የሰሜን እዙ የጌታቸው ጉዲና ክህደትና የአማራ ክልል መንግስት አፀፋ (አያሌው መንበር)

የጠቅላይ አቃቢ ህግ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያላቸው መያዛቸውን ገልፀዋል።ለዓመታት ስሙን የዘነጋነው (ሚዲያዎችም ጭምር) አልሸባብ የተባለው ሽብርተኛ ቡድንን ዛሬ በአዲስ አበባ ስሙ ሲጠራ ስሰማ “አኬልዳማ” የሚለው የእነ መለስ ድራማ ትውስ ይለኛል።

አኬልዳማ ድራማ ተሰርቶ መጥቶ አብዲ ከማል ያነበበው ሰሞን ቢሮ ስንገባ ይጨንቀን ነበር።በወቅቱ ብዙ የግምገማ ሀሳቦችም ተሰንዝረዋል።

አኬል ዳማ ብዙዎችን ለማጥመድ፣የህዝብ ድጋፍ ለማግኘትና አለማቀፍ ማህበረሰቡን ቀልቡን ለመግዛት በመንግስት ደህንንነት (የፀረ ሽብር ግብረሀይል) የተቀነባበረ ስለመሆኑ ብዙም አያጠራጥርም።

ዛሬ አቃቢ ህጉ “ከአልሸባብ ጋር ሆነው ሽብር ሊፈፅሙ …” ምናምን ሲሉ ያሉትን መረጃም 25% እውነት 75% ተቀባይነቱ እየተዳከመ ያለውን የአብይና መንግስትና መዋቅሩን የህዝብ ድጋፍ ለማስገኘት ታቅዶ የተሰራ የአኬልዳማ አይነት አድርጌ ነው የምወስደው።

ባለፈው ወር አንድ ግለሰብ ስለሽብርተኝነት ሲያወጋ “ሀገራችን በሽብር እየተናጠች ነው፣ሽብርተኞቹ ደግሞ ሁሉን ኬኛ የሚሉ ናቸው” በማለት ተናግሮ ነበር።ያው ሰሚ ስላልነበረው (ወይም መንግስትም የኬኛ አቀንቃኞች ቡድን አካል በመሆኑ) ይህ ኬኛ ትንሽ ዘግየት ብሎ ሜንጫና አጠና ይዞ አዲስ አበባ መከሰቱ ይታወሳል።ሰሞኑን ደግሞ የጉዲናን ትጥቅና ስንቅ ጭምር ይዞ በምንጃር፣በከሚሴ፣በአጣየና በማጀቴ ተከስቶ ነበር።

እናም የአብይ አቃቢ ህግ “አልሸባብ” እያለ የአማተር ቲያትር ከሚሰራ ኦነግን ቢያስተምር ይሻለው ነበር።ቤተመንግስት ውስጥ ያለውን ኦነግን ፍፁም ጨዋ በማድረግ ሶማሊያ ድረስ መሄድ አማተርነት ነው።

====================

በጀዋር መሀመድ በኩል ተደጋጋሚ ዛቻና ዘለፋ የደረሰበት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አለሙ ሰሜ (ለማን ሊተካ ይችላል ሲባልም ነበር) መባረሩን የኦሮሞ ሚዲያዎች ዘግበዋል።አቶ አለሙ የኋላ ዘሩ ከሰላሌ ኦሮሞ የሚመዘዝ ነው።የባሌና አርሲ ኦሮሞ በሰላሌ (ሸዋ)ና ጅማ ኦሮሞ ላይ የበላይነቱን ለማሳየት በሚያደርገው ጥረት አለሙ ሰሜ ተባሮ በአዲሱ አረጋ ተተክቷል።አዲሱ የባሌ ሰው ይመስለኛል።

ኦሮሚያ ክልልን ጀዋር እንደሚያስተዳድረው ይህ “የቄሮ መንግስት” ዘመቻ ውጤት ማሳያ ነው።

=================

የአማራ ክልል መንግስት ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በመተማና በከሚሴ በቡድን የተደራጁ ሀይሎች ወታደራዊ ስልጠና እያደረጉ ነው፣እነዚህ ለህዝቡ ስጋት ናቸው ብሎ መገምገሙ ይታወሳል።

የመተማው ቶሎ ርምጃ ስላልተወሰደበት ለ60ሺህ ዜጎች መፈናቀልና ከ50 በላይ ንፁሃን ሞት ምክንያት ሆኗል።

የከሚሴው ጦስም መፈናቀል ብዙም የከፋ ባይሆንም ከመተማው ያልተናነሰ ህይወትን ቀጥፏል።የሁለቱም ጉዳይ ተቀራራቢ ነው።
የመተማው ህወሃት የሚደግፈው ቅማንት ሲሆን የከሚሴው ፅንፈኛ ኦሮሞዎች እና ህወሃት (በድብቅ ይደግፈው ይሆናል) ኦነግ ናቸው።

በዚህ ላይ በየደረጃው ያለ ፀጥታ አደጋውን ለመቀነስ ከህዝብ ጋር ሆኖ ታግሏል።ይህንን የኦነግ አይን ያወጣ ወረራ ታድያ የመቀሌው ሰሜን እዝ አዛዥ ጌታቸው ጉዲና አይኑን በጨው አጥቦ አማራ እርስበርሱ ነው የተጋጨው በማለት በብሄራዊ ቴሌቪዥኑ በስልክ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የጌታቸው መግለጫ ከዞኑ የፀጥታ ሀላፊ፣ከወረዳዎችና ከክልሉ መረጃዎች ሁሉ ሊለካ በማይችል ማይል የራቀ ነው።ኦነግ እና በቡድን የታጠቁ ሀይሎች መሆናቸውን ከ10 ወር በፊትም የገመገመው ክልል በግልፅ እውነታውን ተናግሯል።ይሁንና ጉዲና ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል።እንዲያውም ክልሉን ኮንኗና።

በዚህ የተከፋው የአማራ ክልል መንግስት ተከታዩን ማብራሪያ ለBBC አማርኛ ሰጥቷል

<<የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚጠብቀውን የፖሊስ አካል ህዝባዊ አመኔታ እንዳይኖረው ለማድረግ ታልሞ የሚሰጡ መግለጫዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

የአማራ ክልል የጸጥታ መዋቅሩ ተልዕኮውን በሚገባ የሚያውቅና የህዝብን ደህንነት የሚጠብቅ እንጂ መልሶ የአማራን ህዝብ የሚጎዳበት ምክንያት የለውም።>>

((የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኅላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ፡፡))

እንግዲህ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ነው የሀገር መከላከያን ይመራል የተባለ ወንበዴ የአማራን ፀጥታና ህዝብ የሚወቅሰው።እርግጥ ጉዲና ይህንን እንዲል የፌደራል መንግስቱ ግፊት እንዳሳደረ ታውቋል።

=======================

የሁሉም ነገር መሰረቱ ኢኮኖሚ ነውና አንድ መረጃ ቲፕ ላድርጋችሁ።ይህ ስጋት የእኛም ጭምር ነው።

“የአፍሪካድህነት መጠን በ2030 አሁን ካለበት የከፋ እንደሚሆን የዓለም ባንክና IMF አስታውቀዋል።
በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ አለማድረግ፣በአንዳንድ ግዙፍ የግብይት ተቋማት የገንዘብ ቀውስ መግጠምና በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖሊሲ አለመጣጣም ወይም ላልተጠበቀ ችግር መዳረግ ምክንያት ናቸው” ብሏል ኦል አፍሪካ።

https://www.facebook.com/ayalewmenber/videos/2219444041474042/

 

3 thoughts on “የሰሜን እዙ የጌታቸው ጉዲና ክህደትና የአማራ ክልል መንግስት አፀፋ (አያሌው መንበር)

  1. እንደጠቀስከው <> ብሎአል የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኅላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ፡፡
    ችግራችሁ (ያንተ እና የገደቤ) ያለው እኮ “የአማራ ክልል” እና “የአማራ ህዝብ” በሚሉት መካከል ልዩነት መኖሩን አለማወቃችሁ መሰለኝ። የጸጥታ መዋቅሩ “የአማራን ህዝብ የሚጎዳበት ምክንያት የለውም” ስትሉ፣ በአማራ ክልል ዉስጥ የሚኖሩትን ሌሎችን ማህበረሰቦች ግን ላለመጉዳቱ አልተናገራችሁም! በቅማንት፣ በአገው አሁን ደግሞ በከሚሴ ኦሮሞው ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋን ያካሄደ አካል ከሌላ ቦታ አልመጣም! ነው ጀነራሉ ያሉት።

  2. Why do you target OLF is clear. By targeting the OLF you are targeting the Oromo people. Please calm down and accept the reality on the group. You have to accept the administration of Dr Abiy to save Ethiopia from disintegration. If not you can peacefully use Article 39. Otherwise shut your mouth, the statement of General Getachew is right and I am hopeful that he will track down those perpetrators in regional security apparatus. You raised about “kegna”, yes Ethiopia is Kegna. When you cry for Addis Ababa, no question it belongs to the Oromo because it did not fall from the sky but built over Oromo land, we move to Gondar( the city built and protected by the Oromo). Do you know king Iyoas who spoke only Afan Oromo in his palace of Gondar. Gondar was protected by more than 3000 best Oromo cavalry during his rule. If you consider yourself as pure Amhara and live around Gondar, count your grandfathers back up to five, six or seven. Then surely you become Oromo. Please do it and then you trust me. Then you prove the ‘Kegna Politics’.

  3. በጀዋር መሀመድ በኩል ተደጋጋሚ ዛቻና ዘለፋ የደረሰበት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አለሙ ሰሜ (ለማን ሊተካ ይችላል ሲባልም ነበር) መባረሩን የኦሮሞ ሚዲያዎች ዘግበዋል።አቶ አለሙ የኋላ ዘሩ ከሰላሌ ኦሮሞ የሚመዘዝ ነው።የባሌና አርሲ ኦሮሞ በሰላሌ (ሸዋ)ና ጅማ ኦሮሞ ላይ የበላይነቱን ለማሳየት በሚያደርገው ጥረት አለሙ ሰሜ ተባሮ በአዲሱ አረጋ ተተክቷል።አዲሱ የባሌ ሰው ይመስለኛል።ወንድሜ አንድን መረጃ ለህዝብ ይፋ ከማድረግህ በፊት እውነተኝነቱን ብታረጋግጥ ምን አለበት? አንተንም ትዝብት ውስጥ ከመግባት ያድንሃል፡፡ ለመሆኑ በዚህ ከፅሑፍህ ውስጥ ቆርጬ ከወሰድኩት ሀሳብ ውስጥ እውነት የሆነው ነገር የቱ ነው? ህዝብን ባናደናግር፣ የጥቂት ስልጣን ጥመኞች መጠቀሚያ ባናደርግና ሰላሙን ባናናጋው ምን አለበት? ልቦና ይስጣችሁ ለሀገር አተራማሾች ግን ደግሞ ምንም አታመጡም:: የኢትዮጵያ ህዝብ ላይለያይ በደምና በአጥንት ተሰናሰለ ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.