ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነርነት 89 ግለሰቦች ተጠቁመዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ 89 ግለሰቦች መጠቆማቸውን አስታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ ጸሐፊ ዶክተር ተመስገን ባይሳ እንደገለጹት፥ ጥቆማው ከመጋቢት 1 እስከ መጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ተካሂዶ የእጩዎች ምዝገባ ተጠናቋል።

ህብረተሰቡ እጩ ዋና ኮሚሽነር መጠቆም እንዲችልም ሚዲያን በመጠቀም ማስታወቂያ መነገሩንም ጠቅሰዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፥ የጥቆማው ሂደት ግልጽና አሳታፊ እንደነበር መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የእጩ ተመዝጋቢዎችን የስራ ልምድና የትምህርት ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሚያስፈልግ ለኮሚቴው ሃሳብ ቀርቦ ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ መክሮ በሁለት ቀናት ውስጥ ስራውን ለማጠናቀቅ ወስኗልም ነው ያሉት።

EBC

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.