ከጋዜጠኛ የሰብአዊ መብት ተሞጋች እስክንድር ነጋ የተላለፈ መልእክት !!!

ዛሬ መጋቢት 20/2011 በራሥ ሆቴል ለአለም አቀፍ ለሃገር ውሥጥ ጋዜጠኞች እንዲሁም ለተለያዩ አካላት ለነዋሪውም ጭምር ጋዜጣዊ መግለጫ ለመሥጠት ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ከበላይ አካል ትእዛዝ ተሠቶናል ያሉ በርካታ ፓሊሶችን የያዙ ሃላፌዎች ቀድመው በራሥ ሆቴል በመገኘት ጥሪ የተደረገላቸውን ጋዜጠኞች ዲፕሎማቶች ነዎሪዎች እንዳይገቡ የከለከሉ ሢሆን የባላደራ ኮሚቴውም በሠአቱ የደረሠ ሲሆን እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡
ኮሚተው በአቶ እስክድር ነጋ አማካኝነት በሆቴሉ በር ላይ መልክት ለማሥተላለፍ የሞከረ ሢሆን ምንም መልእክት እንዳያሥተላልፍ ተከልክሎል በሥፍራው የተገልፕልኘነውም ከአካባቢው እንድንበተን ተደርገናል፡፡
አሁንም አጠቃላይ ሁኔታውንና የቀጣይ ጉዞውን በተመለከተ መግለጫ የምንሠጥ ሢሆን ግዜውንና ቦታውን እናሣውቃለን፡፡
ለአብሮነታችሁ በታላቅ ኢትዮጵያዊ አክብሮት እናመሠግናለን፡፡
ድል ለዲሞክራሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.