በዶ/ር አቢይ አንድ ዓመት አገዛዝ የመሬት ወረራ፣መጤ ሰፋሪና አዲስ አበባንና ሁሉንም ኬኛን ቀፋፊ ስሞች ሰማን

ወንድወሰን ተክሉ

ብዙም ሳንርቅ ይህን ጸሀፊ ዶ/ር አቢይ እራሳቸው አስገድደው ተቃዋሚያቸው አድርገውታል፡፡ በክህደታቸውም በርካታ ደጋፊዎቻቸውን ሜዳ ላይ ያለምንም ይሉኝታ በትነዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በአስራ አንደኛ ወራቸው ላይ ሆነው ነው፡፡ እንግዲህ የመረጡትን እየሰጠን ነው፡፡ የእሳቸው ምርጫ እኛን ባእድ አድርጎ ጠላት ማድረግ ሆነና ይመቾት ብለናቸዋል፡፡

የክቡር ዶ/ር ጠምር አንደኛ ዓመት በዓለ ሲመት በሸርስተን እየተከበረ ነው፡፡በከፍተኛ ወጪ ድግስና ውሎ አበል ለሰበሰቧቸው ወገኖቻችን አሞግሱኝ፣አድንቁኝ አጨብጭቡልኝ ቢሉም ወቀሳ ስለተቸራቸው ጦፈዋል፡፡
በአንድ ዓምእት ቆይታቸው ያየነውን ድቃይና መከራ እማላውቀው ሰው በዝርዝር አስቀምጦት ሳገኝ ላቅርቤዋለሁ ፡፡ ሌሎቻችሁ ደግሞ ጥሩ ስራ የተባለውን አስፍሩላቸው፡፡

****
በጠቅላይ ሚንስተሩ አብይ አህመድ ዘመነ መንግስት

– ኢ/ር ስመኘው ተገደለ

– አባይ ግድብ ተቋረጠ

– 23,000 በብሔር ግጭት ሰው አለቀ

– 3.1 ሚልዩን ህዝብ ተፈናቀለ

– መስጊዶችን ቤተክርስቲያኖች ተቃጠሉ

– የሃይማንት አባቶች የአገር ሽማግሌዎች ተደበደቡ

– ሁለት ዩኒቨርሲቲ የብሔር ግጭት ማእከል በመሆናቸው ተዘጉ

– ወላጆች ልጄ ዩኒቨርሲቲ ይማርልኝ ብለው ልከው ሬሳ ተቀበሉ

– አዲስ አበባ የኛ ናት ተብሎ ለ12 አመታት ገንዘቡ ቆጥቦ ዛሬ ነገ ቤት ይደርሰኛል ሲል የነበረ ህዝብ ተሸማቀቀ

– ቤቶች በዶዘር በብሔሩ ምክንያት ፈረሰ

– የተፈጥሮ ድርቅ ሳይኖር በመንጋዎች ጌዴኦዎች ከአገራቸው 1,000,000 ህዝብ ተፈናቅለው እህል የሚያደርስላቸው አጥተው በርሃብ ተገረፉ፣ አለቁ።

– ባንኮች ተዘረፉ።

– ዜጎች ተገድለው ተቃጠሉ። ስርዓት አልበኝነት በየቦታው ሰፈነ። ቆመጥ፣ ሜንጫና ገጀራ ነገሰ።

እንግዲህ ዶ/ር አብይ አህመድ ከእቅዳቸው 1% ይህን ሁሉ ከሰሩ 2% ቢሰሩ ኖሮ አገሬ ምን ይውጣት ነበር?

የዶ/ር አብይ መርሕ ምንድነው?

– የኢኮኖሚ ፖሊሳችን እስከ አሁን ተለይቶ የታወቀ ነገር የለም። አዳዲስ ፕሮጀክቶች ለመስራት ይቅርና የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ተቃርጠዋል ።

– የውጭ ጉዳይ ፖሊሳችን ምን ይመስላል ብለን ስንጠይቅ ዶ/ር አብይ ከጎሮቤት አገሮች በአግባቡ የማይታወቁ ፊርማዎች እየተፈራረመ ሲሆን አንዳችም ውል ወደ ፓርላማ ቀርቦ የፀደቀ ነገር የለም።

– የፖለቲካ መርሕ ምን የመስላል? እስከ አሁን የታወቀ ነገር የለም።

በዚህ አንድ አመት አንድም ቀን ትልቁ ጠላት የሆነውን ድህነትን ለማጥፋት መሰራት ስላለባቸው ስራዎች ሲያወራ ሰምተን አናውቅም።

አገሪቷን ህወሓት ከዘፈቃት የብሔር ቀውስ ሊያወጣ የሚችል ስትራቴጂ ሲያቀርብ አላየንም። በአንፃሩ #አንደራደርም የምትለዋን ቃል ከሚመሩት የፓርቲያቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል።

ዶ/ር አብይ የእቅድዎን 2% ሳይሰሩ እባክዎ ከስልጣን #ይውረዱ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ለፋይናንሺያል ታይምስ ከዚህ ቀደም በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ብዙ የሰራኋቸው ቢኖሩም ከእቅዴ አንፃር ግን የሰራሁት 1% ብቻ ነው ብለው ነበር።

የሰሯቸው ስራዎች ከላይ የተዘረዘሩት ሲሆኑ ከእቅዳቸው አንፃር የእቅዳቸው አፈፃፀምስ 2% ቢሆን ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትኖር ይሆን?

2 COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.