ኦዴፓ በውስጡ አራት ቡድኖች አሉት (ግርማ ካሳ)

ኦዴፓና ከኦነግ ጋር አንድ እንደሆነ አድርገው የሚወስዱ ወገኖች አሉ። ለምን እንደዚያ እንደሚሉ ይገባኛል። ኦነጎችና ጽንፈኛ ቄሮዎች ህዝብ ሲያሸበሩ ኦዴፓ በበቂ ሁኔታ ሕግን ማስከበር ካለመፈለግሁ ወይም ካለመቻሉ የተነሳ እንደ ኦነግ ስለፈረጁት ነው። ይሄን ብዙ ሊደንቀን አይገባም።

ሆኖም ምንም እንኳን ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ከኦነግ ጋር ውስጥ ውስጡን የሚሰሩ የኦዴፓ/ኦህዴድ አመራርና ተራ አባላት ቢኖሩም ሁሉም እንደዚያ ናቸው ማለት አይቻልም። በተለይም ዶ/ር አብይንና አቶ ለማን ኦነጎች ናቸው ማለት ከመስመር ያለፈ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ ትልቅ ስህተት ነው።

ኦዴፓ ውስጥ ሁሉም አንድ አይደሉም። በአስተሳሰብ የተከፋፈሉ ናቸው። በኔ እይታ ቢያንስ አራት ቡድኖች አሉ ብዬ አስባለሁ።

አንደኛው ቡድን – የወለጋ ሰዎች ያሉበት በዋናነት የነዳዎድ ኢብሳን ኦነግ ውስጥ ውስጡን የሚደገፍ ቡድን ነው። ይህ ቡድን በአሁኑ ወቅት በድርጅቱ ውስጥ ብዙ ተጽኖ ፈጣሪ አይደለም። በተለይም ኦዴፓ በወለጋ የዳዎድ ኢብሳን ቡድን ለመምታት ከተነሳ በኋላ አንገቱን የደፋ ቡድን ነው።

ሁለተኛውና በጣም ችግር ፈጣሪ የሆነው ቡድን በአብዛኛው የባሌና የአርሲ ሰዎችን ያቀፈው፣ ከጃዋር መሐመድ ጋር በቅርበት የሚሰራው ቡድን ነው። ይህ ቡድን በዳዎድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ጋር ትልቅ ጠብ ያለው ቡድን ሲሆን፣ ከሌሎች እስላማዊ ከሆኑ ኦነጎች ጋር ግን በጥምረትና በመናበብ የሚሰራ ነው። ይህ ቡድን በአሁኑ ወቅት በኦዴፓ ውስጥ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች የተቆጣጠረ፣ ከወለጋው ቡድን ይልቅ ለለማ ቲም ትልቅ ራስ ምታት የሆነ ቡድን ነው። ወ/ሮ ጠይባ ሁሴን የኦሮሞ ክልል መንግስት ም/መስተዳደር፣ ለየገጣፎ፣ የአሰላ፣ የሱሉልታ…ከንቲባዎች …እዚህ ቡድን ውስጥ ነው ያሉ ናቸው ተብሎ ነው የሚገመተው። ይህ ቡድን የለማ ቲም እንደሚገባው ወደፊት እንዳይሄድ ያደረገ፣ እነ አቶ ለማ በሌላው ማህበረሰብ ያገኙትን ድጋፍ እንዲያጡ ውስት ውስጡ የሚሰራ፣ ከዞኢህ በፎት የቀረጹ ቪዲዮዎች የሚለቅ ቡድን ነው።

ሶስተኛው ቡድን የለዉጥ ሃይል የሚባለው ቡድን ነው። በዋናነት ከጂማና ከሸዋ የመጡ አመራሮች በብዛት ያሉበት ቡድን ነው። የለማ ቲም አባላት የዚህ ቡድን አካላት ናቸው። እነ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ አቶ ለማ መገርሳ፣ አቶ ታከለ ኡማ የመሳሰሉ ያሉበት።

አራተኛ – ከሁሉም ኦሮሞ ክልል በሕወሃት ጊዜ ያገኙ የነበሩት ጥቅም ይቀርብናል ብለው የሚሰጉ፣ የሕወሃት ደጋፊዎች ያሉበት ቡድን ነው። ይህ ቡድን ታክቲካሊ ከነጃዋር ጋር ከሚሰራው የኦዴፓ ቡድን ጋር የተቀራረበ ነው። የለማ ቲምን ማዳከም።

እንግዲህ ኦዴፓ ውስጥ ያሉትን በጅምላ ኦነግ ከማለት፣ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ የለዉጥ ሃይሎችን ማጠናከር በጣም አስፍላጊ ነው ባይ ነን። ማጠናከር ስል ጭፍን ድጋፍ ማለቴ አይደለም። ጥሩ ሲሰሩ ደግፎ፣ ሲሳሳቱ ገንቢ የሆነ ጠንካራ ትችት ማቅረብ ማለቴ ነው። ገንቢ እስከሆነ ድረስ ተቃወሞና ትችት በራሱ የማጠንከር አቅም አለው።

በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ሃይሉ (የለማ ቲም) በኦዴፓ ውስጥ አብላጫ ድምጽ የለዉም። ለዚህም ነው አንዳንድ ውሳኔዎች ለመወሰን የሚቸግራቸው።
ሻለቃ ዳዊት ወድልደጊዮርጊስ ቢቢሳ ላይ ፣ “ለውጥም የለም። ለውጥ ማለት የስርአት ለውጥ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም የጠየቀው የስርአት ለውጥ ነው። እዚህ ችግር ውስጥም የከተተን የነበረው ስርአት ነው። አብዛኛዎቹ ነገሮች እንዳሉ ናቸው” ሲሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረታዊ ለዉጥ የለም ሲሉ ነው የተከራከሩት።

ሆኖም ሻለቃ ዳዊት ዶ/ር አብይ አህመድ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት በግለሰብ ደረጃ ያስመዘገቡት ትላልቅ ውጤት እንዳሉ ግን ሳይገልጹ አላለፉም። “ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀየሩ የሚባሉት ነገሮች በስርአት አቅጣጫ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በግል በወሰዷቸው እርምጃዎች ነው። ነገር ግን ይሄ ለለውጡ ሁኔታውን ለማመቻቸት ነው እንጂ በራሱ እንደ ለውጥ ልንመለከተው የምንችለው ነገር አይደለም” ነበር ያሉት።

እነ ዶ/ር አብይ ምንድን ነው መሰረታዊ ለውጥ እንዳያመጡ ያገዳቸው ብለን ብይጠይቅ መልሱ በኦዴፓ ውስጥ ድርጅታዊ አቅም ማጣት ነው የሚል ምላሽ ነው የሚሰጠው።
“በዚህ ሁኔታማ መቀጠል አንችልም። ይህ ድርጅታዊ አቅም እንዴት ሊመጣ ይችላል ? “ የሚለው ጥያቄ በቀጣይነት ሊነሳ የሚችል ጥያቄ ነው። ለለማ ቲም በኦዴፖ ውስጥ ድርጅታዊ አቅም የማግነት እድላቸው በጣም የመነመነ ነው። እነ ዶ/ር አብይ ሊኖራቸው የሚችለው አማራጭ ሁለት ነው። አንደኛውማ የሚሻለው ከሌሎች የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ኦዴፓን ማፍረስ ነው። ያኔ የኦዴፖ ጸንፈኛና ለውጥ-ጠይ አባላት በዉህድ ፓርቲ ውስጥ አብላጫ ድምጽ አይኖራቸውም። እንደውም ከድርጅቱ ወጥተው ኦነጎች ሊቀላቀሉም ይችላሉ።

የኢሕ አዴግ አባል ድርጅቶ ውህደት እንደሚመሰርቱ እነ ዶ/ር አብይ በስፋት ቢናገሩም ገና የተረጋገጠ ነገር የለም። በኦዴፓ ያሉ ለውጥን የማይፈልጉ ቡድኖች “ኦዴፓ ዉህደቱን አይቀላቀልም” ብለው በመወሰን በድምጽ እነ ዶ/ር አብይን ሊረቱ ይችላሉ። እንደዚያ ከሆነ በኦዴፓ ያለው የለዉጥ ሃይል፣ የለማ ቲም፣ ራሱን ከኦዴፓ ነጥሎ ፣ የለዉጥ ሃይሎችን ይዞ ከሌሎች የኢሕአዴግ ድርጅቶች ጋር መቀጠል ይችላል። ያኔ ኦዴፓ ቢኖርም ፣ እነ ዶ/ር አብይ የሌሉበት ኦዴፓ ያው ጥርስ የሌለው ጅብ ሆኖ ይቀራል።

3 COMMENTS

  1. “እንግዲህ ኦዴፓ ውስጥ ያሉትን በጅምላ ኦነግ ከማለት፣ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ የለዉጥ ሃይሎችን ማጠናከር በጣም አስፍላጊ ነው ባይ ነን። ማጠናከር ስል ጭፍን ድጋፍ ማለቴ አይደለም። ጥሩ ሲሰሩ ደግፎ፣ ሲሳሳቱ ገንቢ የሆነ ጠንካራ ትችት ማቅረብ ማለቴ ነው። ገንቢ እስከሆነ ድረስ ተቃወሞና ትችት በራሱ የማጠንከር አቅም አለው።”

    ግርማ ካሳ ለውድ ሀገር ቅን ማሰብ እንደዚህ ያለ አመለካከት ነው:: በጎ የሚሰሩትን ማበረታታት ከሁሉም ወገን የሚጠበቅ መልካም ስራ ነው::

  2. አሁን ከልብህ አውቀህም ይሁን ተሳስተህ የኢትዮጵያን ግማሽ የሚሆነውን የማህበረሰብ ክፍል ጠል መሆንህን ነግረከን አረፍከው። ድንቄም የለውጥ ሃይል ደጋፊ እንዳንተ የለም።

  3. Girma is kebitse tesfa. Look what Abiy is doing. He filled all important positions with Oromos, from defence to finance and here comes Girma Kassa to lecture about change agent. There is a change agent to create Oromia. Who cares about that project. Wake up from your sleep and organize those that worry about Ethiopia. OPDO and OLF final goal is to massacre in Addis Abeba like the one they did in Kesmissie. That is why Eskinder et al. are worried and tried to organise themselves. Let us join them and stop blah blah. Understand that both Lemma and Abiy are imposters. You do not have to go anywhere to confirm this. Just count the number of people displaced.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.