ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማን ይሆን የሚያማክራቸው? (መሐመድ አሊ)

1) ጥጋበኛ ዘረኞችና አሸባሪዎች በማን አለብኝ ባይነት በዙሪያው እየፈነጩ; የዘረኝነትና የጥፋት መርዛቸውን የረጩና/የሚረጩ ህዝብን ከህዝብ ያጋጩና/የሚያጋጩ; በርካታ ንፁሃን ዜጎች እንዲገደሉ; በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንዲፈናቀሉ ያደረጉና/እያደረጉ ያሉ አደገኛ ሰዎችና ቡድኖች ባሉበት ሁኔታ ሙስና የፈፀሙ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ ማለት ጆሮን የሚያቆም ዜና አይደለም። ይህ ማለት የሀገርን አንጡራ ሀብትና ንብረት የመዘበሩ ሙሰኞች “አይታሰሩ” ማለት አይደለም። ከዚያ በላይ ግን የዘር ፍጅትን ያነሳሱና/በማነሳሳት ላይ ያሉ አደገኛ ሰዎችና ቡድኖች ባሉበት ሀገር ሙስና በሁለተኛ ደረጃ ሊታይ የሚችል (secondary) ጉዳይ ይመስለኛል።

2) ብሔራዊ ፓርከቻችንን እያጋዬ ያለውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት ብሔራዊ ርብርብ እንዲደረግና ዓለማቀፋዊ ድጋፍን ከመጠየቅ ይልቅ ብሔራዊ የፅዳት ዘመቻ እንዲደረግ ያውጃሉ። በርግጥ የትኛው ይቀድማል?

3) በየአካባቢው የመንግሥትን አካላት ጭምር ያሳተፈና ዐይን ያወጣ የዘር ግጭትና ፍጅት ሥጋት እያንዣበበ ባለበትና በዚህም ሳቢያ በከሚሴና አጣዬ አካባቢ ንፁሃን በተቀጠፉበት ሁኔታ እሳቸው እንደ ኳስ ሜዳ/ስታዲዬም ያሉ የመዝናኛ ቦታዎችን/ፕሮጀክቶችን ሲመርቁ ይታያሉ። የዚህ ፖለቲካዊ አንደምታው ጠፍቶኝ አይደለም። ይሁንና እንደተራራ ገዝፎ ከፊታችን የተጋረጠው ችግር በእንዲህ ዓይነት ዜናዎች የሚሸወድ አይመስለኝም። ነገሩ “እዬዬም ሲደላ ነው” እንዲሉ ነው።

4) በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ዜጎች በሥራ አጥነትና በመኖሪያ ቤት ዕጥረት/ኪራይ ችግር በሚሰቃዩበት ሁኔታ 29 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የአዲስ አበባ ተፋሰሶች ልማት ፕሮጀክትን ይፋ ያደርጋሉ። እንዲህ ዓይነት ፕሮጀክቶች የከተማዋን ውበትና የቱሪስት መስህብን በመጨመር ረገድ ያላቸውን ሚና አላጣሁትም። በተጨባጭ ግን መሬት ላይ ያለው ችግር ከፍተኛ ሥራ አጥነትና የመኖሪያ ቤት ችግር ነው። ስለሆነም ይህን ያህን ገንዘብ ማግኘት ከተቻለ ለሥራ ፈጠራና ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ መዋል ነበረበት ብዬ አምናለሁ።

5) ድሆች ከቤተሰቦቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ለ40/60 እና 20/80 ኮንዶሚኒዬም ቤቶች ባጠራቀሙት ገንዘብ የተገነቡ ቤቶችን መረከብ ባልቻሉበት ሁኔታ የዱባይ ባለሀብቶች ለገሀር ላይ ስለሚገነቡት ዘመናዊ አፓርትመንት ማውራት ብዙም ስሜት አይሰጥም። ሀገሩን እንደሚወድ አንድ ዜጋ በሀገሬ ረጃጅምና ያማሩ ህንፃዎችን ማዬትን ጠልቼ አይደለም። ነገር ግን ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ገንዘባቸውን ከፍለው ለዓመታት በተስፋና በሰቀቀን የሚጠብቁ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ባሉበት ሁኔታ የውጭ ባለሀብቶች እንዳስፈላጊነቱ በዚህ ዘርፍ እንዲያግዙን ማድረግ ሲገባ በ50 ቢሊዮን ብር ስለሚገነባ የቅንጦት ሰፈር ሲነገር መስማት ሊያስፈነድቀኝ አይችልም።

6 COMMENTS

 1. ለተቀማጭ ሠማይ ቅርቡ ነው ::

  ዳር ቆሞ የሆነ ያልሆነውን መቀባጠር ቀላል ነው፡፡ ሁሉን ነገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ የሚሠራ ይመስል ፡፡ የጠቅላይ ሚሩን ሐጥያት ና ክስ ለማብዛት እንዲህ ሲሆን…..እንዲያ አደረገ ….እንዲያ ሲሆን…..እንዲህ አደረገ የሚል የሚያስተዛዝብ ወሬ ለሐገር የሚጠቅም አይደለም፡፡

  ለዘመናት ይህችን ሐገር ሠንጎ የያዛት ቋጠሮ በአጭር ጊዜ አንድ ሠው ይፈታዋል ብሎ ማሠብ ነባራዊውን የሀገሪቱን ሁኔተ ያለማወቅነው፡፡

  ያም ሆነ ይህ የተገኘውን ለውጥ appreciate እያደረግን ና አየተለማመድን የተሻለ እንዲሠራ መደገፍ እንጂ እንደለመድነው ስንጠላለፍ ስንወድቅ ስንነሳ እንኖራታለን እንጂ የትም አንደርስም፡፡

 2. Abye Amede is responsible for all critical situation every corner of the country ….he is clueless in leadeship, he is not decisive making solition, and influenced by morrow nationalism ethenic hardliners, over exitement of holding power with no maual of leadeship, no prioroised plan and objective simply moving from countery to countery place to place nonsense & impractical non stop talke He is totaly useless & chilidish!

 3. bye Amede is responsible for all critical situation every corner of the country ….he is clueless in leadeship, he is not decisive making solition, and influenced by morrow nationalism ethenic hardliners, over exitement of holding power with no maual of leadeship, no prioritised ageneda, plan and objective simply moving from countery to countery place to place nonsense & impractical non stop talke. He is totaly useless & chilidish!

 4. The current government of Ethiopia doesn’t know which problems needs to be tackled first. it’s just like putting the cart before the horse. If you want to solve the country’s problems, first of all change this damn constitution. Then the country needs national reconciliation. People are killing each other because of ignorance. Work for the safety of each and every individual in the country and stop displacement. After that change the currency, tackle unemployment in the country, change the stupid land lease, and lastly go to Welega to play soccer. For God’s sake don’t put the cart before the horse!

 5. አቶ መሀመድ አሊ :- በጣም ጎበዝና አስተዋይ ሰዉ ነህ። በአጭር እዉነቱን ግልፅ አድርገኸዋል። አስተያየትህን ቀጥልበት።

 6. አቶ መሃመድ፤ ለአገርዎ ቁም ነገር መስራት ከፈለጉ እስኪ የአንድ ጠቃሚ ፕሮጀክት (ትንሽ ብትሆን እንኳ) ሃሳብ አፍልቀው ያስተባብሩን። ያን አሳክተን ደግሞ እርስዎ ወይም ሌላ ሰው የተሻለ እቅድ ይዞ ሲያስተባብር በዛ ላይ እንሰራለን። ሌላን መውቀስማ ማን ያቅተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.