ዛሬ ባህርዳር ላይ ስብሰባ የጠራው ግንቦት 7 ነው። መሳሪያ ይዘው በመውጣትም ተቃውሞ ያደረጉት የግንቦት 7 ወታደሮች የነበሩ ናቸው

ውብሸት ሙላት

የግንቦት 7 ወታደሮች ወረታ ካምፕ ውስጥ ተጥለው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ይታወቃል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋም ባህር ዳር ብዙ ጊዜ ቢሄዱም ወረታ በመሄድ የወታደሮቹን ችግር ለመፍታት፣ያለምንም ዓይነት ሥራ እንዲቀመጡ የተደረጉትን፣ ጥረት ማድረግ ይገባቸው ነበር።

የኦነግ፣ የኦብነግ፣ የአድኃን፣ የአርበኞች ግንባር ወታደሮችን ክልሎቹ የተቀበሏቸው ሲሆን የግንቦት 7ን ግን የፌደራል መንግሥት እንዲረከባቸው እነ ፕ/ር ብርሃኑና አንዳርጋቸው ጽጌ ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር።

ይህን ባለማድረጋቸው የተቀየሙ ወታደሮች መሳሪያ ይዘው ቢመጡ በዋናነት መወቀስ ያለበት ራሱ ግንቦት 7 ነው። ለዚያም ይመስላል ወደ ወረታ ያቀኑት። በግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች እንደተካዱ የቆጠሩት ወታደሮች ድርጊት አሁንም በድጋሜ መወቀስ ያለበት ግንቦት 7 ነው።

ከዚያ ውጭ ያው የሰልፍ አደራረግ ሕግ (ሰልፍ ሲደረግ በሕግ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላትን በሚመለከት ሳይዛነፉ አሟልቶ) የሚጠይቀውን መስፈርት ማሟላት፣ መጣስ በፍጹም የለበትም

 

1 COMMENT

  1. ኣብኖች !
    ግንቦት 7 በጠራው ስብሰባ ስለተነሳው ውዝግብ የናተን መግለጫ/ኣቁዋም በናፍቆት እየጠበኩ ነው።ዝም ልትሉ ከቶ ኣይገባች ሁም !
    በቅርቡ በደሴ የተፈጸመውን እናስታውሳለን።
    Thanks

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.