ራያ ላይ እየሆነ ያለው ግድ የሚለው ማነው?

እምባ ጠባቂ (ከዓመት በፊት እንባ ነጣቂ) እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚባሉት በሕዝብ በጀት የሚተዳደሩ ተቋማት ዛሬም ጆሯቸው ላይ ተኝተዋል? ራያ ላይ እየሆነ ያለው ግድ የሚለው ማነው? ይህን የዜጎች ብሶት ምን ይስማ? ከወደ ራያ የሆነውን ደጀኔ አሰፋ ይፋ አድርጓል።ያንብቡት ሼር ያድርጉ

እውነት ግን እኛ ኢትዮጲያዊነን?

ይህ ኢትዮጲያ ምድር ነው ስደተኛ የለም የሞተ የለም እያሉ የሚቀባጥሩት የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል ከራያ አላማጣ ፓሊስ ጋር በመተባበር ቆቦ ሂደህ ነበር በሚል ሰበብ ብቻ ያለምንም ቃል ጥያቄ እንደዚህ በግፍ ቀጥቅጠው ወንድማችን አበበ ታደሰን ልከውታል። አማርኛ መናገር ሃጢያት ነው እንዴ? ማንነትን መጠየቅ ያስጨፈጭፋል እንዴ? እንዴት ሰው ከተወለደበት ቀየ በመንግስት ታጣቂወች ይፈናቀላል? የእኛን እኮ ለየት የሚደርገው ህዝብ ወይም ቡድን አይደለም ግፍ የሚሰራብን የመንግስት አካል ነኝ የሚለው ሽፍታ የህውሃት ቡድን እንጅ።

የኢትዮጲያ መንግስት እንኳን የለም የኢትዮጲያ ህዝብ ፍረዱን!!!!
ፍትህ ለራያ ህዝብ!!!!

Via አማረ ደሳለኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.