ይድረስ ለዶር ህዝቀኤል ገቢሳ ኢትዮጵኛን በተመለከተ(ከአባዊርቱ)

ከትላንት በስትያ ወትሮ እንደልማዴ
LTVን ስቃኝ ቤቲን በመልመዴ
የህዝቀኤል ቅኝት አስታውሶኝ ቁምነገር
ላነሳ ፈለኩኝ የተረሳ ነገር፤፤
እንዲህም ነገሩን የጫት አጥኚው ምሁር
ለሁሉ መግባቢያ ለገሱ አንድ ምክር፤፤
አማርኛው ቀርቶ ቢሆን ኢትዮጵኛ
ሁሉ ከተስማማ ላንቃወም እኛ
ይሆን ከሆነልን ለቶጵያ መዳኛ
እስቲ እንዲህ ልማለድ ለኢጆሌ ኬኛ!!
ምሁሩ ባይሉም የቁቤው ቤተኛ፤፤
እናንት ወገኖቼ ትውልደ ዖሮሞ
በፅሞና አድምጡኝ በጣም በአርምሞ፣፣
ላቲን ዖሮሚፋን አግብቶ እንደዋዛ
ሲያሰቃያት ኖሩዋል ይህ ገልቱ ፈዛዛ፣፣
፪፰ አመት ያላቻ ጋብቻ
ወይ ትዳር አልሆነ ወይም ጉዲፈቻ
ፅልመት ስላጨልን ደረሰ መፋቻ፣፣
እንደኔ እንደኔ እንደ ልቤ ቢሆን
ምራቁን የዋጠ ሸበቶ ፈልገን
እንዳር ዖሮሚፋን ሸበላ ፈልገን
ምን ሮማ ወሰደን «ኢትዮጲስ» ሳለልን፣፣
ግእዝ ያሳደገው የኛው ኢትዮጵኛ
ይሆናል ግድ የለም አብሮ አደግ ቤተኛ ፣፣
ባይሆን እንዳይጎዳት ገሩዋን ዖሮሚፋ
ህግጋት መንደፍ ነው እንዲሆናት ተስፋ፣፣
የላቲኖን ትዳር እስካሁን ካየነው
ያልገባበት የለም ፍፁም ቀላዋጭ ነው
ሲሻው ሱማሌ ሴት ካልሆነም ሲዳማ
ከሀዲ ሰላቶ ስራው የተግማማ
አልመርጥም ላቲኖን ለእናት ዖሮሙማ፣፣
እስቲ ለምሳሌ ህዝቀኤሌ መጥቶ
የዚህን ሰርግ ጥሪ በቁቤ አጉልቶ
ይፃፍልን እስቲ በደንብ ተንሰራፍቶ
ከዛም እንጠይቀው “ማ ገባው” ብለነው
ከመቶ ሚሊዮን ህዝብ ስንቱን ላንጋብዝ ነው?
መቼስ የሰርግ ጥሪ መዘዙ ብዙ ነው፣፣
ወትሮም ፍቅር ካለ በትዳር መሰላል
የኛው ኢትዮጵኛ ለኛዋ ልጅ ያምራል፣፣
ደሞ ያምራል ስለው በትእቢት እንዳይቆም
ዖሮሚፋ እንደሆን አቻዋን አታጣም፣፣
ኬንያ ብትወርድ ጠንበለሎች አሉ
ሌት ተቀን በፀሎት ” ኑ እንጋባ” ሚሉ:)
ሆኖም!
ግእዝ የቶጲኛው ሁሉንም ወካይ ነው
ያማራ ርስተጉልት ብሎ ያለው ማነው??
ቤቲ በዚህ ጉዳይ ምክንያትሽ ድንቅ ነው
እስቲ አትከፉብኝ ትዳር ከባድም ነው፣፣
ላቲኖ የኛን ልጅ በድፍረት ጠልፎብን
ከልካይ ሳይኖርበት “እኛን” ሳይጠይቁን
እያነባች አለች ታያለች ስቃዩዋን፣፣
የስቃይ ምልክት ምንድነው ካላችሁ
ከጋብቻ ወዲህ ያለውን አይታችሁ
ፍረዱኝ እናንተው ያለውን ሁኔታ
የትምህርቱን ነገር ያለውን እውነታ፣፣
የዖሮሚፋ ልጆች በገጠር ያሉቱ
ላቲኖ በርዞት ይህ “የሰው” ገልቱ
ሳይንሱን ሳያውቁት መርምረው በብርቱ
ይመጣሉ ሸገር ወደመሀል ገብያ
እዛም ነገር ያለው ልክ እንደዖሮምያ
እጅ አይሻል ዶማ የሌለው ማብቅያ፣፣
እናሳ!
ግእዝን ሞሽረን መክረንም ገዝተን
ኢትዮጵኛ አባቱን ቃልኪዳን አስገብተን
በወግ እንዳራት መልካም ልጃችንን፣፣
የስርጉም አዳራሽ ሸገር ይሁንልን፣፣
ከጋብቻው በፊት ወገን እንዲስማማ
የልጅ ሽማግሌ ድምፁ የተሰማ
ቆፍጣናው ዖሮሞ ክቡር አቶ ለማ
ያውጅ ስርጋቸውን ከታላቁ ማማ፣፣
ማማውም ሸገር ነው ያፍሪካ መዲና
ስርጉን የሚረብሽ ኩታራ ይምጣና
መቼስ ሰርግ ሲባል አፍራሽ አይቀርልን
በሺመልም ቢሆን እንተያያለን፣፣
እንደው ለጫወታው ነው እንዲህ ማለቴ
ሰርግማ ፍቅር ነው አምናለሁ ካንጀቴ፣፣
 ግን ግን
የጥሪው ካርድ ላይ ፅልመት አይካተት
ሰርጉም ሰርግ አይሆንም “እነሱ” ያሉበት
ከንግዲህ ይተውን አባገዶች አሉን
ብንሳሳት እንኩዋ ቀድመው “ሀይ” የሚሉን፣፣
እናም ዖሮሚፋ ወገን ተትረፍርፎ
ያገር ልጅ ይሻላል ጣይው ያን ጅላንፎ፣፣
ላቲኖም አትሞኝ ግባ ወዳገርህ
ከእምዬ ቶጵያ መዳራት ይቅርብህ፣፣
እንኩዋን ለዖሮሚፋ ለኔዋ ዘንካታ
አልመኝም አንተን መልስ የኛን ካርታ
እዛው “ሮማ” ጥፋ አንት የ “ሰው” ወስላታ፣፣
ለሱማሌም አትሆን እንኩዋን ለሲዳማ
ለህዝባችን  ላትሆን ፍታ የኛዋን ልጅ አንት ክፉ ገገማ፣፣
ይህን የኔን ጥሪ በክፉ ያያችሁ
ከመነቃቆሩ አይሻል ብላችሁ?
ኬኛ ፖለቲካ እንድያ ለምትሉ
ኬኛ አቃፊ ነው አርፋችሁ ቁጭበሉ፤፤
ከሚለያይ ጉዳይ አንድ ላይ ብንሰራ
ሁሉም የየጥጉን ይዞ ባያቅራራ
እንቀርፈው ነበር መከራን በጋራ፤፤
አሁንም አልመሸም ቅንነቱ ካለ
ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ማድረግ በተቻለ፤፤
ቅንነት ካነሳን መቼስ መሞት ላይቀር
ሙስጠፌን ከምስራቅ አቢቹን ከሸገር
ደጉን ሰው ከምራብ ደቡብ አንዱም ሳይቀር
ህዝባችን ደጋግ ነው ከፅልመቶች በቀር፤፤
ጥንት ጨቅላ እያለሁ ያስተዋልኩት ነገር
ትግራይ ማተብ ነበር የአማኞች መንደር፤፤
ዛሬም  እንዲህ ሆነው ተከበው በፈንጅ
ደጋጎች አይጠፉም ተቀፍድደው እንጅ
እናም ወገኖቼ አንፈራረጅ
ክፉው ያገር ያምራል ከደጋግ ፈረንጅ፤፤
መጋቢት 2011 አመተ ምህላ

7 COMMENTS

 1. ” ይድረስ ለዶር ህዝቀኤል ገቢሳ ኢትዮጵኛን በተመለከተ(ከአባዊርቱ) ”

  I only read the title.

  When will Native Ethiopians, some 90% of the Ethiopian population, run out of patience ?

  The truth is, Native Ethiopians have not yet used all the weapons in their arsenal against extremist oromos.

 2. @Lema
  By Native you mean indigenous and the majority perhaps? If so, I will tell you when:

  1) When oromos and amharas seriously wake up and smell my most favourite Yirgacheffe coffee.

  2) when Ethiopian elites scratch beneath the surface and realize not all human likes are indeed humans. There indeed are digital rats masking as humans. @Lema is the project leader of their Digital Early Response Team (DERT),

  3) when Ethiopians pause and reflect on their own emotions before uttering a single word,

  4) when the MIGHTY oromo and Amhara extreme right wing intellectuals realize the dwarf tplf has outsmarted and soon outlive them while they are fighting that dwarf’s war, sadly, on their own land sacrificing their own family members in the process. SHAME ON YOU ENABLERS!!

 3. @አባዊርቱ;
  Do you seriously believe that of all Oromo intellectuals, there is no one who could have advocated for Fidel, had it been suitable for Oromiffa?? You are either too habesha(nized) and see everything Oromo negatively only, or you are too delusional to believe in Habesha demagogy. You have admitted that you do not right or read Oromiffa in Qube. Have you ever tried to write a few paragraphs in Oromiffa using Fidel? If yes, show us! Else, how do you know (other than Habesha propaganda) that Fidel is suited to Oromiffa?

  Please translate the following sentence into an other language you like:
  1) ጋላ እሳቲ ጋላ ፈአቴ ጋላ ካኤ። 2) ጋራን ጋራ ጋራ ካጄሌ 3) ባላን ባላ ባላ ቃቡ ባቴ ባላ እራ ቡቴ
  Let me know how many meanings you have found for each sentence (if you have understood them!). Then I will show you how that is easy using Qube. (NB: No repition of same words here! all the words with the same Fidel transcriptions have actually different meanings)

 4. @ Abawirtu

  I read your comment, and realized that the issue is about the Latin alphabet.

  We Native Ethiopians should perhaps warn these foolish oromos: don’t continue insulting us by using the Latin alphabet inside Ethiopia or we will ban the Oromigna language among Native Ethiopians, making that tribal language less important than Tigrigna and Somaligna.

  Enough with the “eshururu” policy towards these foolish oromos.

  * ” @Lema is the project leader of their Digital Early Response Team (DERT),”

  >>> Hmmm …

  * ” 4) when the MIGHTY oromo and Amhara extreme right wing intellectuals realize the dwarf tplf has outsmarted and soon outlive them while they are fighting that dwarf’s war, sadly, on their own land sacrificing their own family members in the process. SHAME ON YOU ENABLERS!!

  >>> “… fighting that dwarf’s war”, hmmm …, you should blame tribalists, above all oromo tribalists, who were supposed to say “NO” when TPLF gave them land that never belonged to oromos. They are greedy and foolish. If they were wise they would have returned the land that belongs to all tribes (including oromos) and Ethiopia. But as we can see they are refusing to return back the land TPLF stole from other tribes and gave them. How come they don’t know that buying a stolen property is a crime ?

  So you think the Oromo and Amara elites are going down and TPLF is rising again ? I don’t know, but if Oromo elites go down who are tribalist it is not a bad thing. If Amara elite tribalists go down too not a problem. Tribalism is evil, it makes enemies out of Ethiopians, making the country an easy target to foreigners as we saw during the TPLF era.

 5. Re: Please translate the following sentence into an other language you like:
  1) ጋላ እሳቲ ጋላ ፈአቴ ጋላ ካኤ። 2) ጋራን ጋራ ጋራ ካጄሌ 3) ባላን ባላ ባላ ቃቡ ባቴ ባላ እራ ቡቴ
  Let me know how many meanings you have 

  Very easy dear አባጫላ starting with your own name. Notice how easy that is. We could extrapolate even further into ጫ ላ as stretched two fidels would have different meaning as ጫ ላ (ጄ’ዲ) (to mean dhi); and together would mean good riddance (ጥርግ በል). Futhermore, ጫላ = በለጠ = የአህል ዘር = ጥርግ , etc Now, back to your questions:

  1) ትርጉሙ፤ በ ግመሉ ላይ ስንቁን ጭኖ ወደ ቄዬው ሊነሳ አኮበኮበ ወይም
  ወደ መጨረሻው ግመሉን ጭኖ ወደቤቱ ሊሄድ ቆረጠ
  ወይም
  ወደመግቢያው ስንቁን ጭኖ ሊሄድ አኮበኮበ ( 3 different meanings)

  2) ሆዴ እንለያይን ከጀለ
  ወይም
  ልቤ/ሆዴ ላይ ላዩን ይሻል
  ወይም
  ሆዴ የሩቅ ሩቁን ይሻል (ያንተ ቢጤውን የቅርቡን በወዳጅነት አብሮን ያደገውን ፊደል ትቶ የሩቅ ሩቁን ባእዱን ላቲን እንደመሻት ቅቅ)

  3) ጠንጋራዋ ቅጠል ቅጠሉን ተሸክማ ከቅጠሉ ወደቀች ወይም ወረደች
  ወይም
  ባላ ወይም ቅርንጫፍ ቅጠል ቅጠሉን አዝላ ለቅጠሉም አልበቃች
  ወይም
  ውቃቢ ወይም ፅልመት ቢጤዋን ልትይዝ ሄዳ ከፅልመት ስልጣንዋ ወረደች
  ወይም
  ፅልመት ፅልመትን ልታድን ሄዳ ሌለኛው ፅልመት ላይ አረፈች ወይም ቢጤዋን አገኘች

  Look, I would like to know list of names of these oromo intellectuals who came up with qubee for our people. I honestly believe they have not consulted with various scholars on ethiopic fonts. I also believe our monasteries, various religious figures and orthodox scholars around Debrelibanos in particular and shoa in general have not been sought after. Our moslem imams from Wello and Harar should have deliberated over several months before adopting qubee. I am not a linguist ; but I know growing up in rural shoa in various awrajas, I assure you geez Fidel would have beautifully represented oroomifa. የአንድን ህዝብ መግባብያ ፊደል ስትቀይስ ብዙ ጊዜ ወስደህ ህብረተሰቡን በጥልቅ አወያይተህና ቡራኬ ተቀብለህ እንጂ የህዝቡ ልሂቃን በበጎ ፍቃዳቸው ብቻ የሚቸሩን ልገሳ መሆን የለበትም፤፤ ወያኔ ለራሱዋ ጉዳይ ይህን ብታፋጥንና ብትደግፍ አይገርመኝም፤፤ በሪሳ ከ 40 አመታት በፊት በኦሮሚፋ የገዝን ፊደል ተጠቅሞ የሚወጣ የዖሮሚፋ ጋዜጣ ነበር፤፤ ቅንነቱ ቢኖርና ያ ቢሰፋና ቢገፋበት ኖሮ ፊደሉን እንደፈለግነው ለኦሮሚፋ እናሳድገውና እናፋፋው ነበር፤፤ ለምሳሌ ‘ ፀ ‘ ን ‘ ደ’ ግምባር ላይ ስትለጥፈው አንተ dha የምትለውን ቃል ይሰጥ ነበር ፤፤ ለምሳሌ በዳዳ ወይም badhadha የምትለውን (የ ፀን ጭንቅላት ‘ደ’ ላይ ተጭነህ የምታወጣው ቅላፄ ይሆናል ማለት ነው፤፤ እኔ ለምሳሌ« ‘ዳን » በራሴ ፍቃድ እንደዛ ነው የምጠቀመው፤፤

  Lastly, our oromoo intellectuals had their own best interest at heart when they crafted qubee for our people. If you look at it logically, you may arrive at the same conclusion. Look, how many of our farmers or common people are familiar with Latin alphabet? Majority of our people are at least familiar with Fidel fonts whether they deploy it for their day to day living or not. These poor souls were not consulted when the intellegentia imposed qubee upon them. Nobody took statistical sampling of any kind. TPLF supported and totally endorsed the Qubee scheme and alas, it is the lingofranca of oroomos now. I for one assure you it is never too late to reverse this. Oroomifa will not thrive under qubee. If you want to nurture oroomifa and slowly give it a multiregional stature, one should open up venues to reach as many people as possible. I miss level headed oroomo intellectuals of yesteryear – not Beqele Gerba types who really is doing the opposite for ዖሮሚፋ or ዖሮሙማ for that matter. ሜ ቱቱቅጤ ጋራ ናንሃሜሲን አቤ! ኦፊ ማሉም ታኡሳቲ? ናማ ባራቴ ሞቲ? ማኑማ ሂ’ዳ ሳኒቲ ሳሙሳ ቱቃኒላታ? ኦዶን ባዬ ኢሳፋርሱ ናሳልጲሳ? ጄ’ዲ ሲላስ ማልቱ ና’ዳጋአፍ፤፤ ናጋፋናን ማሌ፤፤ ናጋቲካ!

 6. የረሳሁት ዋንኛው ነገር፤፤

  ፊደል ወይም ፅሁፍ እንደንባቡ ሳይሆን እንደአረዳዱም ነው፤፤ 3ቱን ጥያቄዎችህን ዖሮሞ ላልሆነ እንኩዋንስ የተለያየ ትርጉም ሊሰጥህ አንዱንም አይወጣውም፤፤ ጭራሽ ስድብ ሆኖ ያርፈዋል፤፤ ከትርጉም ጀርባ ኮኖቴሺን አለና፤፤ እናም ችግሩ የቃሉ ፊደሉ ላይ አረፍና የሚሰጠው ቅላፄ ሳይሆን የሚወስነው የተጠቃሚው ማንነትም ጭምር ነው፤፤ ስለዚህም የቁቤ በለው የፊደሉ ተጠቃሚው ዋንኛው ዖሮሞ ከሆነ የላቲኑ ፊደል ይሁን የፊደላችን ልዩነት አይኖረውም፤፤ ልዩነቱ የግ እዝ ፊደል ከዖሮሞው ጋር ለረጅም አመታት አብሮ መኖሩና ህዝባችን እንደፈለገው እየጠረበ እንደሚመቸው አርጎ ቀርፆ ሊስተናገድበት መቻሉና መቅለሉም ነው፤፤ በዚህ ላይ ተጨማሪው ትርፍ ዖሮሞ ያልሆነው ያገራችን ህዝብ ዖሮሚፋ ማወቁ ይጠቅመናል እንደህዝብ ከሚልም ነው፤፤ ቀዋንቀዋም አንደኛው ማደጊያው መንገድ ይህው ነውና፤፤ በየምሽጋችንማ ከሆን እንኩዋን አገራዊ ልንሆን ለክልልም አንተርፍም፤፤ አማኑማ ዮ ሲጋሌፍ! ሌላው ቁቤ ከመጣ ወዲህ የዖሮሞ ልጆች ኢንግሊፋ እንዳሽቆለቆለ ልብ ብለሃል? መረጃው ስላለኝ ነው፤፤ ምን ችግር አለው እንዳትለኝ ብቻ፤፤ ናጋን!!

 7. አባዊርቱ; ዱፍቴ??
  Congratulations, you got an ‘F’ in Oromiffa test!
  First, you did not understand the point of my question, i.e. if a sentence (mind you, not a single word, but the full sentence) can have multiple meanings, how are you going to put your message through?? If you want to read a story, how would it be interesting if you have to reread each and every sentence multiple times just to find out its meaning??

  I stated that each word with same transliteration in Fidel are all different (differ in intonation, vowel length, etc, so have different meanings) but have only one Fidel representation. Eg. ‘ጋላ’ can stand for ‘gaala’ (camel), ‘galaa’ (provisions, ስንቅ), ‘gala’ (return journey), ‘galla’ (let’s go home), ‘gaallaa’ ( that pejorative word you know), a total of 5 words, 4 of which are nouns! All the four nouns can take any of the 3 positions in the example sentence! in addition, ‘ካኤ’ can stand for 2 verbs (ka’e (started, stood up) or kaa’e (put)). The combinatoric gives, how many possible sentence? Good 4*3*3*2 = 72, even if repititions are disallowed!

  You see how you gloss over this technical KO for Fidel !! You and all Habesha intellectuals, who mostly do not even speak Oromiffa show a parade of sentimentalism, stating how Oromos and Amharas are inter-married, bla bla, but never mention this unsurmountable technical problem. And, if you may not know, no amount of political haranging has ever solved a technical problem!

  What did you understand with the ‘greeting’ ‘ዱፍቴ??’ ‘Dhuftee’ or Dhuuftee’ or duuftee?? Specially verbs pose a tremendous problem, because the ambiguties run through all the denomination of the verbs (present, past, future, forms, 1st, 2nd and 3rd person, singular or plural, etc).

  But you see how one can easily differentiate the words using Qubee! Not to leave you with an ‘F’, to encourage you to “double your ‘endeavour to learn qubee 0;”, let me give the other ambiguous words in Qubee: Mind the position of double vowels and consonants!
  ‘ጋራ’ – ‘gaara’ (mountain), ‘garaa’ (stomach), ‘gara’ (to, towards) (3)
  ‘ባላ’ – baala (leaf), balaa (accident), ballaa (skew eyed, blind), baallaa (forked branch) (4)
  ‘ዱፈ’ – dhufe (መጣ), dhuufe (ፈሳ), duufe (ተንጋደደ) (3)

  You stated: “I assure you geez Fidel would have beautifully represented oroomifa (sic!).” That is only for the gullible! But I do not need an assurance, I know what I am talking about!

  Baradhu! “Man lernt nie aus!” say Germans. መማርን ጨረስኩ! አይባልም ማለታቸው ነው።
  Nagaatti!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.