አገር አንዳትፈርስ ….. ህገ መንግስቱ ይሻሻል! (ለማ ከቶሮንቶ)

ለማ ከቶሮንቶ

ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የተለያዩ ለውጡን አየመሩ ያሉ የአገሪቱ ባለስልጣናት አሁን በአገሪቱ አየተከሰተ ያለው ዘር ተኮር ስደት እና መፈናቀል መከሰት ምክንያት ባለፉት አያ ሰባት አመታት ውስጥ በአገሪቱ ተንስራፍቶ በነበረው ዘረን መሠረት ባደረገ ፖለቲካ የተዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ወጤት መሆኑን ይገልጻሉ። ይህ ዘረን መሰረት አድረጉ ከመሰረቱ በተበዳይ እና በዳይ ብሄር ትርከት ጥንስስ ላይ የተመረኮዘ ፖለቲካ ጠላት በሌለበት ማደግ ስለማይችል አንዱን ብሄር ተጨቋኝ ሌላውን ብሄር  ጨቋኝ እና ጠላት አድረጉ በመሳል የአገሪቱን ህዝቦች በማባላት ስልጣናቸውን ለማራዘም በተነሱ ጥቂት ነጻ አውጭዎች የተቀነቀነ ሃሳብ ቢሆንም ዛሬ በእነዚህ ነጻ አውጭዎች የተነገራቸውን በሬ ወለደ ትርከት ስምተው እና በዚህም መልክ የተጻፉ ልብ ወለድ ድርሳናትን አንብበው እና ተቀብለው የተጠመቁ እና የቆረቡ አያሌ በብሄር እና በዘረኝነት ፖለቲካ የሰከሩ የፓለቲካ ሰካራሞችን ማፍራት ችለዋል።

ልዩነት እና ዘረኝነት  ህግ መንግስት እና ደንብ ወጥቶለት በመንግስት ባጀት ተመድቦለት በስልጠና ተደግፎ ሲስበክ ፣ የዘር ማንነት የፓለቲካው ዋና መሃከል ሆኖ የስልጣን እና የሀብት ምንጭ ሲሆን ፣ እራስን በራስ ማስተዳደር እስከ መገንጠል የሚል ሰበካ ከሚገባው በላይ ሲራገብ ትግላቸው ፍሬ ያፈራ በመሰላቸው እና ዛሬ በአገራችን ላይ ሊያስከትል የሚችለወን ጉዳት እና ሊያመጣ የሚችለውን ጦስ እና ፍዳ ሊገምት የሚችል አይምህሮን ባልታደሉ ጥቂት ስግብስግብ ሰዎች አየተገዛን ዛሬ በአገራችን እየሆነ ያለውን ለማየት ተፈርዶብናል።። ከበታችነት ስሜት የሚመነጨውን የመበደል ስሜታቸውን ለማስታገስ ፣ በሰለጠነ መንገድ ልዩነቶችን እና ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ትህግስትን ባለመታደላቸው ምክንያት የሚመነጨውን የአኩራፊነታቸውን ጽባይ ለማስታመም ፣ ሁለን ለራስ ለማድረግ ከሚፈጠር ስሜት የሚመነጨወን የስግብግብነታቸውን በሽታ ለመታከም ሲሉ አገርን አንደ ቅርጫ በክልል ከፋፈለው የተቆራመቱት የአንድ ወቅት አድለኛ የዘረ ፖለቲከኞች ያለጥበብ እና እውቀት ያሻቸውን ሀብት እና ስልጣን በመቆጣጠር አገር እና ህዝብን መግዛት ያመቻቸው ዘንድ ከፍፋይ ፣ አግላይ እና ገንጣይ ህግ መንግስት ፣ ደንብ እና ስረሃት አውጥተው በአውርነት እየመሩ ለህዝቡ ይሄ ነው የሚባል ለውጥ ሳያመጡለት ዛሬ ላይ አድርሰውናል።

ዛሬ ግን አንደትላንቱ አይደለም ። ትላንት ከፋፋይ ፣ አግላይ እና ገንጣይ በሆነ ህገ መንግስት አየተመራ በነበረው የፖለቲካ ስረሃት የተዘራው የዘረኝነት ፣ የልዩነት እና የጥላቻ ፖለቲካ  ዛሬ ላይ አገር አፍራሽ ፍሬ አያፈራ ፣ ኢትዩጵያውያን ለዘመናት አብረው በመኖር ያደረጁትን የአንድነትን እና የመከባባር ህይወት እየሸረሸረ ፣ የአገርን ሰላም እየነሳ ፣ ህዝብን እያሰደደ እና አያፈናቀለ አገረንም ወደ ማፍረስ አያደረሰ ይገኛል። ዛሬም ትላንት የነበረው ከፋፋይ ፣ አግላይ እና ገንጣይ ህግ መንግሰት ፣ ደንብ እና ስረሃት ከስሩ አልተገረሰሰም። ስለሆነም የአገርን አንድነት መሸረሸር፣ የአገርን ሰላም መንሳት ፣ ህዝብን በሚናገረው ቋንቋ ወይም በተፈጠረበት ዘር ምክንያት ማግለል ፣ ህዝብን ማሰደድ እና ማፈናቀል ህጋዊ መስሎ አየቀጠለ ይገኛል።

ዛሬም ማገናዘብ በማይችለው የጠበበ አህምሮአቸው እና በእንጭጭ አስተሳሰባችው ህዝብን መንዳት የሚፈልጉ ፣ አገርን አየበጠበጡ እና ሰላማችንን እየነሱን ያሉት የሰከሩ የዘር ፓለቲከኞች  በቁጥር ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ ጥቂት የዘር ፖለቲካ አስፋፊዎች ከሌላው ሰላም ወዳድ ህዝብ በላይ ያለፍረሃት እና ይሎኝታ ቢስነት ጮክ ብለው  ስለሚናገሩ የበዙ ድምጾች መስለውም ይታያሉ። ዋናው ነገር ግን የሚያነሱት ጥያቄ እና የሚያቀንቅኑት ጫፍ የረገጠ ዘረኝነት ደግሞ መነሻውም መድረሻውም  ‘’ህጋዊ እና ህገመንግስታዊ’’ ነው። እነዚህ ጥቂት ዘረኛ ፖለቲከኞች በመገንጠል ማስፈራራት የሚፈልጉትን ለማግኘት እና ህዝቡን ወደሚፈልጉት የጨለማ መንገድ ለመምራት የሚጠቀሙት እና የሚያራግቡት ፣ አንደራደርብትም ብለው የሚያስፈራሩበት ፣ በፈለጉት ጊዜ መዘው በማውጣት አገርን የመበጥበጥ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚጠቅሱት  የዘር ፖለቲካ አስፋፊዎች ተሰባስበው ከጻፉት ህገመንግስት ውስጥ ነው። የግል ጥቅማቸውን እና ስልጣናቸውን እስካስጠበቀ ድረስ በሰፊው ህዝብ ላይ በአጠቃላይም በአገር ላይ አያደረሰ ያለው የመበታተን አደጋ አይታያቸውም ። አንዲታያቸውም አይፈልጉም።ይህ ሆኔታ ደግሞ መንግስትን ጥርስ የሌለው አንበሳ አንዲሆን አድርጉታል። ስለዚህም በመንግሰት አፍንጫ ስር ተቀምጠው ፣ በመንግስት ባጀት አዲስ አበባ ውስጥ ቆጭ በለው ፣ መንግሰት ጥበቃ እና አንክብካቤ አያደርገላቸው ዘረኝነትን ፣ አግላይነትን ፣ ልዩነትን እና ጥላቻን ይሰብካሉ።

ልዩነት በህግ እና በስልጠና በመንግስት ባጀት ተደግፎ በሚቀንቀንበት አገር ፣ ጥላቻ  እና ከፋፋይ አስተሳሰብ በፖለቲካ ልሄቃን በአደባባይ በሚነገርበት እና ተጠያቂ በሌለበት አገር ፣ የፖለቲካው መሰረት እና ጥንስስ በዘር ላይ የተመሰረተ በሆነባት አገር ውስጥ ፣ ከአገር እና ከመንግስት የሚገኙ ጥቅሞች ተመሳሳይ ቋንቋ ባላቸው ሰዎች በመቧደን ብቻ በሆነባት አገር ፣ የኔ ዘር ከማንም አይበለጥም ከማንም ዘርም አያንስም ስለዚህም አንደ አንድ ሰው በአገሬ የሚገባኝን መብት አገኝቼ በሰላም እኖራለሁ ብሉ ማሰብ እና ኢትዩጵያ አትፈርሰም አያሉ መፎከር  ወይም በየሚዲያው እየቀረቡ ለህዝቡ  መናገር ፍላጉት ይሆናል አንጂ ተግባሪዊ ግን ሊሆን አይችልም።

በእውቀት ፣ በልምድ ወይም በስልጠና ሳይሆን የዘር እና የጎሳ ማንነትን ለማመጣጠን ሲባል ስልጣን በዘር ተዋጻኦ በሚታደልባት አገር ውስጥ ፣ ቡድኖችን እንጂ አኔን መስል ምስኪን ዜጎችን በመሬት ወይም በአገር ባለቤትነት በማያወቅ ህግ መንግስት የምተዳደር አገር ውስጥ ፣ የቡድኖች መብት የግለሰቦችን መብት በሚደፈጥጥ ህገ መንገስት በምትመራ ሀገር ውስጥ ፣ አንድን አካባቢ ለተወሰኑ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ በባለቤትነት በሚሰጥ ህገመንግስት በምትመራ አገር ውስጥ ፣ ማንኛውም ዞን ወይም ወረዳ አራስን በራስ ማስተዳደር በሚል ሰበብ ባኩረፈ ጊዜ ሁሉ የራሴን ክልል መመሰረት እችላለሁ ብሉ እንዲነሳ ብሎም አንዲገነጠል በሚፈቅድ እና በሚያበረታታ ህገ መንግስት የምተዳደር አገር ውስጥ የዘር ጥያቄ ሳይኖረኝ ፤ ስራዪን ሰርቼ ፤ የደህንነት ስጋት ሳይኖርብኝ ፣ የልቤን  ተናግሬ በሰላም መኖር አችላለሁ ፣ አገር አትፈርስም  ማለት አገር አንዳትፈርስ  ከመፈለግ ወይም ከመመኘት በስተቀር የሚያመጣው ነገር አንዴት ሊኖር ይችላል?

አገር በአንድ ቀን ላይፈርስ ይችላል።  ነገር ግን ከበፊት አንደ አገር የነበረን  አገራዊ አንድነት ፣ ማህበራዊ ትስስር እና የአብሮ መኖር ግንኙነታችን አየፈረሰ አንዳለ የሚያሳዩ በመላው አገራችን እየተከሰቱ ያሉት መፈናቀሎች እና ስደቶች ፣ በየሚዲያው የምንሰማቸው ከፋፋይ እና አግላይ ንግግሮች ፣ የምናስተውላቸው የመጣውልህ ሽለላዎች ፣ የምንሰማቸው የጥላቻ ክርፋታዎች እና ከኢትዩጵያዊነት አሴት እና ባህል ያፈነገጡ ጭካኒዎች እና ማግለሉች  የሚያመለክቱት ቀስ በቀስ እንደ አገር አየፈረስን መሆኑን ነውና ከተያዝንበት የዘረኝነት ደዊ አንፈውስ ዘንድ በፍጥነት መደሃኒቱን መውሰድ ይግባናል።

ኢትዩጵያ አትፈርስም ስላልን የማትፈርስበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ዛሬ ለመኖር አስቸጋሪ ሆነው የሚገኙት አንደ ሶሪያ ፣ ሊቢያ ፣ አራቅ እና ሌሎች አገራት ትላንት ከኛ በተሻለ ሳላም ፣ ብልጽና እና አድገት ውስጥ የሚገኙ አገራት አንደነበሩ ልብ ይሏል።

ሳያቃጠል በቅጠል አንዲሉ…..ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ እንዳይተረትበን ለዚህ ያደረሰንን ዋና ምክንያት ከሥር መሰረቱ ፈልገን እና ተወያይተን መድሃኒቱን ፈልገን መውሰድ ይኖርብናል። ። መድሀኒቱም ዜጉችን የአገር እና የመሬት ባለቤት የሚያደርግ ፣ በግለሰቦች መብት ላይ ተመርኮዙ የቡድኖችን መብት የሚያከብር ፣ በዘር ላይ ተመስርተው ማንም ሌላውን ብሄር አንድጨቋች በመቆጠር እና በነጻ አውጭነት ሽፋን የሚሚሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚገድብ ፣ ሁሉም የኢትዩጵያ ዜጉች ለስልጣን እና ለአገር ባለቤትነት አኩል መብት አንዲኖራቸው የሚያደርግ ፣ በዳይ እና ተበዳይ ፣ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ፣ መጤ እና ሰፋሪ ፣ ባለቤት እና ነዋሪ የሚሉ ልዩነቶች አንዲፈጠሩ የማያበረታታ ፣ በዘር ላይ የተመሰረተውን የፖለቲካ ፣ የመሬት እና የሀብት ባለቤትነት የሚቀይር የተሻሻለ ህገመንገሰት እንዲኖር በማድረግ  ነው ።

2 COMMENTS

 1. The ultranationalists like you are behind the most of the crises in Oromia and elsewhere. You try to provocate the decent people for violence. Violence is your daily business at this  time in order to manipulate the the reform of the PM. You are dreaming for transnational period,  so that you may again ascend to power. But is unrealistic dream. But now you try to sell yourself as a humanist. Generally, your mind setups are inhuman and very selfish. You have been plundering Oromia with your associates by cooperating with the TPLF on the last 28 years. The ultra nationalists like you were the mastermind of the Finfinne Master plan. You have been evicting the Oromo from Finfinne and its surrounding in the last 140 years continously. But no more business as usual.

  You are crying loudly, because you are afraid of the rebirth of Ethiopia as a brand new democratic multinational republic country. You are dreaming to bring back the era of Menelik, so that you and your associates can scramble for Oromia again. You claim time and again that the existence of Ethiopia will be vanished as country, if the Amharic speakers are not dominantly in frontlines in all sectors. But this a void slogan of the ultra nationalists. The malicious politics of the hatemongers will not work in the new Ethiopia any more. The scramble for Oromia like the Menilik’s era is no more possible. But Eskinder and his associates can keep on their dreaming in the coming millions of years. No more business as usual.

  Let me make it clear: The arrogance and stubbornness of the ultra  nationalists will not last long. They can bring out whatever they have in their backward and corrupted stores. This time is not like the era of Menelik.

  Finfinne is an integral part of Oromia legally and historically. It is a capital  city of  Oromia. But it is a home city for different ethinc groups of Ethiopia equally. It is a seat of the federal republic government of Ethiopia. Besides  that it serves as a capital city of Africa. Those  who called themselves Amahara cannot get special privileges. They will be treated like all other Ethiopians equally. If they don’t want to see the presence of the Oromo people with its language and culture, they can go back to their home region peacefully. 

  The other alternatives will not be tolerated. Period! You will never teach and dictate us what to do in Oromia. 

  The politics of one language, one culture and a single nation cannot be accepted any more in Ethiopia. Don’t forget that such demands have no room in today’s Ethiopian politics. But now temporally you can make noise here and there. That is all what you can do right now.

  De-Amharanisation of the whole Ethiopian politics is indispensable and absolutely necessary in order to reform and reshape Ethiopia as a country of multinational state. The politics of one language, one culture  and a single nation cannot be accepted any more. Also there is no Ethiopian identity as some idiotic individuals try preach us those like the chameleon Ermias Legesse. It is a fake identity and ridiculous. Dissociating Ethiopia from the politics of Menilik is indispensable for emancipation of all  the nations and natinalitis in Ethiopia.

   

 2. እርምጃችን ላይ የፈለግነውን ያህል ጥንቃቄ ብናደርግ ፣መንገዱ ሄዶ ሄዶ ገደል ከሆነ መጨረሻው መሰባበር ነው ።
  በሀገራችንም ጉዳይ ሺ ውይይት ቢደረግ፣ ባለስልጣኖች ቢቀያየሩ ፣ የህግ ጋጋታ ቢወጣ የኣንድነታችን የጉሮሮ ኣጥንት የሆነው ሀገራችንን እንደ ቅርጫ ስጋ ለጎሳዎች ያካፋፈለ ፣ ብሎም ” የኔ ፣የኔ ” ኣስተዛዛቢ የህጻን ጥያቄን ይሰፈነ ህገ መንግስት ተሽሮ ሀገራችንን የሁላችን በእኩልነት ባለቤትነት ባረጋገጠ ሰነድ ካልተተካ መጨረሻው ውዽቀት ነው።
  እርግጥ ነው በግርግር ይሁን በነበራቸው ጉልበት የማይገባቸውን ያገኙ ጥቅመኞች፣ ስግብግቦች፣ ወከልነው ለሚሉት ህዝብ ማፈሪያ የሆኑ ፣ ለራሳቸው ክብር የሌላቸው ለታሪክ ደንታቢሶች ,predatory ምሁራን እሪታ መቅለጡ የማይቀር ነው ። ዋሸው እንዴ ገመዳ,በቀለ…??
  ቢያንስ እኩልነትን ማቀንቀን የሞራል ልእልናን ነው የሚያሳየው፣ ትንናት የበታች ሆኜ ተሰቃይቻለሁ ብሎ የሚያላዝን ዛሬ የበላይ ካልሆንኩ ሲል ያማል ፣ያስንቃል፣ድሮም ለራሱ ከርስ እንጂ ለህዝብ ያልታገለ ከንቱ መሆኑን ነው የሚያሳየው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.