አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በመዲናዋ እየተከናወኑ ባሉት የለውጥ ስራዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
የአንድ ዓመት የለውጥ ሂደቱን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ውይይት እያደረጉ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በውይይቱም ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ የተከናወኑ የለውጥ እርምጃዎች ግምገማ እና ቀጣይ የከተማዋ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይም ምክክር የሚደረግ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ መድረክ ላይ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ 1 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ አመራሮች ይሳተፋሉ።
በቀጣይም የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው የሚወያዩ መሆኑ ተገልጿል።