ኦነግን ሳውቀው፤ (መስቀሉ አየለ)

አንድ የደርግ ዘመን ጀነራል ባንድ ወቅት ከሚያውቁት ጨልፈው ሲናገሩ ” እኔ ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ በሻምበል ማእረግ የነበርኩ መኮንን ስሆን ከኦጋዴን እስከ ኤርትራ ያለውን ግንባር ጨምሮ በአራቱም ማእዘን ነበርኩ። አሶሳንና ከወለጋ በቡሬ በኩል እስከ ጎጃም ያልዋልኩበት ቀጠና የለም። ነገር ግን ደርግ ኦነግን ከቁም ነገር ቆጥሮ አንድም ቀን ይኽ ነው የሚባል ወታደራዊ ዘመቻ ያደረገበትን አጋጣሚ አላየሁም፤ አልሰማሁም።

በእርግጥ አልፎ አልፎ በአሶሳና ወለጋ አካባቢ ‘ብቅ ብለዋል’ የሚባል ወሬ ሲሰማ በጦሩ ውስጥ ያሉትንና ሴቶች የሚበዙበትን መደበኛ የኪነት ቡድን አባላት እንልካቸውና እነሱ እየነዱ ይዘዋቸው ይመለሳሉ። ከዚያ ውጭ ደርግ ከነበረው ቁመና አንጻር ኦነግን በማይክሮስኮፕ እንኩዋን ለማየት የሚቸግረው በመሆኑ ጀሌዎቹን ትንሽ የግንዛቤ ማስጨበጥ ትምህርት መሳይ ብጤ ሰጥቶና መክሮ ከመልቀቅ ውጭ እነሱን እንደ ጦር ምርኮኛ ቆጥሮ ካምፕ ውስጥ አስሮ ያከረመበት ግዜ አልነበረም።እንደው የዘመኑ ማለቅ ካልሆነ ኦነግ ብሎ የስጋት ምንጭ ም ማለት ይሆን …?”ሲሆን ጥያቄውን በጥያቄ አንጠልጥለው ይተዋሉ….

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.