ጲላጦስን ልቆ ይሁዳን አስናቀ! (በላይነህ አባተ)

ካድሬው አረገና ምሁር ፕሮፌሰር፣
ንስን እንደሚሻ እንደ ቆሌ እንደ ዛር፣
ስንቱን አስደፍቆ አስደፋው ተእግሩ ሥር?

ትናንት በጆሮው ዛሬ ደሞ ባፉ!
ሕዝብን ይሸጠዋል ምናለበት እሱ!

የይሁዳን ክህደት የምጠረጥሩ፣
የጲላጦስን ፍርድ ጭራሽ የማታምኑ፣
አቢይ እጅ ሲታጠብ ኑና ተመልከቱ፡፡

በሰላሳ ዲናር አምላክ እንደ ሸጠው፣
የአስቆርቱ ይሁዳ እንደተረገመው፣
ጆሮ ጠቢ ሆኖ ስቱን ነው ያስበላው?

ወጣት አዛውንቱን ሲያሳንቀው ኖሮ፣
ሰላይ ጆሮ ላሽን ሲያሰማራ ከርሞ፣
“እጄ ንጡህ!” አለ ዓይኑን በጨው ታጥቦ፡፡

የለገሰን ጣቶች እንደ ጡት ጠብቶ አድጎ፣
አገር በከተፈ ደቁኖ ቀስሶ፣
ሰው በላ ማፈያ ሲያገለግል ባጅቶ፣
“አገር አልበደልኩም!” አለ ድርቅ ብሎ!

እንደ እስስት መልኩን እየቀያየረ፣
እንደ ጓሳም እባብ ስልክልክ እያለ፣
ስንቱን ጆሮ ነድፎ በመርዝ አስገደለ?

የሕዝብ የቤተሰብ ወግ እየለቀመ፣
ስንት ዘር አስጠፋ ወህኒ እያሰለበ?

ተሰፈር ተመንደር ወሬ እየቃረመ፣
ስንቱን ከርቸሌ ውስጥ በእሳት አስጠበሰ?

እንደ ቆሪጥ ነገር ወሬ እያሸተተ፣
ሽቦውን ቀጣጥሎ ስልክ እየጠለፈ፣
ስንቱን አስወግቶ ዓይኑን አስፈረጠ?

ስኖር ኢትዮጵያን ዘፈነና አንዳፍታ፣
ምሁር ተብዮውን ከበሮ እያስመታ፣
በሰማእት ገላ ጦሩን ዳግም ሰካ!

በጆሮ ጠቢነት “ሰው” ስላሰቀለ፣
ይሁዳ በፀፀት ራሱን ገደለ፣
አቢይ ግን በኩራት ከዙፋን ቁጭ አለ፡፡

“ምሁራን ጠቢቡ”ን እያንከረፈፈ፣
የሞኝ የቂሉን ልብ እያንጠለጠለ፣
አቢይ ክህደቱን አሁንም ቀጠለ፣
ጲላጦስን ልቆ ይሁዳን አስናቀ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መጋቢት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

7 COMMENTS

 1. አቤት መቻኮልህ በሾለው ምላስህ
  ጥላሸት መቀባት ሆነና ተግባርህ
  ወሬ ሳታጣራ በጣሙን ተቻኩለህ
  የገላው ልጅ አቤ ባፍጢምህ ሊደፋህ
  ኤርሚን ዋቢ አርገህ በኛ ላይ ባልተፋህ!!!!

  ዳሩ ምን ያረጋል አጃቢ አታጣም
  ወሬ ስንቁ ደፋር የፅልመት ቅርሻታም
  ድንገት ከጠበከኝ ተመልሼ አልመጣም፤
  የርቱ ናማ ገዲ አላስተናግድም፤፤

  ከንቀት ጋር

 2. Abaaa Wirtuuuuuuuuu! Geletu

  Abebe does not have to tell us. We all know he was spy of TPLF and director of ENSA. Henece your body Abiy was resposible for the tortures and killings of our people.

  TPLF supporters tried to protect, the Criminal Meles because he was Tigre and gave them the opporutnity to rob. You Abaaaaaa Wirtuuuu is trying to protect the Criminal Abiy because he is OROMO and he is fulfiling the Kegna Dream. Shame on you!

 3. baaa Wirtuuuuuuuuu! Geletu

  Abebe does not have to tell us. We all know he was spy of TPLF and director of ENSA. Henece your body Abiy was resposible for the tortures and killings of our people.

  TPLF supporters tried to protect, the Criminal Meles because he was Tigre and gave them the opporutnity to rob. You Abaaaaaa Wirtuuuu is trying to protect the Criminal Abiy because he is OROMO and he is fulfiling the Kegna Dream. Shame on you!

 4. ” የለገሰን ጣቶች እንደ ጡት ጠብቶ አድጎ፣
  አገር በከተፈ ደቁኖ ቀስሶ፣
  ሰው በላ ማፈያ ሲያገለግል ባጅቶ፣
  “አገር አልበደልኩም!” አለ ድርቅ ብሎ!

  እንደ እስስት መልኩን እየቀያየረ፣
  እንደ ጓሳም እባብ ስልክልክ እያለ፣
  ስንቱን ጆሮ ነድፎ በመርዝ አስገደለ?

  የሕዝብ የቤተሰብ ወግ እየለቀመ፣
  ስንት ዘር አስጠፋ ወህኒ እያሰለበ?

  ተሰፈር ተመንደር ወሬ እየቃረመ፣
  ስንቱን ከርቸሌ ውስጥ በእሳት አስጠበሰ?

  እንደ ቆሪጥ ነገር ወሬ እያሸተተ፣
  ሽቦውን ቀጣጥሎ ስልክ እየጠለፈ፣
  ስንቱን አስወግቶ ዓይኑን አስፈረጠ? ”

  Well, someone who worked with Debretsion Gebremichael could not be an innocent person.
  But could the author provide evidences about the crimes Abiy committed to the media ?

  What should worry us more than the crimes Abiy committed in the past is what he could be doing now.

  Abiy and ODP could be involved in a plot to dismantle the ancient African country Ethiopia !
  And, Eritrea, the West and Arabs could be plotting with Abiy and ODP.

  Warning, a nazi and black hater Trump would be extremely happy if he could dismantle Ethiopia. He would be very proud of that, his supporters too. So, the Trump administration would gladly help Abiy and ODP to dismantle Ethiopia. You should have that in mind.

 5. በላይነህ አባተ እጅግ የተናቀ
  ጲላጦስን ልቆ ይሁዳን አስናቀ?
  በየዘመናቱ ብቅ ይላል አዝማሪ
  ልዩ ውበት ያለው የግጥም ደርዳሪ
  አይመጥንምና ያንተውስ ክርፋት
  ወዲያ ነው የጣልኩት የቆሻሻ ቅርጫት

 6. Demeke= Abaa wirtuu ? Lemma

  What evidence you need? You all know what the devils at INSA were doing? They were slaughtering, burning and amputating people. Weren’t they? Was not Pastor Abiy the director of INSA?

  Your are trying to defend a henious criminal!

 7. Tedla G Woldeyohannes

  This is hilarious.

  Dawit Kidanework

  “ጠቅላያችን ለብዙ አመት ከወያኔ ጋ ሆኘ ምንም አገሬን የሚጎዳ ነገር አልሰራሁም ነው ያሉት። እኔ ምለው የደብረሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ ነበሩ እንዴ ?” Yafet Abel
  See Translation

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.