ሱዳንን ለ30 ዓመት ያህል የመሯት ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣናቸው ወረዱ

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን መውረዳቸው ተገለፀ፡፡

የፕሬዝዳንት አልበሽር ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የተገደዱት በአገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል በሚል ካለፈው ታህሳስ ጀምሮ ከተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ በቁልፍ ተቋማት፤በድልድዮች በአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢዎች የአገሪቱ መከላከያ ኃይል ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

የፕሬዝዳንት አልበሽር ከስልጣን መውረድ እርግጥ መሆንና የሽግግር ምክር ቤት ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እየተደረገ እንደሆነ ሮይተርስና አል አረቢያ ቲቪ ዘግበዋል፡፡

ሱዳናዊያኑ ላለፉት 5 ወራት ሲያካሂዱት የነበረውን ተቃውሞ ላለፉት አምስት ቀናት አደባባይ ላይ በማደር ጭምር ማጠናከራቸው ፕሬዝዳንት አልበሽርን ከስልጣናቸው እንዲወርዱ አስገድደዋቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት አልበሽር የተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ ቃል ቢገቡም፣ ህዝቡ ስር ነቀል ለውጥ ነው የምንፈልገው በሚል ተቃውሞውን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

አልበሽር በመፈቅለ መንግስት እ.አ.አ ከ1989 ወደ ስልጣን ከመጡበት ጀምሮ ሱዳንን ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎች በአገሪቱ መከለላከያ ኃይል አካባቢ ይሰጣል የተባለውን መግለጫ እየተጠባበቁ ነው፡፡

ምንጭ-ሮይተርስና አል አረቢያ ቲቪ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.