የአዲስ አበባው አዴፓ የቁም እስረኛ ሆኗል (ተመስገን አባተ)

አዲስ አበባ የሁሉም ናት ብሎ ሊታገል የወሰነው አዴፓ እንዳይንቀሳቀስ በኦዴፓ ታስሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአዴፓ አመራሮች ከስብሰባም ከስራም ታግደዋል።

አመራሮቹ ደሞዛቸው እየተከፈላቸው ነገር ግን ከስራና አስብሰባ ታቅበው እንዲቆዩ ነው የተነገራቸው።

ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው የብአዴን/አዴፓ የአዲስ አበባ ተወካይ አመራሮች የወረዳ አመራሮች ናቸው።

በኦዴፓው አቶ ጥላሁን ፈቃዱ ስራ አስፈፃሚነትና በህወሀቱ አቶ ግዳይ ስራ አስኪያጅነት በሚመራው የቦሌ ክፍለ ከተማና በስሩ በሚገኙ ወረዳዎች የአዴፓ ተወካዬች ከስራ ውጭ ሆነዋል።

ለምሳሌ ደሞዛችን ለጊዜው ስላልቆመ ስማችን አትጥቀስ ያሉ በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 1 እና 7 አመራሮች እንደታገዱ አረጋግጫለሁ።

ጉዳዩ ከሚዲያ ደርሶ ህዝብ ከሚያውቀው ሳይሰሩ መክፈልን መርጧል የአቶ ታከለ ኡማ መንግስት።
ከዚህ በተጫማሪ በየወረዳው በደምብ ማስከበር ጽ/ቤት ሲመሩ የነበሩ የአዴፓ አመራሮች (በአብዛኛው የኮማንደርነት ማዕረግ ያላቸው )ሀላፊዎች በልዩ ልዩ ዘዴ እንዲገለሉ ተደርጓል ።

ክዚህ በፊት 24 የአዴፓ የአ.አበባ አመራሮች በከንቲባ ታከለ ኡማ ትዛዝ መነሳታቸው ይታወሳል። 1የከተማ፣ 1የክ/ከተማና 22 የወረዳ አመራሮች ነበሩ የተነሱት።

®ተመስገን አባተ

ይህ እንደሚመጣ እናውቅ ነበር ትልቅ ተገዳዳሪ ስለሆን እኛን ሳያውቁ የሚፈርጁ አሉ፣ስለ እኛ ለማወቅ የፈለገ ኑ ቤታችን ክፍት ነው ። "አብን ህዝቦችን አስተባብሮ ኢትዮጵያን ይታደጋታል!"

Posted by ያብባል አማራ on Wednesday, April 10, 2019

3 COMMENTS

  1. min ayachihu, gena hulum amara ke’addis abebana akababiwa mulich tedergo teterargo yiwotal. yih bayhon kemlase tsegur yineqel. endayayazachew bihon fetari tebkon enji eskahunim alkolin nebber.

  2. ለትህነግ (TPLF) የቀኝ እጅ ሆነው ህዝብ ሲገድሉና ሲያስገድሉ፣ ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ የነበሩ ለምን ተነሱ ነው እሮሮው?? ህዝቡ የልጆቹን ደም እና አጥንት ገብሮ የወያኔ የሰቆቃ አገዛዝ እንዲያከትም ሲያደርግ፣ እነማን ከስልጣን እንዲወገዱ ጠብቃችሁ ነበር?? 60% የኢህዐደግ ቀኝ እጅ ቢሮክራቶች እኮ አማሮች ነበሩ! እና እነርሱ አይነኬ ሆነው ማን ይነሳ ታዲያ?? ገና ምኑ ታይቶ?!

  3. ” እነማን ከስልጣን እንዲወገዱ ጠብቃችሁ ነበር?? 60% የኢህዐደግ ቀኝ እጅ ቢሮክራቶች እኮ አማሮች ነበሩ! ”

    Well, that makes sense if they are not replaced by Oromo tribalists.

    If what you said is true then you are implying that the article is a TPLF propaganda.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.