ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ ወግ ስብሰባ መዝጊያ ላይ ያደረጉት ንግግር ላይ ጓደኛቸው አቶ ለማ ስላደረጉት ንግግር ምንም ሳይተነፍሱ ቀርተዋል (ያሬድ ጥበቡ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ ወግ ስብሰባ መዝጊያ ላይ ያደረጉት ንግግር የሚደመጥ ነው። ብዙ ቁምነገሮችን አንስተዋል፣ የመጨረሻ ማሰሪያ ቃላቸውም በኢትዮጵያ ቀጣይነት ላይ መሆኑ ደስ የሚል ነው። ሆኖም ፣ ፓርቲያቸው ኦዴፓ በአዲስ አበባ ላይ የወሰደውን አቋም፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚያደርገውን ማፈናቀል፣ እርሳቸው በተገኙበት ስብሰባ የህዝብ ስብጥርን ስለመለወጥ ጓደኛቸው አቶ ለማ ስላደረጉት ንግግር ምንም ሳይተነፍሱ ቀርተዋል።

በአንፃሩ የባልደራሱ ስብሰባ ውጤት የሆነውን የነእስክንድር ነጋን የባለአደራ ኮሚቴ መደራጀትና እንቅስቃሴ አምርረው አውግዘዋል። ለምን ለማውገዝ እንደመረጡ ዘርዘር አድርገው በተናገሩ ጥሩ ነበር ። ሆኖም ያን ለማድረግ አልደፈሩም ፣ ወዮላችሁ ብለው አዲስ አበቤውን ማስፈራራት ነው የመረጡት። በምርጫ ቢሸነፉ ሥልጣናቸውን ለማስረከብ ዝግጁ መሆናቸውን በጣም በርግጠኝነት የተናገሩ መሪ፣ አዲስ አበቤው ከአብራኩ ባልወጡ የኢህአዴግ ካድሬዎች ከሚገዛ፣ በየቀበሌው ተሰብስቦ ከጎረቤቶቹ፣ ክፉ ደጉን ከሚያውቁለት ወገኖቹ መሃል የቀበሌና የወረዳ መሪዎቹን ቢመርጥ ለምን ዶክተር አቢይን ከነከናቸው?

እንደሚናገሩት ለዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ራሳቸውን ተገዢ የሚያደርጉ ከሆነ፣ የአንድ የአዲስ አበባ ቀበሌ ነዋሪ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያደርገውን ጥረት ለመኮነን ለምን ጨከኑ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ አዲስ አበባ ውስጥ የሚደረግ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ጥረት፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ የኦሮሞ ክልል ከተሞች ፍላጎት ጋር የሚቃረን አስመስለውም አቅርበዋል ። ሆኖም ይህ ምን ያህል እውነት ነው? ለምሳሌ ሱሉልታን ወይም ለገጣፎን ብንወሰድ፣ ለምንድን ነው የሱሉልታ ወይም ለገጣፎ ነዋሪ የአዲስ አበባ ቀበሌዎች በሰላማዊ ዴሞክራሲያዊና ግልፅ መንገድ ጊዜያዊ ህዝባዊ አስተዳደሮችን ቢመሠረቱ የሚከፉት? የጠቅላይ ሚኒስትሩ አረዳድ የተሳሳተ ነው።

አዲስ አበባ ውስጥ የሚደረግ ነፃ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የህዝብ አቅም ግንባታ፣ ሱሉልታንና ለገጣፎን ለተመሳሳይ ዴሞክራሲያዊ ተስፋ ያነሳሳቸዋል እንጂ፣ እንዴት አዲስ አበባ በነፃነት ይተዳደራል ብለው ቅር አይሰኙም። በእርግጥ በአዲስ አበባም ሆነ በሱሉልታ ወይም ለገጣፎ ኢህአዴግ ከባሌ ወይም አርሲ ወይም ጎንደር አምጥቶ የጎለተበት ካድሬ ቅር መሰኘቱ አይቀርም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በዚህ ሥልጣን ላይ ያሉት የካድሬያቸውን ፍላጎት ለማሟላት ሳይሆን፣ ሃገራችንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ተስፋ ለማሸጋገር በመሆኑ ፣ በአዲስ አበባ የተጀመረውን ለውጥ አንዲት ጋትም ቢሆን ወደፊት የሚያራምድ እንቅስቃሴ በበጎ ዐይን ማየት እንጂ ዛሬ በካድሬያቸው፣ ውሎ አድሮ በራሳቸው ሥልጣንም ላይ የሚመጣ አድርገው ማየት አልነበረባቸውም።

ይህንን ለማለት ያስገደደኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ምርጫው እስኪጠናቀቅ ከአቢይ በቀር ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሌለ መታወቅ አለበት” ብለው በአፅንኦት መናገራቸው ነው። ሃቁ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ የሚሠራ እንኳንስ እንቅስቃሴ ሃሳቡ እንኳ ያለው የለም ። ከዚህ በፊት በግሌ ለሽግግር ምክርቤት ምሥረታ ጥሪ አድርጌያለሁ። ይህንንም ሃሳብ ሳቀርብ ከምክርቤቱ የተውጣጣ የሥራአስኪያጅ ኮሚቴ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ምክትላቸውን በምክር እየረዳ ሽግግሩን በዴሞክራሲያዊ ተስፋ እንዲያጠናቅቅ ለማገዝ ነው። ወደዚህ እሳቤ የመራኝም፣ የቲም ለማ ቅቡልነት በብርሃን ፍጥነት እያሽቆለቆለ መምጣትና፣ የሃገራዊ ደህንነትና መረጋጋት በዚያው ፍጥነት እያሽቆለቆለ መምጣት ነው። ቲም ለማን የሚተካ፣ ሆኖም የሃገሪቱን እምቅ ሃይል የሚያንፀባርቅ የሽግግር ምክርቤት መኖር ፖለቲካ አመራሩን ስለሚያጎለብተውና፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ከኦዴፓ ተፅእኖና እስር ነፃ አድርጎ ፣ ያቺ የጌዶዎ እናት እንዳለችው “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆኑ የጌዶዎም መሆናቸውን” ለዓለሙ በማረጋገጥ፣ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና ተአማኒነት ያለው የፖለቲካ አመራር ማእከል ቢኖረን የተሻለ አማራጭ ነው በሚል ያቀረብኩት እሳቤ ነው። አሁንም ከዚህ የተሻለ ምርጫ ያቀረበ ፖለቲከኛ ወይም አሳቢ አላየሁም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህን ሃሳብ ሊጠሉትና ሊያጣጥሉት አይገባም ። ኢትዮጵያን የሚያህል የመቶ ሚሊዮኖች ሃገር በሳቸው ትከሻ ላይ ብቻ የተተወ እንዲሆን መፈለግ የለባቸውም። ቢያንስ የተቋም መልክ ካላቸው ሃገራዊ ሃይሎች የተመረጠ የሽግግር ምክርቤት ተቋቁሞ በሥራ ሊያግዛቸው ይገባል። ለዚህ ሃሳብ ፈፅሞ እምቢተኛ ከሆኑና ፣ የለውጥ አመራሩ ከኢህአዴግ ምክርቤት መውጣት የለበትም ብለው ካመኑ፣ ምክርቤቱን ስብሰባ ይጥሩና ሽግግሩን የሚመራዉ አካል እንዲመሠረት አድርገው፣ እነዚህም መሪዎች እነማን እንደሆኑ ህዝብ አውቆት፣ በአፋጣኝ ሃገሪቱ የምትፈልገው ሰላምና መረጋጋት ይመሥረት ።

“ሽግግሩን ግዴለም ለእኔ ተውት፣ እኔ አሻግራችኋለሁ” ብለው ቃላቸውን አምነን በተግባር የሆነው ግን ዛሬ የምንገኝበትን አዘቅት ስለፈጠረ፣ ዶክተር አቢይ አሁን የቀረቻቸውን ቅቡልነት አሟጠው ሳይጨርሱ፣ ራሳቸውን ከኦዴፓ እስርና እግረሙቅ አላቆ ነፃ በማውጣት በመከላከያውና ደህንነቱ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር አጥብቆ ኢትዮጵያን ወደተረጋጋ የዴሞክራሲ ተስፋ ሊያሻግር የሚችለውን የሽግግር ምክርቤት እሳቤ እድል ቢሰጡትና፣ ለዚህም ያላቸውን ድጋፍ በነገው ዕለት የተጠራውን የቀበሌዎች ስብሰባ ባለመተናኮልና፣ የሚገባውን የደህንነት ጥበቃ በመስጠት፣ ነፃ የወጣ ህዝብ ሊሠራ የሚችለውን ተአምር ለማየት ቢተባበሩ ተገቢ መስሎ ይሰማኛል።

ቢያንስ እንደ ምሁር፣ በተለይም ስለደህንነት አጥብቦ የሚያጠና ሰው በመሆናቸው፣ የአንድ ቀበሌ ህዝብ ነፃ ሲሆንና ራሱን ማስተዳደር ሲጀምር ከኢህአዴግ የተሻለ አመራር የመስጠት አቅም ይኑረው አይኑረው ለማየት ይችሉበት ይመስለኛል። በእኔ እምነት የሰፈሬ የአራዳ ሰው ተሰብስቦ ኢህአዴግ ከፋርጣ ካመጣውና “መኪና እንዳይበላው” መንገድ አሻጋሪ ከተመደበለት ካድሬ ይልቅ፣ የሰፈሩ ሰው ተሰብስቦ ከመሃሉ የሚያወጣው መሪ የተሻለ ብቻ ሳይሆን ማወዳደር እንኳ ሃጢያት እንደሚሆን ለዶክተር አቢይ ስናገር በልበሙሉነት ነው። ቦሌም፣ ለገጣፎም፣ ሱሉልታም ተመሳሳይ ነፃ ህዝባዊ ምርጫዎች ቢካሄዱ ከጥሙጋ፣ አርሲና ባሌ ከመጡት ካድሬዎችና ጨካኝ ከንቲባዎች ይልቅ፣ የነዚህ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ከመሃላቸው ብሶታቸውን፣ ፍርሃታቸውን፣ ተስፋቸውን የሚያውቅ መሪ የመምረጥ አቅማቸው የትዬለሌ ነው። የነገ ሰው ይበለን! ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር! የነገዎቹን ስብሰባዎች ለማገድ ወይም ለመተናኮል አስበው ከሆነ እባክዎ ከፈጣሪዎ ጋር ሲያለቅሱበት ይደሩ! እባክዎን! በህዝብ ነፃነት የተጎዳ ሃገር የለምና! ፈጣሪ ቀናውን ያሳይዎ!

6 COMMENTS

 1. ኦዴፓ/ ኦነግ: የእስክንድር: እንቅስቃሴ: አርበትብቶአቸዋል: ለምን?? እነሱ: ካስቡት: ቅዥት ጋር: ስለማይሄድ: በጣም: ያማል: እየሆነ: ያለው: ሁሉ: እነ: አብይ: ህዝቡን: ንቀውታል: ጃዋርን: የመስለ: አሽባሪ: እንደ ፈለገው: ሲሆን: ምንም: አይነት: ችግር: የለም: ለምን?? ይፈለጋል: ጃዋር: ከጀርባው: አይዞህ: ብሎ: የሚያበረታታው: እንዳለ: ግልፅ: ነው: ኦነግ: 18 ባንክ: ሲዘርፉ: ዝም: ተባሉ: ለምን?? ይፈለጋል: ስዎች: ከኦሮሞ: ክልል: በግፍ: ሲፈናቀሉ: ዝም: ይባላል: ለምን??: ይፈለጋል።
  የአዲስአበባን ኬኛን: ቅዥት: ለመተግበር: የአዲስአበባን: ወጣት: ማሽማቀቅ: ይፈለጋል: ነገር ግን: “እግዚአብሔር: ታላቅ: ነው: አይሳካላቸውም” የዋሁ: እስክንድር: ስላማዊ: እንቅስቃሴ: ስለጀመረ: አብይ : እልህ በተሞላበት: ሊያስፈራራ: ፈለገ: አህያ ውን: ፈርቶ: ዳውላውን ይሉታል: ይሄ ነው: እውነት: ሁሌም: አሽናፊ: ናት: ድል: ለዲሞክራሲ: ኢትዮጵያ: ለዘላለም: ትኑር።

 2. I used to believe that Yared Tibebu is one of those rational politicians. But with some of his writings he has already justified that I was wrong. His writings unmasked his true personality. Now I realized that Girma Kassa was shaped and thought by Yared Tibebu concerning his political stands. That is why Girma Kassa writes here and there his nonsense pieces about the so called Shewa.

  Yared Tibrbu tries sometimes to sell himself as someone who has been struggling for the rights of the whole Ethiopian peoples. But he is one of the anti-Oromo elements. He can keep on his nonsense. The Oromo are self sufficient to protect their natural rights and to regain all their political and economic rights in thier fathers’ land, Oromia sooner or later. Watch out!

 3. Yared Tibebu and Dawit Woldegeorgies are the worst ultra nationalists of the Amharic speakers. Dawit Woldegeorgies accuses the PM Dr. Abiy Ahmed as an incompetent leader. This stupid guy from the Derg era consider himself as a brilliant and competent intellectual of our time. But he is good only for nothing. His writings are full nonsense. He has been selling himself as expert on Africa by the help some Americans. He is one of the hardliners from the Amhara community who believes firmly in the superiority of the Amahara elites. His concerns were never about the ordinary Amahara people throughout his life. He works only for his belly like a pig.

  Yared, Dawit and Eskinder Nega and their friends have been suffering with the mentality of racism like some of the former white south Africans who grew up in the culture of Apartheid. Likewise Eskinder and his associates behave like some racist white settlers of Southafrica who tried to claim their own state within Southafrica at the beginning of the 90th. Those individuals were growing up with the mentalities of apartheid and they cannot accept the Africans as an equal human being. Therefore, it was a shame for them to live with the Africans as an equal citizen. We have been entertaining such latent apartheid and segregation mentalists in Ethiopia since the Era of Menelik. For them the Oromo nation is subhuman and it’s cultural and social values are irrelevant. But now the time of such individuals with antihuman mentalities is up. No more segregation and discrimination of the Oromo nation and it’s culture and laguage in it’s own homeland. The sleeping giant is awake. 

  Cheap propoganda  is not helpful  for you and your associates. No power on earth will stop the Oromo people from fulfilling its aspirations as a freedom loving nation to regain its human dignity and rights. It is up to you to respect this great nation for the sake of your own benefits. 

  Let me make it clear: Your malicious politics will never work in the new Ethiopia. The scramble for Oromia like the Menilik’s era is no more possible. The  persistent stubbornness and greediness of the ultra nationalists like you will help even more as a fuel in strengthening and speeding up the de-Amaharaization of the whole Ethiopian politics in order to substitute it with the politics of a true multinationalism. 

  While you are pointing to the others with one finger, three of your fingers are pointing at you. Stop your hypocrisy! First of all  you have to clear yourself. You have been waging war on the Oromo people with the help of your media ESAT and your organization Ginbot 7. Last time the rude and arrogant Berhanu Nega has declared war on the Oromo properties in Finfinne as soon as he arrived in Finfinne. Your associates have been campaigning against the beloved Oromo  leaders like Obbo Lemma Megerssaa, Takle Uma, Jawar Mohammed and others. But such nonsense will be helpful for strengthening the unity of the Oromo people.

 4. “በየቀበሌው ተሰብስቦ ከጎረቤቶቹ፣ ክፉ ደጉን ከሚያውቁለት ወገኖቹ መሃል የቀበሌና የወረዳ መሪዎቹን ቢመርጥ ለምን ዶክተር አቢይን ከነከናቸው?”

  የምትገርም ሰው ነህ:: አንተ ይህንን አሜሪካ ማድረግ ትችላለህ: ህጋዊ መንግስት እያለ ህገወጥ ምክር ቤት አታቋቁምም:: ትታሰራለህ:: ችግሩ 27 አመታት ተረግጦ መገዛት የለመዱ ሰዎች ሙሉ ነፃነትን ለመተግበር እየተቸገሩ እንደሆነ እያየን ነው:: የመንግስት ስራ ህግንና ስርአትን ማስከበር ስለሆነ ዶክተር ዐቢይ ይህ ሁሉም በፍቅር ስርአት ይይዛል ከሚል ህልም በአስቸኳይ መውጣት ይኖርበታል:: ህጋዊው መንግስት በዚህ ወቅት የዐቢይ መንግስት ነው:እስክንድር መንግስት መሆን ከፈለገ በግልፅ የፖለቲካ ድርጅት ተቀላቅሎ ለህዝብ ምርጫ ይቅረብ::
  ሌላው ስለአዲስ አበባ ካድሬዎች አንስተሀል የእናንተው የልብ ወዳጆች እነበረከት ስምኦን ያዋቀሩዋቸው ናቸው::

 5. በጣም የሚገርም ፖለቲካ በሃገራችን አየተካሄደ ነው። ጠቅላዩ ፯ኛው ንጉስ ደግሞ ንግግር ከማብዛታቸው የተነሳ ኣንዱን ካንዱ ማጋጨት ጀምረዋል። አረ ለመሆኑ ለዙፋኖ የሚያሰጋው የወያነ ቡቺላው ጃዋርና ጓደኞቹ ወይንስ አስክንድር ነጋ ነው? ኦዲፓ ስራውን በደንብ ቢሰራ ኖሮ አስክንድርም የጋዜጠኝነት ስራውን ተረጋግቶ ይሰራ ነበር። ነገር ግን አይምርዋቸው በጠባብነት ከተያዘው ጥቂት ግለሰቦች የሚወጣው መርዝ ከተማዋን ሰላም አየነሳት በመሆኑ አንድ ለማለት መነሳቱ አንደዜጋ ትክክልና ኣስፈላጊ ነው። ንጉስ ሆይ፤ ይህ አንቅስቃሴ ግን የርሶን ዙፋን በምንም መልኩ አያውከውም። አንደውም ለችግሩ መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል። አክባሪዎ።

 6. Gemada, you are simply moron , imbecile gala, nothing more nothing less, whom do you think you can throw into confusion ?!, the politics of the galas are all based on fabricated stories and you will lose as ever , bastard moron gala !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.