በአማራ ብሔረተኞች እየተፈጸመ ያለው አስነዋሪ እና ሕገ ወጥ ተግባር ሊወገዝ እና አጥፊዎችም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል

ያሬድ ሃይለማሪያም

በአማራ ክልል ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታየ ያለው ጽንፍ የያዘ ብሄረተኝነት ከብሶት አቀንቃኝነት ወደ ጥቃት ሰንዛሪነት መሸጋገሩ ሌላው የአደጋ ምልክት ነው። ዛሬ ጠዋት በደሴ ከተማ በ አቶ ብሩክ አበጋዝ እና #BrookAbegazMegassa እና ከታች በፎት የሚታየው ጓደኛው ላይ የተፈጸመው ድብደባ በጠባብ ብሔረተኝ ስሜት ናላቸው የዞረ የክሉ አክራሪ ቡድኖች የፈጸሙት መሆኑን አካባቢ ላይ ካሉ ሰዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ። ይህ በአማራ ክልል እየታየ ያለው አደገኛ አዝማሚያ ከዚህ በፊትም በተለያዩ መልኩ ስገለጽ ተስተውሏል።

+ ከወራት በፊት በደሴ የተለየ የፖለቲካ አቋም ባራዱ ሰዎች ላይ ድብደባ ተፈጽሞ ማውገዛችን ይታወሳል፣
+ በደብረ ማርቆስ ከተማ አቶ በረከትን አድናለው ያለ መንጋ የግለሰብ ንብረት አውድሟል፣
+ አንዳንድ ከክልሉ ውጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች ስብሰባ እንዳያደርጉ እና ጽ/ቤቶች እንዳይከፍቱም ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና ጥቃትም ተሰንዝሮባቸዋል፣
+ በጎንደር ዩንቨርሲቲ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ አቶ ብሩክ አበጋዝ እና አቶ Seyoum Teshome እንዳይገኙ መደረጉም ይታወሳል።

ይህ አይነቱ ሕግን የተላለፈ እና የሌሎች ዜጎችን የመደራጀት፣ ሃሳብን የመግለጽ እና በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት የሚጥሱ ተግባራት በክልሉ ውስጥ እንዳዲስ እየተንሰራፋ በመጣው የአክራሪ ብሔረተኝነት ስሜት እና ጽንፈኞች አድራጎት ተደጋግሞ መታየቱ በክልሉ ውስጥ የሚታየውን አንጻራዊ ሰላም አደጋ ውስጥ ይጥለዋል።

የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስቱ እነዚህን በዜጎች ነጻነት እና መብት ላይ እገዳ የሚጥሉ እና ከዛም አልፈው አካላዊ ጥቃት የሚሰነዝሩ አክራሪ ብሔረተኞችን ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል። ከዚህ የወንጀል አድራጎት ጀርባ ያለ የተደራጀ አካል ይሁን የፖለቲካ ፓርቲ ካለ በሕግ ሊጠየቅ ይገባል።

ብሔረተኝነት እንኳን አክርረነው በለስላሳውም ቢያዝ እንካ የግለሰቦችን መብት አደጋ ላይ የሚጥል አግላይ፣ ገዳቢ እና አጥፊ መንፈስ ነው።

5 COMMENTS

 1. You better keep ur anti- Amahara propaganda. Yo can go hell. Viva Amhara! Death to all anti- Amhara stooges.

 2. በወሎ የተካሄደው ግጭት አላስፈላጊ ነው:: ሆኖም አማራውን የበለጠ ሸንሽኖ ለማዳከም የወሎ :የጎጃም : ጎንደር እያለ ወያኔ ቢያደራጃቸው አይገርመኝም::የጎጥ ሽንሸና የህውሀት መተንፈሻ ሳምባ ነው:: ጎንደር ቅማንት አማራ እያሉ ተገማምዶ የሚኖረውን ህዝብ ይበትናሉ::
  27 አመታት አማራ የተረገጠው በአማራነቱ ብቻ ነው::ይህን የማያውቅ ዝግምተኛ አማራ በየጎጣጎጡ የለም ብሎ መገመት አይቻልም::የዜግነት ፖለቲካ አጫፋሪዎች ከዚህ ክፍፍል የሚገኝ ምንም ትርፍ አይኖርም::አማራ ተመልሶ ላለመተኛት ተንስቷል:: በመላው ኢትዮጵያ ይደራጃል::የማንንም እኛ እናውቅላችሗለን ሞግዚት አስተዳዳሪ አይፈልግም:: አማራ ታላቅ ህዝብ ነው::በጎጥና በጎሳ ሳስቶ እራሱን አይመለከትም::

 3. እኔ በጣም የሰለቸኝ ነገር ቢኖር አሾክሻኪ፡ወያላ፡በሌሎች ፍዳና ስቃይ ለመታወቅ የሚፈልግና እንደ አይጥ ከዚያም ከዚያም የሚሽሎከለክ፡ውጭ ሃገር እየኖረ ፖለቲካ የማያውቅና ትምህርት ያላገኘ የመንደር ወሬ የሚሰበስብ እንደዚህ አይነቱ ነው ለሃገር እድገት እንቅፋት የሚሆነው።
  ይሄ ጸሃፊ እንደሚለው “ከመንደር ሰዎች እንደሰማሁት” ብሎ አማራን ዘረኛ ለማድረግ ይፈልጋል።
  እንደሰማሁት የሚባል ነገር የለም። ህዝብን ከመወንጀልህ በፊት መረጃ ማቅረብ አለብህ።
  እንደሰማሁት የምትል ከሆነ ሌላ ድብቅ አጀንዳ አለህ ማለት ነው።
  ምን ማረጋገጫ አለህ የደህንነት ሰራተኞች አለማድረጋቸውን?
  ምን ማረጋገጫ አለህ ሌሎች በድብቅ የተደራጁ ሃይሎች አለማድረጋቸውን?
  ምን ማረጋገጫ አለህ የአማራውን ድርጂት አብንን ለማሳጣት በአብይ አስተዳደር(አዴፓ፤ኦዴፓ፤ህወሃት) የተደረገ ሴራ አለመሆኑን?
  እኔ ሰውን መደብደብ አጥብቄ እቃወማለሁ ግን በማላውቀው ነገር የአማራ ዘረኞች ናቸው ብዬ ስም አልጥፍም።
  የአንተ የመብት ተከራካሪነት አማራን ተሳድበህ የስልጣን መወጣጫና ታዋቂነት ለማትረፍ ከሆነ አደብ ብትገዛ የሚሻል መሰለኝ። አማራ ዘረኝነት ይካሄድበታል እንጂ ዘረኛ የሚያስብል መረጃ ልታቀርብ አትችልም። ዝም ብለህ እንዳመጣልህ አትቀደድ(ላሜ ቦራ አትሁን)።

 4. When the Amhara do it wrong, when the olf idiot fascists do it right, what is this ? bullshitting or what ?!, get lost anti Amharas !, we are awake never to sleep back again any more not even to the slightest, get out of our way or woe betide You !
  Long Live The great people of Amhara !

 5. The ethnic mobilization of the Amhara is or nor will be a risk nor a threat to the territorial integrity of Ethiopia. Its sole objective is a question of survival. As everyone knows including its enemies , tplf and olf, the people of Amhara have been paying a priceless sacrifice for the concept of Ethiopianhood, in terms of life and other physical and mental tribulation to date. The people of Amhara have been targeted and victimized only because it has been the guardian and defender of Ethiopia and Ethiopianhood as well as on a basis of its ethnicity. Now, its survival is greatly endangered and so it first has to prioritize its survival which is obviously understandable. However, it does not mean that the people of Amhara shall secede from the nation that its ancestors have built unlike thte moron tplf and olfites. A strong and formidable amhara organisation is an assurance to the survival other brothers and sisters who are Ethiopian. It has to be clear that such an organisation of the Amhara should under no circumstance be viewed as a threat to other Ethiopians except to those arch enemies of the Amhara the tplfites and their puppet olfites. The Amhara are arisen never to flinch nor appease its enemies as before just in the interest of Ethiopianhood. They have witnessed the outcome of appeasing the enemies and have now started talking to them in the sole language they seem to understand and will continue doing its assignment until Amhara-phobia sentiment is stamped out of the face of Ethiopia and an Ethiopia that treats its children equally is built.Those of you who are barking here and there against the people of Amhara , where have you been when they have been targeted and victimized only because they arre Amharas and only because they are the defenders of Ethiopia over the past 50 years in a row ?! now simply shut up and witness the history the people of Amhara are making. That is the only chance you have now or drink the cup of defeat as well as speed up the time of your downfall, period !
  The Amhara shall remain engaging its enemies like never before , but you may keep on barking.
  No more messing the Amhara !
  One Amhara for all Amhara and All Amhara for one Amhara !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.