ኢትዮጵያ ውስጥ ያልታወቁ በራሪ አካላት” (UFO) ተከሰቱ 

በአጣዬ፣ ማጀቴ፣ ሰንበቴ እና ካራ ቆሬ አካባቢዎች ጥቃት የፈፀመው ኦነግ ሣይሆን ‘ያልታወቁ በራሪ አካላት’ (UFO) መሆናቸውን “ተረጋገጠ”

ይህንን ጥቃት “ሲመረምሩና ሲመራመሩ” የነበሩት የኦነግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቶሌራ አደባ “የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ምንም አይነት የታጠቀ ኃይል በአጣዬ፣ ማጀቴ፣ ሰንበቴ እና ካራ ቆሬ በተባሉ አካባቢዎች አልነበረውም፤ የለውምም …ጥቃቱን ያደረሱት አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ የፌድራልም ያልሆነ ወይንም የክልሉም [የአማራ ክልል] ያልሆነ ባንዲራ ይዘው ነው የሚሔዱት።… በአካባቢዎቹ ለተፈጸሙት ጥቃቶች ተጠያቂው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተባለው የፖለቲካ ፓርቲ ነው::” ሲሉ ገልፀዋል::

የሚገርመው በምርምር ድርሣናቸው የተከበሩ አቶ ቶሌራ አደባ UFO’s የያዙት የድርጅት አርማ የማን መሆኑን ከመግለፅ ተቆጥበው ጉዳዩን ‘ሆድ ይፍጀው’ በማለት አልፈውታል

1 COMMENT

  1. ቀንም ሆነ ሌሊት ቅዠትህ የሚታይህ አዕምሮህ ላይ ተቀርጾ የቀረው አንድ አርማና አንድ ድርጅት ብቻ ነው። ለሌላ እዉነታ ቦታ የለህም! ችግርህ ያ ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.