ስለ ምንድን ነው የምንነጋገረው? (ከስመኘው ጎበና)

ከስመኘው ጎበና

በቀዳማዊ ሀይለስላሴ የአገዛዝ ዘመን ውጭ አገር ትምህርት የተከታተሉ ኢትዮጵያዊያን የማስትሬት ወይም የባችለር ዲግሪያቸውን በፖስታ ቤት በኩል ላኩልን እያሉ ወደ ሀገራቸው ገስግስው ይመለሱ ነበር ሲባል ሰምቼአልሁ.። በወታደራዊ የደርግ አገዛዝ ጊዜ ለትምህርት ወደ ውጭ አገር በተለይም ወደ አሜሪካ፣ ወደ ካናዳ፣ ወደ ኤውሮፓ ወዘተ መውጣት ገነት እንደመግባት ይቆጠር ነበር። ይህም ሆኖ አብዛኛው ኢትዮጵያዊያን በመላው አለም ከመሰደድም አልፎ በየባህሩ ህይወታቸውን ያጡትና በአክራሪ የእስላም ቡድኖች አንገታቸው ሊቢያ ላይ የታርዱት በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ነው።

በሚያሳዝን ሁኔታ በተለይ ኢትዮጵያዊያን ውጭ አገር ለትምህርት ተልከው ተምረው በተለይም ለብዙ አመታት ውጭ አገር ኖረው ይህንንም ተከትሎ በተለይም በህግ በማሀበራዊ በአስተሳስብ ትምህርት ተምረውና ከመማርም ባሻገር ተዋልደው የኖሩ ለምሳሌ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን እንደ ምሳሌ ማነሳት ቢፈቀድልኝና  https://www.youtube.com/watch?v=amVeXXoDhGg ላይ በአደረጉት ቃለ መጠይቅ አዲስ አበባ የኦሮሞ ዋና ከተማ ነች ሲሉ በእውነትም እኚህ ሰው ይህንን ያሀል ጊዜ ይህንን ያሀል አመት ጀርመን አገር ኖረው ነበር እንዴ ብዬ እራሴን እንድጠይቅ አስገድዶኛል።

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የህይወት ታሪክዎ እንደሚያመለክተው  https://de.wikipedia.org/wiki/Negasso_Gidada ከ 1974 እስከ 1991 ጀርመን አገር ኖረዋል። ታዲያ የጀርመን ፌደራል መንግስት ህገ መንገስት ቁጥር 1 ምን ይላል?

(1) Die Würde des Menschen ist unantastbar. Sie zu achten und zu schützen ist Verpflichtung aller

staatlicher Gewalt.

ስው ስው በመሆኑ ክቡር ነው። ይህ ክብሩም  አይንካም። ይህንንም ማክበርና መከላከል የማንኛውም የመንግስት ሀይል ሀላፊነት ነው ይላል።

በኢግሊዝኛ አንቀጽ (1) Human dignity shall be inviolable. To respect and protect it shall be the duty of all state authorit (Basic Law for the Federal Republic of Germany) ማለት ነው። ይህንንም ጸንሰ ሀሳብ በተመለከተ አቦ ለማ መገርሳ ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ቃል በቃል በሚባል ሁኔታ ስለተናገሩት በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው  እፈልጋለሁ።

እስኪ ለዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጥያቄ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ?!

ታዲያ በእርስዎ ፕሬዘዳንትነት ጊዜ ካላ ነጥብ ፤ድርብ ሰረዝና  ነጠላ ሰረዝ ክጀርመን የተኮረጀው የህገ መንግስት ደንብ የወረቀት ላይ ነብር ብቻ ሆኖ  ቀረ ወይስ ወደ ተግባር ተተረጎም?

እርስዎም እንደሚያውቁት የጀርመን ፌደራል መንግስት 16 አገሮችን ያቀፈ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የጀርመን ዋና ከተማ በርሊን (Berlin) ከ 16 ቱ አገሮች ውስጥ አንደኛዋ ነች። በርሊን በበራንቦርገር (Brandenburg) አገር ውስጥ የተከበበች አገር ነች። እስኪ እርስዎ አጋነው ለማቅረብ እንደሞከሩት በበርሊንና በብራንድንቦርግ አገሮች መካከል ችግር አለ? መልሱ በፍጹም የለም ነው!

ትንሽ ሁኔታውን ለማብራራት በርሊንና ብራንደንቦርግ ወደ 1 አገርነት እንዲዋሀዱ ነዋሪዎችም ድምጽ እንዲሰጡበት ተደርጎ ነበር። የነዋሪዎቹስ ድምጽ ወደ 1 አገር እንጨፍለቅ አሉ?  በፍጹም ሁለቱም አገሮች ያለንን የአገርነት ደረጃ እንደያዝን እንቀጥላለን ነው ያሉት!

ከዚሁ ሳንወጣ ከ 16 አገሮች አንዱ የሆነው የሀምቦርግ ከተማ (Hamburg) በ ኒደርሳክሰን (Niedersachsen) በሽለዝቪሽ ሆልስታይንና  (Schleswig Holstein) በብሬመን (Bremen) አገሮች የታጠረና የተከበበ ከተማ ነው። የሀምቦርግ ከተማ ከኒደርሳክሰን ከሽለዝቪሽ ሆልስታይንና ከብሬመን አገሮች ጋር ወይም እነዚህ ሶስት አገሮች ከሀምቦርግ ከተማ ጋር ችግር አላቸው?  መልሱ በፈጹም የለባቸውም  ነው።

በዚህም ላይ እርስዎ የዶክተሬት ጥናታቸውን  Challenges to Democratic and Economic Transition in Ethiopia, Kenya and Sudan: – A Comparative Study of the Political,Economic and Social Structures in the three Countries/ በሚል አረዕስት ላይ እንድተመራመሩ መረጃዎች ያሳያሉ።

ታዲያ በጥናትዎ፣ በምርምርዎና ከዶ/ር ጹሁፎዎች ጋር በወረቀት ላይ ያስቀመጡትና አሁን የሚስጡት ጋዚርጣዊ መግለጫ ይጣጣማሉ?

አሁን ደግሞ እስኪ በጀርመን የብዙ አገር ዜጎች ነዋሪነት ስብጥር ወደሆነችው የፍራንክፎርት አም ማይን ከተማ (Frankfurt am Main) እና የጀርመን ዋና ከተማና አገር በርሊን ልመልሳችሁ። በነገራችን ላይ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም በፍራንክፎርት ከተማ  ለበዙ አመታት ኖረዋል።

ፍራንክፎርት ከጀርመን ትልልቅ ከተሞች  ውስጥ የብዙ ሀገራት ዜጎች ሰብጥር ያሉባት ስትሆን የአውሮፓ የጋራ አገራትም (EU) ማዕከላዊ ባንክ እዚህ ፍራንክፎርት ከተማ ውስጥ ሲገኝ ፍራንክፎርትም የፋይናንስ ማዕከል ከሚባሉት የአውሮፓ ከተማዎች ውስጥም አንዱዋ ነች።

በፍራንክፎርት ከተማና በበርሊን ዋና ከተማ የብዙ አገር ዜጎች በነዋሪነት የሚኖሩባቸው የብዙ አገር ባሀሎችም የሚስተናገዱባቸው (Multi Kulti = Melti Cultur) ከተማዎች ሲባሉም ይህ አጠራር  እንዲያው ዝም ብሎ የተሰጠ ስም አይደለም። በሌሎች የጀርመን ትላልቅ ከተማዎች ብቻ ሳይሆን በጀርመን በትንንሽ ከተማዎችና መንደሮች ብዙ የውጭ አገር ዜጎች በሰላም ከአገሬው ህይብ ጋር ይኖራሉ።

በ 2008 አመተ ምህረት በፈራንክፎርት ከተማ ከተቆጠረው  641.153 የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ 242.650 ነዋሪዎች የውጭ አገር የዘር ግንድ ያላቸው ናቸው። ይህም  ማለት 37.9% ናቸው። በ 2018 በፍራንክፎርት ከተማ 741.093  ነዋሪዎች  በነዋሪነት የተመዘግቡ ሲሆን ክዚሀም ውስጥ ብዙ የተለያዩ አገር ዜጎች የሚኖሩባተ ከተማ ነች።  ባለው የስታስኪት መረጃ መሰረት የውጭ አገር ዜጋ  ነዋሪ ቁጥር በፈራንከፎሮት አም ማይንና በበርሊን ውስጥ የስንት አገር የወጭ አገር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ይኖሩባቸዋል የሚለው ጥያቄ ተገቢ ስለሆነ እስኪ አሁን የሁለቱን ከተማዎች ሰንጠረዥ እንመልከት። እዚህ ጋር ማሳሰብ የምፈለገው ይህ ቁጥር የትውልድ አገራቸው ሌላ አገር ሆኖ በተለያየ ምክንያት የጀርመን ዜግነት የወሰዱትን ዜጎች አይጨምርም።

ከዚሀ ቀጥሎ ያለውን ስንጠርዥ ይመልከቱ

የፍራንክፎርት ከተማ የበርሊን ከተማ
የፍራንክፎርት ከተማ የውጭ አገር  ዜጎች ቁጥር በ 31 ታህሳስ 2018 ፍራንክፎርት ነዋሪ የሆኑ የሌላ አገር ዜጎች https://en.wikipedia.org/wiki /Demographics_of_Berlin#Population_by_nationality
ጀርመናዊያን 2,998,456
1  Türkei ቱርክ 25.395  Türkei ቱርክ 98,046
2  Croatia ክሮሺያን 16.286  Polen ፖላንድ 57,109
3  Italien ጣሊያን 15.242  Syria ሲሪያ 34,445
4  Polen ፖላንድ 12.496  Italien ጣሊያን 29,912
5  Rumänien ሩሜኒያ 10.779  Bulgarien ቡልጋሪያ 29,414
6  Serbien ሰርቢያን 9214  Russland ራሺያ 24,178
7  Bulgarien ቡልጋሪያ 8678  Rumänien ሩሜኒያ 22,395
8  Spanien እስፔን 7282  Vereinigte Staaten አሜሪካ 20,222
9  Indien ሀንድ 6908  Frankreich ፈረንሳይ 19,664
10  Griechenland ግሪክ 6510 Serbien ሰርቢያን 19,601
11  Bosnien und Herzegowina ቦስኘን … 6079  Vietnam ቬትናም 17,281
12  Marokko ሞሮኮ 6074  United Kingdom ትልቁዋ ብሪቲን 15,898
13  Afghanistan አፍጋኒስታን 4911  Spanien እስፔን 14,683
14  China ቻይና 4646  Griechenland ግሪክ 14,401
15  Frankreich ፈረንሳይ 4605  Croatia ክሮሲያን 13,605
16  Portugal ፖርቱጋል 4003  Ukraine  ዩክሪን 12,206
17  Russland ራሺያ 3376  Afghanistan አፍጋኒስታን 12,080
18  Japan ጃፓን 3353  Bosnien und Herzegowina ቦስኘን … 11,742
19  Eritrea ኤርትሪያ 3157  Austria አውስትሪያ 11,730
20  Vereinigte Staaten አሜሪካ 3147  China ቻይና 11,466
21 Andere ሌሎች 60.480 Other Middle East and Asia ሌሎች መከካለኛው ምስራቅና ኤሲያ 76,868
Insgesamt ድምር 222.621 Other Europe  ሌሎች አውሮፓዊያን 75,688
    Africa አፍሪካ 31,771
    Other Americas  ሌሎች አሜሪካዊያን 23,114
    Oceania and Antarctica  የኦሲያንና አትላንቲክ 5,133
    Stateless or Unclear ዜግኔታቸው የማይታወቅ 22,806

 

ከላይ የተመለከቱትን እውንታዎች ስንረዳ ታዲያ አዲስ አበባ በአለማችን ላይ የሌለች ልዩ ከተማ መሆን አለባት ለዚያውም ልናመሰኛቸው የሚገባቸው ቀዳማዊ ሀይለስላሴ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ዋና ከተማ በሎም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በሎም የብዙ አገራት አምባሳደሮችና የብዙ አለም አቀፍ ድርጀቶች መቀመጫ ስላደረጉልን ሊመሰገኑ ሲገባ አሁን የእርስዎ መግለጫ ህዝብን ከህዝብ መለያየት አይደለም

የእኛ አገር ሰው ሆነው ከዚህም በላይ የማህበራዊ ጥናት ተማራማሪና ጥናት አድርገው በዚህም ላይ ተጨምሮ ጥናትዎ በኢትዮጵያ፣ ኬኒያና ሱዳን ላይ የተመረኮዘ ሆኖና፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት የነበሩ እንደዚህ አይነቱን መግለጫ ሲሰጡ ቢያንስ ቢያንስ አዲስ አበባ ላይ ፕሬዘዳንት ሆነው አገልግለው ከእርስዎ ብዙ ማገናዘብ ሲጠባቅ ይህንን ቃለ መልልስ ሲሰጡ የሞራላዊ ግዴታና ፕሬዘዳንትህ ነኝ ብለው ላስተዳደሩት የኢትዮጵያ ህዝብ ይሉኝታ አይሰማዎትም? በዚህ ላይ ትንሽ ለማከል መለስ ዜናዊ ከስልጣንዎ ሲያባርርዎት አንድነት ውስጥ እስክ ፕሬዘዳንትነት ለስልጣን የተራወጡት በኢትዮጵያ አንድነት የተዘጋጀውን ኢትዮጵያዊ ሀይል ለመከፋፈል ወይም ድብቅ አላማዎን ለማሳካት ነበር?

በእኔ ግምት በአሁኑ ወቅት ከፊታችን የተድቀነው ችግር የሰላም መጥፋትና አለመረጋጋት፣ የበዙ ወጣቶች ስራ ፈትነት፣ የአገራችን የህዝብ ቁጥር አገሪችን ከመታመርተው ምርት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆን ፣ ጉቦኛነት መንገስና የማእከላዊ መንግስት ህጋዊነትን ተግባራዊ ባለማድረግ የተፈጠረ ህግ የለሽነት ህግ አልበኝነት ነው.።

 

2 COMMENTS

  1. No wonder that you are a son of the Gobana who sold his own essence for the sake temporarily leftovers from his master. Finally he died without grace and love. Still now the remember him with negative memories about deeds against the Oromo people.

  2. ስመኘው ጎበና፣
    ችግርህ ምንድርነው?? ይህ የዘከዘክው ከነጋሶ ቃለ ምልልስ ጋር በምን ይገናኛል?? ወይ እንዲያው ስለጀርመን ሃገር ትንሽ አዉቃለሁ ለማለት ከሆነ፣ ሰውዬውን እዚህ ማንሳት አያስፈልግም! ፊንፊኔ (አ አ) ነጋሶ ስላለ ሳይሆን በኦሮሚያ ህገ መንግስት ዉስጥ እንዲያ ስለተቀመጠ ነው። ድርቅና ወይም ድንቁርና ካልሆነ በስተቀር ፍንፍኔ የኦሮሞዎች ርስት፣ የኦሮሚያ እምብርት ለመሆኑዋ ሌላው ቢቀር አ አን በ2 እጥፍ ለማስፋት ባለፉት 27 ዐመታት ብቻ 1.5 ሚሊዮን ኦሮሞ መፈናቀሉ በቂ ምስክር ነው። ስለማታዉቀዉ ከመዘላበድ በፊት ጠይቅና ተረዳ!

    የሚገርመው፣ ፊንፊኔ (አ አ) የኦሮሚያ ዋና ከተማ ሆነች፣ የኦሮሚያ አካል፣ ወደ ጨረቃ ትወሰዳለች አሏችሁ የማይገናኝ ሺህ ነገር የምትቀባጥሩት?? “አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ዋና ከተማ በሎም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በሎም የብዙ አገራት አምባሳደሮችና የብዙ አለም አቀፍ ድርጀቶች መቀመጫ … ቅብጥርሶ” ምን አመጣው?? የፊንፊኔ (አ አ) አስተዳደር በኦሮሚያ ስር ቢሆንስ እነዚህን በምን መልኩ ይለዉጣቸዋል?? የሚያስለፈልፋችሁ ሌላ ነው! Nothing other than Oromo-phobia!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.