መንግስት በኦነግ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ ሊዋጥልኝ አልቻለም * (ፋሲል የኔዓለም)

ኦነግ ከሰላማዊ ትግል ይልቅ የሃይል አማራጭ ያዋጣል ብሎ ካመነ መንግስትም በተመሳሳይ ቋንቋ ሊያስረዳው ይገባል። ወገን ወገኑን የሚያድንበት እንጅ የሚገድልበት ሁኔታ ባይኖር ምኞቴ ነው። ነገር ግን ከመግደል ውጭ የማያስደስተው ቡድን ሲመጣ፣ የሞትን መራርነት እንዲቀምሰው ማስተማር ያስፈልጋል። መንግስት ኦነግን ለማሸነፍ አቅም አጥሮኛል ካለም ዜጎችን እርዳታ ይጠይቅ። አንድ ቡድን ታጥቆ እንደ ፈለገ ጥቃት ሲፈጽም በትዕግስት ከታለፈ፣ ሌላውም ራሱን ለመጠበቅ ሲል፣ አሁን ከታጠቀው የጦር መሳሪያ በላይ ለመታጠቅ ይገደዳል። ይህ ደግሞ በአገሪቱ ያሉ የተለያዩ ሃይሎች በማያባራ የመሳሪያ ፉክክር ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።

ኦነግ ዳውድ ኢብሳን ከአመራርነት ማንሳቱን አስታውቋል። በግሌ ጥርጣሬ አለኝ። ኦነግ እንደ አየርላንዱ Sinn Féin የኢትዮጵያን IRA አቋቁሞ፣ በማስፈራራት የፖለቲካ ተሰሚነት ለማግኘት ሙከራ እያደረገ ይመስለኛል። እነ አቶ ዳውድ ከኦነግ መለየታቸውን ማረጋገጥ የሚቻለው ታጣቂውን ሃይል አውግዘው መግለጫ ሲያወጡና መንግስት ለሚወስደው እርምጃ ድጋፋቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው። እስካሁን ይህን ያደረጉ አይመስለኝም። በአሁኑ ሰዓት የኦነግን ሁዋላ ቀር አካሄድ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ማያያዝና ጉዳዩ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ግጭት አድርጎ ለመሳል መሞከርም፣ ኦነግ ከሚፈጽመው ወንጀል ያላነሰ ሌላ ወንጀል መሆኑ ልብ ሊባል የገባል ። የኦነግን አካሄድ የሚጠሉ ኦሮሞዎች፣ ኦነግን ከሚደግፉት በቁጥር ቢበልጡ እንጅ አያንሱም። ኦነግ በየቦታው ለሚያስነሳው ጥቃት ሃላፊነቱን የሚወሰዱት የኦነግ አመራሮችና ደጋፊዎቹ ብቻ ነው። ምስኪኖቹን የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች እርስ በርስ ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራ፣ ዛሬ ባያስጠይቅ ነገ፣ በምድር ባያስጠይቅ በሰማይ ማስጠየቁ አይቀርም።

@Fasil Yenealem

4 COMMENTS

 1. ኢሳት ላይ ከነመሳይ መኮነን ጋር ሆናችሁ፣ የዉጪ ሃገር ፊልም አቀነባብራችሁ ኦሮሞ ላይ ሶማሌን አስነስታችሁ ያስጨፈቸፋችሁ እና 1 ሚልሊዮን እንዲፈናቀል አስተዋጽዖ ያደረጋችሁት አንሶ አሁን ደግሞ አማራን ልትቀሰቅሱበት ነው?? ኢሳትን የሚያክል ሜዲያ ይዛችሁ የመንደር ወሬ ከሚታናፍሱ፣ እንደዕዉነተኛ ጋዜጠኛ ነገሮችን ከስሩ አጣርታችሁ ለህዝብ ማቅረብ ካቃታችሁ፣ ህዝብን ከህዝብ ከማጋጨት ምናለ ዝም ብትሉ?? ለኦሮሞ ያላችሁ ጥላቻ ወሰን እንደሌለው እናዉቃለን። ነገር ግን ዉጥናችሁ ኦሮሞን ብቻ የሚጎዳ ሳይሆን፣ ባፍ የምትሞቱላትን ኢትዮጵያ ሊያፈርስ እንደሚችል ተገንዘቡ!

  You have the OLF as scapegoat for every ill in that country. OLF is not that stupid to incite conflict between Oromos and other ethnics, neither is it that potent to go beyond the borders of Oromia to involve in other peoples’ affairs. Make investigative journalism or shut up!

 2. አባ ጫላ
  ከአንተ ጋር እዚህ ልስማማ ነው:: ህውሀት ቅጭትን እይፈጠረ በኦነግ እያላከከ ይህ በስሜት የሚነዳ ሁሉ ልክ የተዘጋጀለት ጉድጏድ ውስጥ እየገባ ነው:: ኦሮሞንና አማራን ማጋጨት የህውሀት ወደስልጣን መመለሻ መንገድ ነው:: ይህ ወሎና ሸዋ የሚካሄደው ለፍርድ የሚፈለጉት የህውሀት ባለስልጣኖች የሚያቀነባብሩት ድራማ ነው:: ልክ ሰኔ 16 በኦሮሞዎች አቀነባብረው ኦነግ እንዳደረገው ስራ:: ለምንሰጠው ትችት ነግሮችን ከመስረቱ መመርመር ያስፈልጋል

 3. አባጫላ

  ያንተን ሀሳብ የምጋራው ይህንንም ተመልክቼ ነው….

  የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦችን ለማጋጨት የተደገሰች ሴራ!! (አምዶም ገብረስላስ)
  April7/2019
  አጣየ ማለት በኦሮሚያ ዞን የተከበበች የሰሜን ሸዋ ዞን አንድ ከተማ ነች የኦሮሚያ ዞን ደግሞ በወሎ በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች የተከበበች ዞን ነች ስለዚህ አጣየ ላይ ኦነግ በሚል እንቅስቃሴ እየተሞከረች ያለች ጠባ ጫሪ ሴራ ሆን ተብላ ከላይ በጠቀስኳቸው ዞኖች የተከበበችውን የኦሮሚያ ዞን ኑዋሪወች በአማራወች ለማስጨፍጨፍ እና የአማራን እና የኦሮሞን ህዝብ ወዳጅነት ለማፈራረስ ይረዳ ዘንድ መቀለ ተደብቀው በወንጀል የሚፈለጉ የቀድሞ የኢህአዴ ባለስልጣናት አቀነባባሪነት እና በተጨማሪም የመሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ብጥብጡን እንዳስጀመሩት መረጃወች ደርሰውኛል።

  ስለዚህ የተከበራችሁ የአማራ እና እና የኦሮሞ ሰላም ወዳድ ህዝቦች ሆይ የምትመኟትን ኢትዮጵያን ለማግኘት ስትሉ ከዚህ በፊት መቶ አመት የማይፈታ የቤት ስራ ሰጥተናቸዋል እያሉ ሲመፃደቁ በተባበረ ክንዳችሁ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እግሬ አውጭኝ ብለው መቀለ በየሆቴሉ እንዲከራተቱ እንዳደረጋችሁት ሁሉ አሁን አጣየ አካባቢ ኦነግ በሚል ስያሜ በቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በአሁኑ ሰአት ደግሞ የህግ ተፈላጊወች በሆኑት የዘራፊወች ስብስብ የተፈጠረላችሁን የጥፋት ድግስ አንድ ሆናችሁ እንደምታከሽፉ እምነቴ ነው!!!!

  እ/ር ኢትዮጵያን አብዝቶ ይባርክ!!!!አሜን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.