የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዝርፊያ በላይ ለአገር ደህንነትም ሥጋት ሊሆን ይችላል (ሰርፀ ደስታ)

  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአሸባሪው ኦነግና ሌሎች ጸረ-ኢትዮጵያውያን የገንዘብ መተላለፊያ የመሆን አደጋ አለው፡፡
  • ያም ባይሆን ባንኩን የሚመሩት የባንኩን ጥቅም በፊት ለሚሰሩባቸው ባንኮች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ሌላው ስጋት ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በፊት ይሰሩባቸው የነበሩት ባንኮች ውስጥ በቅጥር ብቻ ሳይሆን የሼር ባለድርሻም እንደሚሆኑ ይታሰባል፡፡
  • በኢትዮጵያ ውስጥ ለወያኔ ቀኝ እጅ የነበረውና አሁን አገርን ለአደጋ የዳረገው በዋናነት የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ ነው፡፡ በጥላቻ ትርክት ሕዝቡን ከማንነቱ አውጥተው የሴራ መፈጸሚያ አድርገውታል፡፡ በሌሎችም ዘንድ ጥላቻ እንዲስፋፋ ምክነያት ሆኗል፡፡
  • የጌደዎን ሕዝብ ጨምሮ በደቡብ ብዙ ሕዝብ አደጋ ላይ ነው፡፡
  • የበኩሌን ድርሻ ለማበርከት ከሰዎች ጋር እየተነጋገርኩ ነበር፡፡ በተለይ የኢትዮጵያን ሕዝቦች የማቀራረብ ሥራ፡፡ እኔ የሚዲያ አጋጣሚው ቢኖረኝ ብዙ ንድፈ ሀሳቦች አሉኝ፡፡ ግን ለዚህ እንኳን መድረክ የለም፡፡

ኢትዮጵያን አሁን ለደረሰችበት ያበቃት ከጅምሮ በጥላቻና ዘረኝነት ሴራ አገርንና ሕዝብን ለማፍረስ በተነሱ ሰዎች ነው፡፡ የወያኔ ቡድን ሕዝብንና አገርን በማጥፋት ቡድኑ (ግለሰቦቹ) እንዴት ትልቅ ቦታ መድረስ እንደሚችሌ እያሴሩ ነው ዛሬ የደረሱት፡፡ ሕሊና፣ ስብዕና፣ እምነት፣ ምንም ዓይነት ለሰበዓዊ ባሕሪ የሚስማማ አቋም አልነበራቸውም፡፡ በሚሊየን የሚቆጠር የትግራይን ሕዝብ በረሀብ በማስፈጀት ዓለም ዓቀፍ እርዳታ ለማግኘት ተጠቅመውበታል፡፡ የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሐውዜንን በቦንብ እንድትደበደብ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ተርፎ ኧረ ተው ያላቸውንና ኢትዮጵያዊነት አመለካከት አለው የሚሉትን በባዶ ስድስት የሴራ ፐሮጄክት ጨርሰውታል፡፡ በመጨረሻ ለእነሱ አኩይ አመለካከት የተገዛ የአእምሮ ባሪያን ትውልድ ፈጥረው ወደ መሐል ተቀላቀሉ፡፡ አማራ ከጅምሩ ማጥፋት አለብን ብለው የተነሱበት አላማ ስለነበር በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚችሉትን ሁሉ በአማራው ላይ አድርገዋል፡፡ የአማራን በሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንዲጠላ ለማድረግ ሁሉንም አድርገዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በልዩ ሁኔታ የተጠቀሙበት ኦነግን ነው፡፡

ኦነግና በአጥቃላይ የኦሮሞ ፖለቲካ ቢባል ይሻላል ዓላማው ራሱ አንዳችም ከነጻነት ጋር የተገናኘ አልነበረም፡፡ ዋና ዓላማው ሌሎችን መጥላት ነው፡፡ 50 ዓመት ያልተሳካለት ምክነያቱም የነጻነት ዓላማ ሳይሆን የነበረው ሌሎችን ከማጥፋት ጋር ነበር፡፡ የዛሬዎ የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉ እስኪመስል ድረስ የምናየው የመረረ ጥላቻና ዘረኝነትን ከሌላው ሕዝብ በተለየ ለኦሮሞ ሕዝብ ሲሰብክ ኖሯል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት አውጥቶ በጥላቻ አሳብዶ ኦሮሚያ በሚባል የሥደት ምድር እንዲኖር አድርጎታል፡፡ ኦነግና የኦሮሞ ፖለቲካ ለወያኔ ቀኝ እጅ ነበር፡፡ 27 ዓመት ወያኔ እድል ያገኘው በኦሮሞ ፖለቲካ ነው፡፡ ይሄ የኦነጎች ስብከት ብዙው የሚባል የኦሮሞ ሕዝብ በተለይ ደግሞ የተማራው ይበልጠው በሚባል ሁኔታ ያመነበት በመሆኑ ኦሮሞን ዛሬ ትክክሉ የቱ ነው ተብሎ በአመክንዮ ለመደራደር አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ በ27 ዓመት ከአማራውም ባልተናነሰ ኦሮሞ መከራ ከተቀበሉት ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ሆኖ ጥላቻው አሁንም ከአማራ ጋር ነው፡፡ ግልጥ ማለት ስላለበት ነው እንዲህ የምናገረው፡፡ ልብ በሉ በኃይለስላሴ ዘመን ኖረው ዛሬ በሕይወት ያሉ ጥላቻ የለባቸውም፡፡ ጥላቻው ያለው በጥላቻ ትርክት ተመረዞ የሚሰቃየው ያኔ አማራ ገዛ በሚለው ዘመን ያልኖረው ነው፡፡ ሲጀምር የኦነግና ወያኔ አላማ ሕዝብን ከመሠረታዊ ማንነቱ በማውጣት የራሳቸው የአስተሳሰብ ባሪያ ለማድረግ ነው፡፡ የኦሮሞ ክብር የሆነውን ታሪክ በጥላቻ አጥቁረው የእነሱን ወሮበላ አስተሳሰብ ጫኑበት፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ታላላቅ ገድል የፈጸሙና ዛሬ ይሄ አውሬ ትውልድ ሊያፈርሳት የሚተራመስባትን አገር አገር አድርገው የሠሩለትን ሁሉ ጥላቻ በአበላሸውና በነወረ አእምሮው ረገመ፡፡ በኦሮሞ ፖለቲካ ታዋቂ ለመሆን ጥላቻ ልዩ መሥፈርት ነው፡፡ ጥላቻ የምትናገር ከሆኑ ትወደዳለህ፡፡ ማንም ሁን ዋናው ጥሩ የጥላቻ ችሎታ ይኑርህ፡፡ ይሄ ነበር ለእንደነ ተስፋዬ ገብረአብና ጂጂ ኪያ የመሳሰሉ ሳይቀሩ በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ተጽኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያደረጋቸው፡፡ የእነ ጀዋር ስኬትም ይሄው ነው፡፡ ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ለማውረድ  ይቸግራል ይባላል፡፡ ይሄው ነው የሆነው፡፡ ኦሮሞ ያልተጋጨው ሕዝብ የለም፡፡ አሁን ላይ ዛሬ ትልቁ የአገር ችግር የሆነው የኦሮሞ ፖለቲካ ነው፡፡ እርግጥ ለእኔ ከበፊቱም የኦሮሞ ፖለቲካ እንጂ ወያኔ እድል ሊኖራት እንደማይችል አውቅ ነበር፡፡

የተማረው የኦሮሞ ማህበረሰብ በአብዛኛው በጥላቻ ስለሰከረ ጠፍቷል፡፡ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ያለው ጥላቻ እጅግ የከፋ ነው፡፡ ሁሉንም ሕዝብ ይጠላል በተለይ ግን እሱ ሐበሻ የሚለውን ሕዝብ አምርሮ ይጠላል፡፡ እሱ ሐበሻ ከሚላቸው ሕዝብ ጋር ትስስር ያለውን የኦሮሞ ማህበረሰብም እንዲሁ ይጠላል፡፡ ዛሬ በሸዋ ኦሮሞ ላይ ያለው ጥላቻ የዚሁ መሠረት ነው፡፡ አሳዛኙ የተማረው ኦሮሞ የገዛ ቤተሰቡን ሁሉ ነው የሚጠላው፡፡ ዛሬ ከሸዋ ተወልደው በኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ልክፍት ተለክፈው ለገዛ ወገናቸው ጠላት የሆኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሸዋን ለሚፈልጉት ይጠቀሙበታል፡፡ ዛሬ ለውጥ ለተባለውና እነ እንትና የሚፈነጩበት የመጣው የወለጋ ኦሮሞ ታግሎ አልነበረም፡፡ እንደውም ወለጋ ምዕራብ አካባቢ እንጂ እነ ነቀምት ብልጦች ነበሩ፡፡ ሸዋ በከተሞች መስፋፋት በሚል በመቶ ሺዎች ቤተሰብ ተፈናቅሏል፡፡ ይሄን በነጻነት ያኖረው ነፍጠኛው አላደረገም፡፡ ሐበሻም ተብሎ የሚጠራው አደልም፡፡ ሌላ ቀርቶ የወያኔ ድርሻ እንኳን ትንሽ ነው፡፡ ዛሬ የፖለቲካ ቁማር መቆመሪያ የሆነው የኦሮሞ በአዲስ አበባ ና ዙሪያ ቦታዎች ተፈናቀለ የሚል ፕሮፓጋንዳ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል እንደሚባለው ነው፡፡ ሸዋን ያፈናቀለው በኦሮሞነት ሥም የሚነግደው የወለጋና የአርሲ የመሬት ነጋዴዎች ናቸው፡፡ ተመልከቱ ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ ገላተን፣ ዱከም፣ ሰበታ ማን ነው ያፈናቀለው?   አስተውሉ በገዛ ቦታው ራሱ ቢሸጥ የአካባቢወ ሰው ሊወቅሰው ሊገስፀው ይችላል፡፡ እሱም በሆን በገዛ ሕዝቡ የከፋ ነውር አይፈጽምም፡፡ የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን ግን ዛሬ እንዴት እንደተቀራመቷቸው አስተውሉ፡፡ ነውር የለም ነውረኞች ጋር፡፡ ሱሉልታና ለገጣፎ ከአርሲ ሌሎቹን ከወለጋ አምጥተው የሸዋ ከተሞች አስተዳዳሪ አድረገዋል፡፡ ከወለጋና አርሲ መጥቶ የሸዋን ገበሬ አፈናቅሎ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ቤት ይሰራለታል፡፡  ነውር አይፈሬዎቹ ይሄን እያደረጉ ግን አሁንም ሳያፍሩ የኦሮሞ ገበሬ ተፈናቀለ እያሉ ነው፡፡ ይሄ የኦሮሞ አደገኛው ቡድን አንዱ ማሳያ ነው፡፡

አሁን ወደ ሥልጣን ሲመጣ በአንድ አመት ጊዜ ይሄው የኦሮሞ አደገኛና በጥላቻ የታወረ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ ቡድን የኢትዮጵያን ትልልቅ ተቋማትና ወሳኝ ቦታዎች  ያለምንም ነውር እየተቀራመተ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከእነዚህ ሰለባዎች አንዱ ነው፡፡ በገቢዎች ሚኒስቴር እንዲሁ የከፋ ችግር እንዳለ እየተነገረ ነው፡፡ አዲስ አበባ  አስተዳደርም ላይ የሆነው ይሄው ነው፡፡ ወደ ባንኩ ስመጣ ሰሞኑን በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናልባንክ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተዛወረው ግለሰብ ታወቀበት የሚባለው ሥራው ከወለድ ውጭ ቁጠባ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ስኬታማ አድርጓል የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ የወለድ ነጻ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው? እኔ እስከሚገባኝ የኢትዮጵያ እስላምም ሆነ ክርስቲያን ለዚህ ንግድ የሚሆን አመለካከት የለውም፡፡ ጥቂቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለጥቆማ ይበቃል፡፡ ወደፊት በምንሰማው እንዳንደናገጥ ነው፡፡  ስለዚህ ባንክ ባለፈው በግሌ የደረሰውን ተናግሬ ነበር፡፡ አንድ አባ ዊርቱ የተባለ ሰው ለምን ገረመህ ትክክል ነው አይነት መልስ  ሊሰጠኝ ሞክሯል፡፡ እንደ እውነቱ እኔን አይገርመኝም፡፡ ከዚህም የከፋውን ዘረኝነት አይቼዋለሁ፡፡ እንደውም ሁኔታው ያስደነገጠው ጓደኛዬን ነበር፡፡ እኔንም ይሰማዋል ብሎ ደብሮት ነበር፡፡

አሁን አደጋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገንዘብ ኪሳራ በላይ ለአገር ደህንነት አደጋ እንዳይሆን ነው፡፡ ይሄን ሁሉም እንዲያስብበት ከወዲሁ እጠቁማለሁ፡፡ ለኦነግም ሆነ ለሌሎች ጽንፈኛ ሀይሎች በገንዘብ እንዲደራጁ ሊያደርግ እንደሚችል እሰጋለሁ፡፡ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሊኖር ከሚችል ጥላቻ ባሻገር እነዚህ ግለሰቦች የተሰበሰቡት ከግል ባንክ ነው፡፡ እንደሚገባኝ በእነዚህ የግል ባንኮች የተወሰነም ቢሆን ሼር ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ጥቅሞች በሴራ ወደ እነዚህ ባንኮች እንደሚያዛወሩ አለማሰብ ስህተት ነው፡፡ እነዚህ ባንኮች በተለይ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የተመሠረተው በዘረኝነት ላይ እንደሀነ እያወቅን የኢትዮጵያን የሆነ ገንዘብ በእነዚህ ግለሰቦች አማካኝነት ላለመዝረፉ ምን ዋስትና አለ? አባ ዊርቱ አብይ አደለም የሚመድበው ብሎ ሊያስተባበል ይፈልጋል፡፡ ይሄን አይን ያወጣ ነውር በእጁ መፈረሙና አለመፈረሙ አደለም፡፡ እንዲች ያለች ድራማ እሱም ያቅባታል፡፡ እኔ አላውቅም ይላል በአደባበይ የሆነውን፡፡ እንዲህ ያለ ቀልድ የለም፡፡

ዘሬ ለደቡብ 18 ሚሊየን ብር ለደበብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ተሰጥቷል፡፡ በቀጣይም ኪሊኒክ በየአገራቱ እያሰራ እንደሆንም እየነገረን ነው፡፡ የመንግስት አሰራር ራሱ የማይገባው፡፡ ይሄ ተቋም የመንግስት ተቋም ነው፡፡ የሕዝብ ተቋም ነው፡፡ መንግስት ከዚህ የገንዘብ ተቋም የሚያገኘውን በተፈለገበት ቦታ በእቅድ ይሰራበታል እንጂ ባንኩ በቀጥታ ኪሊኒክ የሚገነባበት ምን የሚሉት አሰራር እንዶነ ተመልከቱ፡፡ ለደቡብ 18 ሚሊየን ብር ወርውሮ ኦነግን በገንዘብ እያፈረጠመ ሕዝቡን ያፈናቅላል፡፡ ቦታ ይወራል፡፡ ሲጀምር የዚህ ሁሉ ቀውስ ምክነያት ማን ነው? ዛሬ ጉጂ እኮ ጉልበት የሆነው በፌደራል ደረጃ የተቀመጠው የኦነግ/ኦዴፓ ቡድን ነው፡፡ ጌዲዮ እያለቀ ያለው እኮ ሆን ተብሎ ነው፡፡ ሰዎችን ወደ ቄያቸው መመለስና በኑሮአቸው ራሳቸውን እንዲያስተዳደሩ አንዳችም አልተሞከረም፡፡ ምክነያቱም የተወረረው መሬት የኦሮሞ እንዲሆን ነው ከጅምሩ ሴራው፡፡ ጌዲዮ ብቻ አደለም ሌሎች ብዙ ሕዝቦች፡፡ ለነገሩ ከኦሮሞ የተዋሰን አንዱም ሕዝብ ሰላም የለውም፡፡ ይሄን ማን ፈጠረው፡፡ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ ነው ስንል ያለምክነያት አደለም፡፡ ኦሮሞ አቃፊ ነው፤ ኦሮሞ የአባ ገዳ ልጅ ነው፤ ይባልልኛል፡፡ እውነቱ ግን በዚህ ከቀጠለ አደጋው እየመጣ ያለው በኦሮሞ ነው፡፡ ወያኔ ከለቀቀ በኋላ እኮ ሁሉም ነገር ታየ፡፡ ነውር የለሽ  ስግብግብነት፡፡ የከፋ ዘረኝነትና ጥላቻ፡፡ በኦነግ የጥላቻና ዘረኝነት የተበከለው ትውልድ እንደ ትክክለኛ አስተሳሰብ የተቀበለው ነው፡፡

አብይና ለማ ነቀምት ላይ ኳስ ሲጫወቱ የነበረው ሂደት ነበር ትልቁ የጉዞአቸው አላማ የሚመስለው፡፡ ሕዝብ እንዲህ ግልብ አካሄድ መምራት ከተቻለ ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ መለስን የሚያወደስ እየበረከተ መጥቷል፡፡ የአብይ ነገር ከቀን ወደ ቀን ሲብሰበት እንጂ ሲሻለው እያየን አደለም፡፡ ያለመቻል ቢሆን ብዙዎች ሊያግዙት በቻሉ፡፡ አዝናለሁ፡፡ የምር ብዙ ያመኑት ሰው ሌላ ሆኖ ሲገኝ ይደብራል አይገልጸውም፡፡ ዛሬ አዎሮፕላንና ሄሊኮፕተር እያስነሳ ወደፈለገው ቦታ መሄድ እንደመሪ ምን መስሎ እንደሚታዮው አላውቅም፡፡ አሁን ነቀምት የሄዱበት ምክነያት ምንድነው ተብሎ ቢጠየቅ ሕዝብ ያየው እንግዲህ ኳስ ሲጫወቱ፡፡ ከሄሊኮፕተር እንዴት እንደወረደ፡፡ የሆን የማሽን ገን የያዙ ጠባቂቆቹ እንዴት እንደነበር የሚያሳይ ትዕይንት ነው፡፡ በአለፈው ደቡብ ሱዳን ከአውሮፕላኑ እንዲሁ ማሽን ገን የታጠቁ ሲወርዱ አይቼ አዝኛለሁ፡፡ እንደሚገባኝ ፕሮቶኮል የሚባ ነገር አለ፡፡ እንዲህ የፊልም ቀረጻ በሚመስል ሁኔታ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎቹ ይደብራሉ፡፡ ለዛ ነው ሰውዬው ተራ የሰውን ትኩረት ለመሳብ የሚያደርጋቸው ነገሮቹ ከመሪነት ቦታ እያወረዱት ያሉት፡፡ አዝናለሁ፡፡ ጉዞዎቹም እንደ አገር መሪ ሳይሆን ዝም ብሎ ያለ ዓላማ ይመስላሉ፡፡ ዓለም ላይ ታላላቅ የተባሉት አገራት ሳይቀር አልፎ አልፎ በጣም በታቀደ ሁኔታ ካልሆነ ዝም ብለው ተነስተው አውሮፕላን ማዘዝ ስለሚችሉ ብቻ ከአገርአገር አይዞሩም፡፡ አዝናለሁ!  አብይን ለማንም ሕዝብ ከልብ ተቀብሏቸው ነበር፡፡ ዛሬ ላይ እንደዛ አደለም፡፡ እኔ ስለእነሱ አዝናለሁ፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ውጤት ነው፡፡ እነሱ ራሳቸውም በሴራው ላለመኖራቸው እርግጠኞች አደለንም ባይኖሩ እንኳን በኦሮሞ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የግድ ሌላውን መጥላትና ቢያንስ ደንታ ቢስ መሆን ግዴታ ነው፡፡ የኦሮሞ ተፈናቃይ ቦታ እየተሰጠው ነው፡፡ የጌዲዮና ሌሎች ብዙ የማንሰማቸው ከኦሮሚያ ጋር የሚዋሰኑ የደቡብ ሕዝቦች ችግር ውስጥ ናቸው፡፡ ሳይፈናቀሉም ረሀብ እያጠቃቸው ያሉ ቦታዎች በርክተዋል፡፡ ሰሞኑን በባሌ ረሀብ ያጠቃቸው ሰዎች እየበዙ ነው እየተባለ ነው፡፡ አብይ ጊዜ ሰጥቶ አገርን መምራት ትቶ ስለራሱ ፊልም ይለቅልናል፡፡ ሰው ምን ይለኛልንም አላወቀም፡፡ የአቅም ጉዳይ ቢሆን በረዳንው፡፡ እኔ በራሴ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርብ ሥራ ለመሥራት የራሴ እቅድ ነበረኝ፡፡ ይሄንኑ እቅድ ከሰዎች ጋር እየተነጋገርኩ ነበር፡፡ ችግሩ ግን ሁሉም በሚያየው እውነት ተስፋ ቆርጧል፡፡

በነገራችን ላይ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ አንዱ ማሳያ በእስፖረታዊ እንቅስቃሴ እንኳን ያለው ተሳትፎ ነው፡፡ ሩጫውን እንዳትሉኝ፡፡ እሱም ቢሆን እኮ ከወለጋ አይታሰብም፡፡ አነሰም በዛም ብዙዎች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፕሪሚየም ይሳተፋሉ፡፡ እንግዲህ ሕዝብን ከሚያቀራርብ አንዱ ስፖርት ነው፡፡ ኦሮሚያ ከሚባለው ክልል በአጠቃላይ አዳማ ብቻ ነው፡፡ አሁን ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም በአንድ ወቅት ሰበታ ጥሩ ነበር፡፡ደቡብ ጥሩ ነው፡፡ በዞን ደረጃም ጥሩ የሚንቀሳቀሱ አሉ፡፡ የነቀምቱ ስታዴየም ብዙ ገንዘብ እንደፈሰሰበት እናውቃለን፡፡ አንቦ ላይ ደረጃውን የጠበቀ የኦሎምፒክ ስታንዳርድ ተብሎ በአንድ ወቅት ሲፎከር ነበር፡፡ ብዙ ገንዘብ ተዘርቦባቸው ይሆናል ግን ምን ያደርጋሉ፡፡ ኦሮሞ ከእነዚህ አይነት ተሳትፎ ወጥቷል፡፡

ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

 

1 COMMENT

  1. ሰርፀ ደስታ፣
    ለመሆኑ እስከ አሁን ልብስ አልጣልክም? ዘመዶች አሉህ? “Maraatuu warratu hidhata” ይላል ኦሮሞ። አርዕስትህ እና በመጀመሪያ ላይ ያስቀመጥካቸው 5 ነጥቦች ለማበድህ ጥሩ ማስረጃ ናቸው! ዝርዝሩ ዉስጥ መግባት ከእብድ ጋር መጯጯህ ስለሚሆን፣ ያ ደግሞ እብዱን የባሰ ስለሚያሳብደው መተዉ ይሻላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.