በእስክንድር ነጋ ዙሪያ ጣል ያደረጉት ቁም ነገር ! “ብረት ለበሱ ….እስክንድር ነጋ” (ከ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

” …አሳሪዎቹም ጉልበታቸውን ከጭንቅላታቸው አላወጡም! ታሳሪውም አልሰለቸውም…. “

አንዲት የአሜሪካ ሴት ልጇን አንድ ሰካራም መኪና እየነዳ ሲሄድ ገጭቶ ገደለባት፤ እርር! ድብን! ብላ አዘነች፤ አልበቃትም፤ የአንድ ሰው ትግል ጀመረች፤ አሜሪካን አዳረሰችው፤ እናቶች ሁሉ ተሰባሰቡላት፤ ከዚያ ቀስ እያለ ሌሎችም ሁሉ እየገቡበት ትልቅ አገር-አቀፍ ንቅናቄ ሆኖ እየጠጡ መንዳት በሕግ እንዲከለከል አደረገች፤ በዚች በአንድ ሰው ብርታት አሜሪካ የተሻለ አገር ሆነ።

በኢትዮጵያችን በየቀኑ ቤት እየፈረሰ ሰዎች እንደአበሻ አገር ቆሻሻ በየመንገዱ ላይ እየተጣሉ ሲያለቅሱ እናያለን፤ መንግሥት አለ? ማንም ምንም አያደርግም፤ መንግሥት አለ? ባለሥልጣኖቹም የማፍረስ ትእዛዛቸውን ያስተላልፋሉ፤ አፍራሾቹም ሥራቸው አድርገውት ያፈርሳሉ፤ መንግሥት አለ? እንዲያውም ለምዶባቸው ቅርስ የተባለውን የደጃዝማቹን ቤት አፈረሱት! መንግሥት ማለት አፍራሽ ግብረ ኃይሉን የሚቆጣጠረው ነው መሰለኝ!

ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል እንደሚባለው ሆኖ እስክንድር ነጋ የሚያለቅሱትን ሰዎች አስተባብራለሁ ብሎ ተነሣ፤ ጠጠር አንወረውርም እያለ! የፍቅር፣ የመደመር፣ የይቅር ባይነት ዲስኩር ትዝ ብሎት፣ የክርስቶስን ትምህርት አስታውሶ ለተገፉትና ተስፋ ለቆረጡት ተናገረ፤ በሕግ ተማመኑ ብሎ፤ ይለይልህ ብለው ራሱን አስፈራሩት! እኔ ሳውቅ እስክንድር ነጋ ሲታሰር ሲፈታ ሠላሳ ዓመታት የሆነው ይመስለኛል፤ አሳሪዎቹም ጉልበታቸውን ከጭንቅላታቸው አላወጡም! ታሳሪውም አልሰለቸውም! እኛም አልተለወጥንም!

2 COMMENTS

  1. “አሳሪዎቹም ጉልበታቸውን ከጭንቅላታቸው አላወጡም! ታሳሪውም (እስር) አልሰለቸውም! እኛም አልተለወጥንም!” ትክክል ብለዋል “ፕሮፈሶር”! እርስዎ የቀድሞ ስርዐት ናፋቂነትዎን፣ እስክንድርም በቀደመው የኢህአፓ የሽብር ስልት ሃገርን በመበጥበጥ ለስልጣን መቋመጥን፣ አሳሪዎቹም የመደብደብ፣ የማሰርና የመግደልን ልምድ አልተዋችሁም!

    “Die reinste Form des Wahnsinns ist es, alles beim alten zu belassen und zu hoffen, dass sich etwas ändert.” A. Einstein.
    በኔ ትርጉም፣ “የመጨረሻው የዕብደት መልክ፣ ሁሉንም እንደነበረው ትቶ፣ አንድ ነገር ይቀየራል ብሎ መመኘት ነው!”

  2. ፕሮፌሰር መስፍን በንጉሱ ዘመን የተማሪውን ትግል ስለደገፉ በግዞት ግምቢ ሃገርገዥ ሆነው በዚያም ትግሉን በመቀጠላቸው ተነስተው ነበር:: በደርግ ዜመን የብሄረሰቦች ጥናት ሲባል የኢትዮጲያ አንድነት ጥናት ይሻላል ብለው መንግስቱን ፊትለፊት ሲናገሩ ከጥንት ጀምሮ አባቶቻችን ያቆዩንን ሃገር በብሄርሰብ አንከፋፍል ያሉት ትንቢት በወያኔ ተፈጸመ:: ደርግ ሊወድቅ ሰሞን የባለኣአደራ መንግስትና ሃገራዊ እርቅ ሲሉ ደርግ የሃገር ጉዳይ የባልናሚስት ጉዳይ አየደለም ብሎ ተሳልቅቆባቸው ነበር:: ወያኔ ገና ከመግባቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን መረሸን ሲጀምር የሰውልጅ መብት አስከባሪ ድርጅትን በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰርቱ ፕሮፌሰር መስፍን ነበሩ::ከዚያም ከባልደረቦቻቸው ጋር ቅንጅት ፓርቲን መስርተው ምርጫውን በከፍተኛ ደረጃ ሲያሸንፉ ወያኔ የምርጫ ካርዶቹን ሰርቆ ምክር ቤቱን ተቆጣጥሮ በግፍ ሲገዛ ፕሮፌሰር መስፍንና ባልደረቦቻቸው በወያኔ ጀሌዎች ሲሰደቡ በስተርጅና ሲደበደቡ ከርመው ታሰሩ:: ሲፈቱም ፕሮፌሰር ስያታክቱ ወያኔን በግሩም ብእራቸው ሲፋለሙ ቆይተዋል:: በቲም ለማ የበጎ ትግል ጅማሬ የመጀመሪያው አድናቂ ፕሮ መስፍን ሲሆኑ ብዙዎች ተሳቅለውባቸው ነበር:: የነአብይ መንግስት የከፋ ግድያ በመሰቀል አደባባይ በመሪው ጭምር ሲያደርጉ ከቡራዩ ጀምሮ እስከምእራብ ወለጋ ኦነግ ሸኔና ባለሜምጫው ጃዋር ጃዋር ዜጎች ፈግተው የሰሩትን ቤት እንዳይረከቡ ደም ይፈሳል ብሎ ሲዝት ምንም ያልተነፈሰ ጭራሽ ለጃዋር ባልደረቦች ቤት የሸለመ የአብይ አስተዳደር ባለሜንጫውን ጃዋርንን ትቶ ባለብእሩን እስክንደርን ያለኣአግባብ በጦርነት ቅስቀሳ ሲከስና በጀሌዎቹ መጠነ ሰፊ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲጀምር የሰሜን አሜሪካ ምሁራን ከላኩ የማሳሰቢያ ደብዳቤ ለየት ያለ ጥብቅ ተችን ለኣአብይ ኣአህመድ መንስግት ፕሮፌሰር መስፍን ማቅረባቸው የሚመሰገን የተለመደ የሃገርና ይህዝብ ባለአደራነታቸውን የሚያሳይ ነው:: በዘር መነጽር በማየት መተች ያስተዛዝባል::የፕሮፌሰር መስፍንን መልካም ስራ የሚያጠለሹትን መቸም ሃቅን ይሰማሉ አየሰሙም ያያሉ አያዩም ብሎ ቅዱስ መጽሃፍ የገለጻቸውን ማሳመን ባይቻልም የፕሮፌሰሩን ሃቀኛ ታሪክ መከተብ ግን የግድ ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.