ለማ አንክድም ከማንም በላይ ዋጋ ከፍለሀል! ግን በሴረኞች አትቀደም!! (ሰርፀ ደስታ)

አዎ ንግግሮች እየተቆረጡ ለጥፋት ማስፋፊያ የሴረኞች መጠቀሚያ ሆነዋል፡፡ ሴረኞቹ ግን አጋጣሚን ተጠቅመው ነው ይሄን የሚያደረጉት፡፡ አጋጣሚዎቹ ደግሞ እንደገባኝ አንተ በግል ላትፈጥረው ትችላለህ የኦሮሚያ አስተዳደር በሚሰራው ስህተት ግን ብዙ ለሴረኞች የተመቹ ነገሮች እየሆኑ ነው፡፡ እንደ እውነቱ እኔ ለማን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እሰማዋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ሱሴ ከማለቱም በፊት፡፡ የሚናገረው ከውስጥ እንጂ ለውሸት እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ እኔ ኦሮምኛ እሰማለሁ እንደተባለውም ለማ ተናገረ የተባለውን ሰምቼ ብዙም የተለየ እንዳልሆነ ግን ከኋላ ምን ሊል እንደሚችል የተረዳሁት መስሎኝ ነበር፡፡ የእኔና የለማ የአብይም ችግር ኦነጋውያን እንደልባቸው ሲፈነጩ ጭራሽ ልክ ነው በሚል መግለጫ ጭምር ያወጣው የኦሮሚያ ምክር ቤት ነው፡፡ እረዳለሁ እንደምክር ቤት ለማ በዚህ ጉዳይ ባይስማማ እንኳን  ብቻውን መግለጫውን ማቆም አይችልም፡፡ ግን በእኔም ዘንድ ነገሮች እጅግ ግር ብለውኝ ዛሬ የተናገረውን ቃል ልሰማ ብችል በቀጥታ ምን እየሆነ ነው ብዬ ብጠይቅ እጅግ ፈልጌ ነበር፡፡ አዎ ሊመጣ የነበረውን ብዙ ጥፋት ለማ እንዳቆመው መቼም ቢሆን አልክደውም፡፡ እውነት ነው፡፡ ስጋቴ ለማም በነገሮች ብዛት ተቀየረ ወይ ማለት ነው በሚል እንጂ ለማ በፊት ለማታለል ተናገረ የሚል እምነት የለኝም፡፡ አሁን ጥሩነቱ እውነቱን ተናገረው፡፡ አዎ ከአንተ በፊት የመናገር ሞራል የለውም፡፡ ይሄን በክብር ሕዝቡ ተቀብሎታል፡፡ ይሄንንም እኮ ብዙዎች አምነውና ተማምነው ብዙ ተብሏል፡፡ ግን ለለማ የምናገረው አሁንም ተቀድማችሁ እንደነበር መካድ አይቻልም፡፡ አዎ አማራ ውስጥ ያለ አማራ፣ ትግራይ ውስጥ ያለ ትግሬ አደለም በሌላ ክልል የሚኖረውን እሱ ወገኔ የሚለውን (በዘረኝነት) ደራሹ  አደለም፡፡ ድሮም እኮ የሚባው ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት ነው፡፡ ይሄን ብሎ ሕዝባችን በፍቅር ኖሯል፡፡ አሁን ግን እጀግ ዘግናኝ ዘረኝነትና ጥላቻ እያጠፋን ነው፡፡ ለማ አትቀደም! ዛሬ የተናገርከውን ለሴረኞች መልስ ለመስጠት ሳይሆን ፊት ለፊት ሁሌም ተናገረው፡፡  ኦሮሚያ ውስጥም ሆነ አገሪቱ በአጠቃላይ ውስጥ ያለውን ችግር ከማንም በላይ ትረዳዋለህ፡፡

ጥላቻ ሲሰበክ የኖረ ሕዝብ በቀላሉ አሁንም ለሴረኞች ሴራ የተጋለጠ ነው፡፡ የአንተን ገጽታ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ የሠረት በዋናነት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ ምን አልባትም ዛሬ ከተናገርከው በጣም አስደንጋጭ የሚሆንባቸውና ሌላ ዘመቻ ሲያደርጉብህ ትታዘባለህ፡፡ የአንተ በጣም በኢትዮጵያውያን መወደድ ችግር ማነቆ የሆነባቸው ብዙ ናቸው፡፡ አንተ የኦሮሚያ ፕሬዘዳነት በብዙ ኦሮሞዎችም ተደማጭነት ያለህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ሲቀበልህ አደጋ የሚሆንባቸው ብዙ ናቸው፡፡ እያወራህ ያለህው ኢትዮጵያዊነትን ነው፡፡ እያወራህ ያለውን አደገኛ የሆነውን የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ከማንነቱ ወጥቶ በጥላቻና ዘረኝነት ስንት ለፍተው ለራሳችን እንደፈለግንው ልንዘውረው አዘጋጅተንዋል በአሉበት ወቅት እኮ ነው ኦሮሞን ከአንተ በላይ ኢትዮጵያዊ የለም እያል እየሰበክ ኦሮሞን ወደ ኢትዮጵያዊነት ስሜት እያመጣህው፡፡ ለዘመናት ሲሞሉት የነበረውን የጥላቻ ትርክት እያረክስህ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ ይሄ አደገኛ የሆነባቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ችግሩ ትልቁን ፈተና ብቻህን ተወጥተህ ለወሮበሎች በመብት ስም እድል በመስጠታችሁ የተነሳ ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው ነው በሕዝብ ዘንድ መልሶ ጥርጣሬ እንዲኖር የሆነው፡፡ እንደ እውነቱ ዛሬም ከአብይ ይልቅ እኔ ለማን አምናለሁ፡፡ በዛ ቀውጢ ወቅት በሙሉ ነብሴ ነበር እከታተለው የነበረው፡፡ ምን አልባት በዛ ወቅት ስጽፋቸው የነበሩትን ጉዳዮች ተመልሶ ላነበበ እንኳን ለሌላ ለኔም ይገርመኛል፡፡ በተለይ በአንድ ወቅት እነ ለማ አለቀላቸው እጃቸው ተቆረጠ በሚል ውስጣቸው እየተደሰተ ግን ላይ ላዩን የቁጭት በሚያስመሰል ሕዝብን ተስፋ ሲያስቆርጡ በነበሩበት ወቅት እግዚአብሔር ለወሮበሎች አሳልፎ ዳግም አይሰጠንም የሚል ጽኑ እምነት ስለነበረኝ እንኳን እኔ እናንተ ራሱ እርግጠኛ ያልሆናችሁበትን እውነት እንደሚሆን በድፍረት እጽፍ ነበር፡፡ በወቅቱ ከጻፍኳቸው ሁለቱን ሊንክ ከዚህ በታች እተዋለሁ፡፡

https://www.satenaw.com/amharic/archives/53380?fbclid=IwAR3ygjyJmq8SXhV0ICYYnDbhAoK0R6-QNGxldhj_s8fVmK9m6emYqZzh8Kc

https://www.satenaw.com/amharic/archives/52963?fbclid=IwAR0fLf4KL-KnVRcxPJu9L3B1h39_Enck-h-ZfL_Ju16Oz9OJPsa-K5vzLfg

ይሄ ነብይነት አደለም፡፡ እጅግ ስታስብበት እግዚአብሔር የሚሆነውን ነገር እንድታስተውል ያደርግሀል፡፡ ለማ በእነዛ ቀኖች ብቻውንም የሆነባቸው ነበሩ፡፡ ዋጋ ከፍያለሁ ቢል ቀላል ዋጋ አልከፈለም፡፡ ከባድ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ያን እንዲያደርግ ስለፈቀደ እንጂ አንዳንዱን እሱም ቢሆን በኋላ ለምን እንዳደረገው ቢጠየቅ መልስ ያለው አይመስለኝም፡፡ ውሳኔውና ቁርጠኝነቱ ግልጽ ነበር፡፡ ይሄን እያደረገ ያለን ሰው እግዚአብሔር እንደማያሳፍረው ግልጽ ነበር፡፡ ተሳክቶለታል፡፡ ለውጡ ከመጣ በኋላ ግን በተፈጠረ ክፍተት ለማ በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬ እንዲሆን በአለ በሌለ አቅማቸው ሴረኞች ሊሰሩ እድል በማግኘታቸው ሆነ፡፡ የዛሬው ንግግሩ እንዴት እንደሚያምርበት አየሁት፡፡ በድፍረት ዋጋ ከፍያለሁ ሊል አስችሎታል፡፡ አዎ ልክ ነው! ይሄን ለመዘንጋት ሩቅ ጊዜ አደለም ዛሬም አራቱ ቡድኖች ስብሰባ ተሰብስበው ከጨረሱ በኋላና ወያኔ የራሷን መግለጫ ከአወጣች በኋላ የለማ አካሄድ የምርና የማይመለስ መሆኑን የተረዳችው ወያኔ ለማ በይፋ ለሕዝብ የራሱን መግለጫ እንዲያወጣ የተገደደችበትን አራቱን ቡድን እንመራለን የሚሉት ግለሰቦች በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ሲናገሩ የነበረበትን መንፈስና የለማን ግልጽ ከሶስቱም ያፈነገጠ ብቻውን ሕዝቤ በሚል የቆረጠ አቋሙን የተናገረበትን ቀን ዛሬም አየዋለሁ፣ እሰማዋለሁ፡፡ ዛሬ የተናገረው ንግግር ጥሩ ፈዋሽ ነው፡፡ ግን በዚህ ንግግር እጅግ የሚበሳጩ እንደሚኖሩ ሰሞኑን ታዩታላችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ዙሪያ ስለሚፈናቀሉ ዜጎች በግልጽና በእጭሩ ልናገር፡፡ እንደ እውነቱ እነዚህ ዜጎች የትኛውንም መጠን ያለው ካሳ በሉት ቢከፈሉ ቅር የሚለው ጤነኛ ሰው ያለ አይስለኝም፡፡ ችግሩ የእነሱ ነገር በኦሮሞነት እየተሰላ ሁሌ የወሬ ማዳመቂያና የወሮበሎች መጠቀሚያ ሲሆኑ ማየት እጅግ ያሳዝናል፡፡ ወሮበሎቹ የእነዚህ ዜጎችን በኦሮሞነት እንዲሰፈሩ ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ሊሰጣቸው የሚችለውን ጥቅም ሁሌ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆነዋል፡፡ በኦሮሞነት ከወለጋና ባሌ አርሲ እየመጣ በእነሱ ሰበበ ለመጠቀም እንጂ የእነዚህ ሚስኪን ገበሬዎች መፈናቀል ጉዳዩ አደለም፡፡ መንግስት እንደመንግስት አሁን ግልጽ አቋም  ወስዶ ለእነዚህ ዜጎች እንደ ዜጋ የሚገባቸውን ካሳ መክፈል ግዴታው ነው፡፡ ኮንደሚኒየም መሥጠት ትንሽ ነገር ነው፡፡ ገበሬ ከመሬቱ ተፈናቀለ ማለት የሕይወቱ ዋስትና ነው የተነጠቀው፡፡ የኮንደሚኒየም የመኖሪያ ቤት ሰጥቶ ካሳ ከፍያለሁ ማለት አይቻልም፡፡ ገበሬው ይኖር የነበረው ደሳሳ ጎጆ ሊሆን ይችላል ግን ከመሬቱ ያመርት ስለነበር እሱም ቤተሰቡም አይራብም፡፡ የኮንደሚኒየም ቤት ቢሰጠው ቤቱ ሊቀየር ይችላል ገን የመኖር ዋስትነው አደለም፡፡ ከኮንደሚኒይም በታች ያሉ ክፍሎች በንግድነት እንዲጠቀም በሐሳብ ደረጃ ጥሩ ሊሆን ይችላል ግን አሁንም በቂ አደለም፡፡ ከለመደው የሥራ ባህልም ማንሳት ሌላ ችግሩ ነውና፡፡ ስለዚህ መንግስት እንደመንግስት እነዚህ ገበሬዎች የተባሉት የኮነደሚኒየም ቤትና የንግድም ክፍል እንዳሉ ሆነው በከተማ ግብርና በዘመናዊ መልኩ እንዲደራጁ በማድረግ ምቹ በሆኑ ቦታዎች ራሳቸው የሚሰሩበት የከብቶች፣ የዶሮዎች የአትክልት ሌላም ሊሆን ይችላል በቋሚነት የሚጠቀሙበትን እግረ መንገድም ለከተማቸው ምርት አቅራቢ የሚሆኑበትን እድል ቢፈጥር ጥሩ ነው፡፡ ይሄን በስልጠናና በገንዘብ ቢታገዙ ገበሬዎች በቀላሉ የሚሠሩት ነው፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባ የወንዞች ፕሮጄክት የከተማ ግብርና አንዱ ዘርፉ ሊሆን ይገባል፡፡ ይሄ ፕሮጄክት ለከብቶችና ሌሎች እንሰሶች ለማርባት ላይመች ይችላል፡፡ ለአትክልት ግን ሁነኛ ፕሮጄክት ነው፡፡ አሁንም ብዙ ቦታ አትክልት ይመረታል፡፡ አሁን እየተመረተ ያለው አትክልት ግን በጣም አደገኛ በሚባሉ ከፍሳሽ በሚመጣ ሄቪ ሜታልስ (ከባድ ንጥረ ነገሮች) የተበከለ በመሆኑ የካንሰር በሽታ ሊያመጣ ትልቅ አቅም አለው፡፡ ውሃው በፕሮጄክቱ ንፁህ ከሆነ ከብዙ ቦታዎች ከሚመረቱ አትክልቶች በተሻለ ተመራጭ ይሆናል፡፡ ለከተማው ቅርብ መሆኑና ከማሳ እንደወጣ ለተጠቃሚ መድረሱም አንድ ጥቅም ሆኖ፡፡ የገበሬዎቹ እርሻ ወደፊት ለከተማው ሕዝብ መዝናኛም ይሆናል፡፡ ገበሬዎቹን በዘመናዊነት ማደራጀትና ዘመናዊና ውበት ያለው ጋርደን እንዲያደርጉት ማድረግ ነው፡፡  ለከተሜውም እርሻ ማለት ምን እንደሆነ በቅርበት ለማሳየት፡፡ አታክልቶች በማሳቸው ላይ ምን እንደሚመስሉ ለማሳየት፡፡ ከብቶችና ሌሎች እንሰሶች ሊያረቡበት የሚችሉበትን ቦታ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡ የከተማውን ንፅህናና ሌሎች ሁኔታዎችን በማያውኩ መልክ፡፡ ወደፊት አቅማቸው እየጎለበተ ሲመጣ ቢያንስ የእነሱ ልጆችና የልጅ ልጆች የትልልቅ የዚሁ መስክ ካምፓኒ ባለቤት ይሆናሉ፡፡ ሰዎችን ራሳቸው ሰርተው በሚለወጡበት ሁኔታ ማዘጋጀት እንጂ በቁሳዊ ካሳ ዋስትና መስጠት አዳጋች ነው፡፡

አመሰግናለሁ!

ለዑል አባት ቅዱስ እግዚአብሔር የቀና ሐሳባችንን ያሳካ! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

 

 

2 COMMENTS

 1. አዎን ለምዬ በዛች በክፉና በመጨሻዋ ቀን እንደ ፋሲካ በግ አንገቱን ሰጥቶ አትዮጵያን ያደነ ጀግና ነው፡፡ በዚህ ከተስማማን እንዴት ሆኖ ነው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከሞተላት ሀገር በተቃራኒ የሚቆመው? ለምዬ የዚህ አይነት ስብዕና የለውም፡፡ ሁልጊዜም ኢትዮጵያዊነት ሱሱ ነወ፡፡ ነገር ግነ በፖለቲካ አአለም ውስጥ ብዙ ውጣ ውረዶች ስለሚኖሩ አንዳንዴ ከምንጠብቃቸው ነገሮች ውጪ ሲነገሩ ፤ ሲባሉ ስንሰማ አንሽበራለን እንደናገራለን ፡፡ ግን ዕወነቱን ጊዜ ያወጣዋልና ለመፍረድ አንቸኩል ፤ ልንታገስ ይገባል እላለሁ፡፡ ከለምዬ ጎን ልንቆም ይገባል
  በዚህ አጋጣሚ ከእንድ አመት በፊት ለለምዬ ክብር ስል የገጠምኩትን ግጥም በድጋሚ ላካፍላችሁ፡፡
  ለምዬ ለምዬ ኢትዮጵያዊነቴ፣
  የክፉ ቀን ደራሽ እንባዬን አባሼ፣
  የዜግነት ክብሬ መከታ ጋሻዬ፤
  የሠላም የፍቅር የአንድነት ተስፋዬ፤
  ለምዬ ለምዬ ኢትዮጵያዊነቴ፤
  አንተን ስልሰጠኝ ይመስግን አምላኬ

 2. Dear Tsertse
  I like most things you write. But this one is making me raise my eye brows as it is just a support letter to Lema and vouch what is happening in and around Addis Ababa. See the solution to the problem of forcibly displaced people is to protect their rights and let them go back where they were and where there life is. Not bring them to what is a foreign place and a foreign way of life, which is what you are advocating. One has to think about the financial, social and mental stress these people are going through when they are forced again to do what they don’t want to do this time by the people they are counting on. The intent should be to do things right rather than expedite. Also you always believed in keeping an eagle eye on politicians and never be swayed by their words. What happened? Like you said, the success of Lemma’s vision (if there is a vision) depends in controlling and leading his party in the right direction. If he can not or does not then either there was no vision or his qualities as a leader is non existent. You very well know he is surrounding himself with known extremists, taking hugging pictures with them and never once did he show to the larger Ethiopian population he is keeping clear of them. That’s a problem? But I have to agree and you have to agree the time is now at the moment to do what he said and show Ethiopians what he is doing.
  Enqoqo

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.