በባህርዳር የሚገኘው የአባይ ድልድይ በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአባይ ድልድይ ለማስገባት በዛሬው ዕለት ስምምነት ተፈረመ፡፡

በባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ጥያቄ ሲነሳበት የቆየው ይህ ድልድይ በ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ነው የሚገነባው፡፡

ይህን ድልድይ ለማስገባት የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ግንባታውን ከሚያከናወነው ሲሲሲ ከተባለ የቻይና  የኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ውል ተፈራርመዋል፡፡

የፊርማ ስነ ስርዓቱም የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

(fana)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.