“የኢትዮጵያ ቋንቋ መሆን ያለበት ኢትዮጵኛ ነው።” ፕሮፌሰር እዝቅኤል ጋቢሳ (በአበበ ገላው)

በጄ ፕሮፌሰር! እንደርስዎ “ሎጂክ” ከሆነ የአፍሪካ ቋንቋ አፍሪካኛ፣ የአውሮፓ አውሮፓኛ፣ የአሜሪካ አሜሪካኛ፣ የኬንያ ኬንያኛ… መሆን ይገባዋል። ይሁንና ቁጭ ብሎ ይገባዋል ማለት ቀላል ነው። እነዚህን አዳዲስ ቋንቋዎች ፈጥሮ ማስፋፋት ብዙ ስራና ትልቅ ጥበብ ይፈልጋል።

ፕሮፌሰር ትምህርት መማር የሚጠቅመው ፈረንጅኛ ለመሸምደድ እና ጠማማ ሆኖ ባደባባይ ለመታየት አይመስለኝም። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን የገጠማት ችግር በሃያ ሰባት አመት የተዘራው መርዛማ የዘር እንክርዳድ ድሃውን ህዝብ እያባላ ለመፈናቀል፣ ለሞትና ለስደት ሚሊዮኖችን እየዳረገ መሆኑ ነው።

እንደርስዎ የተማረ ምጡቅ ላሉብን የጋራ ችግሮች መፍትሄ ማፈላለግ ሲገባው ህዝባችን የበለጠ እንዲራራቅና እንዲባላ ስራዎትን ትተው እንቅልፍ አጥተው የለየላቸው የዘር ፖለቲካ ነጋዴዎችን ሻንጣ ይዘው አገር ላገር እየዞሩና ሚድያ ላይ በኩራት ብቅ እያሉ መርዝ ይረጫሉ።

ኘሮፌሰር አይሳሳቱ። ቋንቋን መጥላት እና ማንቋሸሽ ሞኝነት ነው። እርስዎ በኩራት ምላስዎን እያጠማዘዙ የሚናገሩት እንግሊዝኛ ከሁሉም ቋንቋዎች የከፋ ታሪክ አለው። የሁዋላ ታሪኩ ግን ዛሬ ቋንቋውን ጠልተን አንናገረውም ብንል የምንጎዳው እኛው ነን። በዚህ ዘመን እንደ እንግሊዝኛ አይነት አለም አቀፍ ቋንቋ የእንግሊዞች ብቻ ነው ብሎ መስበክ ሞኝነት ነው። አማርኛም በታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያን ያስተሳሰረ ብሄራዊ ቋንቋ እንጂ ያማሮች ብቻ ቋንቋ እይደለም።

ፕሮፈሰር እያስተዋሉ! የተማረ መሃይም ከመሆን እራስዎን ያድኑ። ይህን ከባድ ፈተና ያለቅን ልቦና ስለማያልፉት ጥላቻ ያረገዘ ልብዎን ይፈትሹ። የጋራ መዳኛችን ኢትዮጵያዊንት ነው ብላ ከርስዎ ጋር የተጣላችው አስተዋይ ልጅዎ ጋር ከልብ ይታረቁና ከጥበት የመውጫውን መንገድ ምሪኝ በሏት….

3 COMMENTS

 1. ጫት መቃም ትውልድ አፍራሽ እንደሆነ ጀርመናዊው ሳይንቲስት ከዘመናት በፊት እንዲህ ይለናል “ራስን አደንዝዞ ሰውን እንደ እንስሳ ያራምዳል ብሎን ነበር”. የፕሮፌሰሩ እይታ ጨለማ ነው። በ21ኛው ዓለም ላይ ተቀምጦ ስለ 19 ክፍለ ዘመን የጀርመን የዘር ጉዳይ የሚያነሳ ጭፍን የዘር አቀንቃኝ ነው። የሚያሳዝነው ነገር እንደ ህዝቅያስ ያሉ የዘር ፓለቲካ ያሰከራቸው ዛሬን ነገን ሳይሆን ያለፈ ታሪክን እያነሱ ሰውን አስለቃሾች ናቸው። በመሰረቱ እንደዚህ ያሉ ምሁራን ለሃገራችን የዘር በሽታ ጽኑ መሆን ምክንያቶች ናቸው። ሰልፋቸው በቋንቋቸውና በጎጣቸው ብቻ ሰለሆነ።
  ወደ ጫት መቃም ስንመለስ በአሜሪካ የዲኢኤ መመሪያ መሰረት የተከለከ ሲሆን ከብዙ ጉዳቶቹ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡Hallucinations, Blurred vision, Loss of appetite and mental confusion. ምሁሩ ግን ያለምንም እፍረት ከቡና ጋር አመሳስሎ ሲናገር አላፈረም። የሃገሬ ሰው የተማረ ይግደለኝ ይላል። ለካስ እውነት ነው ተምረናል የምንለው ነው ህዝባችንን የምናበራየው። በዛሬ ላይ ተቀምጦ ሚኒሊክ ይህን ሰራ ያን አደረገ እያለ ያላዝናል። ቋንቋ መግባቢያ ነው ሲሉት በአሜሪካ ካሉ ነጭና ጥቁር ህዝቦች ጥቅም ጋር ለማያያዝ ይሞክራል። አይ መማር በአፍንጫዬ ይውጣ። ድንቄም ትምህርት። አማርኛ የአማራ ቋንቋ ነው ብሎ የሚያምን እንዲህ ያለ የተወላገድ ምሁር ለሃገር ጠቃሚነት የለውም። እሱን በመሰሉ ወስላቶች አመራር ነው አሁን የኦሮሚኛ ቋንቋ በላቲን እንዲጻፍ የተደረገው። ሃገርን እያፈረሱ፤ ሃገር በቀል ቋንቋዎችን እየጠሉ የነጭ ነገርን መናፈቅ የአፍሪቃ በሽታ ነው። ፕሮፌሰሩም የያዛቸው በሽታ በምንም መድሃኒት አይድንም። አማራ፤ ትግሬ፤ መሬታችንን በመጢዎች ተነጥቀን እያሉ እሳት በማያያዝ ሰውን ሲያጫሩ ይኖራሉ። ልብ ላለው ግን እንዲህ አይነት እይታ ያላቸው ሰዎች ቦታቸው አማኑኤል እንጂ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሆን የለበትም።

 2. እኔ እነዚህ ሰዎች ሊያስገርሙንም ሆነ ሊያሳዝኑን አይገባም:: የመጡት የተሰማሩት ለዚሁ ኢትዮጵያን የማፍረስ ተልእኮ ነውና::
  የኦሮሞ ህዝብ ግን አርቆ ማየት ተስኖት የነሱ ፈረስ እየሆነ ይመስለኛል:: ኃላ እነሱ ተልእኳቸው አልሰምር ሲል ሌላ ተገዝተው ወደሚሰማሩበት መሰል የክፋት እና የጥፋት ተልእኮ ይሄዳሉ:: ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚቀረው ግን የኦሮሞ ህዝብ ነው::
  የኦሮሞ ህዝብ አትሸወድ ኢትዮጵያ አትፈርስም::
  እግዚአብሄር የሰራትን ሀገር ሰው ሊያፈርስ አይችልም:: ኢትዮጵያዊነት ደግሞ መባረክ እና መታደል ነበር እንደው እንዳለመታደል ሆኖ በእጅ ያለ ወርቅ ሆነባችሁ እንጂ…

 3. “እንደርስዎ “ሎጂክ” ከሆነ የአፍሪካ ቋንቋ አፍሪካኛ፣ የአውሮፓ አውሮፓኛ፣ የአሜሪካ አሜሪካኛ፣ የኬንያ ኬንያኛ… መሆን ይገባዋል።” ካለ አዎ፣ አማርኛው ካልገባህ በፈረንጅኛው: the is no language called ኢትዮጵኛ! There is a language called Amharic and it is the language of the Amhara people. Same as Arabic is the language of the Arabs, English is the language of English people, so is Amharic the language of the Amhara people. Should one hammer that into your heads? Why do some people show off with their ignorance?? ይህን ያህል ድንቁርና ተሽክማችሁ ፕሮፈሰሩን ለመሳደብ መንጠራራት ምን የሚሉት ትዕቢት ነው??

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.