ለአቶ አድማሱ ዳምጠው የኦሮሚያ መንግስተ ቃል አቀባይ! ወዴት ወዴት! (ሰርፀ ደስታ)

በመጀመሪያ ቁመሩን አቁሙት፡፡ ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚል ዘመቻ ተከፍቶብናል እይላችሁ ራሳችሁ እየጻፋችሁ ከኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ ልትደበቁ ትሞክራላችሁ፡፡ ኦሮሞን አገር ከገነቡና ከመሩ አባቶች ታሪክ አውጥታችሁ የራሳችሁ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ ባሪያ ለማድረግ ብዙ ሰርታችኋል በብዙ መልኩም ተሳክቶላችኋል፡፡ አገር መምራት ደለም የተበታተነችን አገር እንድ አድርጎ መገንባት የቻሉትን አባቶች ኢትዮጵያ ትዘክራለች፡፡ አቶ አድማሱ ዛሬ የኦሮሞን ሕዝብ ማስፈራሪያ ያደረጋችሁት የሚኒሊክን ታሪክ ባነሳብዎትስ፡፡ 80 በመቶ የሚኒሊክን መንግሰት ሲመራ የነበረው ማን ነበር? የአንጎለላው ተወላጅ ሚኒሊክ ማንም ይሁን የአንጎለላው ገበየሁ ጎራ ማን ነበር? የሜታው ሀብተጊዮረጊስ ዲነግዴ (አባ መላ) ማን ነበር? ኢያሱስ ኃይለ ስላሴስ ማን ነበሩ? መቼም እነዚህ ሁሉ ጎጃሜና ጎንደሬ ናቸው ብለው ለጊዜው ሊከራከሩ አይችሉም፡፡ ትንሽ ቀይቶ ግን በጥላቻና ዘረኝነት ያደገው ይሄን ከማለት አይመለስም፡፡ ጎበና ዳጬ ኦሮሞ አደለም የሚል ዘመቻ ተከፍቶ አይቻለሁና፡፡ ለጊዜው ጎበና ከሚኒሊክ ባልተናነሰ በኦሮሞ የዘርና ጥላቻ ፖለቲካ ስለሚጠሉ አላነሳብዎትም፡፡ እንዳይደነግጡ፡፡ የጀግኖቹ መንፈስ ዛሬም ከመቶ ምናምን ዓመት በኋላ ጥላቻና ዘረኝነት ያመከነውን ትውልድ ያስደነግጠዋልና፡፡ አዎ ግን በኦሮሞነት ከኦሮሞ መንደሮች ውጭ ማለፍ ስለማይቻል በዘረኝነትና ጥላቻ ማንም አገር አደለም ሰፈሩንም አይመራም፡፡

ስለ ዘር ከጠየቁኝ ደግሞ እኔ ስለ ዘር በብዙ እጥፍ ከእርሶ የተሻለ ግንዘቤው እንዳለኝ እነግርዎታለሁ፡፡ የታወቅሁ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ነኝ እያለ እንዳቅራረው ወሮበላ አደለም፡፡ ይህ ታዋቂ የፖለቲካ ምሁር ነኝ የሚለውና ከሳን ፎርድ ተመርቂያለሁ የሚለውን ግለሰብ ከዚህ በፊት ሳሙኤል ዘሚካኤልን ሆኖ ሲከውን የነበረውን ሰው አይነት እንደሆነ ብዙ ጊዜ ተናግሬያለሁ፡፡ ሰርቲፊኬት አቅርብ ብለን እንሞግትም ሰታን ፎርድ በመቼ ዓመት ገብቶ እንደነበር ካወቅን ችግር የለውም በጥቂት ደቂቃ ውስጥ እናጣራለን፡፡ እስኪ ግን  ኦሮሞስ ማን ነው? አማርስ ማን ነው? ትግሬስ አፋርስ ሱማሌሰ ማን ነው? የእርግማን ልጆች በቅለው አገር እስከሚያረክሱ ድረስ ኢትዮጵያውያን ማን ናቸው? በጅምላ ብዙዎች እንደሚደበላልቁት መጀመሪያ ሰው ነኝ እንደሰው ላሰብ ብቻ አልልም፡፡ ምድር ላይ የተለየ ዘር ያለው የዓለምን ዘሮች ሁሉ በደሙ የያዘ ሕዝብ አካል እንደሆንን እኔ አውቃለሁ፡፡ ከሙያዬም ጋር ስለሚያያዝ ይሄን ማወቅ ለእኔ የተለየ ነገር አይሆንምና፡፡ ከታች ይመልከቱት፡፡ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ትግሬ፣ አማራ፣ ዙማሌ የሚሉትን መርጠው የምስሉን ቀለሞች የመልከቱት፡፡  ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት በሰፊው ስላብራረሁ ፈልገው ያንብቡ፡፡ ኢትዮጵያና አካባቢዋ የዚህ ዘር መኖሪያ ምድር ነው፡፡ ሶስት ነገዶች በወናነት በይፋ አንደ ሆነው የተቀላቀሉበት፡፡ በአለም ትልቁ የጄኔቲክ ብዝሀነት የሚታዩበት፡፡ የሚገርመው ከሌላው አፍሪካ እንኳን በግልፅ የሚቀርቡበት (ለናጄሪያዊው ከኦሮሞው፣ ይልቅ ኢንግሊዛዊው ሊቀርበው ይችላል፣ ኦሮሞው ግን ከናይጄሪያ ይልቅ ለፈረንሳዩ በጣም ቅርብ ነው)፡፡ የአሊ ቢራ ማልቱ አዳን ኑባሴን ለአንባቢዎቼ ብጋብዝ እወዳለሁ፡፡ ይህ ዘፈን ብዙ ቅኔ ያለበት ነው፡፡ በዘረኞች ዘመን ጠቦ በኦሮሞነት ቢዘፈንም ጉዳዩ ኦሮሞን ብቻውን የሚመስል አደለም፡፡ ኦቦሉዋን ሰዲ የተባሉትን የሶስቱን ግዙፍ ነገዶች በምስሉ ተመልከቱ፡፡ የውሀ ሰማያዊው( ጥንታዊው ሌቫንት፣ ቢጫው፣ የእኛው አሪ፣ ወይን ጠጁ ምን አልባትም አገው ወይም ሌላ ጥንታዊ በዚህ ምድር የኖረ ነገድ)፡፡ አሊ ቢራን (ኦሪጂናሉን) ለዘር ፖለቲካ ከመዋሉ በፊት በፊት

http://oromp3.com/index.php?a=track&id=260&name=ali-birra-guitar-maaltu-addaan-nu-baase

ወደተ ተነሳሁበት ጭብጥ ልመልስዎት፡፡ እየሆነ ያለውን አደባባይ የወጣን እውነት ለማስተባበል ከመሞከርና የበለጠ ችግርን ከመፍጠር ቆም ብሎ አስቦ ችግሮችን መፍታት ብልህነት ነበር፡፡  ችግሮችን ለመፍታት ፍላጎት አለመኖሩ ብቻም ሳይሆን ሰዎች የሚናገሯቸውን እውነታዎች በማስተባበል እንወጣዋልን ከጅምሩ የተነሳንበትን አገርንና ሕዝብን ማፈራረሳችንን እንቀጥላለን አንድ ቀን ይሳካልናል አይነት ነገር ይመስላል፡፡  ለመሆኑ የኦሮሞ ፖለቲካ እርሶ በአረዳድ ልክ ነው? እስኪ ለማ በባለፈው ለውጥ ወቅት ትንሽ ፍንጭ የምትመስል ኢትዮጵያዊነትን ከአነሳበት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውጭ የኦሮሞ ፖለቲካ የዘርና ጥላቻ ፕሮፓጋንዳን እንደ ልዩ ስልት የሚጠቀም አደለም? ዛሬ የኦሮሞን ፖለቲከኛ ሌላውን ከአልጠላ ጸረ-ኢትዮጵያ ከአልሆነ ሺ ጊዜ አመክነዮዋዊ (ሎጂካል) ቢሆን በትውልዱም ኦሮሞ ቢሆን የሚቀበለው ኦሮሞ ስንት ነው? ዛሬ በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ አሸናፊ ለመሆን የዘርና ጥለቻ ቀመም ካልጨመሩበት አይሆንም ብላችሁ አደለ እንዴ የኦነግን ፖሊሲ ቀምታችሁ የምትሰሩበት? 27 ዓመት ኦሮሞ ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ እንዲወጣና ከታሪክና ከማንነቱ እንዲጣላ አድርጋችሁ ስትሰሩበት ኖራችሁ፡፡ በዚህ ብዙ ትውልድ በዘርና ጥላቻ የበከላችሁም ቢሆን አሁንም ያልተሸነፈላችሁ ብዙ እንዳለ ስላወቃችሁ ዛሬም ቀሪውን ሕዝብ ወደምትፈልጉት የጥላቻና ዘረኝነት ክምችታችሁ ለማስገባት እየሰራችሁ እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው፡፡

አቶ አዲሱ ለመሆኑ ይሄ መልዕክትዎ ምንድነው? በክልሉ ሕዝብና መንግስት የተከፈተው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሊቆም ይገባል፡፡ ሲጀምር ሕዝብ ውስጥ አይደበቁ፡፡ ችግሩ ያለው ሕዝብ ውስጥ አደለም፡፡ የፖለቲካ መሪዎችና ሕዝብን የሚያነሳሱ አሸባሪ ወሮበሎች እንጂ፡፡ ስለዚህ አሁንም መንግስትና ሕዝብ እያሉ መንግስት ነኝ ከሚለው የፒዲኦ/ኦነግ ሴራ ጋር ኦሮሞን ሁሉ ደምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተገከፈት ዘመቻ አስመስለው ለማቅረብ አይሞክሩ፡፡ የሚታየው ግልጽ ነው፡፡ አዎ ብዙ የኦሮሞ ሕዝብ በዘርና ጥላቻ ፖለቲካችሁ ተበክሏል፡፡ የዛን ያሀል ደግሞ የነበረ የሕዝብ አብሮነት ለመመለስ የሚጥሩ አያሌ የኦሮሞ ሕዝብ ልጆች አሉ፡፡ ያም ሆኖ ማንም ሰው ከሕዝብ ጋር ጸብ የለውም፡፡ እየተነሳ ያለው ጉዳይ ሆሉ ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር እያያዛችሁ ሕዝቡን መደበቂያ ያደረጋችሁት እናነት ናችሁ እንጂ፡፡  ግልጽ የሆነው ነገር በኦሮሞ ፖለቲከኞችና የዘርና ጥላቻ አራማጆች ላይ አሁን እየከረረ የመጣ ዘመቻ አለ፡፡ ይሄ ደግሞ ከብዙ ትግስት በኋላ የመጣ መማረር ነው፡፡

በየቦታው የሽብርና አመጽ ቀስቃሾችን ሕዝቡን በጥላቻና ዘረኝነት እንዲያነሳሱ ሆን ተብሎ ሁኔታዎችን አመቻችታችሁ ዛሬ የዚህ ሥራችሁ ወጤት ሲገለጥ ጭራሽ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል አይነት ዘመቻ ተከፈተብን ማለታችሁ ሳያንስ በሕዝባችን ላይ በሚል ሕዝብ ውስጥ መደበቅ መሞከራችሁ ቀጥሎም ላለመታረም መወሰናችሁ ነው፡፡ ገጀራ ተይዞ ሊያውም ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ሲፎከር፣ በጠራራ ጸሀይ የድሆች ቤት በግሬደር ሲፈርስ፣ በጠራራ ጸሀይ እኛ ከአለፈቀድን አዲስ አበባ ኮንደሚኒየም አይታደልም፣ በሚሊየን የተጠጋ ሕዝብ እናንተ በፈጠራችሁት የዘርና ጥላቻ ፖለቲካ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ በረሀብና በሽታ እያለቀ የሚታየው እውነት ገዝፎ በሕዝብ ዘንድ ከእናነተ ጋር ተያይዞ መወራቱ ነው ተከፈተብን የትሉት ዘመቻ? ይሄም ሆን ጉዳዩን ከሕዝብ ጋር ያያዘው ከአለ ያለመብሰል ሊሆን ይችላል፡፡ በግልፅ እየተነገረ ያለው የፒዲኦ/ኦነግ ቡድን አገርና ሕዝብን እያመሰ ነው ነው፡፡ ሕዝብ ውስጥ አይደበቁ፡፡ በዚህ ዘመቻ ባሉት ውስጥ ይሄን እያሉ አከሉት ብዙ ኦሮሞዎችም አሉና!  እስኪ ልጠይቅዎት ይሄ የሚታየው ሁሉ እየሆነ ያለው የሌላ ማህበረሰብ አቀንቃኝ ፖለቲከኞች ምክነያት በተፈጠረ ችግር ቢሆን ምን ትሉ ነበር?

ሰሞኑን በለገጣፎ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ሰዎች መልስ ሲሰጡ የነበሩት የከተማዋን ከንቲባ ታዝበናል፡፡ በጥላቻና ዘረኝነት ፍትሀዊ ውሳኔ ሊኖር አይችልም፡፡ በግልጽ በባለስልጣናቱ ንግግር የሚሰመው የጥላቻና ዘረኝነት ስሜት ነበር፡፡ አሁን አሁን ብዙውን ሰው ሌላ ጥያቄ እንዲያነሳ የጋበዘው ግን የሱሉልታም፣ የለገጣፎም ከንቲባ ተብለው የተመደቡት ፈጽሞ ለዚያ አካባቢ ማሕበረሰብ ባሕህል እንኳን  የማይውክሉ እንደሆኑ ስናይ ነው፡፡ ግልጽ ነው ሸዋ ለኦዴፓ/ኦነግ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ ስላለተመቸ ከሀላፊነት ማግለል ብቻም ሳይሆን ከጅምሩ የዳጬ ዘር በሚል ልዩ ፍረጃ ከኦሮሞነትም እንዲገለል ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን በዶ/ር አለሙ ስሜ ላይ የተከፈተው ዘመቻ የዚሁ አካል አንዱ መሆኑ ስናወቅ ነገሩ አሁንም ኦዴፓ/ኦነግ ምን ያህል ሸዋን እንደሚፈራው ታዝበናል፡፡ ግን ስለ አለሙ ስሜ ዘመቻ ለምን ዝም አሉ? ይህ ማለት ሸዋ አንድም ኦዴፓ/ኦነግ ውስጥ የለም ማለት አደለም፡፡ የኦዴፓ/ኦነግ የጥላቻና ዘረኝነት አራማጅ እስከሆነ ድረስ ችግር የለም፡፡ሸዋ የዳጬ ዘር የሚሆነው የአባቶቹን ታሪክ አስቦ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን አልለቅም ባይ ከሆነ ነው፡፡ ሁሉም የሰፈሩ አስተዳዳሪ በሆነበት ዘመን የሸዋ ከተሞች ከሩቅ በመቱ ለአገሩም ለሕዝቡም ባይተዋር በሆኑ ከንቲቦች ይመራሉ፡፡ ግን ገጀራ ይዘው ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ሲፎክሩ የነበሩባት ከተማ በማን ነው የምትተዳደረው፡፡ ከለገጣፎና ሱልልታ ከንቲባዎችስ ጋር ምን ግንኙነት አላቸው? ሕዝብን በሜጫ አንገቱን እላለሁ እያለ ሲፎክር የነበረው ወሮበላ አሸባሪ በማን እርዳታ ነበር በየቦታው እየሄደ ሕዝብን ሲቀሰቅስና ሲያደራጅ የነበረው? ከጁኔዲ ሳዶ ጀምሮ የነበረ ጥንስስ አደለም? ለነገሩ ከጁኔዲን ሳዶ ሳይሆን የሚጀምረው በጣም የቆየ ነው፡፡ ይችን ታሪክ ግን እነሱም ትንፍሽ አይሏትም፡፡ አብዛኛው ኦሮሞም አይገባውም!  እነዚህ ከንቲባ ተብለው በለገጣፎና ሱሉልታ የተሰየሙ ግለሰቦች ተወልደው በአደጉበት ቦታ ያለውን ፖለቲካ የሚረዱ አሉ፡፡ እየሆነ ያለው ትልቅ የሴኩሪቲ ስጋት እንደሆነ ሳላስታውስ አላልፍም፡፡ ሁሉም ሰው ግን ሊረዳው የሚገባው እነዚህ ሰዎች ሙስሊም ስለሆኑ አደለም ችግሩ የሚታወቅ ከውጭ ጠላቶች ጋር የተሳሰረ ሰንሰለት መኖሩ ነው እንጂ፡፡   ስለዚህ ጉዳይ ግን ከዚህ በላይ ማውረት አልፈልግም፡፡  አሁንም ግን እየተናገርን ቀጥሎ ሲሆን ስናይ እጅግ ያሳዝናል፡፡ አሁን እየሆነ ያለውን ለማስቀረት ቀድመን በግልጽ ተናግረን ነበር፡፡ ግን ማን ይሰማል?

ሰሞኑን የጌደኦ ሕዝብ መፈናቀል ጉዳይ ከሚያስመርሩ እይታዎች ነው፡፡ በእርግጥ ድምጽ ያላቸው ሰዎች ችግራቸው በጊዜ ይታወቃል፡፡ የለገጣፎዋ ከንቲባ እንዳለቸው የለገጣፎ ቤት የፈረሰባቸው ቢያንስ የሚያይ አካል ስላለ ነው፡፡ ማንም የሚታዘብ ባይኖር ምን ሊሆን እንደሚችል የጌዲኦው እውነት ምስክር ነው፡፡ ግን አሁም ይሄ ነገር ጌዲኦ ብቻ ነው ወይ የሚለው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው፡፡ ጋምቤላ፣ ሌላ ብዙ የሚናገርላቸው የሌሉ ሕዝቦችስ? በየቀኑ የጥጋበኛ ሽብር እየሰማን ሚስኪኖች በየቦታው ምን እየደረሰባቸው እንደሆነ ቆም ብለን እናስተውል፡፡ የዴቻ ቡድን ነኝ የሚል ሌላ የጥላቻና ዘረኝነት ቡድን ሰሞኑን በአዋሳ ሲደነፋ ነበር፡፡  አንዱ በጥጋብ የሌላውን ንብረትና ሐብት ለመዝረፍና ለማጥፋት ይደነፋል ሌላው በረሀብ ያልቃል፡፡ የጌዲኦ ጉዳይ በአንድ ወቅት ለማና ደመቀ ጎብኝተውት ነበር፡፡ ግን ምን አደረጉ የሚለው ነው አሁን ጥያቄው፡፡ አሁንም ሌሎች ዜናውን ባያወጡት ሰዎች ማለቃቸው የቀጥል ነበር? አብይ ዛሬ ቦታወ ላይ ሄዶ አይቷል፡፡ ጥሩ ግን እሰከዛሬ ምንም መረጃው የለኝም ሊል ይችላል? አሁንም ለሕሊና ፍርድ ያመች ዘንድ አለገምትም፡፡ በአጠቃላይ ግን መንግስት እንደመንግስት ከአልሰራ አገርና ሕዝብ ከዚህም የከፋ ችግር እንደሚገትመው እንታዘባለን፡፡ ወሮበሎችና አሸባሪዎች የሌሎች ንብረትነ ሀብት ለመቀማት እንደፈለጋቸው በአገሪቱ ያናጥራሉ ሕዝብና አገር እንዳይረጋጋ በየቦታው ሴራቸውን የዘራሉ፡፡ ዞረው መንግስት ሆነው ዘመቻ ተከፈተብን ይላሉ፡፡ ለዚህ ሁሉ የኦሮሞ ፖለቲካ ምክነያት አልሆነም ብሎ ማስተባበል ይቻላል? በመጨረሻም አቶ አድማሱ ዳምጠው በሕዝብና አገር ላይ የተነሳውን ኦዴፓ/ኦነግ ሴራ ማጋለጥ ግድ ነው፡፡ ኦዴፓ ውስጥ ይበልጠው ጸረ-ህዝብና አገር የሆነው ኦነግ እንደተሰገሰገበት ግልጽ እናያለን፡፡ ይሄን ለማስተባበል ከመሞከር ረስን ማጽዳት ነው፡፡ ዛሬ ኦዴፓ ውስጥ ከኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊነት ወገን የሆኑ ችግር ውስጥ እንደሆኑም እንታዘባለን፡፡

በመጨረሻም ስለ አዲስ አበባ ጉዳይ አሁንም ላነሳ ፈለግሁ፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል አደለችም፡፡ ኦሮሚያ የሚባለው ክክል ራሱ በሕግ መሠረት መፍረስ ያለበት ጸረ-ሕዝብ የሆነ አንቀጽ አስፍሮ ራሱን መስተዳደር ያደረገ ክልል ነው፡፡  አዲስ አበባ የሸዋና የኢትዮጰያ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ አልፎም የመናገሻ አውራጃም ነበረች! ምንክነያቱም ሸዋም፣ መናገሻ አውራጃም፣ ኢትዮጵያም የኢትዮጵያውያን ነበሩና፡፡ ወደፊት ሸዋ ተመልሶ ራሱን የቻለ አስተዳደር ሲሆን በእርግጥም አዲስ አበባ የሸዋ መዲና ትሆናለች፡፡  አዲስ አበባ በሕግም በተፈጥሮም የሚኖሩባት ሕዝብ ከተማ ነች፡፡ ኦሮሚያ ደግሞ የኦሮሞ ብቻ ክልል ነው ተብሎ የተወጀበት ክልልነው፡፡ ይሄን የምለው እኔ አደሁም የክልሉ ሕገ-መንግስት እንጂ፡፡ ለዛም ነው በይፋ ማንም እንደፈለገ ይሄ ቦታ የኦሮሞ ነው እያለ የሚደነፋው፡፡ የዛሬው ኦሮሚያ የሚባለው የጸረ-ኢትዮጵያውያን አንቀጽ ተጠቅሶበት የተሰራው ክልል ግን ዋና ከተማ ልትሆን አትችልም፡፡ ሁሉም የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚስማሙበት ኦሮሚያ የኦሮሞ ነው በሚል ነው፡፡ ስለዚህ ጂግጂጋም የሱማሌ ነው፡፡ አብዲ ኢሌ በክልሉ ሕገ-መንግስት መሠረት ኦሮሞን ከጂግጂፋ ማሰውጣት መብቱ ነበር፡፡ ሰሞኑን ስለአንቀጽ 39 የሚዘፍኑ የኦሮሞ ፖለቲካ አክቲቪስቶችን ተዝቤያለሁ፡፡ ዛሬ እንደ 1983 እባካችሁ የሚል ያለ መስሏቸው እንደሆንም አላውቅም፡፡ ማንም መገንጠል የፈለገ ይሞክረው፡፡

ስለ ኦሮሞ ፖለቲካ ብዙ ጽፌያለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ እውነቶችን ለማስተዋል ይረዱ ዘንድ በሰፊው ለማሳይት ሞክሬያለሁ፡፡ ብዙ ጊዜም አንዴት መስተዋል እንዳልቻልን ሳሰብ እያዘንኩ፡፡ ለማ እንደብልጭታ በአንቀሳቀሰው የኦሮሞ ኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ ብዙ ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ ወጤቱም ግልጽ ነበር፡፡ በኢትዮጵያዊነት ከሆነ ማንም የሚያቆመው እንደሌለ፡፡ ነገሩ ግን ብዙም ሳይቆይ በጸረ-ኢትዮጵያ ኦነጋወያን ተጥልፎ አሁን ያለበት ላይ እናየዋለን፡፡ ብዙ በሕዝብ ዘንድ ትልቅ ክብርና ስም ያላቸው ድንገት አጋጣሚን ጠብቀው ውስጣቸው ያመቁትን ዘረኝነትና ጥላቻ ሲያፈነዱት ታዝበናል፡፡ በቀለ ገርባን ለጎንደር ሕዝብ ተወካይነት እንዲወዳደር የጠቆምኩበት ጊዜ ነበር፡፡ ነገሩ በሬ ሞኙ ሆኖ ሳይው ራሴን አሳፍሮኛል፡፡ ሰሞኑን ተጨማሪ  አውቃቸዋለሁ የምላቸውን  ለመታዘብ ያበቁኝን ክስተቶች አይቻለሁ፡፡  ይህ ማለት ግን አሁም ብዙዎች በጸረ-ኢትዮጵያውያን የተመረዘውን የኦሮሞ ፖለቲካ እየታገሉት ያሉ እንዳሉም አውቃለሁ፡፡  ይበልጠውን ነገሮች አሁን እየጠሩ መጥተዋል፡፡ አቶ አድማሱ ዳምጠውና ቡድናቸው ከዚህ በኋላ በማለባበስ የሚያልፋቸው እንደሌለ ተረድተው ከሚሆነው አስተሳሰብ ቢቀላቀሉና ገጽታቸውን የሚቀይር መልካም ነገር ቢሰሩ እንላለን:: የዘረኝነትና ጥላቻ ፖለቲካን ግን በመሸፋፈን ብዙ እንፋበታለትን ተብሎ ታስቦ ከሆነ ቆይተን እናዋልን ውጤቱን፡፡

 

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!አሜን!

ሰርፀ ደስታ

1 COMMENT

  1. Habeshas know no shame when they audaciously exhibit their hypocrisy! One has to say that in the open! See here, ሰርፀ ደስታ declares “አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል አደለችም፡፡ ኦሮሚያ የሚባለው ክክል ራሱ በሕግ መሠረት መፍረስ ያለበት ጸረ-ሕዝብ የሆነ አንቀጽ አስፍሮ ራሱን መስተዳደር ያደረገ ክልል ነው፡፡” and states with the same breath, “አዲስ አበባ የሸዋና የኢትዮጰያ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ አልፎም የመናገሻ አውራጃም ነበረች! ምንክነያቱም ሸዋም፣ መናገሻ አውራጃም፣ ኢትዮጵያም የኢትዮጵያውያን ነበሩና፡፡”
    In simple terms, he states that Addis Ababa is not part of Oromia, because the Oromia state is “illegal”, whereas the colonial province of Shewa and its district surrounding the capital city of the newly established Minilik’s empire” were not only legal but also natural !! So is the weird “logic” of Habeshas!

    ካዘነላችሁ ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣችሁ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.