ተጋኖ ለለፉት 45 አመታት የቀረብልንን የታሪክ ረብሻ በቀላሉ ዘግተን የወደፊቷን ልጆቻችን የሚኖሩባትን እንዲሁም እኛም የምንኖርባትን አዲስ ስርአት ለመምስርት በቀላሉ  ያስችለናል።

የለውጡ መሪዎች በተለይም በመንግስት መንበር ላይ ያላችሁት ዋና ትኩርት መሆን የሚገባው ይህ ነው ። በህዝብ እንድተመረጠ መንግስት አይነት  የሃሰት ስሜት እይተሰማችሁ፣ የሽግግር ግዜ መሆኑን በመዘንጋት ሌላ ራእይ መቃዥት ውስጥ መግባት እንደ ገና ወደ ማንፈልገው ምናልባትም ከበፊቱ ወደ ባሰ የዘር ፖለቲካና የእርስ በርስ ግጭት፣ ሃገር መብታተን ደርጃ ሊያመራን ይችላል።

እናንተም ሰከን ስትሉ የሚደግፋችሁም ደግሞም አማራጭ አጥቶ የሚከተላችሁን ህዝብ ሰክን ሲል፣  መንግዶቹ ሁሉ ይጠራሉ። ቡና ሳይሰክን፣ የተበጠበጠ ጠላም  ሳይረጋ ቢጠጣ እንድማይጥም ሁሉ የችኩል፣ ትኩሳት ማራገቢያ፣ ግብታዊ እርምጃም የትም አያደርስም።

በአገራችን ሰላም ሳይሰፍንና እርቅ ሳይነግስ በኢትዮጲያዊነታችን ሰው መሆናችንን  አወቀን፣ ተርጋግተን ማስብ ሳንችል፤ በሩጫ በዲሞክራሲ ስም ምርጫ ማድርግ ማለት ለሌላ ጥፋት መዘጋጀት ነው። አስፍስፈው፣ ከኔ በላይ ለህዝቤ ተቆርቋሪ የለም የሚሉ በተወሰኑ  ስግብግብ የስልጣንና የሃብት እንዲሁም የታሪክ ሽሚያ በሚፈልጉ የፖልቲካ ፓርቲ ግለሰብ መሪዎች  የጥላቻ፣ የመከፋፈል፣ የዘረኝነት፣ የቂም በቀል፣ የታሪክ ቁርሾ እና ይህ መሬት ለኛ ይገባናል በሚሉ የምርጫ ግዜ መፈክሮች እንዲድናግር እድል መስጠትና በህዝቡ ላይ ታልቅ ሴራ ና ስህተት መጫን ይሆናል።

እርቅና ሰላም ከመጣ ቦሗላ እስካሁን ሲከፋፍለን የነበርውን በወያኔ የሚመራው የኢሕአዲግ  መንግስት ኢትዮጲያውያንን አዳክሞ፣ ለረዥም ግዜ ለመግዛት፣  በላይችን ላይ የጫነውን፣ ወደፊት ሊበጠብጥን የሚችለውን ህገ-መንግስቱን እንመርምርዋለን።  ብንፈልግ አዲስ ህገ-መንግስት ሁሉም ህዝብ የተሳተፈበት የተሻለ ህግ-መንግስት እናረቃለን ወይም ካለው ህገ-መንግስት ወስጥ የሚርብሽንን አስወገደን የሚጠቅመውን ይዝን አዲስ የሚያስማምንን ጨምርን ሰላማዊ አገር እንመስርታለን።  በወያኔው ህግ-መንግስት ካልተዳኘን ከሚል ችገር ያድነናል። ይህንን ሳንደርግ ብንቀር ደግሞ በ ህግ ይዳኘን ወይም  ህግ እናክብር ስም  በተባላሸው የወያኔ ህግ መዳኝት ይሆንና ከፋፋይ ችገር ውስጥ እንገባለን። ህግ-መንግስቱ ለወያኔ ስርአት ብቻ እንዲጠቅም እንጂ ኢትዮጲያውያንን  በእኩልነት፣ በሰላም ዲሞክራሳዊ መንግስት ጥል ስር እንዲኖሩ ተብሎ አስቀድሞ የተዘጋጀ አይደለም። አዲስ ወይን ባርጀ፣ባፈጀ በተቀደድ አቆማዳ አይቀመጥም።

ሃልፊነት የሚሰማው ኢትዪጲያዊ ወገን ወይም የህዝብ ፍቅር  ያለው የፖለቲካ ድርጅት እንዲሁም የመገናኛ  አውትሮች (Mass Media and Social media) እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ የመብት አስክባሪ፣ አስተማሪ ድርጅቶችንም ጨምሮ የለውጡ መሪዎች ህዝቡ ጋ ወርደው በደንብ አስተምረን፣ በጎሳ ላይ የሚመስርት ፖለቲካ ስርአት አግላይና  ፡”አንርሱና እኛን” የሚከተል  ከፋፋይ  የፖለቲካ ብልሹ  አደርጃጀት መሆኑን አውቀን  በህግ ማገድ ይገባናል። በሃይማኖት፣ በጾታ፣ በእድሜ  በመሳሰሉት ልዩነቶች የፖለቲካ ፓርቲ እንዳልተፈቀደ አውቀን የጎሳ ፖለቲካ ድርጅትን ማስቀረት አለብን።

እርግጥ ነው አገራችን የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል፣ ወግ፣ አኗኗር  ና እሴት ያሉባት ሀብታም የሆነች አገር ናት። ይህ ወብታችንና አና  ውርሳችን ነው እንጂ መሆን ያለበት  የመለያየትና የመራራቅ፣ የመክፋፈል ምንጭ መሆን የለበትም። እንዚህ ልዩንታችን ለአገዛዝ እንዲያመቹ፣ማሰሪያና፣ ማስፈራሪያ መሆን የለባቸውም። እነዚህን ውርሶቻችንን የሚያሳድግ፣የሚጠብቅ የመንግስት መዋቅር በሚንስቴር ደርጃ ብናዋቅርና የኢትዪጲያውንን እህትማማችና ወንድማምች ህዝብ መሆናችን መግልጫ ይሆናል እንጂ ድንበር መወሰኛ፣ ክልል ማበጃ የልዩነታችን መጋርጃ አድርገን ለ አስከፊ አገዛዝ መሳርያ እንዳይሆን አበከረን መከልከል  አለብን።

ይህንን ማድርገ ስንችል፤ ወያኔው ወስኖ ለአገዛዙ እንዲያመቸው ብሎ ያስቀመጠውን የክልል ወስን በቀላሉ በማፈርስ፤   ለእድገት ሀዝብ-ለህዝብ ለማቀራረብ የሚያመችንን፣ ኑሮችንን በተሻለ ለሚለውጥልን  አዲስ የፊዴራል ክልል (states)  መንግስቶችን በመምስርት ስልጣን ህዝቡ አጠገብ ማድርግ አይሳነነም።

በዜግነት የተmeሰረተ ስርአተ-መንግስት ስንምስርት እንደ ኢትዮጲያ ላለ ታሪካዊ አገር በህዝብ የተመረጠ ፕሬዝዳንታዊ  መንግስት ብንመርጥ በተሻለ ሁኔታ አገሩን የሚመራውን መሪ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ የመምርጥ እድል ስለሚኖርው  ህዝቡ ለዲሞክራሲያዊ ሂደት ቀርቤታ እንዳላው በማመን መልካም ስሜት ይፈጥራል።  አንድ የጎሳ ፖለቲካ መሪ እንዴት ተብሎ ለኢትዪጵያዋይን ሁሉ እኩል መሪ ሊሁን ይችላል?  ማንም ኢትዮጲያዊ  በችሎታውና በሚያቀርበው የተሻለ የሃገር አስተዳድር ፖሊሲና ዝግጅት ከየትም ጎሳ ቢመጣ  በህዝብ ቀጠታ በመመርጥ አገር ሊያስተዳደር የሚያስችል እድል ይፈጠራል።

ምንም እንኳ ማእክላዊ (ፌድራል) መንግስት መቀምጫ ከተማ ቢኖረውም ወደፊት በምንምስረትው መንግስት ሌሎች ከተሞች እንዲምስረቱና፤ የተምሰርቱትም እንዲያድጉ ከፍተኛ ጥርት መደርገ ያልበት ሲሆን ሁሉም ነገር ወደ ዋና ከተማው መድርግ የለበትም።  ይህ ሌሎችን ከተሞች እድገት ያቀጫጫል፣ ድግሞም እድገትን ወደ ሌሎች ያገርችን ክፍሎች አንዳናድርግ እንቅፋት ይሆናል። የተመጣጠን እድግት ሲኖር የህዝብ ፍልሰት ራሱ መልክ ይይዝና አላስፈላጊ ውጥርቶችን እጅጉ ይቀንሰዋል። የማእክላዊ (ፌድራሉ) መንግስት የተለያዩ የሚንስቴር መስሪያ ቤቶችን በተላያዩ ከተሞቻችን  ማድርግ ይችላላል። ዘመናው ቴክኖሎጅ በመጠቀም ስራን በቀላሉ ማቀላጠፍ ስለሚቻል ሁሉን ነገር ባንድ ቦታ መከምር አያስፈለግም። ይህም የፌድራል መንግስቱን በሁሉም ኢትዮጲያን ሰፈር ቅርብ ያደገዋል።

እያንዳንዱ  ያስተዳድር ክፍለ-ሃገር (Federal region) እና  ትላልቅ ከተሞች  በህዝብ በተመርጡ የአስተዳድሩ ነዋሪዎች እንዲመራ ማደርግ ተገቢ ይሆናል። የፌድራል መንግስቱ ( states) የሚመሩ መሪዊችን (Governor) አና ከተሞችን የሚያስተዳድሩ   ከንቲባዎች  (Mayor) በቀጥታ በህዝቡ ቢመርጥ የትሻለ ይሆናል። ይህም ህዝቡ በቀጥታ የፖለቲካ አስተዳድር ምርጫ  ሂደት ላይ  የተሳታፊነት (ዲሞክራሲይዊ ሂደት) ያደርገውል።

 

ክፍል ፫ ይቀጥላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.