አዴፓ ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ውይይት የተለያዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሜቴው በክልሉ ያለውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች በተመለከተ የተለያዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል፡፡

ለሁለት ቀናት በቆየው ግምገማ ለውጡን ለማስቀጠል የሚረዱ ተግባራቶች ጥሩ ቢሆኑም በሂደቱ ግጭቶች እና የሰላም ውስንነቶች መፈጠራቸውን ገምግሟል፡፡

በዚህም ለውጡን ለማጠናከር በሚያስችል ሁኔታ አመራሩን የማጠናከር ሥራ መሠራቱን የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮሐንስ ቧያለው በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል፡፡

ከሰሞኑ በደሴና በባህ ዳር ከተማ ከህብረተሰቡ የሰላም ፍላጎት ጋር የሚጣረሱ የተፈፀሙ ተግባራት ህገ ወጥና ተቀባይነት የላቸዉም ብለዋል፡፡

ተግባራቱ በአዴፓም ሆነ በክልሉ መንግስት ተቀባይነት የላቸዉም፣ በመሰል ተግባራት የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ፓርቲው አሳስቧል፡፡

በለውጥ ሂደቱ የተገኙ መልካም እድሎች እና የህዝቦች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እየተረጋገጠ መምጣቱን ፓርቲው ገልጾ፣ በሂደቱ ያጋጠሙ የፀጥታና አንዳንድ ችግሮች ተከስተዋል ብለዋል አቶ ይኃንስ ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በክልሉ መረጋጋት እየተፈጠረ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ሰፊ የህዝብ መነሳሳት የተፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል።

የህግ የበላይነት ከማክበር አኳያም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮች እንዳሉ ፓርቲው ገልጾ ይህም ቀስ በቀስ እየተስተካከለ መምጣቱንና ከጉረቤት ክልሎች እና ህዝቦች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እየተከናወነ ያለውን ስራም በጥንካሬ መገምገሙን አመልክቷል።

የህግ የበላይነት ከማክበር አኳያም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮች እንዳሉ ፓርቲው ገልጾ ይህም ቀስ በቀስ እየተስተካከለ መምጣቱንና ከጉረቤት ክልሎች እና ህዝቦች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እየተከናወነ ያለውን ስራም በጥንካሬ መገምገሙን አመልክቷል።

ፓርቲው ከሁሉም ህዝቦችና እህት ድርጅቶች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዳለው ገልፀው፣ የሚኖሩ የሀሳብ ቅራኔዎችም ዲሞክራሲያዊ በሆነ ውይይት መፈታት እንዳለበት እንደሚያምንና በዚህ በኩልም የሀሳብ ቅራኔዎችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የአዴፓ የጽ/ቤት ኃላፊው አመልክተዋል።

ማእከላዊ ኮሚቴው አስተማማኝ ሰላምና የህግ የበላይነት እንዲከበርም ፓርቲው ለህዝቡ ጥሪ አስተላልፏል።

ሪፖርተር፡- ስመኘው ይርዳው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.