ከአፋር ወጣቶች ዱኮ ሂና የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

በሀገራችን ከአንድ አመት በፊት የተጀመረው ለውጥ በአፋር ክልል ከ6 ወራት በፊት ተጀምሯል ይባል እንጂ እስካሁን ምንም ነገር አልተጀመረም።
በክልሉ ሲነሱ የነበሩ የህዝ ጥያቄዎች በአፋጣኝ መመለስ የነበሩባቸው ቢሆኑም እስካሁን የተለወጠ ነገር አለመኖሩና ህዝቡ ቀደም ሲል የታገለለትን ጥያቄዎች እንዲመለሱለት ዳግም ወደ ትግል እየተመለሰ ይገኛል።
በጣም ኃላፊነት በተሞላበትና በአከባቢው ችግሮች እንዳይፈጠሩ በሰላማዊ መንግድ የተደረገው ትግል የተወሰኑ ሰዎች ወንበር ከመቀየር አልፎ መሰረታዊ ለሆኑ የህዝብ ጥያቄዎችን በተግባር መመለስ አልቻለም።
እንዲያዉም ቀደም ስል የነበሩና የቆዩ ችግሮች ተባብሰው የቀጠሉበትና ህዝብን ያስቆጡበት ሁኔታ መኖሩን በግልጽ እያየን ነው።

የሀገር መከላኪያ ሰራዊት ሰላም በማስከበር ስም በሰፈሩበት አከባቢዎች ከኮንሮባንድስቶች ጋር በመሆን ንጽሃን አርብቶ አደሮች ላይ የሚያደርጉትን ግድያ አጥብቀን የምንኮንነው እና በተለይ ደግሞ መከላኪያ ተለውጧል በተባለበት በአሁኑ ወቅት ንጽሃን በመንግስት መሰራያ መግደል በአስቸኳይ መቆም አለበት።

ትናንት 28/06/2011 በአፋር ክልል ጋዋኔ አከባቢ የአኢትዮጲያ መከላኪያ ሰራዊት በጥይት ደብድበው የገደሉት ወጣት ላይ የተፈጸመው የጭቃነ ግድያ በፉጹም ጠቀባይነት የለለዉም።
ይህንን ድርግት የፈጸመው የመከላኪያ አባልና ትዕዛዝ የሰጡ ኃላፊዎች በህግ እንዲጠይቁ እንጠይቃለን።
ይህን አይነት ድርግት ይህ የመጀመሪያው ስላልሆነ የመከላኪያ ሰራዊት ከአከባቢው ለቆ እንዲወጣና የክልሉ መንግስት ሙሉ በሙሉ ሰላም የማስከበር ስራ እንዲሰራ እንጠይቃለን።
አከባቢዉን ጠንቅቆ የማይውቁና በጥቅም ከኮንትሮባንድስቶች ጋር የተሳሰሩ ሆድ አደሮች በዚህ አከባቢ ሰላም ማስከበር ሰላማይችሉ ችግሮቹ ሳይባባሱ የሚመለከተው አካል ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥ እናሳስባለን።

በተጨማሪም በአጠቃላይ በክልሉ በየቦታው የሚነሱ ተመሳሳይ ጥያቄዎች እንዲሁም የቆዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ህዝብን በማዋያየት በአስቸኳይ ሊመለሱ ይገባል።
በውጭ ሀገራት መንግስታት የሚደገፉ ታጣቂዎች ሳይቀሩ ወደ ክልላችን እየገቡ ህዝብን እያሸበሩ ያሉበት ሁኔታና የኢትዮጲያ መንግስት ማስረጃዎች እያለዉ የሚያደርገው ዝምታ ህዝባችን በዜግነታቸው ላይ ጥያቄ እንዲኖራቸው እያደረገ ይገኛል።

ከሀገር ዉጭ ከሚገኘው የዲፕሎማሲ ጥቅም በፊት የዜጎችን ሰላምና የሀገር ሉዓላዊነት ማስከበር ሊቀድም ይገባል።

እኛ የአፋር ወጣቶች ዱኮ ሂና ከአመታት በፊት የህዝብን ትግል ዳር ለማድረስ የጀመርነዉን ትግል አሁንም በሰላማዊ መንገድ ከህዝባችን ጎን በመሆን እንደምንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

የተከበሩ የአፋር ወጣቶች በጎሳ፣ በአከባቢና በጥቅም ሳይለያዩ የህዝብችን መሰረታዊ የሆኑ ጥይቄዎችን በማንሳት አብሮ በተቀናጀ መልኩ እንዲታገሉ እንጠይቃለን።

አሁን ክልሉን እየመራ ያለው አመራር በጎሳ፣ በኔትዎርክ እና በቡድን በመከፋፈል በዛው ልክ የህዝባችን አንድነት መከፋፈሉን በአስቸኳይ አስቁሞ ለውጡ የሚጠይቀዉን አማራር መስጠት ካልቻለ እኛ ትናንትም ሆነ ዛሬ የምንታገለው የህዝባችን ጥቅም እንዲከበርና የሰለጠነ ፖለቲካ እንዲጀመር እንጂ የነበረው አሰራር ሌሎች አዳዲስ ሰዎች እንዲቀጥል ስላልሆነ ልብ ያለው ልብ እንዲገዛ ከወዲሁ እናስጠነቅቃለን።

የአፋር ወጣቶች ዱኮ ሂና

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.