ጋዜጠኛ አበበ ገላው በነአምን ዘለቀ መልቀቂያ ላይ (አበበ ገላው)

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አባል የነበረው ነአምን ዘለቀ ለድርጅቱ የጻፈውን የመልቀቂያ ደብዳቤ በጥሞና አነበብኩት። ነአምን ኢትዮጵያን ከህወሃቶች መንጋጋ ለማላቀቅ በተደረገው ትግል ጉልህ ሚና የተጫወተ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን በቅርብ የምናውቀው ሁሉ መመስከር እንችላለን።

በተለይ ብዙዎች ፖለቲካን የግልና የቡድን ጥቅም ማራመጃ፣ ሴራ መጎንጎኛ በሚያደርጉበት በዚህ ጠልፎ የመጣጣል ዘመን የራሱና የቤተሰቡን ጉዳይ ወደ ጎን ትቶ ህዝብን ለማገልገል ከልቡ የሚተጋ እንደ ነአምን አይነት ሰው በጣት የሚቆጠር ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ነአምን ለህሊና ያደረ ሰው ነው። ለነአምን ስንብት ዋና ምክንያት የሆነው ህይወታቸውን ለትግሉ ገብረው ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው በረሃ ወርደው መከራን የተቀበሉ ታጋዮችን መልሶ ለማቋቋም በድርጅቱም ይሁን በመንግስት በቂ ትኩረት አለማግኝታቸው እንቅልፍ ስለነሳው መሆኑን በጻፈው ደብዳቤው ግልጽ አድርጓል።

የቀድሞ የድርጅቱ ደጋፊ እንደነበረና አሁን ደግሞ እንደ ታዛቢ አስተያየት ለመስጠት ያህል ጉዳዩ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን የአመራር ክፍተት የሚያሳይ አንድ እውነታ ነው። በወረታ ካምፕ እንዲገቡ የተደረጉና ከካምፕ ውጭ ሆነው ጉዳያቸውን የሚከታተሉ የድርጅቱ የቀድሞ ታጣቂዎች በድርጅቱና በአመራሩ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ማሰማት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። እነዚህ ታጋዮች ድርጅታችን ተጠቅሞ ጣለን የሚል ቅሬታ ሲያሰሙ አላየንም አልሰማንም ማለት ለማንም የማያዋጣ የህሊና ሸክም መሆኑ ብዙም አያጠያይቅም።

በተለይ ድርጅቱ እራሱን አፍርሶ ከሌሎች ጋር በጣምራ ለስልጣን የሚወዳደር የፖለቲካ ፓርቲ ከመሆኑ በፊት በግልጽ እራሱን ገምግሞ የተሻለ አሰላለፍ ማድረግ ይጠበቅበታል። በተለይም የዜጋ ፖለቲካ እየሰበኩ የሴራ ፖለቲካ የሚያራምዱ አንዳንድ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አባላት ጥፋት እያደረሱና ድርጅቱ እምነት እያጣ እንዲሄድ እያደረጉት መሆኑን የምናውቅ እናውቃለን። በስብከትና ተግባር መሃል ክፍተት መኖሩ ጊዜ ጠብቆ ትልቅ ችግር መፍጠሩ አይቀሬ ነው።

ለማንኛውም የነአምን ስንብት ዋና ምክንያቶችን ድርጅቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ይጠበቅበታል። አርበኝነት ያለ አርበኞቹ ከንቱ ነው።
አበበ ገላው

5 COMMENTS

 1. 1/ አበበ ገላው በያጋጣሚው ራሱን ማግነን አይዘነጋም (ፎቶውን ይመልከቱ)
  2/ ነኣምን ዘለቀ የኢሳት መሥራች/ቦርድ ሰብሳቢ ነበረ፣ አበበ ተቀጣሪ። ሙገሳው አንዱም ውለታ መሆኑ ነው።
  3/ ነኣምን፣ ኢሳትና የኢሳት ጋዜጠኞች፣ አንድ ሰሞን የኤርትራ መንግሥት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ተቀጣሪ መስለው ነበር። ኢሳይያስን ሲያገንኑ። ሀፍረቱን የቻለ፣ ወደ ኋላ ሄዶ ማዳመጥ ይችላል! ኢሳይያስና አሜሪካኖች ሁላቸውንም ጉድ እንደሰሯቸው የሚነግራቸው ጠፋና ነው አዲስ ታሪክ ፈጥረው የሚያዋክቡን? ኢሳይያስ አገራችንን ገና ብዙ ጉድ ይሠራናል። አስቀድሞ በነዳውድ በኩል ገብቶአልና፣ ሲሻው ኦሮሞውን እንደ እኔ ነጻ ውጡ ይላቸዋል፤ ሲሻው ከህወኃት ጋር አንደ ደም እኮ ነን ይላቸዋል። እድሜ ለአሜሪካኖች እና ያለ ዕረፍት ለሚንቀሳቀሱት ለነ ዶ/ር በረከት። እኛማ ኦሮሞ አማራ ማለት አገርሽቶብናል! እድሜ ለነ እስክንድር ነጋና አጃቢዎቹ።
  4/ ነኣምን በሺሆች የሚቆጠር የግንቦት ሰባት አርበኞች ሲለን አያፍርም? ኢሳይያስ ባደራጀው ጉራ ይገባል? ውጤቱ ለመሆኑ ምን ነበር? አሜሪካኖች ሶቭዬት ህብረትን/ኮሙኒዝምን እኛ ነን የጣልን እንዳሉት፣ ህወኃትን ከሥልጣን አባረርን እንዳትሉ ብቻ!
  5/ ወደ ኤርትራ መመለስ አይቻል፤ ሱዳን ወይ ጂቡቲ አይቻል? እንደ ኦሮሞ ግንባር ወለጋ ዞር ዞር ማለት አይቻል፤ ያለው ምርጫ “ተቀላቀልን” ማለት ብቻ ነው። ዶር ዐቢይንና ለማን ማውገዝ ነው።
  6/ ለታሪክ እንዲበጅ፣ ታክቲካችን ከሸፈ ማለት ይሻላል!!
  7/ የነኣምንን ረጅም ሐተታ አንብቤአለሁ፤ ደግነቱ ማንዛዛቱ ብዙ ያልተጠበቁ፣ በሌላ ሥፍራ የጻፋቸውንና የተናገራቸውን የሚቃረኑ ናቸው። ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
  8/ የክርክር ደጅ ሳይዘጋ ያድራል፤ ጅብ የሚገባው ያኔ ነው። በእልክ ከሆነ ሁሉም ጋ እልክ አለ፤ ማንም ለማንም አያጎነብስም። ኢትዮጵያውያን በዚህ ማንም አይችለን! ፈረንጅ፣ if you can’t beat them, join them ይላል። እንደ እኔ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሰማያዊ፣ ወዘተ ማለቱን ትቶ ለጊዜው ያለውን ድርጅት ተቀላቅሎ መጓዝ ነው። በነ ዶር ዐቢይ፣ ለማ፣ ገዱ ፓርቲ ውስጥ እነ ዶ/ር ብርሃኑ፣ አንዳርጋቸው፣ ወዘተ “ቢደመሩ” እነ መለስ እንዲያመቻቸው የመንግሥት አመራር ልምዱ ሆነ ሥልጠና በሌላቸው አባላት የሞሉትን ፓርላማ ፈጽሞ መለወጥ ይችላሉ።

 2. “..8/ የክርክር ደጅ ሳይዘጋ ያድራል፤ ጅብ የሚገባው ያኔ ነው። በእልክ ከሆነ ሁሉም ጋ እልክ አለ፤ ማንም ለማንም አያጎነብስም። ኢትዮጵያውያን በዚህ ማንም አይችለን! ፈረንጅ፣ if you can’t beat them, join them ይላል። እንደ እኔ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሰማያዊ፣ ወዘተ ማለቱን ትቶ ለጊዜው ያለውን ድርጅት ተቀላቅሎ መጓዝ ነው። በነ ዶር ዐቢይ፣ ለማ፣ ገዱ ፓርቲ ውስጥ እነ ዶ/ር ብርሃኑ፣ አንዳርጋቸው፣ ወዘተ “ቢደመሩ” እነ መለስ እንዲያመቻቸው የመንግሥት አመራር ልምዱ ሆነ ሥልጠና በሌላቸው አባላት የሞሉትን ፓርላማ ፈጽሞ መለወጥ ይችላሉ።”

  አቶ/ወ/ሮ አለም አጀማመርህን ሳየው ከአገር ሻጮቹ ግንቦቶች የተለየህ መስለኸኝ ነበር፡ ወደመጨረሻው ከላይ ያሰፈርከውን የግንቦን አማካሪነት ሚና ሳየው ያው አልሸሹም ዞር አሉ ሆነህ አገኘሁህ። ለመሆኑ ብርሃኑና አንዳርጋቸው አንተ ፓርላማ የምትለው ወያኔ ጉሮኖ ውስጥ ቢገቡ እስካሁን ሲሰሩ ከኖሩት የቅጥረኝነት ስራ ማለትም ኢትዮጵያን ከማፈራረስ ውጭ ምን ሊፈይዱ ነው? ለማንኛውም ግንቦቶች ላለፉት አስራ ምናምን አመታት የተዋደቁለት ኦነግና ሻቢያን ኢትዮጵያን በግልጽ እንዲያፈራርሱ ዛሬ የደረሱበት ደረጃ ላይ በማድረሳቸው የቅጥረኝነት ተልእኳቸውን በሚገባ አጠናቀዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ በኦነግና ኦዴፓ ሻቢያ እጅ ውስጥ ወድቃለች። ምናልባትም ነአምን ወይም ብርሃኑን ትሆን ይሆናል ማን ያውቃል?

 3. ውድ “ሮማን”
  “ምናልባትም ነአምን ወይም ብርሃኑን ትሆን ይሆናል ማን ያውቃል?”
  የተሰወረውን የማወቅ ስጦታሽ ለውይይት አያመችም።
  ከሰጠሁት አስተያየት የተመቸሽን ብቻ መርጠሽ ስለሆነ ጊዜ አላጠፋም።
  ቻዎ!

 4. I have great respect for Neamin Zeleke, in view of his contribution within ESAT, also for others like Abebe Gelaw, Sisay Agena, Messay Mekonnen, Berhanu Nega etc, but i have an issue with them, they are pro-USA and pro-West, and in the past that fact prevented them from telling so many key info that were necessary in the fight against TPLF.

  ” ለነአምን ስንብት ዋና ምክንያት የሆነው ህይወታቸውን ለትግሉ ገብረው ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው በረሃ ወርደው መከራን የተቀበሉ ታጋዮችን መልሶ ለማቋቋም በድርጅቱም ይሁን በመንግስት በቂ ትኩረት አለማግኝታቸው እንቅልፍ ስለነሳው መሆኑን በጻፈው ደብዳቤው ግልጽ አድርጓል። ”

  The above sounds too soft, since even a leader of the G7 group has said a while ago that the Abiy government is preventing non-tribalist political groups from operating in Ethiopia.
  The Abiy government, another Western puppet, is starting to behave like a dictator, and Abiy, who preached Ethiopiawinet to get the Ethiopian people’s support but practiced tribalism once in power, has proven to be a liar and tribalist.

  It would be better to now demand from Abiy, either he abolishes the Killil system or he resigns.

  It should be now the job of ESAT and other media to make those demands.

 5. Alem you deliberately avoided my question about your recommendation on berhanu and andargachew’s joining the woyane so called parliament. Do you see any possibility of change while the woyane structure is in place? is realizing real change that simple? If so why did it took decades? The truth is unless an all inclusive democratic system under a united Ethiopia became a reality nothing will change. Worse even the tribal savagery will bring the country in to it’s demise. abiy’s Orwellian ‘medemer’ is a mirage to bye time untill he dismantles Ethiopia. Neamin”s ‘resignation’ and abebe gelaws’ comment is the usual G7 theatrics. The so called G7 army is non-existent and neamin’s fake sympathy is cheap image management. abebe gelaw’s claim of his non-membership with G7 is pure lie. The aim of his denial of his g7 membership is to deny g7’s proprietorship of ESAT.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.