ሱስ ጎርፍ መጣ ደሞ! (በላይነህ አባተ)

—-ሱስ ጎርፍ መጣ ደሞ—

ለሁለተኛው ዙር ጥርጊያ ተዘጋጅቶ፣
ሕዝብ ሊያደነዝዝ ሱስ ጎርፍ መጣ ደሞ፡፡

በመጀመርያው ዙር ሰውን ጥንብዝ አርጎ፣
ይጦብያ ሱስ ናት ሕዝብን አስተኝቶ፣
ወንበር አግዳሚውን ወሰደ ጠራርጎ፡፡

ሱሱን ጭልጥ አርጎ ሕዝብ ሲያንቀላፋ፣
ግንዱን አንከባሎ ተላይ ተሱሉልታ፣
ጉልት አደረገው ታዲሳባ ጫንቃ፡፡

እየዋለ ሲያደር ሱሱ ሲጠንክር፣
ያፈናቅል ጀመር ዜጋ እንደ ባይተዋር፡፡

የሱስ ማደንዘዣ አገር አስተኝቶ፣
ጋሞን አስጠረገ ሸዋ ውስጥ ቡራዮ፡፡

ሱሱ ከቡራዮ እንደ ጎርፍ ፈሶ፣
ጠቅልሎ ወሰደው “መጤን” ለገጣፎ፡፡

ስካር የነዳው ሱስ ስብተን በጥሶ፣
የእንጦጦን አቀበት ሽቅብ ተፈናጦ፣
ሱሉልታን አወከው ውሀ ሙላት ሆኖ፡፡

ይህ የሱስ ነጎድጓድ ወደ ደቡብ ነጉዶ፣
በማበል ወሰደው ጌዲኦን ጠራርጎ፡፡

ሱስ ጅረትን ሆኖ ሰውን ተጠረገው፣
ባህር ሲደርስማ ምን ነፍስ ሊተርፈው ነው?

ሕዝብ ሆይ ነቃ በል ሱሱ ማዕበል ነው፣
የዋጣትን አገር ጠርጎ ሊወስዳት ነው፡፡

የሱስ ጎርፍ ህሊና ይሉኝታ የለውም፣
በውል በምክክር ባማላጅ አይቆምም፣
ገድግዶ የሚያስቀር ያስፈልጋል ግድብ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መጋቢት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

6 COMMENTS

 1. የሱስ ማደንዘዣ አገር አስተኝቶ፣
  ጋሞን አስጠረገ ሸዋ ውስጥ ቡራዮ፡፡
  ሱሱ ከቡራዮ እንደ ጎርፍ ፈሶ፣
  ጠቅልሎ ወሰደው “መጤን” ለገጣፎ፡፡

  የኛ ገጣሚ ፣ ሎሬት ፣ ባለቅኔ ……..

  የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆኑት በክቡር አቶ ለማ መገርሳ ላይ ይህንን የወረደ ትችት ከሚጽፉ የአማርኛ ፊደላትን በድጋሚ ይማሩ፡፡ ቡራዩ ለማለት ቡራዮ ብለው ከፃፉ መሠረታዊ የፊደል እውቀት የሚጎድሎት መሆንዎን ያሳያል ፡፡ የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ

 2. የፊደል ግድፈት!
  አማርኛ ሁለተኛ (ክለተ) ቋንቋው ስለሆነ ነው:: ሞቶ ጊዜ ግጥሚ ይገጥማል ሆኖም እርባና ይለውም:: እጅ እጅ ማለት አልፎ እግር እግር ይላል

 3. እኒህ ዲጂታሎች ግጥም ያውቁበታል
  የበታችኛውን በላይነህ ይሉታል
  መቼስ አያልቅበት የኛውስ መከራ
  ቆርጠን ካልተጋፈጥን አንድ ላይ በጋራ፡፤
  እስቲ በምን ስሌት በምን መመዘኛ
  ለማን ለመተቸት ደፈረ መጋኛ ብሎም ይህ ጉደኛ?
  ራቱ ናማገዲ ብለን እንዳንዘልፈው
  ኩን አጃኢቡማ ብለን እንዳንለው
  ቱርጁማን ፍለጋ ስቆጣ ሊሄድ ነው
  ግዛቱም አይዶለ ምንስ ችግር አለው??

 4. Demeke and Enaw,

  This is laughable. Teach this man Amaric, teach him! Since when the Qube people became experts in poem, kine and amarigna?

  No shame, right? You are runnning crazy with this Kegna politics. Y

 5. ያኔ በየዋህነት ልባችን ተከፍቶ
  ጣና ኬኛ ሲሉ ወገን ሁሉ ሰምቶ
  ከወያኔ ስቃይ ለመገላገል ሽቶ
  ህዝቡ ተቀበለው ያለፈውን ረስቶ
  ጉድና ጅራት ወደኋላ የሚለው ተከተለና
  የሁሉን ከተማ ዲሞግራፊ ማሳበጥ ተከጀለና
  አንዱ ዋና ዜጋ ሌላው ሁለተኛ ተቆጠረና
  ባለሜንጫው ሲሸለም ባለ ብእሩ ተገፋና
  ደም ይፈሳል ባለው የሰዎች ቤት አስቀማና
  ዛሬም የኢትዮጲያ ሱሴ ኣአልነጠፍም ተብልና
  ኑ ላሞኛች ሁ ለልጆቼ ጥሩ ታሪክ ላቆይ በዝና
  ይለናል የሃገር ሱሱን በዘር መቀየሩን ረሳና በስልጣናችን በድለናል ያለ እንዲረሳለት
  በተቀባባ ታሪክ ይሞክራል ህዝብ ለማሳት
  እኛ ግን ነቅተን እንደአይጧ ጉድጕድ ምሰናል
  ድጋሚ ላለመታለል ከራሳችን ጋር ቃል ገብተናል
  የታለሉትንም ሁሉ ንቁ በጊዜ ተመለሱ ብለናል
  ይህው ዛሬ ደረስን ለሙሴ ተብዬ ሲመት
  በሽንገላ ቃላት የሰው ልብ ሊቃትት
  የኢንሳ ወያኔ ስለላን ክፋት የለለበት
  ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ ተኮፈሰበት
  በስልጣናችን በድለናል ያለ እንዲረሳለት
  በተቀባባ ታሪክ ይሞክራየታለሉትንም ሁሉ ንቁ በጊዜ ተመለሱ ብለናልል ህዝብ ለማሳት
  እኛ ግን ነቅተን እንደአይጧ ጉድጕድ ምሰናል
  ድጋሚ ላለመታለል ከራሳችን ጋር ቃል ገብተናል

 6. Abaaaaaaaaaaaaaa WiiiiiiiiiiiRTUuuuuuuuuuuu’s stomach and greed has no limit.
  He is claiming Sekota as well. “ye kotun Aword billa yebibtuan Talech!” You will loose Wolega let alone get Sekota. Tigabih Chereka Dersualnal! Meliso gin yafetihal.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.