አቢይን አስመልክቶ «ጉድ ጉድ » ለምትሉ ሁሉ ጉዳችሁን ስሙት (ከአባዊርቱ)

ሰርፀ ለምትባለው ካንተ ልጀምር እስቲ፤፤ ይሄን «ጉድህን» አየሁት፤፤ ያንተም ጥርጣሬ በዛ፤፤ የንግድ ባንኩን ሆነ መሰል ተቁዋማት ተጠሪነታቸው ለ PEHAA ነው፤፤ አቢይ በቀጥታ አይሾሙም እንደገባኝ፤፤ ያ ከሆነ ደሞ ሹዋሚው በየነ ገ/መስቀል ሊሆን ነው፤፤ የአቢይን ስብእና ብሎም ኢንቴሌክት ያየ (ለኔ ይታየኛል) አቢይ አህመድ አንዲህ ወርዶ በጎጥ ይቀጥራል ልትለኝ ነው ሃላፊነቱ እንኩዋ ቢሆን? የቅዋሜም ወግ እያጣ መጣ እኮ፤፤ ይልቅ  መፍትሄ የምትላቸውን አንድ ሁለት እያልክ አቅርብ፤፤ ለአገር ብዙ ትጠቅማለህ እንደዛ ሲሆን፤፤
 “Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) has appointed Beyene G. Mesqel, an experienced hand in the sector, as a director general of the newly restructured Public Enterprises Holding & Administration Agency (PEHAA)”
And it is this body that appoints head of CBE – not Abiy Ahmed.  ስህተት ከሆነ እታረማለሁ፤፤ ስለንግድ ባንኩ አሰራር ባላውቅም ዋናው የባንኩ ተሹዋሚ ይሆናል የበታቾቹን ደሞ የሚሾመው፤፤ ምናልባት ይህ ሃላፊ ደሞ የበታቾቹን ለብቃታቸው በደንብ የሚያውቅ ከሆነና በዚሁ ብቃታቸው ወይም እንዳልከው በወንዝ ልጅነት ከሆነ እንደምን አቢይ የእያንዳንዱዋን የመንግስት መዋቅር ሹመኛ ሊያውቅ ነው? ትችታችን ቅንነት እንዳይጎድለው ከሚል ነው፤፤ አንድ ነገር ግን የምለው፤ በብሄር ፖለቲካ እስካልተወገደ ድረስ የወንዝ ልጆች ሹመት አይቀርም፤፤ ለዛ ደሞ አቢይ ሳይሆን ይህን ያመጣብን በር ዘግተው እየተጎነጩ በስደታቸውም ከወደ መቀለ የሚሳለቁብን ጨለምተኞቹ ናቸው፤፤ የነሱ መዘዝ ገና በየቀበሌና ማድቤታችን ገብቶ ሌላ 27 አመት ሳያባላን አይቀርም፤፤ ቀላል ፈንጂ ነው እንዴ ቀብረውልን የሄዱት? ያሳዝናል፤፤ በመጨረሻም ስለ ዖሮምያ ባንክ ያልከው ለምን ገረመህ? በንዲህ አይነት ጉዞ መስሎኝ አንድ ትውልድ ያህል የፈጠርነው፤፤ ካለ ዖሮሞ ልጆች በቀር ብለው ወግድ ቢሉህ ለምን ይደንቃል? በዚህ የየጎሳ ጨለማ ጉዞ አልነበር እንዴ ስንደናበር የኖርነው? ወይስ የዖሮሞው ከትግሬው ተለይቶ ነው ጉድ ያስባለህ? ለዚህ መልስ የሚሰጡህ የመቀለው ስደተኞች እንጂ አቢይ ሊሆን አይችልም፤፤ ትግሉና ትልሙም  ይህ እንዲቀር መስሎኝ፤፤ ከነግሳንግሳችን በምርጫ ሊያሻግረን ይመስለኛል በኔ ግምት፤፤ አሳዛኝ ሰውዬ፤፤ በቀረበትና እዛው እነዛ ለጋ ቤተሰቡን ይዞ ዴንቨር  በስደት በቀረ ነበር፤፤ ህዝባችን ውለታ የማያውቅ ነው፤፤  27 አመታት የጎደፈውን በ 1 አመት አፅድተን ለዚያውም በዴሞክራሲ ልንሻገር እኮ ነው፤፤ እንደምን እንደሚቻለን ፈጣሪ ይወቅልን፤ እንጂ፤፤
አቻምየለህ ታምሩ!
ለዝባዝንኬህ ማሳመኛ የሰጠህው አርስት «ለአቢይ አህመድ የገበሩ ክልሎች» እራሱን በደንብ መላልሰህ አንብብና አቢይን ሳይሆን መላውን ህዝባችንን እንደዘለፍክ ካልተሰማህ የሆነ ችግር አለብህ ወንድም፤፤ ደፋር!!! አቢይ አህመድ ዋናው «የገበረው» መዲናው ሸገር ላይ መስሎኝ ፅልመቶች አቢይን ገላግለውት የነበረውንስ ምን ልትለን ይሆን? አይ ህሊናን መሸጥ፤፤ ኦነግን በራሱ ህይወት ላይና እነዛ ምስኪኖች ላይ አዘመተ በለንና ታሪካችንን እንወቀው፤፤
ለለማ ቶሮንቶው በአቢይ ሩዋንዳ ጉዞ ጊዜህንና ጊዜአችንን በከንቱ እንድናጠፋ ለምትጋብዘን ሰውዬ፤
አጃኢባ ነው መቼስ፤፤ ታድያ የሩዋንዳውን እልቂት በሰእላዊ ድርሰት እያዋዙ ፤ እያንዳንዱ ዜጋ እንዴት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዳለቀ ይንገሩን ? የ27 አመታት የዘር ፖለቲካማ ጠንቅ መሆኑንማ ከመደስኮር አልፈው በህልማችን ሁሉ አስከፊነቱን እስክናስበው አላረጉም እኒህ ሰውዬ በዚች አመት ቆይታ? ወይስ ምን ማለቱዎ ነው? አትሊስት ቆሻሻን ማስወገዱን ከኪጋሊ ያዩትን ቢነግሩን የዘረኝነት ቆሻሻነቱን አይምሮችን ይረዳና ያንን ቆሻሻም ለማስወገድ እንተባበራቸው ይሆናል ብለው አስበውስ እንደሆነ? ለማ ቶሮንቶ አስተውለዋል ይህን? እንደ አቢይ የሚያስቡ መቶ ሰዎች ቢኖሩን መከራችን እንዴት በተቃለለ ነበር እላለሁ ለብቻዬ፤፤ ይህ የቆሸሸውን የዘር ህገመንግስት በሰላም አሻግሬ በሚቀጥለው አመት ለሚለውጡት  እሰጣለሁ፤ ለዚህም ምስክሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ብለው አላሉም አቢይ? በዘር ፖለቲካ ህዝቡ ለ 27 አመታት የእለት ጉርሱ አርጎ በኖረበት አገር ፤ ሰውዬው ምን ሊያረጉ እንደተፈለገ በየሚዲያው የምትቸከችኩ ሰዎች ቆምም እያላችሁ እራሳችሁን ጠይቁ እንጂ? አሁን ይህ ፍርደገምድል አስተያየት ማንን ነው የሚጠቅመው? አይምሮው በዘር ፖለቲካ 27 አመታት የተምታታበትን ህዝብ  ወይስ በዛኑ አመታት በጫት ገራባና በፕላስቲክ ጠርሙሶችና ጠማማ ፎቆች የተዋጠችውን ሸገር? እንዴት ነው አካሄዳችን? አይምሮትን ይፈትሹ በደንብ አርገው፤፤
በመጨረሻም
 
ይድረስ ለአቶ ንጉስ ጥላሁን ጠ/ሚር ቢሮ
አቶ ንጉሱ የመንግስት ቃል አቀባይ ዋንኛው ስራ መሆን ያለበት እንፅልመቶች ተክለውልን ያለፉትን ፈንጂ እየተከታተሉ ማምከን ብቻ ሳይሆን ፈንጂው ሌላ ፈንጂ እንዳይዋለድ መሰረት ያለው በዲሲፕሊን የታጀበ አምካኝን ማጎልበት ይመስለኛል፤፤ ጊዜዎን በሀተታ አላባክንምና እስቲ መፍትሄ ያልኩትን ልዘርዝርልዎ፤፤ እለታዊ መረጃ ብዙ ጥቅም አለው ብዬ አስባለሁና፤፤
1) በየቀኑ የ ጠ/ሚር ብሪፊንግ መምራት እና እለታዊ መረጃዎችን ቅደምተከተል ማቅረብ፤፤ አጭር ጋዜጣዊ ቃለመጠይቆች መቀበልና ማስተናገድ፤፤ አሁን እንደምታደርጉት በየመንፈቁ ሳይሆን በየእለቱ፤ ይሁን፤፤ አደለም የለት ምግባችን እንዲህ ወሬና አለባልታ የሆነው ይቅርና  የታላቁዋም አሜሪካ እለታዊ ዋይት ሃውስ ብሪፊንግ ነበራት ያሁኑ ሰውዬ መጥተው አፋለሱት እንጂ፤፤  አቢይ ምን ላይ ተጠምደው እንደሚውሉ ህዝቡ ይረዳ፤፤ ሲያደቡ  የሚውሉ የሚመስላቸው ግብዞች እንዳሉም  አንርሳ፤፤ ይህ ከሆነ እራሳቸውን እንደ CNN የሚቆጥሩ ፊደሉን የማያውቁ ግን ፌስቡክን ሲያገላብጡ የሚውሉትና አየርባየር ጦር የሚሰብቁት ዲጂታል ወታደሮች ወገን ላይ ሳያርፉ  አየርባየር ይመክናሉ፤
2)  የርስዎ አይነቱ ብቃት ያለው ሰው እየቀደመ ይህን ቅን መሪ የሚሰራውንና የሚያልመውን ህዝቡ ዘንድ የሚያደርስለት በሰፊው አልተሰራበትም ብዬ አስባለሁ፤፤ ለዚህም ማስረጃው ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ፓርቲ ወይም ህጋዊ አካል ያለው እንጂ  እኔም 10 ጉዋደኞቼን ይዤ ልስጥ ብል ማን ያቆመኛል? ይህም ከ ኢንፎርሜሺን ክፍተትና የዜጎችን መብትና ግዴታ ህዝቡ ዘንድ ሰርፆ አለመግባቱንም አመላካች ነው በከፊል፤፤ የተማረውም ይህንኑ ማስታወስን ይፈልጋል፤፤ መንግስትና ዜጋም መብትና ግዴታ ተወራራሽ መሆናቸውን ይገነዘባል፤፤
2) ኦሮሞንና አማራን ከርስዎ በላይ በደንብ የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም እንደተረዳሁት አስተዳደጎን፤ ጋዜጣዊ መግለጫውን በሁለቱም  አፍ ቢወጡት ስንቱን የከረረ ፅንፍ ያረግቡ ነበር፤፤ ህዝባችን በተለይ የኔው ወገን ብዙ ብሶት አለበት፤፤ 27 አመታት ደብዛዋ የጠፋው ኢትዮጵያዊነት በተለይ በቄሮዎች አይምሮ ውስጥ መልሶ ማጎልመት እንደገና ተወልዶ መጎልመስን ይጠይቃል፤፤ እጅግ አደንቃለሁ የኦሮሞ ህዝብን ቻይነት እንጂ እንደተደረገበት ደባ መዘዙ ብዙ ነበር፤፤ በሰከነ መንገድ በቁዋንቁዋው ክብርና ማእረግ ተስቶት ሲስተናገድ ብዙ ችግር ይቀረፋል ብዬ አስባለሁ ፤፤ እርስዎ ለዚህ ታድለዋል፤፤ አንድ ያልተጠቀሙበትን አጋጣሚ ላስታውስዎ፤፤ ሚሌንየም አዳራሽ ጁዋር ለ ኦቦ ለማ ላፕቶፕ የሸለመ ጊዜ ነበር፤፤ አማራውን ወክለው ሸጋ ንግግር በአማሪኛ ያደረጉ ጊዜ እንደምን በኦሮሚፋው በደንብ ዘልቀው ደህና አርገው በኩራት በኦሮሚፋው አልደገሙትም ነበር? ቀላል መልክት አልነበረውም፤፤ ዛሬማ ዋናው ቦታ ላይ መጥተዋልና ይህን ፀጋ በደንብ ይጠቀሙበት፤፤ ኦሮሚፋን ማወቅ ክብርም ነው እንደህዝባችን ቁመትና ወርድ፤፤ ሌላው ምንም እንኩዋ እርስዎን ባይመለከት ኦቦ ለማ ጋ ሆነው በፍቅር በየጥሻው ያሉትን የኦነግ ልጆች አሰባስቡ፤፤ መቼስ እውነት እንነጋገር ከተባለ ከ ኦዲፒ የካድሬ «ሊቃውንት» ካብዛኛዎቹ በአማካሪነትም ቢሆን ምርጥ የኦነግ ልጆች አይጠፉም፤፤ ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች ነን አለመታደል ሆነና እንጂ፤፤ እንደውም ከኦቦ ለማ እርስዎና ሌላ ኦሮሚፋን በደንብ የሚያቀላጥፍ አማራ ፈልገው አንዲት ዊኬንድ ላይ መሮን እራሱን ከለማ ያስታርቁ ፤፤ የእናንተ ደሞ ሶስተኛ ወገን ስለሆናችሁ ይሰማሉ፤፤ ሰው መደመጥና መከበር ብቻ  በቂው ነው፤፤ አባገዳዎች ብቻ አይበቁም ባይ ነኝ፤፤
3) ችግር ሲኖር በግምባር መጋፈጥና እዛው መድረክ ላይ ብትንትኑን  ማውጣት፤፤ በይደር ምንም አይደር ከንግዲህ
4) ሚዲያዎች የመንግስትም ይሁኑ የግል ከመንገድ ሲወጡ እዛው እለታዊው ፕሬስ ላይ ማጋለጥና ትክክለኛውን ማስገንዘብ፤፤ ከተሳሳታችሁም እዛው መድረክ መማማር፤፤ ከመደማመጥ ብዙ ትምህርት ይገኛልና፤፤
5) በየ ሶሻል ሚዲያው በተዋቡ የየብሄራት ስም ተደብቀው ህዝብን ከህዝብ የሚያባሉትን፤፤ ህዝብን እያባሉ ዴሞክራሲ ብሎ የለምና የሆነ እልባት ይሻዋል፤፤ ይህ መድረክም የጊዜ ጉዳይ እንጂ አየሩን በበጎ ይለውጠዋል በሂደት፤፤
ለዛሬው የታየኝን እንዲህ ብያለሁ፤፤
በመጨረሻ  አንድ አቢይ ብቻቸውን ምንም አይፈይዱም፤፤  በእጅ የያዙት ነገር ሆነና «ሊቃውንትና» ተቺው አየለና አላወቅንበትም ብዬ እስባለሁ፤፤ እርስዎ በቅርብ ያሉት እኒህ ሰውዬ የተሸከሙትን መከራ ይገነዘባሉ ፤፤ ከባድ ሃላፊነት ነውና  ሁላችሁንም ፈጣሪ ይርዳችሁ፤፤
መልካም የሁለተኛው አመት ጅማሮም ይሁንላችሁ!!
ለመላው ምሁራን!
ዬት ነው ያላችሁት? ድምፃችሁ ሳይሆን የ ሳይበር ዲጂታል ድሮኖች ብቻ ነው የሚሰማው፤፤ በቀደም ብቻ 42 የምትሆኑት ለአንድ አክቲቪስት (ሁላችንም የምናከብረው ቢሆንም በኔ እምነት ከባድ ስህተት የሰራ) እንደዛ ማመልከቻ የፃፋችሁ ዛሬ ፅልመት በሆድ አደሮች እንደዚህ ሲፈነጩብን እንዴት አስቻላችሁ? ኢትዮጵያ ከሞተች በሁዋላ ለቅሶ ልትደርሱ እንዳይሆን፤፤ ማን ይሙት በተለያየ ስም የሚያባሉን እውነት ኦሮሞና አማራ ሆነው ነው? ምንም የፅልመት ሴራ አሸታችሁም? ዝም የሚባልበት ጊዜ ነው? እሺ ዝምስ በሉ፤ እነዚህን የለውጥ ሃዋርያት መልካም ስራቸውን ባይደገፉ እንኩዋ ስማቸውን በተዘዋዋሪ ፅልመቶቹ ሲያጠቁሩ ምነው ሌላ ማመልከቻ ለሞራላቸው እንኩዋ አይታይም? ፍርዱን ለናንተው እተወዋለሁ፤፤
ማሳረግያ ለሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ!
ሻለቃ ዳዊት ወደ አገር ብቅ ብለው ያማክሩልን ያልኩበትን ቀን ነው የረገምኩት፤፡ ከርስዎ ይህን አልጠበኩም ነበር፤፤ አንዱም አማራጭ ሃሳብዎ ለአገር ሰላም ይበጃል ብለው ካሰቡ አዝናለሁ፤፤ የአቢይ አህመድ አስተዳደር ፌይልድ ስቴት አስብሎ እንዲህ ያበቃዎ በ 33 አመታት ላገርዎ በቅተው እዛው አ አ ሸንጎ ተቀምጠው ወቅሰውና ደስኩረው የተመለሱበትን አገር አደል እንዲህ ፌልድ ስቴት ያስባሎት? እንዲህ ነው ምክርና ካውንስሊንግ፤፤የአቢይ አስተዳደር ብዙ ስህተቶች አሉት፤፤ ተሻግረን እስክንጨርስም ብዙ ችግር ይጠብቀናል፤፤ እርስዎ እንደገመቱት ግን እንዲህ አስከፊ ደረጃ አልደረስንም፤፤ የዛሬን አመት ላየና ያለፉትም 12 ወራት ለቃኘ የአቢይ መንግስት አበቃለት ለማለት አያስደፍርም፤፤ የአቢይ አስተዳደር ምናልባት በርስዎ ጊዜ ያልነበረ ዘመናዊ መረጃዎችን ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ፤፤ በዛ ላይ ሆን ብለው ዴሞክራሲን ለማጎልበት ተብሎ እንጂ አሁን ማን ይሙት የየክልሉን ጦሽ ጦሽ በአንድና ሁለት ሶርቲ መገላገሉን እንደው ይቸግር ብለው? አይመስለኝም ምንም እንደርስዎ በወታደራዊ ሳይንሱ ባይገባኝም፤፤ ሆኖም  ለመናገር የማልፈልገው ተፀናውቶት ይሆን ብዬ አስብሎኛል፤፤ አዝናለሁ፤፤ ለብዙ ጊዜ እርስዎንና ኮለኔል ጎሹ እንድትመለሱና እንድትረዱ ስማፀን ነበር፤፤ የጎሹን ባላውቅም በርስዎ ግን አፍሬአለሁ፤፤
ሰላም ይሁኑ ባሉበት፤፤
ሰላም ለአገራችንና ህዝባችን ይሁንልን፤፤
አሜን!!!

2 COMMENTS

  1. Aba Wirtu
    You are a great a** kisser. I hope Abiy and all other groups you support gets you a cushy job for your deliberate blindness. Honestly you deserve it Most people can see you are as bad as all racist Oromos. You support comes from your race rather than reason. I am saddened because you are a lost cause.
    Enqoqo

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.