የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በደቡብ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ማቋቋሚያ የሚውል የዐሥራ ስምንት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊና ከደቂቃዎች በፊት በሀዋሳ በመገኘት ባንኩ ያበረከተውን ድጋፍ ለደቡብ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ሚሊዮን ማቲዎስ አስረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በድጋፍ አሰጣጥ ስነስረዓቱ ላይ አንዳሉት የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ልማት እያበረከተ ከሚገኘው አስተዋጹኦዎ በተጨማሪ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል።

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊና በበኩላቸው ባንካቸው የደቡብ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የአንድ መቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
ባንኩ አሁን ካበረከተው የአስቸኪይ ድጋፍ በተጨማሪ በሰባ ሚሊዮን ብር ወጪ በዘጠኙም ክልሎች የጢና ጣቢያዎችን በማስገንባት ላይ እንደሚገኝም ፕሬዝዳንቱ አመልክተዋል።

DW Amharic

(የቪዲዮ ምስል፦ በሽዋንግዛው ወጋየሁ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.