ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስክንድር ነጋን በተመለከተ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኘው የዜጎች ተቆርቋሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሰጡት መልስ

የተከበራችሁ በሰሜን አሜሪካ የምትገኙ ተቆርቋሪ ዜጎች

ለሀገራችሁና ለሕዝባችሁ በመቆርቆር፣ ሀገራችሁም የተሻለችና የሠለጠነች እንድትሆን በማሰብ የጻፋችሁትን መልእክት ተመልክቼዋለሁ፡፡ እንደ እናንተ ካሉ በሳል ዜጎች የሚጠበቀውም ይሄው ነው፡፡ ችግሮችን በጨዋነት በመመካከርና የተሻለ የመፍትሔ ሐሳብ በማቅረብ መፍታት እንደሚገባ የእናንተ ተግባር አርአያ የሚሆን ነው፡፡

በሀገራችን የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ ያነሣችሁት ሐሳብ ሁላችንም የምንጋራው ነው፡፡ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ማናቸውም ዓይነት መብቶቻቸው ተጠብቀው፣ በየትኛውም አካባቢ የመኖር፣ ሀብት የማፍራትና የመዘዋወር መብት እንዳላቸው መንግሥት ያምናል፡፡ ይሄንንም ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው፡፡ በአንድ በኩል ሕዝባችን የጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ የፈነጠቀውን ተስፋ ለማጨለም በሚሠሩ አካላት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በቢሮክራሲው ውስጥ ያሉ ኃላፊዎች ችግሮችን በእንጭጭነታቸው ለመፍታት ባለመረባረባቸው የተነሣ የዜጎቻችን መፈናቀል መከሠቱን እናምናለን፡፡ ይህም አጥብቆ ያሳዝነናል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ባለፈው አንድ ዓመት በክልሎችና በፌዴራሉ መንግሥት የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ከመጋቢት 2010 ዓም በፊት በሀገራችን ከልዩ ልዩ ቦታዎች የተፈናቀሉ 1,179,061 ያህል ዜጎች ነበሩን፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት 1,581,058 ያህል ወገኖቻችን የመፈናቀል አደጋ ገጥሟቸዋል፡፡ ከመጋቢት 2010 እስከ አሁን 1,020,234 ያህል ወገኖቻችን ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ተመልሰው ቋሚ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡ አሁን በመጠለያዎችና በሌሎች ቦታዎች ሆነው ርዳታ የሚደረግላቸው ዜጎቻችን 1,739,885 ያህል ናቸው፡፡ እነዚህንም ወደ ቋሚ ኑሮ ለመመለስ እየሠራን ነው፡፡ ለእኛ ዋናው ቁጥሩ አይደለም፡፡ አንድም ዜጋ ቢሆን ያለ ፈቃዱ ከሚኖርበት ሥፍራ እንዳይፈናቀል መሥራት አለብን፡፡ ፈተናው ለብዙ ዘመናት ከተከማቹ ሀገራዊ ችግሮች ጋር የተሣሠረ በመሆኑ በአንድ ጊዜ ከምንፈልገው ውጤት ላይ አልደረስንም፡፡ በሂደት ግን ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ ነው፡፡ እንደ ታማኝ በየነ ያሉ የወገኖቻቸው ሁኔታ የሚያሳስባቸው ዜጎች ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ እያየን በመሆኑ ችግሮቻችን እድሜያቸው እንደሚያጥር ርግጠኞች ሆነናል፡፡

እስክንድር ነጋን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ሰብአዊ መብትም እንዲከበር ያደረገውን አስተዋጽዖ እኔም የማደንቀው ነው፡፡ ለዚህ ተጋድሎውም ተገቢው አክብሮት አለኝ፡፡ ያነሣቸውን አንዳንድ ሐሳቦች በተመለከተ ግን መፍትሔው ውይይት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በቅርቡም ባነሣቸው ጉዳዮች ላይ እንደምንወያይ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ባነሣቸው ሐሳቦች ምክንያት በመንግሥት በኩል የሚደርስበት ምን ዓይነት ጫናና ችግር አይኖርም፡፡ ይህን የማናደርገው መንግሥት ለሐሳብ ብዙኅነት ያለው አቋም የማይነቃነቅ በመሆኑ ነው፡፡ የለውጡ አንዱ ምሦሶ ሐሳብን በነጻነትና በኃላፊነት የመግለጥ መብት ነው፡፡

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባለፈው አንድ ዓመት የተለያዩ ተግባራትን አከናውነናል፡፡ የመከላከያና የጸጥታ አካላትን የማሻሻያ ሥራ ሠርተናል፡፡ የመከላከያ ሠራዊታችን በአደረጃጀት፣ በፕሮፌሽሊዝምና በትጥቅ ሀገሩን ለመጠበቅ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ለማስቻል አመርቂ ሥራ ተከናውኗል፡፡ በብሔር ተዋጽዖ ኢትዮጵያን የሚመስል እንዲሆን እየተሠራ ነው፡፡ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ በሕገ መንግሥትና በሀገሪቱ ሕጎች ብቻ የሚመራ ተቋም እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ የማረሚያ ቤቶችን የታራሚዎች አያያዝ ለማስተካከል ሞክረናል፡፡ የፍትሕ ተቋማትን የማሻሻያ ሥራ ጀምረናል፡፡ ከዴሞክራሲና ከሰብአዊ መብቶች ጋር የሚቃረኑ ሕጎችን የማሻሻል፣ አሁን ላለንበት ነባራዊ ሁኔታ የሚመጥኑ ሕግጋትን የማዘጋጀት ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን በቂ ናቸው ብለን አናምንም፡፡ የሕግ አስከባሪ አካላትና ማኅበረሰቡ ለሕግ መከበር የአመለካከት ለውጥ ማምጣት አለባቸው፡፡ ዴሞክራሲ ያለ የሕግ የበላይነትና ያለ ሥነ ምግባር ሊተገበር እንደማይችል ማስተማር እንደ እናንተ ካሉ ሊቃውንት እንጠብቃለን፡፡ የወረስናቸውን ችግሮች ሁሉ በአንድ ጊዜ ለመፍታት የምንችልበት ዐቅም የለንም፡፡ የተለያዩ አካላት የየድርሻቸውን እየተወጡ ሲሄዱ፣ ተቋማዊ ዐቅማችንም ሲዳብር፣ የሕዝባችን አመለካከት ከሚጠበቀው ደረጃ ላይ ሲደርስ የሕግ የበላይነት ይበልጥ እየተረጋገጠ እንደሚሄድ እናምናለን፡፡

ረዥሙን የለውጥ ጉዞ ጀመርን እንጂ አልጨረስነውም፡፡ ካሳለፍነው ይልቅ ከፊታችን ያለው ረዥም ነው፡፡ እንዲህ እንደናንተ ያገባናል የሚሉ ዜጎች በሰከነ መንገድ ለሀገራቸው የሚችሉትን ሁሉ ሲያበረክቱ ነገ ከትናንት የተሻለ ይሆናል፡፡ ጀግናውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይዘን የማንፈታው ችግር አይኖርም፡፡ መንገዳችን ቢለያይም የሁላችንም ፍላጎት የበለጸገች፣ የሠለጠነች፣ አንድነቷ የተጠበቀ፣ በዓለም ፊት በሞገስና በኩራት የምትቆም፣ ዴሞክራሲና ፍትሕ የሰፈነባት፣ ዜጎቿ የትም የሀገሪቱ ክፍል በሰላምና በጤና የሚኖሩባት ኢትዮጵያን መገንባት ነው፡፡ ጉሙ እየተገለጠ፣ ፀሐይዋም ይበልጥ እየወጣች ትሄዳለች፡፡ ያገኘነውን ሀገርን የማሳደጊያ ዕድል ተጋግዘን በጠንካራ መሠረት ላይ እንድናቆመው በዚሁ አጋጣሚ የሀገራቸው ጉዳይ ለሚያሳስባቸው ሁሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር

ኢትዮጵያ: አዲሲቷ የተስፋ አድማስ        Ethiopia: A New Horizon of Hope

ግልጽ ደብዳቤለክቡር ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ (በአሜሪካ ከምንገኝ ተቆርቋሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን)

5 COMMENTS

 1. የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር ለዜጎች ጥያቄ በዚህ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ተሰምቶ አይታወቅም። ዶ/ር ዐቢይ ሊመሰገኑ ይገባል። እስቲ ምሑራን ከዚህ ይማሩ ይሆን? እስክንድር እያደረገ ያለው ትልቅ ስህተት ራሱን አጀንዳ ማድረጉ ነው! ስለ እስክንድር በማውራት ጊዜ አናጥፋ። ከዚህ ቀደም መታሰሩ ቁምነገር መሆን የለበትም። አሁን በሚሠራው ቁምነገር እንገምግመው! የአገራችን ጉዳይ ከአንድ ግለሰብ የሥልጣንና ዋነኛ የመሆን ምኞት ያልፋል። እስክንድር አንዴ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር፣ ከዚያ ከኦቦ ለማ ጋር፣ ከዚያ ከታከለ ኩማ ጋር። አንዳች የሚናገረው በጎ ነገር የለም፤ መንቀፍ ብቻ። ከዚያ ባልደራስ ሆቴል ስብሰባ ጠራ፤ ተናጋሪ እራሱ፣ ጥያቄ መላሽ እርሱ፤ መድረኩን ያስጌጠው ምስል የርሱ። የሚገርመው እስክንድር የሚከሰው ጃዋርም ያው መሆኑ ነው። ጃዋር ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ሚሊንየም አዳራሽ ውስጥ ለኦቦ ለማ ላፕቶፕ ስጦታ አቅርቦለታል። በላፕቶፕ ህወኃትን ተዋጋሁ፣ ቄሮን አደራጀሁ ማለቱ ነበር! የተጋደለው፣ የሞተው፣ የታሰረው ቄሮ። ሙገሳ በስርቆሽ በር የተቀበለው ጃዋር። የሁለቱ አንዱን ጽንፈኛ፣ ሌላውን “ነፍጠኛ” መባባል ይልቅ የሠፈር ልጆች ጨዋታ አስመስሎታል። የአብዛኛው ሕዝብ ስሜት፣ ኦሮሞ ሆነ አማራ፣ ማይክሮፎኑን ጨብጠው የሚያደነቁሩንን ዓይነት ስሜት አይደለም። ሕዝብ በልቶ ለብሶ ልጆቹን አስተምሮ በሰላም መኖር ነው የሚናፍቅ!!

  ዶ/ር ዐቢይና ኦቦ ለማ ያለባቸውን ኃላፊነት እንረዳላቸው እንጂ። የኢሕ አዴግ አባሎች ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፓርቲ ኢሕ አዴግ ብቻ ነው። ኢሕ አዴግ የተዋቀረው በጎሳ ክልል መሠረት ላይ ነው። እነ ዶ/ር ዐቢይ ይህንን አላመጡም። ቀጭን ት እዛዝ ሰጥተው የፈለጉትን ማስፈጸም አይችሉም። ኢህ አዴግ፣ ህወኃት ለራሱ ሥልጣንና ለዘረፋ ያቀናበረው ነው። የኦሮሞ ህዝብ ብዛት (40 ፐርሰንት) ከሌላው የበለጠ ነው። ዲሞክራሲ ከተባለ፣ ህወኃት (አምስት ፐርሰንት) እንደ ሞከረው፣ ከህወኃት እኩል ወይም ያነሰ ተጠቃሚ መሆን አይችልም። የተፈናቀሉት የትም ቢቋቋሙ ለምን ይደንቃል? ኢትዮጵያ ለሁሉም አገር ትሁን እያልን አይደለም? ኦሮሞ በየመስሪያ ቤቱ ቁጥሩ ጨምሮ ቢታይ ለምን ይደንቃል? ቁልፍ የሥልጣን ሥፍራ ህወኃት መያዙ አልነበረ ችግሩ? እንዴት ነው ነገሩ? ልናስተውል የሚገባው፣ ህወኃት የሠራው ግፍ ሥር የሰደደ መሆኑንና ለመንቀል መተባበር እንዳለብን ነው። በጥላቻ ተነሳስተን፣ ዋነኛውን ጉዳይ ባንዘነጋ። የህወኃትን ሥራ ስንፈጽምለት እንዳንገኝ።

 2. We should all be grateful to this honorable man, without exaggeration he is a gift God and he might be the one who has the master key to all the suffering this country had been through. We must trust the man and have to give him time and extend the extra hand he desperately need regardless of what. We shouldn’t loss this man and we all need to pray for a peaceful Ethiopia that is the only option we all have.

 3. ይህ ጉዳይ የግለሰቦች የአብይ አህመዽና የእስክንድር ነጋ አጀንዳ አይደለም የ100 መቶ ሚልዮን ህዝብ ህልውናና መጻኢ ህይወት እንጂ:: የሰሜን አሜሪካ በሳል ወገኖች ተገቢ የማሳሰቢያ ጥያቄ ለዶ/ር ኣብይ መላካቸው የሚያስመሰግን ሲሆን ዶር አብይ ጊዜ ወስዶ መልስ መስጠቱ ለግልጽ ደብዳቤዎች በሃገሪቱ ታሪክ ያልታየ የመጀመሪያው ድንቅ ነው:: ከዚህ በተረፈ የእስክንድር ነጋና የአዲስ አበባ ዜጎች ጥያቄ የመርህ የፍትህ የሃግራችን ህልውና ጥያቄ እንጂ የግለሰቦች ጉዳይ ኣየደለም:: አብይም ሆነ እስክንድር ፐርሰናሊቲ የማሳመር ምኞች ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን የአንድ ከተማ ህዝብ የተከፈተበትን በአንድ ዘር የበላይነት ላይ የተምሰረተ እኩይ ዘመቻን የራስን እድል መብት የመወሰን አለም አቀፍ የታላላቅ ከትሞች (ሜትሮፖሊታን) ወይም ፌደራል ከተሞች መብት በሰላምዊ መንገድ እስክንድርን ለሰው መብትና ለጋዜጠንኝነት ጀብዱ የሸለመ የብእር ማህበር Pen Association ማስረጃ በሚሆነው በብእሩ ብቻ ሲፋለም ሌላው በሜንጫ በገጀራ በዱላ ከነጄሌዎች ሲሰማራ ምንም ያላለ መንግስት የእስክንድርን የብእርና ሰላማዊ ትግል ‘ጦርነት’ ብሎ መክሰስ መንቀፍ ወደከፋ ሃገር አጥፊ ግጭት ሳይገባ በፊት እስክንድር የወሰደው እርምጃም ሆነ የሰሜን አሜሪካ ወገኖች የሰጡት ማሳሰቢያ ሃገራዊ ነው በጣም ወሳኝ አስፈላጊ ጉዳይ ነው::

 4. Well, well! Look at the responses even after this humane and dignified response from the PM. There indeed is no winning no matter how he handles it – fairly or otherwise. We Ethiopians , elite or not, for most part are unfortunately emotional. Look at what Ermias of ESAT for instance is doing to tarnish the good image of this poor hard working PM TO ONLY BE PUT TO HIS PLACE BY ABEBE GELAW. If it weren’t for Abebe’s unwavering journalistic qualities, Habtamu and Ermias would have left us with doubts about Abiy. Most seem focused nowadays on scoring cheap political points. It is terribly sad in this day and age, after sacrificing so many of our country men/women to the brutal TPLF gang, we are still sabotaging one another as though we are cursed as people. Abiy Ahmed is a human being. He may have his short comings as a human being; but on balance, he has been striving to do good for Ethiopia since he came to the “throne”. Imagine for a second the alternative under the current deeply polluted & ethnically enclaved political landscape. Think about it. For those of us especially in the west , it is so easy to criticise, sign and dessiminate petitions. For some, it is actually pastime at coffee shops. For Abiy and very few leading this poorly managed country, it is a matter of choosing between a monster and a tamed down evil in drafting a roadmap for an intricate country like Ethiopia. Abiy was a technocrat who once served the brutal TPLF regime as a director of INSA. He was also a principled technocrat who lost his job because he didn’t fully endorse TPLF’s information handling directives. I for one can’t sit idle in pointing this out to whoever is reading. The likes of psudo opportunistic “journalists” like Ermias and Habtamu need to seriously be sifted from Abebe/Agena like professionals You can be a scientist, journalist or an amazing intellectual from a reputable university; but that alone doesn’t make you a humble or principled citizen. I smell and feel humility in Abiy and I will stand with him until he proves me wrong. Few of you may even go as far as saying I am deeply intoxicated with blind admiration. At my age, I am not the type that blindly fall for anyone let alone a political leader of a country. If I am given a choice among existing politicians or intellectuals – far or near – I choose Abiy Ahmed in a heart beat for Ethiopia. Humility is a virtue. If everybody stops judging the guy and focus on the big picture, I am sure he or she will arrive at the same objective conclusion. Notwithstanding the digital rats that have infested the cyberspace in Ethiopian attire, I am just as concerned as the majority of you out there. I sincerely apologize to the 42 distinguished Ethiopians if I inadvertently questioned your motives.

  Abawirtu.

 5. Dear T. Goshu,
  The words you use are of much interest to me than what you intended to get across.
  “nonsensical …stupid… self-degrading… backward…self- dehumanizing… trapped …hypocracy (sic)…conspiracy… deceivingly stupid…stupidity !”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.