‹‹የሰው አንገትን ከመሠየፍህ በፊት አስብ፣ ምክንያቱም መልሰህ አተክለውምና!!!›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

በኢትዩጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካል  ጉዳተኞች ይኖራሉ፡፡ የትግራይና የአማራ ምሁራን የወልቃይትና የራያን ህዝብ ጥያቄ በምንም መንገድ ወደ ማያባራ ጦርነት መግባት አይኖርባቸውም እንላለን፡፡ የወልቃይት ህዝብ ብዛት 55100 እንዲሁም የራያ ህዝብ ብዛት 87638  እንደሚደርስ ከ1994 ዓ/ም የስታሰቲክስ ቢሮ መረጃ ያሳያል፡፡ የትግራይና አማራ ክልላዊ መንግሥቶች በማኃላቸው የሳሉትን ሰው ሰራሺ የድንበርና ወሰን አስወግደው፣ የጥላቻ ፖለቲካን አስወግደው፣ በሁለቱ በሚነሳ ጦርነት ከውድቀት ሌላ የሚፈይዱት እድገት ስለማይኖር የዲጂታል ዘመን ወጣቶች ወደፊት ለሚጠብቃቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዬች የጋራ ውርስ በመማር ጦርነትንና የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳን በማስወገድ የወልቃይትና ራያን ጉዳይ በሽማግሌዎች መፍታት ይጠበቅባችሆል፡፡ የሁለቱ ክልል መንግሥቶች የወልቃይታና ራያን ህዝብ በኢኮኖሚ በመገንባት፣ የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት፣ የገበያ ቦታዎች በመገንባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ከ150 እስከ 200 ሽህ ለሚደርሰው ህዝብ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በባህል በማቀራረብ የጥንቱን ፍቅራቸውን በማስፈን ወንጀል ከመፈፀም መቆጠብ የሰለጠኑ  ሰዎች መፍትሄ ይሆናል እንላለን፡፡ የኢትዬጵያ ህዝብም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የተፈናቀሉትን ሰዎች ወደ ቀድሞ ስፍራቸው ማስፈር ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያና በኤርትራ የባደማ ፆረና ጦርነት

ከሰባ እስከ መቶ ሽህ ዜጎች ከሁለቱም አገራት እንደሞቱ፣ ምን ያህል ሠራዊት እንደቆሰለና የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁለቱ ክልሎች በወልቃይትና ራያ  ጦርነት መግባት አይጠቅምም እንላለን፡፡  ትግራይም፣ አማራም፣ ወልቃይትም፣ ራያም ኢትዮጵያዊያን ናቸውና!!!

በ1994 ዓ/ም በኢትዩጵያ በተካሄደ የህዝብ ቆጠራ 988,853 የአካል  ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ በዛን ግዜ 53,073,322 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት ውስጥ 1.9 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ የአካል ጉዳተኞች፣በደረሰባቸው የአካልና የስነ-ልቦና ጭንቀት ምክንያት ጤነኛ ሰዎች ሊሰሩት የሚችሉትን ሥራ መሥራት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ገቢ የሚያስገኝ ሥራና የማህበራዊ ኑሮ ህይወት መምራት አይቻላቸውም፡፡ ከሠንጠረጅ ላይ በኢትዩጵያ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ የአካል  ጉዳተኞች ብዛትና የመቶኛ ንፅፅር እንቃኝ፡፡

Table 2-B: – prevalence of disability by regional states of Ethiopia (1994 census)

No ተ/ቁ              Region   

    ክልል

All persons             የህዝብ ብዛት PWD’s           የአካል ጉዳተኞች Ratio     ንፅፅር በመቶኛ
1 Oromiya 18,465,449 333,653 1.80%
2 Amhara 13,828,909 281,291 2.03%
3 SNNP 10,368,449 174,941 1.69%
4 Tigray 3,134,470 90,742 2.80%
5 Addis Ababa 2,100,031 45,936 2.18%
6 Somali 3,382,702 34,156 1.00%
7 Afar 1,097,067 14,140 1.29%
8 Benshangul & Gumuz 460,325 7,341 1.59%
9 Dirdawa 248,549 4,226 1.70%
10 Harari 130,691 2,909 2.23%
11 Gambella 162,271 2,581 1.59%
Total                         53,379,035 991,916 1.85%

PWD (People With Disabilities)

Baseline Study on the Status of Persons with Disabilities and the Influence of the African Decade Pronouncement in Ethiopia may, 2010

የጦርነት አዙሪት፣ኢትዩጵያ ከጦርነት አዙሪት ውስጥ ወጥታ አታውቅም ለአርባና ሃምሳ ዓመታት በተደረገ ውጊያ ብዙ ዜጎቻችን የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ የጦርነት ሰለባ የሆኑ፣ አካል ጉዳተኞች በሃገሪቱ ትክክለኛ ማስረጃ ለማግኘት ባይቻልም፣በአንደኛ ደረጃ በኦሮሚያ ክልል 333,653፣በሁለተኛ ደረጃ  በአማራ ክልል 281,291፣ በሦስተኛ ደረጃ በደቡብ ክልል 174,941፣በአራተኛ ደረጃ በትግራይ ክልል ከ90,742 ሽህ አካል ጉዳተኞች እንዳሉ የኢትዩጵያ ስታትስቲክስ ፅ/ቤት መረጃ ይገልፃል፡፡ ጦርነት የሚያካሂድ አገር በኢኮኖሚ ሊበለፅግ አይችልም፡፡ ደርግና ህወሓት አንባገነኖች በጦርነትና በኃይል የሚያምኑ በመሆናቸው ሃገር በኢኮኖሚ ሊበለፅግና ህዝብ ከድህነት አረንቆ ሊወጣ አልቻለም፡፡ የፖለቲካ ልዩነታችንን፣በጠረጴዛ ዙሪያና በሰለጠነ መንገድ በውይይት ችግሮቻችንን መፍታት እስካልቻልን ድረሰ ዓለም ከደረሰበት ስልጣኔ መድረስ ቀርቶ ዜጎቻችን ከርሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከስደት፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ከሥነ-ልቦና ጠባሳ ለመውጣት አይቻልም፡፡ በጦርነት የሚዳክሩ ሃገራት ምርታቸው የግብርና ምርት፣ የኢንዱስትሪ ሸቀጣ ሸቀጦች ሳይሆን የሃገር ገንቢ ዜጎቻቸው ሞትና የአካል ጉዳተኛ ምርት ሲያጭዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ኢትዩጵያ በጦርነት አዙሪት ውስጥ ተዘፍቃለች፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጦርነት ኢኮኖሚ መቅኒው ድረስ ተበልቶል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በተደጋጋሚ የአስቸኮይ ግዜ አዋጅ ስበብ ብዙ ወጣቶች ገሎል፣አካለ ስንኩል አድርጎል፡፡ በየእስር ቤቱ በኢሰበአዊ ግርፋት ብሁ ዜጎች እግርና እጃቸው ሽባ ሆኖል፣ ሥነ- ልቦናቸው ተናግቶል፡፡ ሃገሪቱን በጦርነት ኢኮኖሚ  ዘፍቆል፣‹‹ሁሉ ነገር ወደ ጦር ግንባር!›› እንደ ደርግ ካለ ሠነበተ፡፡ በሰው ሠራሽ፣ ፀረ-ሰው ፈንጅ፣ ፀረ ታንክ ፈንጅ፣ የእጅ ቦንቦች የጦር መሣሪያዎች የሚሞተውና የሚቆስለው ወገኖቻችን ቤቱ ይቁጠራቸው!!! ለዚህ ነው ‹‹የሰው አንገት ከመሠየፍህ በፊት አስብ፣ ምክንያቱም መልሰህ አተክለውምና!!!››የሚሉት የቻይና አበወች ምክር ማስታወስ የሚገባው፡፡ በ2010 እኤአ የህዝብ ቆጠራ በኢትዩጵያ 805,492 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ ከኢትዩጵያ 73,750,932 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት  1.1 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ በኢትዩጵያ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር ከ1994 እኤአ እስከ 2010 እኤአ መቀነስ ዋና ምክንያት  የህዝብና የቤቶች ቆጠራ ወቅት፣ አባወራዎችና እማወራዎች በጎጂ የባህል ተፅዕኖ ምክንያት በቤተስቡ ውስጥ የሚገኝ አካል ጉዳተኛን ባለማስመዝገባቸው ነበር፡፡ በኢትዩጵያ ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች፣ የህዝብ ብዛት፣የአካል ጉዳተኞች ቁጥርና፣ በፆታ ያለው ንፅፅርን ከሠንጠረጅ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

በኢትዩጵያ ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ብዛት፣ በፆታ በ2010 እኤአ

ተ/ቁ ክልልና ከተማ ማስተዳደሮች የህዝብ

ብዛት

ጠቅላላ የአካል ጉዳተኛ ወንድ

የአካል

ጉዳተኛ

ሴት

የአካል  ጉዳተኛ

1 ኦሮሚያ 26,993,933 282,544 153,231 129,313
2 አማራ 17,221,976 198,694 101,522 97,172
3 ደቡብ 14,929,548 170,113 90,461 79,652
4 ትግራይ 4,316,988 69,017 35,802 33,215
5 አዲስ አበባ 2,739,551 32,630 17,931 14,699
6 ሶማሌ 4,445,219 24,223 14,206 10,017
7 አፋር 1,390,273 9,950 5,887 4,063
8 ቤኒ-ሻንጉል 784,345 8,486 4,621 3,865
9 ድሬዳዋ 341,834 3,778 2,069 1,709
10 ጋምቤላ 307,096 3,549 1,936 1,613
11 ሃራሪ 183,415 1,790 952 838
12 ልዩ ቆጠራ ቦታዎች 96,754 718 386 332
በኢትዩጵያ አጠቃላይ ድምር 73,750,932 805,492 429,004 376,488

ምንጭ‹-  የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣  ኦግስት 2010፣ አዲስ አበባ ገፅ 134-138

በኢትዩጵያ የአካል ጉዳተኞች ትልቁ ችግር ሰው ሠራሽ የአካል ክፍል (Prosthetics)፣ ተሸከርካሪ ወንበሮች፣ምርኩዝ (Crutch)፣ወዘተ የመሳሰሉት መገልገያዎች እጦት የተነሳ አስታዋሽ አጥተው ይሰቃያሉ፡፡

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የትግራይ ክልል ህዝብን በጦርነት አዙሪት ውስጥ አስገብተውታል፡፡የትግራይን ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ፣ ከጎንደር ህዝብ፣ ከአፋር ህዝብ፣ ከወሎ ህዝብ መሬት በመዝረፍ፣ ታላቆን ትግራይ በመሬት ቅርምትና ዘረፋ ለማሳደግ በሚያደርጉት ጥረት ሃገሪቱንና የትግራይ ህዝብን ወደ ማያባራ ጦርነት ውስጥ ከተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በትግራይ ክልል ከ90 ሽህ አካል ጉዳተኞች እንዳሉና ወደፊትም በዚህ የጦርነት አዙሪትና የማያባራ ጦርነት፣ ይህ አሃዝ እንደሚጨምር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ህወሓት በትግራይ ክልል መሽጎ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ህወሓት በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ህዝባዊ ሚሊሽያ 1.2 ሚሊዮን ታጣቂ በማደራጀት፣ በዘረፉትን የጦር መሣሪያ ታንኮችና የጦር አውሮፕላኖች  በመመካት አጎራባች የአማራ ክልሎች አካባቢ ሠፈራ በማድረግ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የአማራም ክልል በተመሳሳይ  ልዩ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ህዝባዊ ሚሊሽያ በማደራጀት ህዝብ በማስታጠቅ ላይ ይገኛል፡፡ በመላ ሃገሪቱ የመሳሪያ ዝውውርና የገንዘብ ዝውውር በአስደንጋጭ መልኩ ሲሽለከለክ ሠንብቶል፡፡ ያለፈው አልበቃ ብሎ ወንድም ወንድሙን ለመግደል በዘር ተከፋፍሎ ዶልቶል፣ ማንም አሸነፈ ማንም የሁላችንም ምርት የወጣቶች እልቂትና የአካል ጉዳተኞች ምርት ከመጨመር ሌላ የወልቃይት፣ ራያና አፋር ወዘተ የመሬት ጥያቄ በሽማግሌዎች ያለምንም ደም መፋሰስ መፍትሄ ማግኘት ይችላል፡፡ ወደ ህሊናችን እንመለስ ለሚቀጥለው ትውልድ ፍቅር እናውርሰው፣ ጥላቻን አናውርሰው፡፡ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሃዋሳ ወዘተ የከተማው ህዝብ፣ በህዝብ የተመረጠ ከንቲባ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በፌዴራል መንግሥት የከተማ አስተዳደር ፖሊሲ በህዝብ ውይይት በማድረግ ተግባራዊ መሆን አለበት እንላለን፡፡ በውይይት ሁሉም ነገር ይፈታል፡፡ ካለፈው ታሪካችን እንማር፡-

 • በኢትዩጵያና በኤርትራ ጦርነት ከሰባ እስከ መቶ ሽህ ዜጎች ከሁለቱም አገራት እንደሞቱ፣ ምን ያህል ሠራዊት እንደቆሰለና የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ መረጃ አልተገኘም፡፡
 • በ1997ዓ/ም ምርጫ ወቅት ከ200 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፣ ከ5000 ሽህ ሰዎች በላይ በጥይት ቁስለኛ ሆነው የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ በ2007/8 ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና የአማራ ተጋድሎ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የአጋዚ ጦር ከ1500 ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ዜጎቻችንን ገድለዋል፣ ብዙ ሽህ ሰዎች በጥይት ቆስለው የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ በጋምቤላ ከ400 ሰዎች ተገድለዋል፣በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፡፡ በሲዳማ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጎች በግፍ ተረሽነዋልና ቆስለዋል፡፡ በአረካ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፡፡ ከለውጡ በኃላ ለእነዚህ ሠማዕታት መታሰቢያ እንኮን አልቆመላቸውም፣ የመለስ መታሰቢያ ለነዚህ ሠማዕታት መታሰቢያ መሆን ይገባዋል እንላለን፡፡
 • በ1994 የህዝብ ቆጠራ በኢትዩጵያ 988,853 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ ከኢትዩጵያ 53,073,322 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት 1.9 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ በ2008 ዓ/ም ምን ያህል የአካል  ጉዳተኞች ይኖራሉ;
 • በኢትዩጵያ ውስጥ 4.6 ሚሊዩን ህፃናቶች ከወላጆቻቸው አንዱን በሞት የተነጠቁ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ሃገሪቱ ከዓለማችን የሙት ልጆች መኖሪያ ለመሆን በቅታለች፡፡
 • በኢትዩጵያ ውስጥ 1.2 ሚሊዩን ህዝብ በኤችአይ ቪ/ኤድስ በሽታ ጋር አብሮ ይኖራል፡፡ 800 ሽህ ህጻናት ከዚህ በሽታ ጋር በተያያዘ ወላጃቸውን አጥተዋል፡፡
 • በኢትዩጵያ በዓመት ከአንድ ሽህ ዜጎች መካከል ዘጠኙ ወደ ሌሎች አገራት ይሰደዳሉ፡፡ በ2015 እኤአ በኢትዩጵያ የሥነ-ህዝብ ቁጥር  99,465,819 ሚሊዩን ውስጥ 795,726 ሽህ ህዝብ በዓመት እንደሚሰደዱ ተገልፆል፡፡
 • በ2011 ዓ/ም 8.3 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል እንደተባበሩት መንግሥት መረጃ መሠረት፡፡ በመላ ሃገሪቱ እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሎ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ ይገኛል፡፡ የዲያስፖራው ዜጋችን በታማኝ በየነ ስብዓዊ የድጋፍ ጥሪ 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ለወገን ያለቸውን ፈጣን እርዳታ ዲያስፖራው ዛሬም ሲሶ መንግሥትነታቸውን አስመስክረዋል እንላለን፡፡

ምንጭ፡-Source:

 1. Baseline Study on the Status of Persons with Disabilities and the Influence of the African Decade Pronouncement in Ethiopia may, 2010
 2. የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የ1994ዓ/ም፣ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በኢትዩጵያ፣ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ጁን 1999፣ አዲስ አበባ ገፅ 60-62
 3. የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ኦግስት 2010፣ አዲስ አበባ ገፅ 134-138
 4. Mekelle University College of Business and Economics Department of Cooperative Studies, The Role of Cooperatives In Unlocking Potentials of People with Disability: The Case of Tigray War Veterans in Mekelle, By Tesfahunegn Hailemariam Degefu/ September, 2011

ሃገሪቱ የግብርና ምርት እንጂ የአካል ጉዳተኛ ምርት አያስፈልጋትም!!!

ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት እንፍታ!!!

በጦር መሣሪያና በኃይል የህዝብ ችግር አይፈታም!!!

ህወሓት/ ብአዴን/ ኦህዴድና ደኢህዴን/ ኢህገዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ምላጭ በመሳብ አረጁ፣ ዘመኑ የሚሻው ህሊናን መሳል ነው!!!

 

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

  በኢትዩጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካል  ጉዳተኞች ይኖራሉ!!!

ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!                      / ፂዮን ዘማርያም

የክልል ዘር ተኮር መንግስቶች ህወኃት/ ብአዴን/ ኦህዴድ/ ደኢህዴን  የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ በክልላቸው ውስጥ ስውር ሥራዎች በማደራጀትና አንዱ አንዱን በመክሰስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን አጦጡፈውታል፡፡

{I} የየክልሎቹ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ሥርጭት የጦርነት መጎሰሚያ መሆናቸው!!! ኦህዴድ፣ ብአዴንና ህወሃት ባለፈው ጊዜ በየግላቸው አንዳንድ መግለጫዎችን አውጥተዋል። እንዲሁም በደቡብ ክልል የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ የክልል ጥያቄ በአጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ ያስነሳው የድንበርና የወሰን ግጭት ወደ ጦርነት እያሸጋገረን መምጣቱ አይቀርም  እንላለን፡፡

{1} ኦህዴድ/ ኦዲፓ በፌዴራል መንግሥት ምንም ድርድር እንደማያደርግ አቆሙን ገለፀ፡፡ ቀጥሎም ኦህዴድ በአዲስ አበባ ዙሪያ ስለተሰሩ የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ከክልሉ መንግሥትና ከሚያስተዳድረው የኦሮሞ ህዝብ ፈቃድና እውቅና ውጪ ቤቶቹን ለባለ እድለኞች የማስተላለፍ ጉዳይ እንዲቆም ከመጠየቅ አልፎ አዲስ አበባን አስመልክቶ የኦሮሞ ጽንፈኞች ለዘመናት ሲያቀነቅኑት የኖሩትን የባለቤትነት ጥያቄ መቀላቀሉን በማያሻማ ቋንቋ ግልጽ አድርጎአል። 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ የተላለፈ ሲሆን በ30 ቢሊየን ብር የቆጠቡ የቤት ሰሪዎች ንብረትና ኃብት ሲሆን ከ1997 ጀምሮ እስከ 2005አም ለ15 ዓመታት ቤት ለማግኘት ይጠባበቁ የነበሩ ሰዎች ንብረት ነበር፡፡ የሞርጌጅ ባንክ (የገንዘብና ቁጠባ ባንክን) ህወሓት /ኢህአዴግ በማፍረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያለስራው የኮንዶሚኒየም ቤቶች አዳይ በመሆን ህወሓት በሄደበት መንገድ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ተረኛው የጦር አበጋዞች መንግስት በዘር ላይ የተመሠረተ ዘረፋ በህዝብ ላይ ለመፈፅም ህግ ጣሰ፡፡ ከህግ አንጻርም አያስኬድም እንላለን፡፡

{2} ብአዴን/ አዲፓ መግለጫ “የትግራይ ክልል እያካሄደብኝ ያለውን የጦርነት ቅስቀሳ ያቁም” በማለት የጦርነት ነጋሪት ጎስሞል፡፡

{3} ህወሃት በትግራይ ህዝብ ላይ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ያሉት “ጽንፈኞች እንጂ እኔ አይደለሁም” በማለት በመግለጫው ላይ ድርጅቱና የትግራይ ህዝብ ጦርነትን ከማንም በላይ አሳምረው እንደሚያውቁና እንዳለፉበት ገልጾ ለሰላምና ለወንድማዊ ግንኙነት ሲል ትእግስትን እንደሚያስቀድም ማስጠንቀቂያ  አዘል መልዕክት አስተላልፎአል።
ህወሓት/ ኦህዴድና ብአዴን ደኢህዴን ኢህአዴግ ድርጅቶች ማዕከላዊ ኮሚቴ መንጋ ፍርድ በስውር ወይም በይፋ፣ በቡድን ወይም በተናጠል የሚሸርቡት  ወይም የሚዘጋጁበት  ጦርነት እንዳለ ተስተውሎል። የየክልሎቹ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ሥርጭት የጦርነት ነጋሪ በመጎሰምና መግለጫዎች በማንጋጋት ያለ አንዳች የህዝብ ውክልና ፣ ህዝብን ከህዝብ የሚያጣሉ፣ የህዝብ አውንታ የሌላቸው የበሰበሰው ኢህአዴግ ዘር ለዘር እያጋጩ በሥልጣን የመቆየት ቀጣይ የቤት ሥራ ለህዝብ በመስጠት ላይ በመሆናቸው እነዚህ የገሙ ኢህአዴግ ካድሬዎች ሙስና ሌቦች ሳይነቀሉ ለውጡ ወንዝ አይሻገርም እንላለን፡፡ ስለዚህ በነዚህ ካድሬዎች የተያዘው ፣ የየክልሎቹ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ሥርጭት ማስቆም አሰቸኮይ ሥራ ነው እንላለን፡፡ አሊያም ተጠያቂነትና ኃላፊነት ወስደው የሚሰሩበት የሚዲያ ህግና ደንብ ወጥቶላቸው ቢቀጥሉ የተሸለ ይሆናል እንላለን፡፡

{II} ክልሎች የራሳቸው መከላከያ ኃይል  በማደራጀት ካራ እያሳሉ ይገኛሉ፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በመቐለ ከመሽገ አስር ወራቶች አስቆጠረ፣ በስብአዊ መብት ጥሰት የተከሰሱና በሙስና ሌብነት ወንጀል የህዝብ ኃብት የዘረፉ ሹማምንቶችን አሳልፈን አንሰጥም በማለት የፌዴራል መንግስቱን ሥልጣን ተጋፋ፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይል ከትግራይ ክልል አይወጣም ብሎ ሠራዊቱን አገተ፡፡ እያለ እያለም የክልሉን የፖሊስ ሠራዊት በማጠናከር፣ ልዩ ኃይል በማደራጀት፣ ህዝባዊ ሠራዊትና ሚሊሽያ እስከ 1.3 ሚሊየን ሠራዊት አስታጥቆ ወደ አማራ ክልል እንዳስጠጋ ያደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ብአዴን/ ኢህአዴግም በተመሳሳይ  የክልሉን የፖሊስ ሠራዊት በማጠናከር፣ ልዩ ኃይል በማደራጀት፣ ህዝባዊ ሠራዊትና ሚሊሽያ አስታጥቆ ውስጥ ውስጡን አደራጅቶ ለውጊያ ተዘጋጅቶል በሚል ሁለቱ ክልሎች ተፋጠው ይገኛሉ፡፡ የኃይማኖት አባቶች የእርቅ ሽምግልናም አልተሳካም፡፡  የየኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ታጣቂ ኃይሎች በጌዲኦ፣  በምእራብ ጉጂ ዞን  ውስጥ እንዲሁም በደቡብ ክልል አማሮና ቡርጅ ወረዳዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ብዙ ሽህ ህዝቡ የእለት ተዕለት ህይወት ህይወቱን እንዳይሮር በማፈናቀል፣ ከ120 በላይ ሰዎች  በመግደል፣ መንገዶች በመዝጋት የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር፣ ጊዜ የሰጠው ቅል ለመሆን ችሎል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትም ለህዝብና ለወገን ደራሽ አለመሆኑ የገባውን ቃል ኪዳን ማፍረሱን አስመስክሮል፡፡ የዳክተር አብይ መንግሥትና መከላከያ  ሠራዊቱ ህግና ሥርዓት ማስጠበቅ ለምን ተሳነው፣ጊዜ ያወጣዋል፣ በአንድ ቀን 17 ባንኮች ተዘረፉ መንግሥት የለም!!! ወሬ ሰለቸን፣ ተግባር ናፈቀን፡፡ ከውኃ አጥማቂው በኃላ በእሳት አጥማቂው ይመጣልና የድሃ እንባ መድረቁ አይቀርም፡፡

{III} ክልሎች የራሳቸው የደህንነትና የስለላ ሥራ በማደራጀት የትግራይና የአማራ ህዝብ በሠላም እንዳይኖርና አርሻውን እንዳያርስ አድርገውታል፡፡ ብዙ ህዝብ ከአማራ ክልል ለመፈናቀል ተገዶል፣ ከትግራይም የተፈናቀሉ አሉ፡፡

{IV} የክልል ባንኮች በማደራጀት፣አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የዘመኑን ባንክ ሲገልፁት፣‘’በሃገራችን የፋይናንስ ዘርፍ ላለፍት ሃያ አምስት አመታት በዘርፉ የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎች አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጎል፡፡ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የህብረት ባንክና ኢንሹራንስ መሥራች እንዳሉት ከሆነ፣ በሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ‹‹የተማቱ አፈጣጠር የተለያየ በመሆኑም ለማዋሃድ የሚቻለውም ቀድሞ ሥራ ሲሰራ ነው፡፡ አንዳንዱ በብሄር፣ አንዳንዱ በፓርቲ፣ ሌላውም በሃይማኖት የተቋቋ ስለሆነ አሁን ባለው ሁኔታ መቀላቀል ያስቸግራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለማንኛውም እውነተኛ ውድድር እንዲኖር ለአገር በቀል ገበያ እኩል ሜዳ ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ያልተስተካከለ ገበያ ውስጥ ተቀምጠን፣ ከጊዜ በኃላ ኢኮኖሚያችን መከፈቱ ስለማይቀር በሚከፈትበት ጊዜ ደካማ ማት ሆነን የውጭዎቹ በቀላሉ እንደ አርጀንቲናና ፊሊፒንስ ኩባንያዎች እንዳንበላ ሥራው ቀድሞ መጀመር አለበት፡፡›› ብለዋል፡፡ የጡብና አዳፍኔ ዘመን ዘር አፈራሽ ባንኮች!!! የኢትዩጵያ ባንኮችና ኢንሹራንሶች የማን ኃብት ናቸው??? የክልል ዮኒቨርሲቲዎችና የእግር ኮስ ክለቦች፣ የመኪና ታርጋ ወዘተ ዘርና ያማከለ ሥራ ሊስተካከል ይገባል እንላለን፡፡

{V} የፌዴራል መንግሥት የባጀት ድልድል፡- የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወኃት)፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለኦሕዴድ)፣ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ለብአዴን)፣ የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) ሹማምንትና ካድሬዎች መደበኛው ባጀት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ለመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ፣ ዳጎስ ያለ ጥቅም ስላለው ሁሉም ወደ ክልላዊ መንግሥትነት የመሸጋገር ጥያቄ እንደ አሸን ፈላ፡፡ የፌዴራል መንግሥት የባጀት ድልድል የክልላዊ መንግሥቶች የመደበኛ በጀት እድገት ለማስተዋል፣-

 • በ2002 እኢአ መደበኛው በጀት 5 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን
 • በ2007 እኢአ መደበኛው በጀት 05 ቢሊዩን ብር፣
 • በ2008 ዓ/ም መደበኛው በጀት 3 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ ተገልፆል፡፡
 • በ2009 ዓ/ም መደበኛው በጀት 0 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ በአንድ ግዜ የ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ጭማሪ
 • በ2010 ዓ/ም መደበኛው በጀት 0 ቢሊዩን ብር ሲሆን በየጊዜው እየጨመረ መጥቶል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የምሁራኖች የክልል ጥያቄ በተለያዩ ከልሎች ውስጥ የተከሰተው ከፌዴራል መንግስት የሚገኘውን የባጀት ጥቅም ለማግኘት እንደሆነ እሙን ነው፡፡  ለምሳሌ በኦሮሚያና በአማራ ክልል መንግሥቶች፣ የሚሰበስቡት ግብርና ታክስ ከ10 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሲሆን የፌዴራል መንግሥት ለኦሮሞና አማራ ክልል መንግስታት ከ40 ቢሊዮን ብር ገደማ በጀት ይመድባል፡፡

የአጋር ድርጅቶች የዘር ድርሻ፤-ለኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች፣ ለሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሶዴድ)፣ለአአፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አዴድ)፣ቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ቤህነን)፣ጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ለጋሕነን)፣ለሃዴድ ሹማምንትና ካድሬዎች፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሃራሪ ክልል ሹማምንትና ካድሬዎች፣ ለአዲስአበባ አስተዳደር ሹማምንትና ካድሬዎች የመደበኛ በጀት ወጪ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ የከተማ አስተዳደር ግብር ከፋዬች በ2010ዓ/ም 40 ቢሊዮን ብር ተሰብስቦል፣ ሃገሪቱ ለ80 ብሄር ብሄረሰቦችን ክልላዊ መንግሥት ቢሆኑ፣  የፌዴራል መንግስት በጀት ምን ሊሰጣቸው ነው፡፡ ሀገሪቱ ደሃ አገር ናት፣ ሠርተን በግብርና የተትረፈረፈ ምርት ካላገኘን፣ በፋብሪካ ብዙ ሽቀጣ ሸቀጦች ካላመረትን፣ በውጭ ንግድ አያሌ ምርት ወደ ውጭ ልከን ምንዛሪ ካለገኘን አገራችን አታድግም፣ ድህነት አይጠፋም እንላለን፡፡

 

ለማጠቃለል የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ፣ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ደቀ መዝሙር የነበሩ የጀሌውን ወጣቶች ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ ዛሬም በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሱማሌ፣ በደቡብ ክልል መንግሥቶች ውስጥ ውስጡን የሚደራጁ የክልል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል፣ ህዝባዊ ሚሊሽያ፣ የደህንነትና የስለላ መረጃ፣ የክልሎች የማስሚዲያ/ የመገናኛ ብዙሃን ሥርጭት ሰጣ ገባ፣ ወዘተ በተደራጀ መልክ ቀጥሎል፡፡  የጦር አበጋዞቹ  የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡ በኢትዩጵያ ውስጥ በዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት  በጉጠኛነት፣ በዘውገኛነትና በዘር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች መኃል፤ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ)፣ ኤርትራ አርነት ግንባር (ኤአግ)፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ እስላማዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦእነግ)፣ ምዕራብ ሶማልያ ነፃ አውጭ ግንባር (ምሶነግ)፣ በሱማሌ (ኦኤንሌኤፍ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ በጋንቤላ ነፃ አውጪ ግንባር (ጋነግ)፣ የሲዳማ አርነት (ሲአን)፣ ቤኒ-ሻንጉል ነፃአውጪ ግንባር፣ አፋር ነፃ አውጭ ግንባር (አነግ) ወዘተ ማዕከላዊውን መንግስት በማዳከም የፖለቲካ ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ስርዓት ሆነ፡፡ በዘመነ-ጦር አበጋዞች በነፃ አውጭ ስም፣ በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግላቸው ሎሌ ጦር ሰራዊት ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን በማደራጀትና በመመልመል በብሔራቸው ስም ስልጣን ለመያዥ ይታገላሉ ጀመር፡፡ የጦር አበጋዞቹ በግለሰቦችና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ጥላቻን በመፍጠር የራሳቸውን የጦር ሰራዊት በማቆቆም ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ፡፡ የኢህአዴግ ህወሓት (የትግራይ)፣ ኦህዴድ (የኦሮሞ)፣ ብአዴን (አማራ)፣ ደቡብ ወዘተ በዘርና ቌንቌ  ላይ የተመሠረተ  የማንነት መታወቂያ የሚሠጡ የንግድ ድርጅት ጋር ይወዳደራሉ፣ በዛም የዘርህ ግንድ ተጣርቶ መታወቂያ ይሰጥህና በጀት ተደልድሎልህ፣ ሥራና ደሞዝ ይቆረጥልሃል ማለት ነው፡፡ ‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ  ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም  ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ የዘርና ቌንቌ ያለት ሃገር በመሆኖ ወደ ሰማንያ መንግሥታት ምሥረታ መሸጋገራችን አይቀሬ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም በጂኦግራፊያዊ አከላለል ቢከፋፈል ግጭት ይጠፋል፡፡ ክልሎችን በዘር እና በቌንቌ በድንበር እየለያዩ መለየት የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ፣ የሃዲያ፣ ወዘተ ‹‹ክልላዊ ብሄራዊ መንግሥት›› በማለት ድንበርና ወሰን ማካለል ወደማያባራ ግጭትና ጦርነት ህዝብን ይከተዋል፡፡ ዛሬ የማናየው በየቦታው የተከሰተው የ3.2 ሚሊዮን የህዝብ መፈናቀል የህወሓት/ ኦህዴድ ኢህአዴግ የፈለሰፈው በዘር እና በቌንቌ ላይ የተመሠረተ የፊዴራል መንግሥት ሥርዓት አወቃቀር ነው እንላለን፡፡

 

 

ሃገሪቱ የግብርና ምርት እንጂ የአካል ጉዳተኛ ምርት አያስፈልጋትም!!!

ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት እንፍታ!!!

በጦር መሣሪያና በኃይል የህዝብ ችግር አይፈታም!!!

ህወሓት/ ብአዴን/ ኦህዴድና ደኢህዴን/ ኢህገዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ምላጭ በመሳብ አረጁ፣ ዘመኑ የሚሻው ህሊናን መሳል ነው!!!

 

በኢትዩጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካል  ጉዳተኞች ይኖራሉ፡፡    ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

ደውሉ ለማን ነው?    For Whom The Bell Tolls?       / ፂዮን ዘማርያም

የትናንቱ ውጊያ ከኮረብታው ላይ፣ ሲያውድ የባሩድ ሽታ፣

በዛ ቅዝቃዜ! ሆድ ሲንቦጫቦጭ፣ ሙቀት በብርድ ሲረታ፣

የጠመንጃ ጩኸት፣ የተኩስ እሩምታ ሰማየ ሰማያቱን ሲነድለው

በዛ ውጊያ የጦር ጀነራሎቹ ትክክል ነበሩ …ማን አለና?

ለባድማ መሬት ብሎ ሰው ይሞታል፣ ግን ለምን? እነሱም አያውቁማ!!!

ያመረቀዘ ቁስላችን፣ ለእነሱ ክብርና ኩራት ሆናቸው!!!

በባድማ! ያ ሁሉ የደሃ ልጅ ረግፎ፣ የአምስቱ የጦር መኮንኖቹ  ሲሳይ፣

በሹመት ላይ ሹመት፣ በሜዳልያ ላይ ሜዳልያ፣ በበላይ ላይ በላይ፣

የእብደትና ህመም ደዌችንን፣ በእርግጥ ያውቃሉ ያሳለፉነውን ስቃይ፣

ታዲያ! ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ካጠፋ፣

የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ

ታዲያ ደውሉ የሚያቃጭለው ለማን ነው? ኩኩሉ ሳይል አውራ ዶሮው፣

የደሃ ልጅ የሆናችሁ፣የእናንተን ዕጣ ፈንታ ልንገራችሁ፣

ከመሞታችሁ በፊት፣ ቀኑን ተሠናበቱ፣ ሰማየ ሰማያቱን እያያችሁ፣

በመጨረሻ እስትንፋሳችሁ፣ ትሁን ንዛዜችሁ ለእናታችሁ!!!

ነፍሳችሁ ስታርግ፣ ትሰወራለች ቀስ ብላ ጥላችሁ፣

በድቅድቁ ጨለማ፣ በነጎድጎዳማ መብረቅ ሲርድ ሰማይ፣

ለተቀጨ ዓላማችሁ ብካይ፣ አጎሩ ለረገፈ መንፈሳችሁ ታላቅ ራዕይ፣

ነፍስ ረቂቅ ሚስጢር፣ እንግዳ ነገር ሆነች ዐይናችሁ ላይ፣

ፀጥታው ባርቆ ይሰማል፣ በዝምታ አድምጥ የልብህ ትርታ ካንተ ስትለይ፣

የብርሃን ጨረር ፈንጥቃ ለስንብት፣ በዚህ ዓለም ከተስፋ ሌላ አረ ምን ሊታይ?

ሞታችሁን ባናይ እንኮን፣ ያዩት ይመሰክሩ የሌት ጨረቃ የቀን ፀሃይ

የዓይነ ስውር ዓይን ሲበራ፣ ሞት በህይወት ልትረታ ትንሳኤ ላይ፣

ታዲያ እማማ፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ከገፋ፣

የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ

ድህነትና ርሃብ፣ በሽታና ሰደት ሳናጠፋ

በቌንቌ ተካለን፣ ማኛ ጤፍ ዘር ስንነፋ

ጦርነት አርግዘን ስናናፋ፣ ድንቁርናችን ምነው ከፋ

ዛሬም ወገን በወገን ላይ፣ በዘር ጦር ሰብቀን ስንነሳ፣

የባደማ ፆረና ሞት አልፈን፣ በወልቃይት፣ራያና አፋር ጦር ሜዳ ደንገላሳ፣

ታዲያ እማዬ ደውሉ የሚደወለው ለእኛ ሞቾች ነው?  ትንቢተ ትንሣዔ ራቀ ምነው?

ጦርነት ‹መቼም የትም አይደገም!!!› ሳንል! መፈናቀላችን ስለምን ነው! ሰደቱንስ መች ለመነው?

የሰው ልጅን ከኃጢያቱ እንፈውሰው፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው? ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

(እኔና አንተ ለምናውቀው፣ በባድማ ጦርነት ለቀበርከው ማሙሽና፣ ለኩኩሻ መታወሻ ትሁን)

ለኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የጦርነት ሠማዕታት ትሁን!!! ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!

(ኦክቶበር 10 ቀን 2018 ተፃፈ፣በማርች 18 ቀን 2019 በድጋሚ የቀረበ፡፡)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.